Logo
YenetaTube
12 hours ago
ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን (Leenat Charity Foundation) በአሜሪካ የተመሰረተ እና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ ያለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። እስካሁን በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በመድረስ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ሞዴስ፣ ደብተር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ አድርሰናል። በከሚሴ ብቻ ሶስት የተለያዩ ትምህርት ቤቶችን ደርሰን ድጋፋችንን አቅርበናል።

የህክምና ባለሙያና ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን መስራች የሆኑት የእናትፋንታ አስማማዉ እንደገለጹት፤ የበጎ አድራጎት ቡድኑ በወንድም ካሊድ ፋውንዴሽን ባደረገው ጉብኝት ለበርካታ አራሶች የንፅህና መጠበቂያዎችን (ሞዴስ) እና ለህፃናት ደግሞ ዳይፐሮችን ያበረከተ ሲሆን በተጨማሪም ፋውንዴሽኑ ለህፃናትና ለአናቶች የምሳ ግብዣ በማዘጋጀት አብሮነቱን አሳይቷል።

የፋውንዴሽኑ ቦርድና የበጎ አድራጎት ቡድን አባላትን ያሳተፈው ይህ ፕሮግራም፣ ድጋፍ የሚሹ አራሶችንና ህፃናትን ለማገዝ የተደረገ በጎ ተግባር መሆኑ ተገልጿል።

ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን በተለይም በገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን በማቅረብ፣ የጤና ትምህርት በመስጠትና ከኢንፌክሽን ቁጥጥር ጋር የተያያዙ ግንዛቤዎችን በመፍጠር ረገድ በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ተመላክቷል።

ለወደፊቱም በገጠር አካባቢዎች የሚገኙና የንፅህና መጠበቂያዎችን ለመግዛት አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በዘላቂነት ለመደገፍ፣ የንፅህና መጠበቂያ ሞዴሶችን እዚሁ አገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት ተቀርፆ እየተሰራ እንደሚገኝ መስራቿ ገልጸዋል።

በአሜሪካ የተመሰረተውና በኢትዮጵያ በተግባር የእርዳታ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ለእናት በጎ አድራጎት ፋውንዴሽን፤ እስካሁን በደብረ ብርሃን፣ ሻሸመኔ እና ከሚሴ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ሞዴስ፣ ደብተር እና የትምህርት ቁሳቁሶችን በቀጥታ ማድረሱ ታውቋል።

👉 ማገዝ ለምትፈልጉ
⚡️Cash | $Enat16
⚡️PayPal & Zelle | +16144056169
⚡️Abyssinia Bank | 266595832
⚡️Commercial Bank | 1000794295305

YenetaTube
12 hours ago
የህገመንግስት ማሻሻያ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍንጭ ሰጡ

በዛሬዉ ዕለት በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ተከናዉኗል፡፡

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሜ ተሰይመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባደረጉት ንግግር፤ በቀጣይ ጊዜያት በሀገራዊ ምክክር ምክረ ሀሳቦች መሠረት የህገመንግስት ማሻሻያ ይኖረናል ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ስለ ሀገሪቱ ቀጣናዊ ጉዳዮች አንስተዋል።

ቁምነገር አየለ

YenetaTube
11 hours ago
የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

YenetaTube
13 hours ago
የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

በነገሥታት ፊት የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ።

የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ገዳም ስትገባ የተቀደሰ ልጅ እንደምትወልድ ተነግሯት የተመለሰችው እናቱ ዮስቲና ትባላለች። ልጅም ሲወልዱ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔርም አንጸው አሳደጉት።

በቤተ ክርስቲያንም የሰማውን “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የምትል ጸሎት እጅጉን ቢወዳት ሌሊቱን ሙሉ በቤቱ እየጸለያት የሚጋደል ሆነ። አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ ጓደኞቹን “ዝናም ይዘንማልና ወደቤት እንግባ” አላቸው። ቃሉን ሊሰሙት ባይወዱ በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ኃይለኛ ዝናም ዘነመ። ገና በአዳጊነት እድሜውም ብዙ ተአምራት ያደርግ ነበር፡፡

በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል። እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ ጌታችን ተገለጠለት። አቡነ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡

ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ ስለማንበቡ፣ ስለተጋድሎው፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። ከሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትንና ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የብርሃን ሠረገላም ሰጠው፣ መታሰቢያውን የሚያደርጉትን እንደሚምርለትም፣ ቃል ኪዳን ገባለት። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ስትለይም ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፤ ገዳማቸውን እንደግፍ ከበረከታቸውም እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

YenetaTube
14 hours ago
የገንዘብ ሚኒስትር የነበሩት አቶ አህመድ ሺዴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ።

YenetaTube
16 hours ago
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ገና በቅድስት ሐና ማሕጸን ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ ተአምራት ታደርግ ነበር፡፡ አንድ አይኗን ያጣች ቤርሳቤህ የተባለች ሴት የሀናን መጽነስ ስትሰማ በደስታ ልትጎበኛት መጣች፡፡ ቅድስት ሐናን እንኳን ደስ አለሽ ብላ ሆዷን ከዳሰሰቻት በኋላ በዚያው እጇ ዓይኗን ብትነካው ዐይኗ በርቶላታል፡፡ ይህን ምሳሌ አደርገው ድውያን እየመጡ ሆዷን ዳሰው ይፈወሱ ነበር፡፡ በመካንነት የነበሩት ወላጆቿ ልጅ ከሰጣቸው ለቤተ እግዚአብሔር ሊሰጡ ስዕለት ገብተው በቅድስት ድንግል ማርያም መወለድ ፍሬ ሲያገኙ ዓለም ደግሞ የመድኃኒቱን እናት አጊኝቷል፡፡ እናታችን ቅድስት ሐና ጸንሳ ሳለች የአጓቷ ልጅ አርፎ እጅግ የአልጋውን ሸንኮር እየዞረች ስታለቅስ ከሞተበት ተነስቶ “የሰማይና የምድር ፈጣሪ አያት ሆይ ላንቺ ክብር ይገባሻል” ብሎ መስክሮ ተመልሶ አርፏል፡፡

አይሁድም “ቀድሞ የእነዚህ ዘር የነበሩ ዳዊትና ሰሎሞን አርባ፣ አርባ ዘመን ገዙን አሁን ከዚህች የሚወለድ ምን ሊያደርገን ነው?” ብለው በድንጋይ ሊወግሯት ተነሱ፡፡ የራማው ልዑል ቅዱሰ ገብርኤል ወደ ሊባኖስ ተራራ ወሰዳቸው፤ በእዚያም በጨለማ ውስጥ የነበረው ዓለም ብርሃን የሚያይባት፣ የእውነተኛው ጸሐይ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው በሦስት ዓመቷ ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨንቆ፤ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ሲቀርብ ወደ ላይ ራቀበት፡፡ በዚያ በተሰበሰቡትም ቢሞክሩ አልሆነም፡፡

ዘካርያስም ሐናን “እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ” አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት፤ በክብር ዐረገ፡፡ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም “የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር” ብለው ታህሣስ 3 ቀን ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለ12 ዓመታትም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ይህችን ብርሃን፣ የብርሃን እናት ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ዘወትር በጸሎታቸው ያስቧታል፡፡ ገዳማቸውን እናግዝ፣ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

YenetaTube
23 hours ago
አዲስ የመንግሥት ምስረታ እና የምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይካሄዳል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ እንዲሁም የኢፌዴሪ አዲስ የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ መስከረም 25/2019 ዓ.ም በይፋ እንደሚከናወን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።

አዲሱ የመንግሥት ምስረታ የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።

በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 58 ንኡስ አንቀጽ 2 በተደነገገው መሠረት የምክር ቤቱ ሥራ ዘመን በየዓመቱ በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ ይጀምራል።

እንዲሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ ወንበር ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ የፌደራሉን መንግሥት ሕግ አስፈጻሚ አካል ይፋ ያደረጋል።

በዚህም የተመረጠው አዲሱ መንግሥት በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ሀገሪቱንና ሕዝቧን የመምራት ኃላፊነት በይፋ ይረከባል።

YenetaTube
22 hours ago
የትምህርት ሚኒስቴር ለ2019 ዓ.ም የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በ2019 ዓ.ም በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች በዕጩ መምህርነት ለመሰልጠን ለሚወዳደሩ አመልካቾች መወዳደሪያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ለሁሉም ክልሎች እና ለከተማ አስተዳደሮች የትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ይፋዊ ደብዳቤ፤ የመቁረጫ ነጥቡ የተወሰነው የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ እና የ2018 ዓ.ም የፈተና ውጤት ባገናዘበ መልኩ መሆኑን ገልጿል።

በዚህም መሰረት በዲፕሎማ (12+2) እና በሰርተፊኬት (12+1) የሙያ ስልጠናዎች መግቢያ ነጥብ እንደሚከተለው ተወስኗል፦

ለዲፕሎማ (12+2) ፕሮግራም ፦

◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 215 እና ከዚያ በላይ

◦ ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 205 እና ከዚያ በላይ

◦ ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ በተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ አካል ጉዳት ያለባቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 185 እና ከዚያ በላይ

◦ በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውራን ወንድና ሴት ተማሪዎች 150 እና ከዚያ በላይ

ለሰርተፊኬት (12+1) ፕሮግራም ፦

- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 210 እና ከዚያ በላይ

- ለተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 195 እና ከዚያ በላይ

- ለአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች 180 እና ከዚያ በላይ

- ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች ተፈታኞች 180 እና ከዚያ በላይ

በደብዳቤው ላይ እንደተመለከተው፣ ይህ የተወሰነው መቁረጫ ነጥብ የሚያገለግለው ለ2019 ዓ.ም (2018 ዓም የ 12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ለወሰዱ) የዕጩ መምህራን ውድድር ብቻ ሲሆን፣ ሌሎች መስፈርቶች በዕጩ መምህራን ምልመላና መረጣ መመሪያ መሰረት ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተጠቅሷል።

@tikvahethiopia

YenetaTube
24 hours ago
የግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን መሪዎች በኢትዮጵያ ግጭትና በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የጋራ መግለጫ አወጡ

ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን በክልሉ እየተባባሰ የመጣውን ግጭት ለመፍታት ፖለቲካዊ እና ሰላማዊ መፍትሄዎች እንዲኖሩ ጥሪ አቀረቡ።

የአራቱ ሀገራት መሪዎች ማለትም የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ፣ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ እና የሱዳን ጦር አዛዥ አብዱልፈታህ አል ቡርሀን በግብፅ ኒው አላሜይን ከተማ ባደረጉት ስብሰባ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫው የኢትዮጵያን በርካታ ፖሊሲዎች የሚቃወም ሲሆን፣ አዲስ አበባን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላቸውን ልዩነት የሚያሰፋ ነው።

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ኤርትራን ጨምሮ ግብፅ እና ሱዳን በመንግሥቱ ላይ የሚዋጉትን የታጣቂዎች ጥምረት ይደግፋሉ ሲል ሲከስ, ባለስልጣናቱ ግን ተሳትፎውን አስተባብለዋል።

የኤርትራ የመረጃ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በበኩላቸው አዲስ አበባ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ምክንያት እየፈለገች ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። እንዲሁም መሪዎቹ የቀይ ባህር ቁጥጥር በባህር ዳርቻ ሀገራት እጅ ብቻ መሆን እንዳለበት የገለጹ ሲሆን፣ ይህም የባህር በር ፍላጎት ላላት ኢትዮጵያ የተሰጠ ምላሽ ተደርጎ ታይቷል።

ግብፅና ሱዳንም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በታችኛዋ ሀገራት ላይ ጉዳት የሚያደርሱ «የአንድ ወገን የተናጥል እርምጃዎችን» አስመልክቶ ስጋታቸውን አንስተዋል።

YenetaTube
2 days ago
የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ረድኤት እና ምልጃ አይለየን🙏

በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡

አባታቸው ጸጋ ዘአብና እናታቸው እግዚእ ኃረያ ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በአንድ ወቅት ታዳጊው ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ለስብከተ ወንጌል እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡

ወላጆቻቸው ካረፉ በኋላም ንብረታቸውን ሁሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ሲወርዱ ገመዱ ቢበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን አጥምቀዋል፤ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡ በደብረ ሊባኖስ ገዳም አስቦ ዋሻ በዙሪያቸው ስምንት ጦሮች ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት በማሰብ ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት አንድ እግራቸው ተሰብራል፡፡

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ለምነዋል፡፡ ከዚህ ዓለም ድካም በሚያርፉበት ነሐሴ 24 ቀንም ጌታችን ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጥቶ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል፡፡

የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ሁሉ ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉና ከበረከታቸው እንድንሳተፍ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

YenetaTube
2 days ago
በተለያዩ አካባቢዎች የሚጠየቀው የአሽከርካሪዎች የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱ ተገለጸ

👉በ2019 የኮቴ ክፍያን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይሰራል ተብሏል

በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እና በፌደሬሽኑ ቅንጅታዊ አሰራር በተከናወነ ሥራ አሽከርካሪዎች የሚጠየቁት አግባብነት የሌለው የኮቴ ክፍያ በ70% መቀነሱን የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሰሪዎች ፌደሬሽን አስታውቋል።

የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንደተናገሩት፤ ክፍያው በሀገሪቱ ሕግ የማይፈቀድ በመሆኑ ከክልሎች ጋር በተደረገ ውይይት እንዲቀንስ ተደርጓል።

በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በጂቡቲ ኮሪደር የሚጠየቀው ክፍያ መቀነሱን ተናግረዋል።

የኮቴ ክፍያ አሁንም ባልቀረባቸው አካባቢዎች በ2019 የበጀት ዓመት ሙሉ ለሙሉ ለማስቀረት መንግሥት እና ፌደሬሽኑ በትኩረት እንደሚሠሩ አቶ ብርሃኔ ዘሩ ገልጸዋል።

በህይወቴ ጌትነት

YenetaTube
2 days ago
የቅዱስ ገብርኤል ምልጃ እና ረድኤት አይለየን፤ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን🙏

“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” 🙏

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ” ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡

አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

YenetaTube
2 days ago
ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ 81 መሰረታዊ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግስት አስረከበ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ እና አዲስ ፖሊሲ የሚፈልጉ 81 መሰረታዊ ምክረ ሐሳቦችን ለመንግስት ማስረከቡን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በአጠቃላይ 394 ምክረ ሐሳቦችን አዘጋጅቶ ማስረከቡን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አጀንዳዎቹን ለክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እንዲሁም ለአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች አስረክበዋል።

የትግራይ ክልልን አጀንዳ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘው ተሻገር በይፋ ተረክበዋል። የፌደራል መንግስትን የተመለከተውን አጀንዳ ከምክረ ሐሳብ ጋር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ተረክበዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን የቀረቡት ምክረ ሐሳቦች ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስበዋል። ዋና ኮሚሽነሩ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሰረት ትግበራዊ ክትትል እንደሚያስፈልገው ጠቁመዋል።

በተለይም አዲስ የሚቋቋመው መንግስት በዚህ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ በአዋጅ የተሰጠው የሦስት ዓመት የሥራ ዘመን የነበረ ቢሆንም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ጊዜው ሁለት ጊዜ ተራዝሞለታል። በዚሁ መሰረት በየካቲት 2017 ዓ.ም ለአንድ ዓመት እንዲሁም በየካቲት 2018 ዓ.ም ለተጨማሪ ስምንት ወራት መራዘሙ ይታወሳል። የኮሚሽኑ የተራዘመ የሥራ ዘመን በያዝነው የ2019 ዓ.ም. ጥቅምት ወር በይፋ ያበቃል።

አሐዱ_ሬዲዮ

YenetaTube
2 days ago
እንኳን ለአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ታኅሣሥ 24 ቀን 1212 ዓ.ም ከካህኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድና በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ብሥራት ተወለዱ፡፡

ወላጆቻቸውም ፍሥሐ ጽዮን ብለው ሰየሟቸው፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት ሥላሴን አመስግነዋል፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው መዓርገ ዲቊናን፣ በ22 ዓመታቸው ደግሞ መዓርገ ቅስናን ከግብጻዊው ጳጳስ አባ ቄርሎስ ተቀብለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ሕፃኑ ፍሥሐ ጽዮን ወደ ጫካ ለአደን በሔዱበት ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ ጸጋ መንፈስ ቅዱን አሳደረባቸው፡፡ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወንጌል ወዳልተዳረሰበት ቦታ እንደሚልካቸውም አስረዳቸው፡፡

ቅዱስ ሚካኤልም ከአዳኝነት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመመለስ እንደተመረጡ፣ ስማቸውም ተክለ ሃይማኖት እንደሚባል፣ ትርጓሜውም ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት እንደሆነ አበሠራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ያላቸውን ንብረት ዅሉ ለቤተ ክርስቲያንና ለነዳያን ሰጥተው “አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የመንግሥተ ሰማያትን በር ትከፍትልኝ ዘንድ እነሆ ቤቴን እንደ ተከፈተ ተውኹልህ” በማለት ቤታቸውን ትተው ወንጌልን ለማስተማር ፈጥነው ወጡ፡፡ በደብረ ዳሞ ገዳምም ለ12 ዓመታት ተቀምጠው ከዚያ ሲወርዱ ገመዱ ገመዱ ሲበጠስ ስድስት ክንፍ አውጥተው በረዋል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምረው በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ ወንጌልን በመስበክና ተአምራትን በማድረግ በርካታ አሕዛብን ከአምልኮተ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር፤ ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናትንም አሳንጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ በደብረ ሊባኖስ ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባትም በዙሪያቸው ስምንት ጦሮችን ተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማም፣ ሞትና ነገረ መስቀል በማሰብ በተመስጦ ለ22 ሌሊትና ቀን ያለ ማቋረጥ በጾምና በጸሎት ተወስነው ሲጋደሉ፤ ከመቆም ብዛት የአንድ እግራቸው አገዳ ተሰብራል፡፡ ደቀ መዛሙርቱም የመንፈሳዊ አባታቸውን የዐፅም ስባሪ አክብረው አኑረውታል፡፡ እግራቸው ከተሰበረ በኋላም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ሌሊትና ቀን ጸንተው ለሰው ዘር ሁሉ ድኅነትን ሲለምኑ ጥቂት ውኃ እንኳ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ እንደ ነበረ መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል፡፡ ጻድቁ አባታችን ምድራዊ ሕይወታቸውን በተጋድሎና በሐዋርያዊ አገልግሎት ከፈጸሙ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፉበት ቀን ሲቃረበ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅዱሳን መላእክት፣ ከወዳጆቹ ጋር መጣ፡፡

በስማቸው መታሰቢያ ለሚያደርጉ፣ ለነዳያን ለሚመጸዉቱ ቤተ ክርስቲያን ለሚያሠሩ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው፣ ስለ ተጋድሏቸው ጽናትም “በሰው እጅ የማይለካውን ይህንን የመንግሥት አዳራሽ ውሰድ” በማለት የጸጋ ልብስ አልብሷቸው፤ በመስቀል ምልክት ያጌጡ ሰባት የሕይወት አክሊላትንም አቀዳጅቷቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ 24 ቀን በዘጠና ዘጠኝ ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ጌታችንም ነፍሳቸውንም በክብር ተቀብሏታል፡፡ የጻድቁን ቃል ኪዳን ያመኑ ገዳማውያን እንደሳቸው ዓለምን ንቀው በተጋድሎ ይኖራሉ፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

YenetaTube
2 days ago
የእናታችን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏

የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳኗ ዘወትር ይታሰባል

ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ የኪዳነ ምሕረት ሥዕል በመባል የሚታወቀው ሥዕል በቤተ ክርሰቲያናችን በስፋት ከሚሳሉት የወላዲተ አምላክ ሥዕል ጭብጦች ውስጥ አንዱ ሲሆን። ከጌታችን ኢየሱስ ቃልኪዳን ስትቀበል በጎሎጎታ የሚያሳየው ሥዕል ትክክለኛው ገላጭ ሥዕል ሲሆን፤ ይህ ሥዕል እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ስፋት የሚጨመረው ጭብጥ ሊለያይ ይችላል፡፡

ለምሳሌ በዚህ ሥዕል ዘይቤ ላይ የሚታዩት መላእክት ቁጥራቸው ሊበዛ አሊያም ሊያንስ ይችላል፡፡ በዚህ ሥዕል እመቤታችንና ጌታችን ቆመው አሊያም ተቀምጠው ጌታችን በቅዱሳን እጆቹ የእናቱን ቅዱሳን እጆች በመያዝ ቃል ኪዳን ሲገባላት አሊያም በቅዱሳት እጁ ቃል ሲገባላት የሚያሳይ ዓይነት ሥዕል ነው፡፡ በዚህ መልኩ እመቤታችን ከተሳለችባቸው አብያተክርስቲያናት መካከል ጎርጎራ ደብረ ሲና (17ኛው መ.ክ.ዘ)፣ አብርሐወ አጽብሐ (19ኛው መ.ክ.ዘ)፣ መቐለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (20ኛው መ.ክ.ዘ)፤ ከጥንታውያን ብራና መጻሕፍት ከተመለከትን በአክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን ግምጃ ቤት የሚገኘው የ17ኛው መ.ክ.ዘ ተአምረ ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ገዳማውያንም ዘወትር በሥዕሏ ፊት ቆመው ይለምኗታል፡፡ እርሷም ልመናና ጸሎታቸውን ታሳርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸውመ እንካፈል፡፡

ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተሰጠው ኪዳን፣ ቀድመው ለነበሩ ኪዳናት ማለትም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖህ፣ ኪዳነ መልከ ጸዴቅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ሙሴና ኪዳነ ዳዊት መደምደሚያ ነው፡፡ ዘለዓለማዊ ስለ ሆነው የማያልፍ የምሕረት ቃል ኪዳን እየታሰበም ዕለቱ በመዝሙር፣ በማኅሌትና በቅዳሴ ይከበራል፡፡ በክርስቶስ ክርስቲያን ለምንባል ለእኛ ለሐዲስ ኪዳን የቤተ ክርስቲያን ልጆችም ይህ አዲስ ውል የተደረገልን ለነፍሳችን ድኅነት በመሆኑ በስሟ እየተማጸንን እንዲሁም መታሰቢያዋን እያደረግን ለተራቡት ማብላት፣ ለተጠሙት ማጠጣትና የተቸገሩትን መርዳት ይገባናል፡፡ ገዳማውያን በበቃል ኪዳኗ ታምነው፣ ዘወትር በሥዕሏ ፊት በጸሎት ይተጋሉ፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

YenetaTube
2 days ago
ከትራምፕ ዛቻ በኋላ የቡድን 7 አገራት ከክምችታቸው 100 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እና ናፍጣ ሊለቁ ነው

የቡድን ሰባት አገራት የዋጋ ንረት ያስከተለውን የአቅርቦት ችግርን ለማቃለል 100 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ እና ናፍጣ እንደሚለቅቁ አስታወቁ።
የቡድን ሰባት መሪዎች በሰጡት መግለጫ፣ ይህ በ20 ቀናት ውስጥ የሚለቀቀውን ነጭ ናፍጣ የሚያካትት ሲሆን "አስፈላጊ ከሆነ ተጨማሪ ናፍጣ ለመልቀቅ ውይይት ይደረጋል" ብለዋል።
አሜሪካን ጨምሮ የላቀ ምጣኔ ሃብት ያላቸው የቡድኑ አባል አገራት፣ እርምጃው ወዲያውኑ ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር እና ለአራት ወራት ያህል እንደሚቆይ ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካን ነዳጅ ወደ ውጪ እንዳይላክ እገዳ እንደሚጥሉ ካስፈራሩ በኋላ በተላለፈው ውሳኔ መሠረትም በቡድን ሰባት አባል አገራት መካከል ኢነርጂን እና የኢነርጂ ውጤቶችን ወደ ውጪ መላክ የሚከለክል ምንም ዓይነት ገደብ አይኖርም ተብሏል።
ቡድን ሰባት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ጃፓን፣ ጀርመን፣ ጣልያን እና ፈረንሳይን የሚይዝ ሲሆን አውሮፓ ኅብረትም በስብሰባዎቹ ተወክሏል።
ትራምፕ ቀደም ብሎ የአውሮፓ አገራት ከክምችታቸው ነዳጅ ወደ ገበያ ለመልቀቅ ካልተስማሙ ከአሜሪካ ናፍጣ ወደ ውጪ እንዳይላክ እንደሚያግዱ አስጠንቅቀው ነበር።
ይህንን ተከትሎ የቡድን ሰባት አገራት ከነዳጅ ክምችታቸው ወደ ገበያ ለመልቀቅ መስማማታቸው በመጪው ወር ከሚካሄደው የአሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ አስቀድሞ ለአሜሪካ ሸማቾች የዋጋ ንረትን እንደሚያቃልል ተገልጿል።
ትራምፕ አርብ ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባጋሩት ጽሑፍ " አውሮፓውያን ከነጭ ናፍጣ ክምችታቸው በብዛት ለመልቀቅ ተስማምተዋል፤ ሒደቱም ወዲያውኑ ይጀምራል" ብለዋል።

የግምጃ ቤት ኃላፊው ስኮት ቢሴንትም ቀደም ብለው በዋጋ ንረቱ "የአሜሪካ አርሶ አደሮች ፣ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና የንግድ ተቋማት ጫናውን መሸከም የለባቸውም" ሲሉ አሳስበው ነበር።
ትራምፕ በኋላ ላይ በዋይት ሃውስ በተናገሩበት ወቅት ግን "ነጭ ናፍጣ ወደ ውጭ የመላክ እገዳ ጠረጴዛ ላይ አልነበረም" ብለዋል።
ቡድን ሰባት ከክምችቱ ነዳጅ ለመልቀቅ ያሳለፈውን ውሳኔ በመጥቀስም ፤ "አውሮፓ ያደረገው በጣም ትልቅ ነገር ነው" ሲሉ ውሳኔውን አድንቀዋል።
"አውሮፓ ብዙ ነጭ ናፍጣ አለው፤ ለዓለም ትልቁን አስተዋፅኦ ያደረጋል፤ እኛም እንደዚያው" ያሉት ትራምፕ ከአሜሪካ ነዳጅ እንዳይላክ እንደማያግዱ አስታውቀዋል። " ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን" ብለዋል።

ትራምፕ ነጭ ናፍጣ ወደ ውጭ እንዳይላክ እገዳ እንደሚጥሉ ያስታወቁት ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሲሆን አስተዳደራቸው አውሮፓ ከክምችቱ እንዲለቅ ጫና ሲያደርግ ቆይቷል።
ውሳኔው የተላለፈበትን ስብሰባ የመሩት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፣ ኅብረቱ በዓለም አቀፍ የኢነርጂ ኤጀንሲ (አይኢኤ) ትብብር ሥር "እስከ 100 ሚሊዮን በርሜል" የሚደርስ ክምችት በአራት ወራት ውስጥ ለመልቀቅ መስማማቱን" ተናግረዋል።
ሆኖም የትኞቹ አገራት እንደሚለቅቁ እንዲሁም በምን ያህል ፍጥነት እንደሚለቅቁ እስካሁን ግልጽ አይደለም።

ነጭ ናፍጣ በተለይ በትራንስፖርት ኢንደስትሪው እና በግብርናው ዘርፍ በብዛት ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የዋጋው ንረት ምግብን ጨምሮ በተለያዩ ወሳኝ ፍጆታዎች ላይ የዋጋ ጭማሪን አስከትሏል።
ግማሽ የሚሆነው የዩኬ ናፍጣ ከውጭ የሚገባ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 31 በመቶ የሚሆነው ከአሜሪካ የሚላክ ነው።
በውሳኔው አሜሪካ ለመጣል ስታስፈራራ የነበረውን እገዳ ማስቀረት መቻሉም ዩኬን ጨምሮ ከውጪ በሚመጣ ነዳጅ ላይ ጥገኛ ለሆኑ አገራት እፎይታን የሚሰጥ ነው ተብሏል።
አሜሪካ በዓለማችን ከፍተኛው ነጭ ናፍጣ ከሚያቀርቡ አገራት መካከል አንዷ ናት። እንደ የአሜሪካ ኢነርጂ ኢንፎርሜሽን አስተዳደር መረጃ ከሆነ በአገር ውስጥ ያላት ማጣሪያ በየቀኑ ከአራት እስከ አምስት ሚሊዮን በርሜል ያመርታል።

ከዚህ ውስጥ 3.6 ሚሊዮኑን አሜሪካውያን የሚጠቀሙበት ሲሆን የነዳጅ አጣሪዎች በቀን ከ1.2 እስከ 1.5 ሚሊዮን በርሜል ናፍጣ ወደ ውጪ ይልካሉ። ይህም አሜሪካን በዓለም ገበያ ወሳኝ አቅራቢ አድርጓታል።
ዋነኛ የነዳጅ አምራች የሆነችው ሩሲያ በነዳጅ ማጣሪያዎቿ ላይ በዩክሬን የተፈፀመባትን ጥቃት ተከትሎ ነጭ ናፍጣን ወደ ውጭ እንዳይላክ አግዳለች። ይህም የአቅርቦት እጥረቱን አባብሶታል።

ነጭ ናፍጣ ከቤንዚን የበለጠ ለማጣራት አስቸጋሪ ቢሆንም ፣ በትራንስፖርት ኢንደስትሪው እና በግብርናው ዘርፍ ጥቅም ላይ ስለሚውል ፍላጎትን መቀነስ አስቸጋሪ ነው።

BBC

YenetaTube
3 days ago
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ25 ኤምባሲዎች ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱ ተገለጸ

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ባሉበት ሆነው የፓስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ በ25 ኤምባሲዎች በኩል ሥራ መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

ተገልጋዮች በአቅራቢያቸው በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በመሄድ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ የተቋሙ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አምቦ መቃሳ ለአሐዱ ሬድዮ ገልጸዋል።

ተቋሙ አገልግሎቱን በሀገር አቀፍ ደረጃ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የቅርንጫፍ ቢሮዎቹን ቁጥር ከ38 ወደ 40 ማሳደጉ ተገልጿል።

ከነባር ቅርንጫፎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ አጣና ተራ እና ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተሞች ተጨማሪ የፓስፖርት ቅርንጫፎች ተከፍተዋል።

በተያዘው የበጀት ዓመት በሁሉም የአንድ መሶብ ማዕከላት የፓስፖርት አሰጣጥ አገልግሎት ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አቶ አምቦ መቃሳ ተናግረዋል።

በህይወቴ ጌትነት

YenetaTube
3 days ago
እንኳን ለሊቀ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን🙏

ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ አጥፍቷቸዋል

በ277 ዓ.ም ጥር 20 ፍልስጤም ልዩ ስሟ “ልዳ” የተወለደው ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሁሉም ክርስቲያኖች ዘንድ ተቀባይነት ካላቸው ሰማዕታት ቀዳሚው ነው፡፡ የአባቱን ሞት ተከትሎ ከሌላ መኳንንት ጋር ያደገው ጊዮርጊስ የክርስትና ጠላት ከሆነው ዱዲያኖስና ከ70ው ነገስታት ጋር የተጋፈጠው የአባቱን ምስፍና እንዲሰጡት ሊጠይቅ በሔደበት ክርስቲያኖችና ክርስትና ሲገፉ በማየቱ ነው፡፡ ጊዮርጊስ ማለት “ብሩህ ኮከብ፣ ፀሐይ” ሲሆን ተጋድሎውን ሲጀምር የሃያ ዓመት ወጣት ነበር፡፡ በቤሩትም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ ክርስትና አስገባቸው፡፡ በነገሥታቱ ፊትም የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡

ምንም እንኳን ንጉሡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሣፍንት ወገን መሆኑን እንደ መግቢያ በመጠቀም ሊያባብለው ቢሞክርም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” ብሎ በእምነቱ ጸና፡፡ ዱድያኖስም ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን ያደርስበት ጀመር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ያጸናው ቍስሉንም ያድነው ነበር፡፡ ሦስት ጊዜ እንደሚሞት እርሱም እንደሚያስነሣው በአራተኛውም የሰማዕትነትን አክሊል እንደሚቀበል ነገረው፡፡ ቃል ኪዳንም ገባለት፤ ለሰባት ዓመትም በጽኑዕ መከራና በሥቃይም እንዲሁም በተጋድሎ እንደሚኖር በዚያም ስሙ በዓለሙ ሁሉ የተገለጠ እንደሚሆን መላእክትም እንደሚያገለግሉትም ነገረው፡፡ ንጉሥ ዱድያኖስም ቅዱስ ጊዮርጊስ ትእዛዙን ባለመቀበሉ ተቆጥቶ አትናስዮስ የሚባል ታላቅ መሠሪ አስጠርቶ በፍጥነት የሚገድል መርዝ ቀምሞ በጽዋ መልቶ አጠጣው፡፡

መርዙ ግን ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ቀረ፡፡ ያ መሠርይም ይህን ድንቅ ሥራ ሲያይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ፡፡ ቁጥራቸውም ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ የሚሆኑ ሌሎች ሰዎች ከእርሱ ጋር በሰማዕትነት ሞተው የሕይወትን አክሊል ተቀዳጁ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ለሰባት ዓመታት በቅድስና ሲጋደል ቆይቶ፣ ታላቅ የምህረት ቃል ኪዳን ተቀብሎ ሚያዝያ 23 ቀን በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ከአንገቱ የወጣው ደም እሳት ሆኖ ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ስለክርሳቶስ ፍቅር ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው የዓለም ደስታቸውን ስለክርስቶስ ፍቅር ትተዋልና በረከታቸው ብዙ ነው፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

እየተከበረ የሚገኘው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል

እየተከበረ የሚገኘው የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል
YenetaTube
3 days ago
እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ነገር ሁሉ ትከልለን፤ ምልጃዋ እና ረድኤቷም አይለየን🙏

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምእራፍ 7÷14 “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” አለን፡፡ በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች። በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የጌታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ የተዋሕዶን ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው አለ፡፡

በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል።ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ፤ እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡

ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

4 days ago
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏

ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት

አባቱን ገና በልጅነቱ ቢሞትበትም ሌላ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ በጦር ኃይል አሰልጠኖ አሳድጎታል፡፡ የስሙ ትርጓሜ “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡ ፍልስጤም ውስጥ ልዩ ስሟ “ልዳ” በምትባል ቦታ በ277 ዓ.ም ጥር 20 ተወለደ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ፡፡ ያሳደገው መስፍን ሲሞትም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ከተማ ሄደ፡፡ በዚያም የሚመለክና ሴት ልጆቻቸውን የሚገብሩለትን ደራጎን ገድሎ ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር መለሳቸው፡፡ የአባቱን ሹመት ለማግኘት ወደ ፋርስም ሲሔድ ንጉሱ ዱድያኖስ ከሰባ ነገሥታት ጋር ጣዖታት ሲያመልኩ ቢያገኛቸው በፊታቸው የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ሰማዕቱ ከመኳንንት ወገን መሆኑን የተረዳው ዱዲያኖስ አጵሎንን ብታመልክ እሾምሃለው አለው፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም “አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን ላንተ ሹመት ስል አልክደውም” አለው፡፡ ዱድያኖስም እጅግ ተቆጥቶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት” በማለት ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡ በእንጨት ላይ ሰቅለው ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምተው ሂድ አሉት፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ሰውነቱን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ሲነሰንስበት ሥጋው መሬት ላይ ወደቀ፡፡

በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ፣ በእሳት አስተኩሶ፣ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ፣ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ፈወሰው፤ ኃይልና ብርታትንም ሰጠው፡፡ በመከራው ብዛት ሦስት ጊዜ ሲሞት ጌታችን ሦስት ጊዜ ከሞት አስነሣው፡፡ ለሰባት ዓመታት ከተጋደለ በኋላም ሚያዝያ 23 በሰይፍ አንገቱን ተመቶ ሲሞት ሰባውን ነገስታት አጥፍቷቸዋል፡፡ ዓለምን የናቁ ገዳማውያን ይህን አብነት አድርገው ይጸናሉ በገድልም ይተጋሉ፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

አቶ አብዱላሂ አደን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ተሰየሙ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ሲሆን አቶ አብዱላሂ አደንን የአስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል፡፡

ከንቲባው በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ ፈፅመው ስራቸውን በይፋ ጀምረዋል።

መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏

እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከአለት ውሀ አፍልቆ መገባቸው፡፡

እነርሱ ግን እዚህ ደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ቆላ ቢሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። የርሱን ከሃሊነት፣ የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥ ቢወድ፣ ሙሴን የውሃ ምንጭ የሌለበት በረሐ ይዘሀቸው ሂድ ብሎት በዚያም መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከእኛ ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል እባቦችን እንዲያርቅልን ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አሉት።

ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ ከንጹህ ነሐስ የእባብ ምስል ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። እንደተባለው ቢያደርግ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። “ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደሰቀለው የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ተብሎ በዮሐንስ 3÷14 እንደተነገረ፡፡ አባቶቻችንም በትርጓሜ ወንጌል የበረሐው እባብ የዲያብሎስ፤ የብረቱ እባብ የጌታ ምሳሌ ነው። በእባብ መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።

በነሐሱ እባብ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም። የነሐሱ እባብ በእባብ አምሳል መሰቀሉ ጌታ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል።

ገዳማውያኑም በመስቀል የተደረገልንን ማዳን እያሰቡ ዓለምን ንቀው፣ ስጋቸውን ጎድተው ይከተሉታል፡፡ የጽድቃቸው አክሊል እርሱ መድኃኔ ዓለም የሚወደኝ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ፡፡

እንኳን ለቅዱስ ዑራኤል ወርሃዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏

ቅዱስ ዑራኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

የስሙን ትርጓሜ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ሲያስቀምጡም “ዑራ” ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን “ኤል” አምላክ ማለት ነው፡፡
በዚህም ዑራኤል ማለት የአምላክ ብርሃን፣ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው ይላሉ፡፡ መልአከ ብርሃናት፣ ለሚጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በስፋት ይገልጹታል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር በመባርቅትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመው ታላቅ መልአክም ነው ቅዱስ ዑራኤል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷2 መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ይሰማራል። ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለትም የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለነቢዩ ሄኖክ ነግሮታል።
እውቀት ተሠውሮበት ለነበረው ኢትዮጵያዊው ሊቅ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በእመቤታችን በድንግል ማርያም ትእዛዝ ፅዋዐ ጥበብን አጠጥቶ ሠማያዊውን ጥበብ የገለጸለት ቅዱስ ዑራኤል ነው። "ዑራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ" ይላልና፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር የሕይወትና የይቅርታ ዝናብ በምድራችን ላይ ያዘንብ ዘንድ እንዲሁም የእርሻችንን አዝመራ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ ለምግብነት እንዲበቃ ከፈጣሪ ዘንድ ምህረትን የሚለምን ነው ቅዱስ ዑራኤል። ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። በዕዝራ ሱቱኤል 13÷38 ተጽፎ እንደምናገኘው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ አእምሮ ለብዎውን ወይም ማስተዋልን ገልጦለታል።

የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል፤ ለዕዝራ ሱቱዔል የሆነለትም እንዲሁ ነውና። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ እርሱ ነው፡፡ ሊቀ መልአኩ የጌታችንን ደም የረጨበት ጽዋ በሀገራችን በኢትዮጵያ እመጓ ቅዱስ ኡራኤል እንደሚገኝ ስፍረዋን የጎበኙ ጸሐፍትና የስፍራው አገልጋዮች ይገልጻሉ፡፡ በርካታ ቅዱሳን አባቶች ምስጢር እንዲገለጥላቸው የረዳቸው ቅዱስ ዑራኤል መሆኑ በበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል እንዲናገሩ፣ የሚጽፉበት ብዕር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ለሕይወት ድህነት የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ቅዱስ ዑራኤል አግዟቸዋል፡፡

ይህም ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ያሳየናል፡፡ ዛሬም በየገዳማቱ ያሉ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ተቋቁመው በጾምና በጸሎት ሲተጉ ይህ ቅዱስ መልአክ ዑራኤል ፈጽሞ ይራዳቸዋል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 8÷4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” እንዲል ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ደህንነት እግዚአብሔርን በሚለምኑት በገዳማውያኑ መካከል ተገኝቶ ጸሎታቸውን ያሳርጋል፤ ልመናቸውን በአምላክ ፊት ያቀርባል፡፡ ቅዱሳን መካናትን ስናግዝ፣ ገዳማትን ስንረዳ፣ በዓታቸውን ስናጸና የገዳማውያኑ ጸሎትና በረከት ይደርሰናል፡፡

ሰላም - እና የሰላም ዋጋ

ፍሬው ከፍያለው
YenetaTube
4 days ago
ኢትዮጵያ አንድ የግብፅ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር እንዲወጡ አሳሰበች

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ በሚገኘው የግብፅ ኤምባሲ ውስጥ የሚያገለግሉ አንድ ከፍተኛ ዲፕሎማት በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ግዛት ለቀው እንዲወጡ ማዘዙ ታወቀ።

ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለግብፅ ኤምባሲ የተላከውን ይፋዊ የዲፕሎማሲያዊ ማስታወሻ (Diplomatic Note) መሠረት በማድረግ የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ በአዲስ አበባ የግብፅ ኤምባሲ የዲፕሎማቲክ አካል የሆኑት አህመድ ሞሀረም አህመድ ሱሊማን (Ahmed Moharam Ahmed Soliman) በኢትዮጵያ መንግሥት ዘንድ ‘ፐርሶና ነን ግራታ’ (Persona Non Grata) ወይም “ተቀባይነት የሌላቸው ግለሰብ” ተብለው ተፈርጀዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ውሳኔ ያሳለፈችው እ.ኤ.አ. በ1961 በፀደቀው የቪየና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ድንጋጌ (Vienna Convention on Diplomatic Relations) የተሰጣትን መብት መሠረት በማድረግ እንደሆነ ተጠቅሷል።

በዚሁ መሠረት ዲፕሎማቱ ማስታወቂያው ከደረሳቸው ጊዜ ጀምሮ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ከኢትዮጵያ ምድር ለቀው እንዲወጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

Via የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

YenetaTube
4 days ago
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ በሚከበረውን የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ አስታወቀ፡፡

ነገ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ፡-

◉ ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ (22 ወይም ጎላጎል አደባባይ ላይ እና ታች)
◉ ከአድዋ ድልድይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ እና ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ)
◉ ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
◉ ከቦሌ ሩዋንዳ ድልድይ ወደ መስቀል አደባባይ (ወሎ ሠፈር አደባባይ ላይ እና ታች)
◉ ከጋዜቦ አደባባይ በደንበል ህንፃ ጀርባ ወደ ፊላሚንጎ እንዲሁም ከጋዜቦ አደባባይ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት (ጋዜቦ አደባባይ)
◉ ከቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ ወደ ለገሃር መብራት (ቅዱስ ቂርቆስ ታቦት ማደሪያ መብራት)
◉ ከቀድሞው ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ በአዲሱ መንገድ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን (ብርሃን ኢትዮጵያ መስቀለኛ)
◉ ከአፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
◉ ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አፍሪካ ህብረት መብራት)
◉ ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
◉ ከሜክሲኮ አረቁ ፋብሪካ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (አረቄ ፋብሪካ መስቀለኛ)
◉ ከሰንጋ ተራ 40/60 ቤቶች መገንጠያ ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መገንጠያ)
◉ ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብሔራዊ ቴአትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
◉ ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትዮሮሎጂ መታጠፊያ)
◉ ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኤሚግሬሽን መብራት ( ጥቁር አንበሳ መስቀለኛ)
◉ ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ)
◉ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኤሚግሬሽን መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
◉ ከንግድ ማተሚያ መታጠፊያ ወደ ፍል ውሃ መስቀለኛ (ንግድ መታጠፊያ)
◉ ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ)
◉ ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ)

ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ጀምሮ የሚዘጋ ሲሆን አሽከርካሪዎች አስቀድመው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እያሳሰበ ከንጋቱ 12:00 ሠዓት ጀምሮ በተጠቀሱት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሳስቧል።

ህብረተሰቡ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘትም ሆነ ጥቆማ ለመስጠት በ01-11-11-01-11 እና በ990 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

YenetaTube
4 days ago
ነገ በግዮን ሆቴል ታሪክ ሊሰራ ነው!
10,000 ስኒ ቡና በአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝገብ ሊመዘገብ ነው።

ነገ ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ የአፍሪካ ድንቃድንቅ መዝጋቢዎች በቦታው ተገኝተው ኩነቱን ይመዘግባሉ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂና ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ይታደማሉ። ለድንቃድንቅ ምዝገባው ብስራትም ርችቾች ይተኮሳሉ። ምሽት ላይ ደግሞ አንጋፋና ወጣት ድምጻውያን ከሚስ ዩኒቲ ጋር ትልቅ ኬክ ይቆርሳሉ የአንድነት ዝማሬም ይዘምራሉ። እርስዎም በቦታው ተገኝተው ከ10,000 ስኒው ቡና እንዲቋደሱና የዚህ ድንቅ ታሪክ አካል እንዲሆኑ አዘጋጁ ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይመንትና ኤቨንት ኦርጋናይዘር በክብር ጋብዞዎታል።

ለበለጠ መረጃ 0989444400 ወይም 0989444411

YenetaTube
4 days ago
ቅዱስ ዑራኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ🙏

መልአከ ብርሃናት፣ ለሚጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በስፋት ይገልጹታል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል፡፡ የስሙን ትርጓሜ ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ሲያስቀምጡም “ዑራ” ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን “ኤል” አምላክ ማለት ነው፡፡ በዚህም ዑራኤል ማለት የአምላክ ብርሃን፣ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር በመባርቅትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመው ታላቅ መልአክም ነው ቅዱስ ዑራኤል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷2 መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ይሰማራል።

ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለትም የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለነቢዩ ሄኖክ ነግሮታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ እርሱ ነው፡፡ ሊቀ መልአኩ የጌታችንን ደም የረጨበት ጽዋ በሀገራችን በኢትዮጵያ እመጓ ቅዱስ ኡራኤል እንደሚገኝ ስፍረዋን የጎበኙ ጸሐፍትና የስፍራው አገልጋዮች ይገልጻሉ፡፡

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፣ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ በርካታ ቅዱሳን አባቶች ምስጢር እንዲገለጥላቸው የረዳቸው ቅዱስ ዑራኤል መሆኑ በበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል እንዲናገሩ፣ የሚጽፉበት ብዕር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ለሕይወት ድህነት የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ቅዱስ ዑራኤል አግዟቸዋል፡፡ ይህም ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ያሳየናል፡፡

ዛሬም በየገዳማቱ ያሉ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ተቋቁመው በጾምና በጸሎት ሲተጉ ይህ ቅዱስ መልአክ ዑራኤል ፈጽሞ ይራዳቸዋል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 8÷4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” እንዲል በገዳማውያኑ መካከል ተገኝቶ ጸሎታቸውን ያሳርጋል፤ ልመናቸውን በአምላክ ፊት ያቀርባል፡፡ ቅዱሳን መካናትን ስናግዝ፣ ገዳማትን ስንረዳ፣ በዓታቸውን ስናጸና የገዳማውያኑ ጸሎትና በረከት ይደርሰናል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

YenetaTube
5 days ago
ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝታቸውም ወቅት የፋብሪካውን የምርት ሂደት ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን አምራች ድርጅቱ ያለውን ዘመናዊ የምርት ሂደት አድንቀዋል፡፡ በመቀጠልም ከትራንሽን ማኑፋክቸሪንግ አመራሮች ጋር በተለያዩ የጋራ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል፡፡