3 hours ago
4ሺህ የሚደርሱ መኪኖች እና ማሽነሪዎች እየተሳተፉበት የሚገኘው የቢሾፍቱ ኢንተርናሽናል ኤርፖርት
#ethiopia #bishoftuairport #megaproject #abiyahmed #aviationhub
5 months ago
🇪🇹 የአድዋ ድል ተደጋገመ!! ✈️
ጠላቶቿ ሊያጠፏት በሞከሩ ቁጥር ይበልጥ የምታብብ ሀገር - ኢትዮጵያ!!
ኢትዮጵያ ከአድዋ መልስ አባይን በመገደብ ታሪክ ሰራች፤ አሁን ደግሞ በአቪዬሽን ታሪክ የጥቁር ህዝቦችን ታሪክ የሚለውጥ አዲስ ጀብዱ በቢሾፍቱ (አቡሴራ) ጀምራለች!
ትናንት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት ይህ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት፤ ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ የኢትዮጵያ ትልቁ ሜጋ ፕሮጀክት ነው።
የፕሮጀክቱ አስደናቂ እውነታዎች፡-
📍 ቦታ፡ ቢሾፍቱ (አቡሴራ)
💰 የግንባታ ወጪ፡ 12.5 ቢሊዮን ዶላር (ይገመታል)
👥 የመያዝ አቅም፡ በዓመት 110 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን ያስተናግዳል።
አንዳንዶች እንደሚሉት የአድዋን ድል መደጋገም የማይሰለቻት ብቸኛ ሀገር ኢትዮጵያ ናት!
እንኳን ደስ ያለን!! 🇪🇹👏
https://youtu.be/kQiuhPQbk...
#ethiopia #adwa #bishoftuairport #megaproject #aviation #history #africa

የኮይሻ ግድብ ግንባታ 72% ደረሰ! 🏗️⚡️
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በመገንባት ላይ የሚገኘው ግዙፉ የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ፤ የግንባታ አፈጻጸሙ 72 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን አስታወቀ።
የፕሮጀክቱ ወሳኝ ኩነቶች፡
💧 ከ2 ዓመት በኋላ፡ ግድቡ ውሃ መያዝ ይጀምራል።
✅ ከ3 ዓመት በኋላ፡ ግንባታው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።
📏 መጠኑ፡ 201 ሜትር ቁመት እና 1,012 ሜትር ርዝመት አለው።
ይህ ግድብ ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እና የኢንቨስትመንት እድገት ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት እንደሚያበረክት ይጠበቃል።
#ethiopia #koyshadam #greenenergy #megaproject #development

በአፍሪካ ግዙፉ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በጥር ወር ይጀመራል
#ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በአፍሪካ ትልቁ እንደሚሆን የሚጠበቀው የቢሾፍቱ (አቡሴራ) ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ በዚህ በጥር ወር በይፋ እንደሚጀመር አስታወቀ።
በ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የሚገነባው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው አቡሴራ በተባለ ሥፍራ በ3,975 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
* የመንገደኞች አቅም፦ ግንባታው በሁለት ምዕራፍ የሚካሄድ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 60 ሚሊዮን፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ ደግሞ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል።
* ዘመናዊ መሰረተ ልማት፦ አውሮፕላን ማረፊያው ሁለት ተርሚናሎች፣ ሁለት የመንደርደሪያ መንገዶች (Runways)፣ የጥገና ማዕከል፣ የካርጎ መንደር፣ ዘመናዊ ሆቴሎች እና የንግድ ማዕከላትን ያካትታል።
* የትራንስፖርት ትስስር፦ ከአዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በፈጣን ባቡር እና በመኪና መንገድ የሚገናኝ ይሆናል።
* አረንጓዴ ቴክኖሎጂ፦ አውሮፕላን ማረፊያው የፀሐይ ኃይልን የሚጠቀምና አካባቢን የማይበክል ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ የሚገነባ ነው።
ፋይናንስ እና ማህበራዊ ኃላፊነት🔎
ለግንባታው ከሚያስፈልገው 10 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 20 በመቶው በአየር መንገዱ ሲሸፈን፣ ቀሪው 80 በመቶ በአፍሪካ ልማት ባንክ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ፋይናንስ ይደረጋል። አየር መንገዱ ከይዞታቸው ለሚነሱ አርሶ አደሮችም 350 ሚሊዮን ዶላር በመመደብ ዘመናዊ ቪላ ቤቶችንና የአግሮ-ፕሮሰሲንግ ማዕከላትን እየገነባ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ፕሮጀክት የአፍሪካ ህብረት "የተሳሰረች አፍሪካን" የመፍጠር ራዕይ እንዲሳካ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #ethiopianairlines #bishoftuairport #megaproject #aviationafrica #economicgrowth
N

Sponsored by
Surafel
Comments