10 days ago
ቱሪዝም፦ የመደመር እሳቤ የተፈጥሮ ጸጋዎቻችንን ወደ ኢኮኖሚ ሞተርነት የለወጠበት ተጨባጭ ማሳያ
***************************
ኢትዮጵያ እጅግ አስደናቂ የታሪክ፣ የተፈጥሮ፣ የመልክዓ ምድር እና እምቅ የባህል ሀብት ያላት ሀገር ብትሆንም፣ እነዚህን ጸጋዎች አቀናጅቶ እና አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል ሥልታዊ ዕቅድ እና ቁርጠኝነት ባለመኖሩ ለዘመናት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተጨባጭ አስተዋጽኦ ሳያበረክቱ ቆይተዋል።
ነገር ግን ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ በሀገራችን ተግባራዊ የተደረጉት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ይህንን የአስተሳሰብ አጥር በመስበር፣ የሀገራችንን እውነተኛ አቅም ወደ መግለጥ ተሸጋግረዋል።
ይህ ስኬት የመጣው የመንግሥትን፣ የግሉን ዘርፍ፣ የማኅበረሰቡን እና የተፈጥሮን አቅም በአንድ የጋራ ሕልም ዙሪያ አስተባብሮ ከሚመራው የመደመር ፍልስፍና ነው። ዜጎች ሀገራቸውን እንዲያውቁ፣ እንዲወዱ እና እንዲኮሩባት የተደረገው ብሔራዊ ጥሪ ቱሪዝምን ከተለመደው የታሪክ ጥበቃ አልፎ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ሞተርነት አሸጋግሮታል።
በቱሪዝም ዘርፍ የታየው ይህ ሥር ነቀል ለውጥ የመጣው ታዲያ ፈጣን እና ፈጠራ በተሞላበት የፕሮጀክት አመራር የተመራ ሥልታዊ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ በ2011 ዓ.ም አዲስ አበባን ለማስዋብ ከተጀመረው እና እንጦጦ እንዲሁም ሸገር ፓርኮችን እውን ካደረገው "ገበታ ለሸገር" መርሐ ግብር ጅማሮውን አድርጓል።
የዚህ ፕሮጀክት መሳካት በ2012 ዓ.ም ልማቱን ወደ ክልሎች በማስፋፋት በጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻ የተፈጥሮ መዳረሻዎችን በከፍተኛ ጥራት ያለማውን "ገበታ ለሀገር" ፕሮጀክትን ወልዷል።
በአሁኑ ወቅት ደግሞ ስምንት አዳዲስ መዳረሻዎችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለማው "ገበታ ለትውልድ" መርሐ ግብር ሀገራዊ የቱሪዝም ገጽታን በመሠረታዊነት እየቀየረ ይገኛል።
የእነዚህን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎች አስተዳደር ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ለተመረጡ ባለሀብቶች መሰጠቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ለመሳብ ሥልታዊ ድልድይ ሆኗል።
በእነዚህ መርሐ ግብሮች የተገነቡት ፕሮጀክቶች የመደመር እሳቤን በተግባር የሚያሳዩ ተጨባጭ የልማት ዕንቁዎች ናቸው።
በደቡብ ኢትዮጵያ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ከአዲስ አበባ ውጪ በማስፋፋት እና ከአባያ እንዲሁም ጫሞ ሐይቆች ተፈጥሯዊ ውበት ጋር በመዋሃድ ለአካባቢው ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል የተገነባው የሎጎ ሐይቅ ሪዞርት 13.3 ሔክታር ላይ ያረፈ ዘመናዊ መገልገያዎችን እና የሔሊኮፕተር ማረፊያን ያካተተ ሲሆን፣ የሰሜኑን የሀገራችን የቱሪስት መስመር የሚያስተሳስር ወሳኝ ማዕከል ሆኗል።
በአፋር ክልል የተገነባው የኒዒን ሌ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ ከአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ ጋር ባለው ቅርበት የተፈጥሮ ፍል ውኃን እና ሐይቅን በማቀናጀት የቱሪዝም አቅምን እያጎላ ይገኛል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባው ደንቢ ኢኮ ሎጅ በበካ የቡና እርሻ አጠገብ ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው የተገኙ የተፈጥሮ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የተገነባ የዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሞዴል ነው። በዚሁ ክልል የሚገኘው የሀላላ ኬላ ሪዞርትም በጊቤ ሦስት ሰው ሠራሽ ሐይቅ ዳርቻ የተገነባ ሌላው አስደናቂ ማሳያ ነው።
እነዚህ ታላላቅ የቱሪዝም መዳረሻዎች በማክሮ ኢኮኖሚክስ ዕይታ የቱሪዝምን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ በከፍተኛ ደረጃ የሚያባዙ ናቸው። ፕሮጀክቶቹ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ቁሳቁሶች እና በኢትዮጵያውያን አቅም መገንባታቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ ውስጥ የሚፈጠረውን የግብይት ዝውውር በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።
ይህ ስትራቴጂ ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት የ10.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ ከያዘችው ግብ ጋር በቀጥታ የሚጣጣም ሲሆን፣ ዘንድሮ ከቱሪዝም ዘርፍ ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ የዚህ የመደመር ቀመር ተግባራዊ ስኬት ነው።
የገበታ መርሐ ግብሮች ከተለመደው የቢሮክራሲ አሠራር ወጥተው በፈጠራ የታገዘ የፕሮጀክት አመራርን በማሳየት፣ የኢትዮጵያን የተዳፈነ ጸጋ ወደ ተግባራዊ ሀብት በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገች ሀገርን ለማስረከብ የተጀመረው ጉዞ ስኬታማ ማሳያዎች ናቸው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #tourism #medemer #gebetainitiatives #economicgrowth #landoforigins

14 days ago
ከፖለቲካ መረጋጋት ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያሸጋግረው አዲስ ተስፋ
**********************
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ስኬት ከሀገራዊ የፖለቲካ መረጋጋት ባሻገር ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ጠንካራ መሰረት የሚጥል ወሳኝ ምሶሶ ነው።
ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት ሊመጣ የሚችለው አስተማማኝ ሰላም እና የተረጋጋ የፖለቲካ ምህዳር ሲኖር ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለኢኮኖሚው መነቃቃት ዋና ቁልፍ ሆኖ ያገለግላል።
በተለይም ረጅም ጊዜ የዘለቁ ግጭቶች እና የትርክት ልዩነቶች በሀገራዊ ምክክሩ አማካኝነት በሰላማዊ መንገድ እልባት ሲያገኙ ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ ይኖረዋል። አጨቃጫቂ ጉዳዮች የጋራ መፍትሔ አግኝተው እንደ ማኅበረሰብ መተማመን እና መረጋጋት ይሰፍናል።
በዚህም ሀገራችን ለግጭት እና ለፀጥታ ማስከበር የምታወጣውን ከፍተኛ የሰው እና የገንዘብ ሀብት ወደ አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ መሠረተ-ልማት ግንባታ፣ እንዲሁም ወደ ትምህርት እና ጤና ዘርፍ እንድታዞር ያስችላታል።
ይህ ሰላማዊ ከባቢ ደግሞ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን በከፍተኛ ሁኔታ በመሳብ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድልን ይፈጥራል፤ ሀገራዊ ምርታማነትንም ያሳድጋል።
በአሁኑ ወቅት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መሪነት እየተደረገ ያለው የምክክር ጉባኤ ይህንን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ እርምጃዎች ናቸው።
በምክክሩ ወቅት የሚነሱ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ፍላጎቶች ታይተው የጋራ መግባባት ላይ ሲደረስ፣ ማኅበራዊ ፍትህ እና ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን ያደርጋል።
ይህ ተግባር ድህነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ ጠንካራ የማኅበረሰብ ትስስርን በማጎልበት እኩልነት የሰፈነበትን ማኅበራዊ ብልፅግና ዕውን ያደርጋል።
ከዚህም በተጨማሪ ሀገራዊ ምክክሩ ጠንካራ እና ገለልተኛ ተቋማትን ለመገንባት መንገድ በመክፈት ለመልካም አስተዳደር መስፈን ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
ግልፅነት፣ ተጠያቂነት እና የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ሥርዓት ሲገነባ ሙስና እና የሀብት ብክነት ይቀንሳሉ።
በአጠቃላይ ሀገራዊ ምክክሩ ሰላምን፣ ማኅበራዊ ፍትህን እና ጠንካራ ተቋማዊ አሠራርን በማረጋገጥ፣ ኢትዮጵያን ወደ ተሟላ እና ዘላቂ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚያሸጋግር ታሪካዊ ዕድል ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #nationaldialogue #sustainablepeace #economicgrowth #ethiopiarising

24 days ago
የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ጤናማ እና የተረጋጋ ሆኗል - የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ
***************
የኢትዮጵያ ባንክ ዘርፍ የተረጋጋ መሆኑን እንዲሁም የመሠረታዊ ገንዘብ ዕድገት መረጋጋት ማሳየቱን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ በሀገራችን ያለው የመሠረታዊ ገንዘብ ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የወለድ በተመለከተ የአጭር ጊዜ የወለድ ተመኖች ከፍተኛ መሻሻል ማሳየታቸውን እና ከማስቀመጫ ወለድ ውጭ ያሉት በሙሉ ከዜሮ በላይ መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡
በግንቦት ወር 2018 የሁሉም የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነዶች አማካይ የወለድ ምጣኔ እና የ91 ቀን የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ አማካይ የወለድ ምጣኔ በቅደም ተከተል 12.3 እና 11 በመቶ በመሆን ካለፈው ዓመት ቅናሽ አሳይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ገበያ በተለይ በአጭር ጊዜ ሰነዶች ላይ ወደ 667.8 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ከፍተኛ የተጨማሪ ፍላጎት ተመዝግቧል፡፡
የኢንቨስትመንት ባንኮች ተሳትፎ መጨመር ገበያውን ይበልጥ እንዳሰፋው ነው ኮሚቴው በመግለጫው የጠቀሰው፡፡
ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበት የ7-ቀን የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ አማካይ የወለድ ምጣኔ በመጋቢት ወር 2018 ከነበረው 18.0 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በግንቦት ወር 2018 ወደ 14.6 በመቶ ደርሷል፡፡
በዚህም የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ አጠቃላይ የግብይት መጠንም 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ የባንክና የፋይናንስ ዘርፉ በቂ ካፒታል ያለው እና የተበላሸ ብድር መጠኑ ዝቅተኛ በመሆኑ ጤናማ እና የተረጋጋ ሆኖ መቀጠሉን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡
ለዚህ አዎንታዊ አፈፃፀም የአጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት ማደግ እና የብድር ተመላሽ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
የባንኮችን ጤናማነት በይበልጥ ከሚያሳዩት አንዱ የሆነው የግል ባንኮች የብድር እና የተቀማጭ ሂሳብ ምጣኔ በ2016 ከነበረው 90.3 በመቶ በ2018 ወደ 72.7 በመቶ ዝቅ ማለቱ፣ የባንኮች የገንዘብ አስተዳደር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን እንደሚያሳይ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡
#ethiopia #ebc #nationalbankofethiopia #bankingsector #financialstability #monetarypolicy #economicgrowth #treasurybills

1 month ago
ከራስ አገዝነት ወደ እሴት ሰንሰለት - የኢትዮጵያ ግብርና የ5 ዓመታት የለውጥ ጉዞ
***********************
ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የታየው ለውጥ በኢኮኖሚ ታሪካችን ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሚይዝ መዋቅራዊ ሽግግር ነው።
ዘርፉ ከኋላ ቀር የአመራረት ዘዴ በመላቀቅ ምርታማነቱ ወደተሻሻለ እና እሴት ወደሚጨምር የንግድ ሥርዓት እየተሸጋገረ ይገኛል።
ይህ ሽግግር የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እና ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ጋር ጠንካራ መስተጋብር በመፍጠር ታይቶ የማይታወቅ ስኬት አስመዝግቧል።
በምርት ዕድገት እና ኮሜርሻላይዜሽን ረገድ፣ በ2012 ዓ.ም 44 ሚሊዮን ቶን የነበረው አጠቃላይ የግብርና ምርት መጠን፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 150 ሚሊዮን ቶን ከፍ ብሏል።
ይህ ከ3 እጥፍ በላይ የሆነ ዕድገት የተገኘው የኩታ ገጠም እርሻ ሥርዓትን በመተግበር እና ሙሉ የግብርና ጥቅሎችን በመጠቀም ነው።
በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርም፣ በ2012 ዓ.ም 48 ሺህ ቶን የነበረው የዶሮ ሥጋ ምርት፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 190 ሺህ ቶን በማደግ የ296 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በተጓዳኝም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከልና 12.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም በማድረግ የደን ሽፋንን ከ17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል።
የገቢ ምርትን ከመተካት አኳያ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራች ሀገር ለመሆን በቅታለች። ሙሉ በሙሉ በስንዴ ምርት ራስን በመቻል የገቢ ምርትን ያስቀረች ሲሆን፣ በብቅል ገብስ እና በሩዝ የተደረገው ጥረትም አስተማማኝ አቅርቦት ፈጥሯል።
በወጪ ንግድ በኩል፣ በቡና ልማት የተከናወኑ ሥራዎች ምርቱን ወደ 1 ሚሊዮን ቶን እንዲጠጋ በማድረግ በ2017 ዓ.ም ብቻ 2.65 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝተዋል።
የግብርና ወጪ ንግድም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ወደ ውጭ የመላክ አቅም በመገንባቱ፣ ገቢው በ2014 ዓ.ም 3 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ችሏል።
ግብርና ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 34 በመቶ አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን፣ ለሀገር ውስጥ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች 70 በመቶ የሚሆነውን ጥሬ ዕቃ ያቀርባል።
ይህን የግብርና እና የኢንዱስትሪ ትስስር ይበልጥ ለማቀናጀት በክልሎች የተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ትልቅ ሚና አላቸው።
እስከ አሁን ከ344 ሺህ በላይ አነስተኛ አርሶ አደሮች እና ከ60 በላይ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከእነዚህ ፓርኮች ጋር ተሳስረዋል።
ለእነዚህ ስኬቶች መሠረታዊው ምክንያት መንግሥት የቀረፀው አዲሱ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ነው። ፖሊሲው የግሉ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
በተወሰደው የታክስ ማሻሻያ እርምጃ ከ1 ሺህ በላይ አስመጪዎች ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን አስገብተዋል።
እነዚህ የግብርና ግብዓቶች እና መሣሪያዎች ደግሞ ከግብር ነጻ ሆነው እንዲገቡ ዕድል ተፈጥሯል። ይህም 37 በመቶ የሚሆነው የአነስተኛ አርሶ አደሮች ማሳ በቴክኖሎጂ እንዲታረስ አስችሏል።
የ8028 ድምፅ-መር የግብርና ማማከር አገልግሎት እና የገጠር ዲጂታል ኪዮስኮችም አርሶ አደሩ ጠቃሚ ቴክኖሎጂን እና የገበያ መረጃን በቀላሉ እንዲያገኝ አስችለውታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #agriculture #agroindustry #valueaddition #economicgrowth #ebc

ኢትዮጵያ አንድ ቪዛ፣ ዓለም በውስጧ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቱሪዝም ዘርፍን አስመልክቶ የሰጡት ማብራሪያ
#tourism #ethiopiadelivers #ethiopia #pmoethiopia #landoforigins #abiyahmed #economicgrowth #ecotourism #greenlegacy #ebcworld
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
#ethiopia | ባሌ፣ ሮቤ - የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገለጹ።
በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia's Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል አበይት ርዕስ ሚኒስትሩ “የመዳረሻ ልማት ብሔራዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር፣ መዳረሻዎች የቱሪዝም መስህቦች ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንቨስትመንት ማዕከላት፣ የማህበራዊ ለውጥ መድረኮች እና የብሔራዊ ማንነት መገለጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
እንደ ዶ/ር አብርሃም ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞቿ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየሰራች ሲሆን፣ የመዳረሻ ልማት እነዚህን ግቦች በተግባር የሚያሳካ ስትራቴጂ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሶፍ ኦማር ዋሻዎች፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ዋንጪ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ ሐይቅ፣ ጣና ሐይቅ፣ ገራልታ እና አርባምንጭን ጨምሮ የኢትዮጵያ መዳረሻዎች ጎብኚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ ተመራማሪዎችን እና ፈጣሪዎችን ከዓለም ዙሪያ ለመሳብ ትልቅ አቅም እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ዶ/ር አብርሃም የመዳረሻ ልማት በትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክስ፣ ግብርና፣ ሪል እስቴት፣ መስተንግዶ እና አገልግሎት ዘርፎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን እንደሚያነቃቃ ገልጸው፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በትስስር እና መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የቱሪዝም፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የሪል እስቴት ዕድሎችን እንደሚያሰፉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች እና የአካባቢ ማህበረሰቦች በመዳረሻ ልማት ዘርፍ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው፣ የኢትዮጵያ መዳረሻዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንትና የፈጠራ ማዕከላት ማድረግ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
#ethiopia #destinationdevelopment #tourism #investment #economicgrowth #getutemesgen #ethiopia #bale #tourism #getutemesgen #ጌጡተመስገን #artificialintelligence #digitalethiopia2030 #mwu

2 months ago
ከፈተና ወደ ከፍታ፦ “ኢትዮጵያን ማንም አያሸንፍም” የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል በተግባር ሲገለጥ
******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም “ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማንም አያሸንፍም” ማለታቸው ይታወሳል።
ይህ ታሪካዊ መልዕክት በወቅቱ ከነበረው ውስብስብ የጸጥታ እና የፖለቲካ ውጥረት አኳያ ስሜት ቀስቃሽ መፈክር አልነበረም፤ ይልቁንም ሀገራችን ፈተናዎችን በጽናት አልፋ ወደ ከፍታ የምታደርገውን ጉዞ ያበሰረ የተግባር ቃል እንጂ።
በወቅቱ በትግራይ ክልል ለሕግ ማስከበር እና ለመልሶ ማቋቋም ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት፣ እንዲሁም ከፍተኛ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎች የበረቱበት ጊዜ በመሆኑ፣ የሀገር ቀጣይነት ራሱ ትልቅ ጥያቄ ውስጥ የወደቀ መስሎ ነበር።
ይሁን እንጂ መፍረሷን የተመኙ ታሪካዊ ኃይሎች በየአቅጣጫው ቢሴሩም ያ የተስፋ ቃል ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ግንባሮች ወደ ተጨባጭ ድል ተቀይሯል። ሀገራችን በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች ታላላቅ ስኬቶችን በማስመዝገብ መዋቅራዊ ሽግግር እያደረገች ትገኛለች።
ፖለቲካዊ ሽግግር እና የሀገረ መንግሥት ግንባታ
በፖለቲካው መስክ ያጋጠሙ የውስጥ መከፋፈሎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ታሪካዊ እርምጃዎች ተወስደዋል።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የነበረውን ጦርነት በዘላቂነት ማስቆም የቻለ ሲሆን ኢትዮጵያ ‘የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሔ’ በሚለው መርህ ችግሯን መፍታት መቻሏን በተግባር ያረጋገጠችበት ነው።
በተጨማሪም የዘመናት የፖለቲካ ቁርሾዎችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰፊ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራዎችን አከናውኖ፣ ዋናውን ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛል። ይህም ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የተጀመረውን የሽግግር ሂደት በተጨባጭ ያሳያል።
እነዚህ ተቋማዊ ግንባታዎችና የፀጥታ መዋቅር ማሻሻያዎች የሕዝብን አንድነት በማጠናከር የመከፋፈል አጀንዳዎችን ማክሸፍ ችለዋል።
የዲፕሎማሲ እና የሉዓላዊነት ድሎች
በዲፕሎማሲው መድረክ ኢትዮጵያ ያልተገቡ ዓለም አቀፍ ጫናዎችን እና የተዛቡ ትርክቶችን በጥበብ በማለፍ ብሔራዊ ጥቅሟን አስከብራለች። እ.አ.አ በ2024 የብሪክስ (BRICS) ሙሉ አባል መሆኗ የሀገራችንን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ ኃይል ማመንጨት የጀመረ ሲሆን በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው ይህ ፕሮጀክት ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን እያሳደገ ይገኛል።
የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) በይፋ መጽደቁም የዘመናት የአንድ ወገን ተጠቃሚነት ታሪክን ወደ ፍትሐዊና የጋራ ተጠቃሚነት የለወጠ ታላቅ የዲፕሎማሲ ድል ተጠቃሽ ነው።
የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አገራዊ ግስጋሴ
የሀገራችን ሁለንተናዊ አሸናፊነት በኢኮኖሚው ዘርፍም ጎልቶ ታይቷል። ተግባራዊ የተደረገው ሁለገብ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ኢንቨስትመንትን የሚስቡ ውጤታማ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ማክሮ-ኢኮኖሚውን አነቃቅቷል።
በጥቁር ገበያ ይባክን የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት በማስገባት፣ በታሪክ ከፍተኛ የተባለ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ላይ መድረስ ተችሏል።
በግብርናው ዘርፍ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታየው መዋቅራዊ ሽግግር ሀገራችንን ከምግብ ጥገኝነት እያላቀቃት ሲሆን ምርቱ መጨመር ብቻ በዓመት ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሪ ማዳን አስችሏል።
ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ የከተማ ልማት እና አረንጓዴ አሻራ
ይህ ሁለንተናዊ መነቃቃት በታላላቅ ፕሮጀክቶችም በግልጽ እየታየ ይገኛል። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን በቀጣዩ ሁለት ዓመታት ይህን ቁጥር 65 ቢሊዮን ለማድረስ እየተሠራ ነው።
በመዲናችን አዲስ አበባ የተጀመረው እና የዓለምን ትኩረት የሳበው የከተማ ኮሪደር ልማት በአሁኑ ወቅት ወደ 75 የሀገራችን ከተሞች በመስፋፋት ከተሜነትን እያዘመነ ይገኛል።
በእነዚህ ዓመታት የተለወጠችው አዲስ አበባ “ደህንነቷ አስተማማኝ አይደለም” በማለት ይቀርቡ የነበሩ አሉታዊ ትርክቶችን በማክሸፍ የዲፕሎማቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ተመራጭ መናኸሪያ ሆናለች።
በተጓዳኝም የአርሶ አደሩን ሕይወት የሚያዘምኑ የገጠር ኮሪደሮች እና ሞዴል መንደሮች ግንባታ ተጀምሯል። በመሰረተ ልማት ረገድ በ"ሚሽን 300" እና በ"አሰንት" ፕሮጀክቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች አዲስ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል።
በዓመት 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ያለው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ይገኛል።
ምንም እንኳን ከቀድሞ የተወረሰ የዕዳ ጫና እና እንደ የዋጋ ንረት ያሉ ማኅበራዊ ፈተናዎች አሁንም ሙሉ በሙሉ ባይቀረፉም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡት እነዚህ ታሪካዊ ስኬቶች የኢትዮጵያ የዕድገት ጉዞ የማይቀለበስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ሕያው ምስክሮች ናቸው።
ከዚህ አኳያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን ማንም አያሸንፍም” ሲሉ የተናገሩት ቃል መሬት የነካና በተጨባጭ መረጃዎች የተረጋገጠ አገራዊ ሀቅ መሆኑን ማየት እንችላለን።
ተግዳሮቶቻችንን ወደ ዕድል በመቀየር እነዚህን አበረታች ውጤቶች አጠናክረን በመቀጠል፣ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ የሁሉም ዜጋ ርብርብና ብሔራዊ መግባባት ወሳኝ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #resilience #economicgrowth #diplomacy #nationaldialogue #ebc

ቤተ ጉራጌ
እዣ : የኢንቨስትመንት ፀሐይ እየወጣላት ነው
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው አዲስ የብረት ማምረቻ ፋብሪካ በይፋ ተመረቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብረት ማምረቻ ፋብሪካ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።
የሀሮት ሪልስቴት እህት ኩባንያ የሆነው ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር መሥራችና ባለቤት አቶ ሰኢድ ኑሩ እንደተናገሩት "ቪታ ሳሉቲ የጣልያንኛ ቃል ሲሆን ሰላማዊ ሕይወት የሚል ትርጉም ይዟል። ሰላማዊ ሕይወት በቤተ ጉራጌ - ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ኢትዮጵያ መልካም ምኞት ለመግለጥ ነው። የቤተ ጉራጌ አኗኗርም ለማመላከት ነው ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የሚገኘውንና የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ የሆነውን ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ፋብሪካን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
አያይዘውም "ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የግል ባለሀብቱ ሚና የላቀ ነው!" ሲሉ አወድሰዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋብሪካ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ መጠንና ቅርጽ ያላቸው የትቦላሬና የላሜራ ብረት 22 ምርቶችን በከፍተኛ ጥራት የማምረት አቅም አለው።
አቶ ሰኢድ ኑሩ ንግግር "ይህ ፕሮጀክት ከህልም ወደ እውነት፣ ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ነው። ሀገራት የሚበለጽጉት በተፈጥሮ ሀብታቸው ብቻ ሳይሆን ራዕይን ወደ ተግባር በሚቀይሩ ባለሀብቶችና በሥራ ፈጣሪ ዜጎች ነው!" ብለዋል።
አቶ ሰኢድ አያይዘውም የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ከህልም ወደ እውነት ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ያድናል ሲሉ አብስረዋል።
ኢንጂነር ናሆም መገርሣ በ5,000 ካሬ ላይ የሚገኘው ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ለ123 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ተዘዋዋሪ የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት ለቀጣናው የኢኮኖሚ እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኒፋክቸሪንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ፋብሪካው በዞኑ የመጀመሪያው የብረት ፋብሪካ መሆኑን አስረድተዋል።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ጥራታቸውን የጠበቁ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በመገንባትና በማስረከብ ከሚታወቀው የሀሮት ሪል እስቴት ጋር እህት ኩባንያ ነው።
ሀሮት ሪል እስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለህብረተሰቡ በማቅረቡ የኢትዮ ህይ 2025 የሪል እስቴት አዋርድ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።
የፋብሪካው አመራሮች ለዚህ ስኬት መገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ለቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር፣ ለባለሙያዎች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
የሀሮት ሪል ስቴት የማርኬቲንግ ኃላፊ ፋንትሽ ሸዋ እንደገለጹት፤ ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ ነው። ተቋሙ ከተመሰረተ 4ኛ ዓመቱን እያከበረ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ ድርጅቱ ለደንበኞቹ በገባው ቃል መሠረት በቦሌ ቡልቡላ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች በይፋ አስረክቧል።
በተጨማሪም ከሁለት ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ በመስቀል ፍላወር፣ በሀያት ፈረስ ቤት እና በቦሌ ቡልቡላ አካባቢዎች የሚገነቡ ተጨማሪ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች እንደሚያስረክብ አስታውቀዋል።
ሀሮት ሪል ስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለገበያ በማቅረቡ በፈረንጆቹ 2025 በተካሄደው የኢትዮ ሪል ስቴት ሽልማት መርሃ ግብር ላይ በጥራትና በዋጋ አቅርቦት የአሸናፊነት ክብርን ያገኘ ድርጅት መሆኑ አብራርታለች።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴልና በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቱን ይበልጥ በማስፋፋት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ባለሃብቱ አቶ ሰኢድ ይህ ስኬት የአንድ ሰው ጥረትና ውጤት ብቻ አይደለም። ከጀርባው ብዙ እጆች፣ ብዙ ዱአዎች እና ጸሎቶች፣ ብዙ ምክሮች ያሉበት ነው። በዚህ መሠረት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ ለኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ለጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲናው አበባ ልማት አ/ማሀበር ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ለባለሙያዎች እና ለሠራተኞቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ሰኢድ የትምህርት ሕይወታቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጥታ የተቀላቀሉት የንግዱን ዓለም ሲሆን፣ መጀመሪያ ላይ በመኪና መለዋወጫ ንግድ በመሰማራትና በመቀጠልም ወደ አስመጪና ላኪነት ዘርፍ በመሸጋገር ረጅም ዓመታትን አሳልፈዋል። በሂደትም የንግድ ሥራቸውን በማስፋት የጀመሩት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ገና በጅማሮው ከፍተኛ የምስጋና ሽልማትና ዕውቅናን ሊያጎናጽፋቸው ችሏል። ባለሀብቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ ዘርፍ በስፋት በመግባት ላይ ይገኛሉ።
በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ያጋጠማቸው የአስተዳደር ፈተና ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሰይድ ሲመልሱ፣ ምንም ዓይነት ችግር እንዳልገጠማቸው በአጽንኦት ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ ከላይ እስከ ታች ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር አካላት አንድ ባለሀብት እውነተኛ አልሚ መሆኑን ከተረዱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ሰይድ፣ ለእሳቸውም የተደረገላቸውን ተገቢውን ድጋፍና ትብብር በሙሉ አመስግነዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ
"በዞናችን ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች ሁሉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዝግጁ ነን፣ በቁርጠኝነትም እንሠራለን! ... ዛሬ ኑ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፦ "የጉራጌ ማህበረሰብ በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች ከተሞችን በማልማትና ጠንካራ የንግድ ሥርዓት በመዘርጋት የሚታወቅ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ባለሀብቶች ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው በልማት እየሳተፉ መሆኑ እጅግ ያስደስታል። ይህ ፋብሪካ የሀገር ሀብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል። ሌሎች ባለሀብቶችም በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።"ለአገርና ለሕዝብ መልዕክታቸውን አሰምተዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አባስ መሀመድን ጨምሮ በርካታ የአመራር አካላት ተገኝተዋል።
"Vita, saluti, peace, life" blends Italian and English expressions of well-being, translating roughly to "life, greetings, peace, and life." This combination evokes a deep desire for a harmonious, healthy existence filled with good energy and wellness.
#manufacturing #factoryinauguration #centralethiopia #guragezone #investment #harotrealestate #vitasaluti #economicgrowth #realestate #housing #bolebulbula #homeownership #ethiopianbusiness #ኢንቨስትመንት #ሪልስቴት #ኢንዱስትሪ #ልማት #የሥራዕድል #ቢዝነስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2.3 ትሪሊዮን ብር ለላቀ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር
***************
የላቀ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለማምጣትና የተጀመሩ ሀገራዊ የለውጥ ጥረቶችን ለማሳካት፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2019 በጀት ዓመት የፌደራል መንግሥት በጀት 2.3 ትሪሊዮን ብር ሆኖ እንዲጸድቅ ረቂቅ ሰነዱን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።
ይህ የተመደበው በጀት ባለፉት አምስት ዓመታት ከተመዘገቡት ስኬቶች መነሻነት፣ እንዲሁም የአስር ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ አካል በሆነው የልማትና ኢንቨስትመንት ግቦች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ይህ የበጀት መጠን ማደግ መንግሥት ካለው የማስፈጸም አቅምና የፊስካል ፖሊሲ ጥንካሬ ጋር የተያያዘ ነው።
መንግሥት በአንድ በኩል ያለው ገቢ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ያሳየ ሲሆን፣ ይህም ገቢ ከታክስ የሚሰበስበውን፣ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ብድሮችና እርዳታዎች፣ እንዲሁም በኤክስፖርት እና ከዲያስፖራ የሚገኘውን ገቢ እንደሚጨምር አስገንዝበዋል።
ባለፉት ጊዜያት የተጀመሩ እና የተጠናቀቁ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የመፈጸም አቅም በተግባር ያሳዩ መሆናቸውን አመላክተዋል። በዚህ መነሻነትም ካለፈው በተሻለ የ2019 በጀትም ለተለያዩ ፕሮጀክቶችና ማህበራዊ አገልግሎቶች ሊውል የሚችል በጀት መሆኑን ጠቅሰዋል።
ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ አያይዘውም የ2019 በጀት ከ2018 ብልጫ ማሳየቱ በትምህርት፣ በጤና፣ በመሰረተ ልማት እና በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ሰፊ መሻሻሎችን ለማምጣት ትልቅ ትርጉም እንዳለው ጠቅሰዋል። ሆኖም የታሰበውን የኢኮኖሚ እድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ባለሙያው ጠቁመዋል።
ሀገራችን ያላትን የሰው ኃይል፣ የውኃ፣ የግብርና እና የማዕድን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት፣ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና ሕገወጥ ንግድን በቁርጠኝነት መግታት እንደሚገባ ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ ገልጸዋል።
ለዚህም የሲቪል ማህበረሰቡ እና የሚዲያ ተቋማት በንቃት በመሳተፍ ሕገወጥ አሰራሮችን እንዲያጋልጡና የሕግ የበላይነት እንዲከበር ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው፣ የዘንድሮው የ2.3 ትሪሊዮን ብር ረቂቅ በጀት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ አቅምና የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው ብለዋል።
በቤተልሔም ገረመው
#ethiopianbudget #budget2019ec #economicgrowth #ethiopianbroadcastingcorporation

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ነው - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
*************************
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፤ ይህም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል ብሏል።
ያለፉት ዓመታት እውነታ በግልጽ እንደሚያሳየው፣ የመንግሥት ቃል የተስፋ ቃል ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም የተከናወኑት ውጤት ተኮር ተግባራት እና የተመዘገቡት ውጤቶች በተጨባጭ የሚታዩ ናቸው ብሏል።
ይህን መነቃቃት መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በ2018 በጀት ዓመት 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢኮኖሚ ዕድገቱ ግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎችን ያካተተና ሰፊ መሠረት ያለው ሲሆን፣ በሂደት ግን ኢንዱስትሪው የዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየወጣ ይገኛል።
ይህም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭመራና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነ መግለጫው ያትታል።
እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ሲሆኑ፣ በዚህም አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ በማሳየት 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይህም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው።
ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂያዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረትን ጨምሮ ውጫዊ ጫናዎች ባሉበት ወቅት ነው።
የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፣ ይህም የሀገራችንን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል።
ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ።
#ethiopia #pmoethiopia #economicgrowth #homegrowneconomicreform #ebc

ቢሊየነሮች ወደ ውጪ ማየት ጀመሩ
#ethiopia | በሕንድ የአገር ውስጥ
የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት መቀነሱንና የንግድ እንቅስቃሴው መዳከሙን ተከትሎ፣ የሀገሪቱ ታዋቂ ቢሊየነሮች በውጭ አገራት የሚገኙ ትልልቅ ኩባንያዎችን በከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በስፋት በመግዛት ላይ ይገኛሉ።
የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ ይህ የሕንዳውያን ባለሀብቶች ከፍተኛ የካፒታል ሽግግር በአገር ውስጥ ሊገጥማቸው የሚችለውን የገበያ ስጋት ለመቀነስና አዳዲስ ዓለም አቀፍ የቢዝነስ ዕድሎችን ለመጠቀም ያለመ መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#indiaeconomy #globalbusiness #billionaires #investment Shift #economicgrowth #bbcnews #marketexpansion

3 months ago
"አፍሪካ ውስጥ 10.2 ፐርሰንት እድገት የምታስመዘግብ ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት፤ ይህን እድገት እናፋጥን።"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #pmabiyahmed #economicgrowth
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #pmabiyahmed #economicgrowth
3 months ago
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመዘገቡ አስደናቂ ስኬቶች
********************
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተከናወኑ የተቀናጁ የልማት ሥራዎች 96 ሺህ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር የተቻለ ሲሆን፣ የመንግሥት የልማት ድርጅቶችም 2.1 ትሪሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማስመዝገብ ችለዋል።
የማምረቻ ዘርፉ የገበያ ድርሻ ከ25 በመቶ ወደ 46 በመቶ በማደግ ከፍተኛ እመርታ የታየበት ሲሆን፣ በወርቅ ኤክስፖርት ረገድም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል።
እነዚህ አሃዛዊ እውነታዎች የሀገራችን የኢኮኖሚ ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው።
#ethiopia #economicgrowth #jobcreation #exportsuccess

የኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከዛሬ ጥረት እስከ ነገው ብሩህ ተስፋ
*************
የዘንድሮው የሠርቶ አደሮች ቀን በኢትዮጵያ ሲከበር ሀገራችን የሰው ኃይሏን ወደ ምርታማነት ለመቀየር እያከናወነች ያለችው መጠነ-ሰፊ ተግባር ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት የተመዘገበው የ9.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ወደ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ ስኬት ለዜጎች አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደ የጀርባ አጥንት ያገለግላል።
በተለይም የኢንዱስትሪው ዘርፍ የ13.2 በመቶ እና የግብርናው ዘርፍ የ7.9 በመቶ ዕድገት ማስመዝገባቸው ለቋሚና ለጊዜያዊ የሥራ ዕድል ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ እና የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ደግሞ ወጣቶች በቤታቸው ሆነው ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲሠሩ አዲስ በር ከፍቷል።
እንደ ኮሪደር ልማት ያሉ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው።
በሌላ በኩል በሕጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው የመንግሥትን መዋቅራዊ ሪፎርም ውጤታማነት ያሳያል።
የስታርትአፕ አዋጅ መጽደቅና የብድር አቅርቦት ማሻሻያዎች ተዳምረው ኢትዮጵያን ሰፊ የሥራ ዕድል እየተፈጠረባት ያለች የነገዋ ብሩህ ሀገር እየሆነች ነው።
ሙሉ መረጃውን ለማንበብ በአስተያየት መስጫው ውስጥ ያለውን ሊንክ ይመልከቱ 🔗👇
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #jobcreation #economicgrowth #digitalethiopia #laborday #homegrowneconomy

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ አዲሱ ስልት ወጪን በመቀነስ ጥራትን ማረጋገጥ ነው
*********************
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ አሁን ላይ ከቦታ ምርጫ ጀምሮ ወደ ስትራቴጂካዊ የኤክስፖርት ኮሪደሮች በማምራት ላይ ይገኛል።
ለዚህም እንደ ማሳያ በሀገር ውስጥ ኩባንያዎችና ባለሙያዎች የተገነባው ቦሌ ለሚ 3 የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ወጪን በ50 በመቶ በመቀነስ የተሻለ ጥራት ሊመዘገብበት ችሏል።
ይህ አዲስ የሥራ አቀራረብ አላስፈላጊ ዕዳን ከመቀነሱም በላይ የሀብት ብክነትን በመከላከል ረገድ ትልቅ ስኬት እያስመዘገበ ይገኛል።
ዝርዝር መረጃውን በኢንፎግራፊክሱ ላይ ይመልከቱ።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #industryparks #economicgrowth #infrastructure #success

"ኢትዮጵያ ታምርት" የጎዳና ላይ ሩጫ
ነገ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል
#ethiopia | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር "ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 4ኛው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ነገ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።
ዓላማው
የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅና በራስ አቅም የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለገበያ ማሳየት ነው።
ተሳታፊዎ
ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና በግል የሚወዳደሩ ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ።
የገንዘብ ሽልማት
በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፦
1ኛ፦ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር
2ኛ፦ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር
3ኛ፦ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር
ይሄ ሩጫ ተራ ስፖርታዊ ውድድር አይደለም፤ የኢኮኖሚ ነጻነታችንን የምናውጅበት መድረክ ነው። 'ኢትዮጵያ ታምርት' በሚል መሪ ቃል የምናደርገው ይሄ ንቅናቄ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህላችንን ያሳድጋል። ነገ መስቀል አደባባይ የሚገኙ 15 ሺህ ሯጮች የሀገራቸውን ምርት እየለበሱ ለሀገራዊ ብልጽግና እንደሚሮጡ ጥርጥር የለኝም።
ነገ መስቀል አደባባይ ለሀገር ምርትና ለጤና እንሮጣለን
#getu #ethiopiatamirt #industryethiopia #10krun #addisababaevents #localproduction #economicgrowth #ethiopianathletics #ኢትዮጵያታምርት #የጎዳናላይሩጫ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ሚድሮክ 10 ማርዮት ሆቴሎችን በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ግዙፉ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ከዓለም አቀፉ የሆቴል ሰንሰለት ማርዮት (Marriott) ጋር በመተባበር በመላ ሀገሪቱ 10 ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን ለመገንባት ማቀዱን ይፋ አደረገ።
በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው "Invest Ethiopia 2026" ፎረም ላይ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ እንደገለጹት፤ ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) ድጋፍ እየተደረገለት ይገኛል።
ሚድሮክ በሆቴል ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ቁልፍ ዘርፎችም ክንፉን እያሰፋ ይገኛል፦
በ25 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የቡና ልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው።
በዘርፉ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በጋምቤላ ክልል በዝናብ መዛባት ምክንያት ተግዳሮቶች ቢያጋጥሙም፣ ኩባንያው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል።
ይህ ተነሳሽነት በሀገሪቱ ያለውን የንግድ ተነቃቃይነት ከማሳደጉም ባለፈ፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #investment #midroc #ebr #marriotthotels #tourism #investethiopia2026 #economicgrowth #addisababa

የኢትዮጵያ አረንጓዴ ወርቅ
10ኛው የሆርቲፍሎራ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ
#ethiopia | ዛሬ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያን የሆርቲካልቸር ዘርፍ ዕድገት የሚያሳይ ታላቅ ኤክስፖ በይፋ ተከፍቷል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ50 በላይ ሀገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት፦ ሆርቲካልቸር ከቡና በመቀጠል ለኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቅ የውጭ ምንዛሬ አስገኝ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል።
ከአጠቃላይ የዘርፉ ገቢ 80 በመቶ የሚሆነው ከአበባ ኤክስፖርት የሚገኝ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ ላኪ ለመሆን በቅታለች።
ከ150 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኤግዚቢተሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ አምራቾችን፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችንና ዓለም አቀፍ ገዢዎችን በአንድ መድረክ አገናኝቷል።
በፖሊሲና በመመሪያ ደረጃ እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች በፍራፍሬ፣ በአትክልትና በቅመማ ቅመም ኤክስፖርት ላይ አዲስ መነቃቃት ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኤክስፖው እስከ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆይ በመሆኑ፣ የዘርፉን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና የገበያ ትስስሮች ለመመልከት አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል በመገኘት እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
#getu #ethiopia #hortiflora2026 #horticultureexpo #ethiopianflowers #agriculture #exporttrade #addisababa #economicgrowth #hortiflora #ሆርቲፍሎራ #አበባናአትክልት #ኤክስፖ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
ካፒታል የቁጠባና ብድር ማህበር በቤቴል አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ
#ethiopia | ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት፣ በቤቴል አካባቢ አዲስ ቅርንጫፉን በድምቀት መርቆ ሥራ አስጀምሯል።
ይህ አዲስ ቅርንጫፍ በተለይ የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የቁጠባና የብድር አማራጮችን ለደንበኞች ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በምረቃው ወቅት የተገኙት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ
አቶ ደረጀ መኮንን ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ ያለው ስኬት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ አዲሱ ቅርንጫፍ የአባላትን የፋይናንስ ፍላጎት በቅርበት ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አረጋግጠዋል።
የካፒታል የቁጠባና ብድር ማህበር ሥራ አስኪያጅ
አቶ ጅሬኛ ነገሬ ቅርንጫፉ ለአካባቢው ነዋሪዎችና አባላት ቀላልና ተመጣጣኝ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት፣ በግለሰቦችና በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የማህበሩ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen
#capitalsacco #ethiopianfinance #bethelbranch #savingandcredit #interestfreebanking #economicgrowth #getutemesgen

6 months ago
''የቡና ዛፍ፣የፍቅር ዛፍ ነው''
📌2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ፌስቲቫል በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሄደ!
#ethiopia | የኢትዮጵያን ጥልቅ የቡና ባህልና ለሀገር አንድነት ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ 2ኛው የኢትዮጵያ የቡና ባህል ፌስቲቫል ታሪካዊ በሆነው በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት ተከናውኗል።
በዋርካ ኮፊ ኃ/የተ/የግ/ማህበር አዘጋጅነት "የቡና ባህላችን ለሀገራዊ አንድነታችንና ለኢኮኖሚ እድገታችን" በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ፌስቲቫል፣ ከቡና መጠጣት ስነ-ስርዓት ባለፈ ትልቅ ሀገራዊ ግብን ያነገበ ነው።
የፌስቲቫሉ ዋና ዋና ክንውኖች
* የዩኔስኮ (UNESCO) ንቅናቄ፦ የዋርካ ኮፊ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሰአዳ ሙስጠፋ እንደገለጹት፣ ይህ ፌስቲቫል የኢትዮጵያ የቡና ባህል በዓለም አቀፉ የቅርስ ተቋም (UNESCO) እንዲመዘገብ የሚደረገው ጥረት አካልና ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
* ባህላዊ ውበት፦ የአስራ አንዱም ክልሎች ልዩ የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት፣ ማራኪ ባህላዊ አልባሳትና የቁሳቁስ አውደ-ርዕይ ለዕይታ ቀርቧል።
* ጥበብና ባዛር፦ ከቡናው መዓዛ ጋር ተደምሮ የስዕል ኤግዚቢሽኖች፣ የእደ-ጥበብ ስራዎች ባዛር እና የተለያዩ ዝግጅቶች መርሃ-ግብሩን አድምቀውታል።
በተጨማሪም በነገረ ቡና ላይ ያተኮረ ውይይት የተከናወነ ሲሆን ''የቡና ዛፍ፣የፍቅር ዛፍ ነው'' የሚሉ እና ልዩ ልዩ ሃሳቦችን በውስጣቸው የያዙ የውይይት ሃሳቦች ተነስተዋል።
የክብር እንግዶች
በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ተወካዮች፣ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የቅርስ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የቡና ላኪዎችና ተመራማሪዎች ተገኝተው የኢትዮጵያን የቡና ጥበብ ታዝበዋል።
ይህ ፌስቲቫል ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ ቡናን ከማህበራዊ ትስስርና ከኢኮኖሚ እድገት ጋር አቀናጅታ የያዘች ድንቅ ሀገር መሆኗን ለዓለም ዳግም ያስመሰከረ ሆኖ አልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #coffeeculture #warkacoffee #adwamemorial #unesco #ethiopiancoffee #unity #economicgrowth #addisababa

💰 5 ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጣው የከርሰ-ምድር ሀብት በአፍሪካ
#ethiopia | የሚቆጠር የወርቅ ክምችት ላይ ተቀምጣ መገኘቷ ተበሰረ። የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን (AFC) ባወጣው አዲስ ሪፖርት መሠረት፣ አህጉሪቱ ከ5 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት የወርቅ ሀብት ባለቤት ናት።
ከዚህ እጅግ ግዙፍ ሀብት ውስጥ ደግሞ 1 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋው እስካሁን ድረስ የሰው እጅ ያልነካውና በከርሰ-ምድር ውስጥ የሚገኝ መሆኑ ተገልጿል።
🌍 የዓለም የኢኮኖሚ ትኩረትና የአፍሪካ ሚና
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የጂኦ-ፖለቲካዊ አለመረጋጋት፣ ማዕከላዊ ባንኮች ፊታቸውን ወደ ወርቅ ክምችት እንዲያዞሩ አድርጓቸዋል። ሪፖርቱ እንደሚያመለክተው፦
* የዋጋ ንረት፦ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 5,000 ዶላርን በመሻገሩ፣ አፍሪካ ያላት ክምችት ከፍተኛ የማክሮ-ኢኮኖሚ አቅም ፈጥሮላታል።
* የመጠባበቂያ ሀብት፦ አህጉሪቱ ይህን ሀብቷን በመጠቀም የውጭ ምንዛሬ እጥረትን መቅረፍና የኢኮኖሚ ጫናዎችን መቋቋም ትችላለች።
🇬🇭 የጋና ተሞክሮ እንደ አርአያ
የጋና መንግስት በቅርቡ የጀመረው የወርቅ ዘርፍ ማሻሻያ ለሌሎች አገራት ትልቅ ትምህርት ሆኗል። መንግስት ወርቅን በቀጥታ በመግዛት የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያውን ማሳደጉ፣ የሀገሪቱን የገንዘብ ምንዛሬ (ሲዲ) ለማረጋጋት ትልቅ እገዛ ማድረጉ ተጠቁሟል።
"ይህ ያልተነካ የአፍሪካ ሀብት በአግባቡ ስራ ላይ ከዋለ፣ አህጉሪቱ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ገበያ ላይ ያላትን ተጽዕኖ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።"
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አፍሪካ #ወርቅ #ኢኮኖሚ #የአፍሪካ_ፋይናንስ_ኮርፖሬሽን #ልማት #africagold #economicgrowth #afc

7 months ago
በአፍሪካ ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በጥር ወር ይጀመራል
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፍሪካ ትልቁ እንደሚሆን የሚጠበቀው የቢሾፍቱ (አቡሴራ) ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በዚህ በጥር ወር በይፋ እንደሚጀመር አስታወቀ።
በ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አቡሴራ በተባለ ሥፍራ በ3,975 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የመንገደኞች አቅም፦ ግንባታው በሁለት ምዕራፍ የሚካሄድ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 60 ሚሊዮን፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ደግሞ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።
* ዘመናዊ መሰረተ ልማት፦ አውሮፕላን ማረፊያው ሁለት ተርሚናሎች፣ ሁለት የመንደርደሪያ መንገዶች (Runways)፣ የጥገና ማዕከል፣ የካርጎ መንደር፣ ዘመናዊ ሆቴሎች እና የንግድ ማዕከላትን ያካትታል።
* የትራንስፖርት ትስስር፦ ከአዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በፈጣን ባቡር እና በመኪና መንገድ የሚገናኝ ይሆናል።
* አረንጓዴ ቴክኖሎጂ፦ አውሮፕላን ማረፊያው የፀሐይ ኃይልን የሚጠቀምና አካባቢን የማይበክል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ የሚገነባ ነው።
ፋይናንስ እና ማህበራዊ ኃላፊነት🔎
ለግንባታው ከሚያስፈልገው 10 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 20 በመቶው በአየር መንገዱ ሲሸፈን፣ ቀሪው 80 በመቶ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ፋይናንስ ይደረጋል። አየር መንገዱ ከይዞታቸው ለሚነሱ አርሶ አደሮችም 350 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ ዘመናዊ ቪላ ቤቶችንና የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ማዕከላትን እየገነባ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ፕሮጀክት የአፍሪካ ህብረት "የተሳሰረች አፍሪካን" የመፍጠር ራዕይ እንዲሳካ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #ethiopianairlines #bishoftuairport #megaproject #aviationafrica #economicgrowth
N

🚆 የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ፃፈ
* በቀን 14 ባቡሮች በመስመር ላይ
#ethiopia | የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አገልግሎት መጀመሩን ተከትሎ ታይቶ የማይታወቅ አዲስ የሥራ ክንውን ማስመዝገቡን አስታወቀ። ተቋሙ በአንድ ቀን ብቻ 14 ባቡሮችን (7 የባቡር ጥንዶችን) በተሳካ ሁኔታ በማንቀሳቀስ የሎጂስቲክስ አቅሙን ለዓለም አሳይቷል።
📦 የጭነት ትራንስፖርት ስኬት
ከተሰማሩት 14 ባቡሮች መካከል 11ዱ የጭነት ባቡሮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ፦
4ቱ የኢትዮጵያን ምርት ወደ ውጭ የላኩ (Export)፣
7ቱ ደግሞ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ (Import) የንግድ ቁሳቁሶችን የጫኑ ናቸው።
ይህም ተቋሙ የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ በታመነ እና ቀልጣፋ መንገድ የመሸከም ብቃቱን በተግባር ያረጋገጠበት ሆኗል።
Passenger & Tourism | የመንገደኞችና የቱሪዝም አገልግሎት
በእለቱ ከጭነት ባሻገር በመንገደኞች ዘርፍም የላቀ አፈፃፀም ተመዝግቧል። በቀን ውስጥ 3 የመንገደኞች ባቡሮች አገልግሎት የሰጡ ሲሆን፦
አንድ የሀገር ውስጥ የባቡር ጉዞ፣
አንድ ዓለም አቀፍ (አዲስ አበባ - ጅቡቲ) ጉዞ፣
አንድ ልዩ የቱሪዝም ፓኬጅ አገልግሎት ተከናውኗል።
🚀 የወደፊት ዕቅድ
የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር (EDR) በዚህ ስኬት ሳይወሰን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቀን የሚንቀሳቀሱ የባቡር ስብስቦችን ወደ 16 (8 የባቡር ጥንዶች) ከፍ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። ይህም የሀገሪቱን የዲጂታልና የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል።
#ethiopia #djibouti #edr #railwaysuccess #logistics #tourismethiopia #economicgrowth #ethiodjiboutirailway

Comments