14 days ago
Sovereign Right to Develop
*************** #gerd #nileriver #ethiopianile #greenlegacy #equitableuse #nilebasin
17 days ago
የኢኮኖሚ ዋልታነቱን እያረጋገጠ የሚገኘው የቡና ምርት
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኮፊ አረቢካ መገኛ ብቻ ሳይሆን፣ ትልቋ አምራች ሀገር የሚል ስም መያዝ እንዳለባትና የኢኮኖሚ ዋልታ ዘፈን ሳይሆን ተግባር መሆን እንደሚገባ ማስገንዘባቸው ይታወሳል።
በመሆኑም “የኢኮኖሚ ዋልታ ቡና ቡና” እየተባለ የተዜመለት የኢትዮጵያ ቡና፣ ዛሬ ላይ በተጨባጭ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና በሰፊ የምርት ማሻሻያ ሥራዎች ሀገራዊ ኢኮኖሚውን እየደገፈ ይገኛል።
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች፣ ዓመታዊ የቡና ምርት መጠን ከነበረበት በየዓመቱ ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ ይገኛል። ዘመናዊ የቡና መስኖ ልማት እና በማሽን የታገዘ የቡና ለቀማ የአርሶ አደሮችን ሕይወት በማቅለል የቡና ምርት ጥራትን ከፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ሀገራችን ባለፉት 17 ዓመታት በአጠቃላይ ካገኘችው 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር የገቢ መጠን ጋር የሚቀራረብ መሆኑን ያሳያል።
የቡና ጥራትን ማስጠበቅና ምርታማነትን ማሳደግ በዓለም አቀፍ ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚረዳ የቡና አምራቾች እና ላኪዎች የሚናገሩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የቡና ምርት ልማትና ጥራት በየጊዜው ዕድገት በማሳየት በተለይም የልዩ ጣዕም ቡና በገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በእጅጉ ጨምሯል።
የቡናው ዘርፍ ከባህላዊ አሠራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በመስኖ ልማት እንዲዘምን ማድረግ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ቁልፍ ሚና አለው።
የላኪዎችን፣ የአርሶ አደሮችን እና የመንግሥትን የተቀናጀ ጥረት አጠናክሮ መቀጠል፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ የኮፊ አረቢካ መገኛ ብቻ ሳትሆን ትልቋ እና ተወዳዳሪዋ የቡና አምራች ሀገር ማድረጉ የማይቀር እውነት ነው።
በሐይማኖት ከበደ
#ebc #greenlegacy #ethiopiancoffee #agritech #sustainableagriculture

19 days ago
ለነገ ምጥቀት ዛሬ መሠረት እያኖረ ያለው የመደመር ዕሳቤ
************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ"መደመር መንገድ" መጽሐፋቸው "በፈጣን ዓለም ውስጥ ቆሞ ማደግ የሚችለው ዛፍ እንጂ ሰው አይደለም" ሲሉ ያስቀመጡት እሳቤ የ21ኛው ክፍለ ዘመንን የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ምኅዳር የሚመራ ጽኑ እውነት ነው።
ዛፍ በአንድ ስፍራ ተተክሎ እና ሥሩን ሰድዶ ያድጋል፤ ፈጣኑ የዓለማችን እውነታ ግን በአንድ ቦታ ረግቶ መቆምን በፍጹም አይፈቅድም።
በቋሚነት በሚለዋወጠው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ፣ የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ውድድር ውስጥ ቆሞ ማደግ አይቻልም።
ረግቶ መቆም ወደኋላ መቅረትን አልፎም መሸነፍን መቀበል ነው። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያረጋገጠችው ታላቅ እውነታም ይህንኑ የፍጥነት ፍልስፍና በተግባር የመተርጎም አቅሟን ነው።
የመደመር እሳቤ የተመዘገቡ ስኬቶችን እንደ ተተከለ ዛፍ ቆመው የሚቀሩ ሳይሆን፣ አዳዲስ የዕድገት አድማሶችን ለመክፈት የሚያገለግሉ የጉዞ ማስፈንጠሪያዎች አድርጎ ይመለከታቸዋል።
የዚህ ተለዋዋጭ እና ፈጣን ጉዞ የመጀመሪያው ማሳያ በዲጂታል ምኅዳሩ የታየው ንቅናቄ ነው። "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ የዛሬን ቴክኖሎጂያዊ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ለመፃኢው ጊዜ ጠንካራ መሠረት እየጣለ ይገኛል።
ወጣቶችን ለ‘ኢንዱስትሪ 5.0’ አብዮት የሚያዘጋጀው የ"5 ሚሊዮን ኮደርስ" ኢኒሼቲቭ፣ ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓት ውስጥ ማቀፉ እንዲሁም የመንግሥት አገልግሎቶች ወደ ኤሌክትሮኒክ ሥርዓት መግባታቸው የዚሁ የፍጥነት ማረጋገጫዎች ናቸው።
የቴሌኮም ደንበኞች አጠቃላይ ቁጥር እና የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ምጣኔ ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉ ኢትዮጵያ የዓለምን የቴክኖሎጂ ፍጥነት ለመቀላቀል ብቻ ሳይሆን በዘርፉ ተወዳዳሪ ለመሆን የያዘችውን ጠንካራ ፍጥነት ያሳያል። እነዚህ ስኬቶች የተጠናቀቁ ግቦች ሳይሆኑ፣ የነገው የዲጂታል ኢኮኖሚ እግሮች ናቸው።
ይህ የተፋጠነ ምጥቀት በኃይል እና በኢነርጂ ዘርፍም የኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ አጉልቶ አሳይቷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የተበታተነ የሕዝብ አቅም ሲደመር የሚፈጥረውን ተዓምር አረጋግጧል።
ይህ ግድብ የውኃ ማጠራቀሚያ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያፋጥን፣ ለጎረቤት ሀገራት አስተማማኝ የኃይል ምንጭ በመሆን ቀጣናዊ ትሥሥርን የሚያጠናክር እና ዘወትር የሚንቀሳቀስ ሕያው የልማት ሞተር ነው።
በግብርናው ዘርፍ የታየው ሥር ነቀል አሠራር የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞን ከተለምዷዊው አዝጋሚ እርምጃ ያላቀቀ ነው።
በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የተገኙ ስኬቶች፤ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚካሄዱት የኮሪደር ልማቶች የተመዘገቡት ዐበይት ስኬቶች ኢትዮጵያ እንደ ዛፍ በአንድ ቦታ ተተክላ የምትቀር ሳትሆን፣ ከዘመኑ የፍጥነት ምኅዳር ጋር እኩል የምትራመድ መሆኗን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው።
የተሠሩት ሥራዎች የትናንት ታሪኮች ወይም የስኬት ማጠቃለያዎች አይደሉም፤ ይልቁንም ሀገራችን በነገው ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የላቀ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንድትሆን የተዘጋጁ፣ ቆሞ ካለመቅረት ፍልስፍና የሚመነጩ እና ወደ ተፋጠነ የምጥቀት ከፍታ የሚያመጥቁ ጽኑ የጉዞ ማስፈንጠሪያዎች ናቸው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #medemer #digitalethiopia #gerd #greenlegacy #ebc

25 days ago
ኢትዮጵያ ዓለምን የምታስተናግድበት ታላቅ ጉባኤ
➡ https://youtu.be/OSXEjO5at...
#pmabiyahimed #cop32 #ethiopia #addisababa #greenlegacy
28 days ago
ከነባር ዕሴት እስከ ዘመናዊ አስተዳደር፡ የመደመር ዕይታ እና የሰው ተኮር ልማት አዲስ ምዕራፍ
*******************
ኢትዮጵያ በብዙ የፈተና እና የለውጥ ማዕበሎች ውስጥ አልፋ ዛሬ ላይ የጸናችው በሕዝቦቿ መካከል ባሉ ጥንታዊ የማኅበራዊ ትስስር ገመዶች አማካኝነት ነው።
የመረዳዳት ባህላዊ ተቋሞቻችን የችግር ጊዜ ማለፊያዎች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የሕዝቡ የእርስ በርስ መደጋገፍ እና የጋራ ዕጣ ፈንታን አብሮ የመቅረፅ ጥበብ ማሳያ ታሪካዊ መሠረቶች ጭምር ናቸው።
የመደመር ዕሳቤ እነዚህን ነባር ማኅበራዊ ሀብቶች እና ጥበቦች ከዘመናዊ የመንግሥት አስተዳደር ፍልስፍና ጋር በማጣመር፣ ልማትን ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባለፈ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ሕይወት በማሻሻል ላይ ያተኮረ ሰፊ ሥራ አድርጎ ይመከታል፤ ይተገብራል።
በመደመር ዕሳቤ የሚከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች በዋናነት የዜጎችን የዕለት ተለት ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይሩ የማኅበራዊ ደህንነት ፕሮግራሞች ናቸው።
የቆየውን "ያለንን የማጋራት" ባህል ወደ ተደራጀ የመንግሥት እና የማኅበረሰብ መዋቅር በመቀየር፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን፣ አረጋውያንን እና አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የማዕድ ማጋራት እና የመኖሪያ ቤት ዕድሳት ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ከዚህ በተጨማሪ ህጻናት በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ የተዘረጋው የትምህርት ቤት ምግባ መርሐ ግብር፣ በነገው ትውልድ ላይ የሚደረግ ትልቅ የሰው ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት ሲሆን፣ ይህም የድሃ ወላጆችን ሸክም ከማቃለሉም በላይ የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራትን ማሳደግ አስችሏል።
በተመሳሳይ የከተሞች የኮሪደር ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችም የሰው ልጅን ምቾት እና ጤና ማዕከል ያደረጉ ናቸው። የመሠረተ ልማት ዝርጋታው የአሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን የእግረኞችንም ምቾት ታሳቢ ያደረገ ነው።
ሰፋፊ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች፣ የህጻናት መጫወቻዎች እና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር በተጓዳኝ የዜጎችን አዕምሯዊ እና አካላዊ ጤና የሚያጎለብቱ ሆነዋል።
በሌላ በኩል ጥንታዊው ጉልበትን አስተባብሮ በጋራ የማረስ እና የመገንባት የደቦ (ጅጌ) ባህል ዛሬ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃ እና ለምግብ ዋስትና በሚደረገው ሀገራዊው የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ላይ ተመልሶ በጥቅም ላይ ውሏል።
በመሆኑም ባህላዊ ዕሴቶቻችንን ሳንለቅ ከዘመናዊ የልማት አስተሳሰብ ጋር አጣጥሞ መጓዝ ልማቱን ማፋጠን ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን ዜጋ የልማቱ ባለቤት እና ተጠቃሚ ያደርጋል።
ይህ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ በመገንባት ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረክብ የሚያስችል ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #humancentereddevelopment #urbancorridor #greenlegacy #traditionalvalues #socialcohesion #ebc

Sponsored by
Surafel
29 days ago
ከዓለም ታላላቅ ከተሞች አዲስ አበባ 2ኛ ወጣች
#addisababa #climateresilience #greenlegacy #corridordevelopment #ethiopiaprogress
30 days ago
በማንሠራራት ወደ ብልፅግና!
**************
ኢትዮጵያ በፈተናዎች ውስጥ አልፋ የማንሠራራትና የትንሣኤ ጉዞዋን በማፋጠን ላይ ትገኛለች።
ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡት ዐበይት ሀገራዊ ስኬቶች የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ በጽኑ መሠረት ላይ እየገነባን ለመሆናችን ተጨባጭ ማሳያ ናቸው።
የሀገር ውስጥ የስንዴ ፍጆታን መሸፈን ብቻ ሳይሆን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንደሚቻል የታየበት የመስኖ ስንዴ ልማት አብዮት የኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ ወደ ሜካናይዜሽን የተሸጋገረበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
የኢትዮጵያውያን የጋራ ሕልምና ጽናት ውጤት የሆነው እና ኃይል ማመንጨት ጀምሮ ለኢንዱስትሪና ለቀጣናዊ ትስስር መንገድ የከፈተው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ባለው ትልቅ ፋይዳ “ዳግማዊ ዓድዋ” ለመሰኘት በቅቷል።
በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የተፈጥሮ ሚዛንን የመጠበቅ፣ የአፈር መሸርሸርን የመከላከል እና የደን ሽፋንን የማሳደግ ዓለም አቀፍ አርዓያነት ያለው የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ሀገራችንን ወደ አዲስ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ምዕራፍ እያሸጋገራት ነው።
አዲስ አበባን ጨምሮ በርካታ ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ለቱሪስቶች ሳቢ በማድረግ መልሰን የገነባንበት የኮሪደር ልማት እና ውበት ኢኒሼቲቭ ታላቅ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትርጉም ያለው የከተሞች ትራንስፎርሜሽን ሥራ ነው።
የሀገራችንን የፋይናንስ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ምህዳር በማዘመን ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋገጥ ወደ ሥራ የገባው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያም የኢትዮጵያ ማንሠራራት የተፋጠነበት ደፋር እና ውጤታማ እርምጃ ነው።
በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ እና በሌሎች ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎች በመታገዝ የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች አቅም እንዲያንሠራራና ተወዳዳሪ እንዲሆን የተደረገው ጥረት ለሀገራዊ ምርት ዕድገትና ለሥራ ፈጠራ ትልቅ መሠረት ጥሏል።
የጉባ ብስራቶችን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየተከናወኑ ያሉ ሜጋ የልማት ውጥኖቻችን በግልፅ የሚያሳዩት፣ አንድነታችንን አጠናክረን ከተጋን የተፋጠነው የማንሠራራት ጉዟችን በአጭር ጊዜ ወደ ሁለንተናዊ ብልፅግና እንደሚያደርሰን ነው።
#ethiopia #greenlegacy #gerd #homegrowneconomicreform #madeinethiopia #revival #prosperity #ebc

1 month ago
ኃያላኑን ከኢትዮጵያ ጎን ያሰለፉት የለውጥ ፍሬዎች
*************
ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም የጀመረችው የለውጥ ጉዞ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መዋቅሮቻችንን በስር ነቀል ሁኔታ ያሻገረ ታሪካዊ ክስተት ነው።
በለውጡ መባቻ የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች መጋጨት ፈጥሮት የነበረው ውዥንብር፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች በጥርጣሬ ፊታቸውን እንዲያዞሩብን አድርጎ ነበር።
ይሁን እንጂ የተጋረጡትን ውስብስብ ፈተናዎች በጽናት በማለፍ እና ማዕከላዊ መስመሯን በመጠበቅ ሀገራችን ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበችው ሁለንተናዊ ዕድገት እነዚህን አጋሮች ወደ ትብብር መድረክ በድጋሚ መመለስ ችሏል።
በተለይም ከአሜሪካ እና ከሌሎች ምዕራባውያን አጋሮች ጋር የታደሰው ስትራቴጂያዊ ትብብር የዚሁ የጸና የዲፕሎማሲ እና የለውጥ ጉዞ አንዱ ማሳያ ነው።
ይህ የአጋርነት መታደስ በተጨባጭ በተተገበሩ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ እና መዋቅራዊ ማሻሻያዎች የተገኘ ውጤት ነው።
ሐምሌ 2016 ዓ.ም የውጭ ምንዛሬ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉን ተከትሎ፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የነበራቸውን ስጋት አንስተው ወደ ሙሉ አጋርነት ተመልሰዋል።
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያጸደቀው የ3.4 ቢሊዮን ዶላር እና የዓለም ባንክ የ10.7 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ የዚሁ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያ ፍሬዎች ናቸው።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ የብሪክስ (BRICS) አባል መሆኗ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተፈላጊነት፣ ሰፊ የገበያ ተደራሽነት እና ጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት በግልጽ ያረጋገጠ ታላቅ የዲፕሎማሲ ድል ነው።
ከዚህ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድል ባሻገር፣ ኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመኗን የሚያደምቁ እና ብሩህ ተስፋን ሰንቀው የተጠናቀቁ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በተግባር አሳይታለች።
ከእነዚህም ግንባር ቀደሙ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተደረገው የግብርና ትራንስፎርሜሽን ነው። በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አማካኝነት ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የስንዴ ምርትን ከውጭ መግዛት ከማቆም አልፈን ወደ ውጭ ገበያ ማቅረብ ጀምረናል።
ለዚህም ታሪካዊ ስኬት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ጥር 2016 ዓ.ም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታላቁን የአግሪኮላ ሜዳሊያ አበርክቷል።
በሌላ በኩል በአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁ እና በከፍተኛ አቅም ኃይል ማመንጨት መጀመሩ የብልጽግናችን አንዱ እና ዋነኛው ምሰሶ ሆኖ ቀጥሏል።
በከተማ ልማት፣ በአረንጓዴ ዐሻራ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎችም አስደናቂ ለውጦች ተመዝግበዋል።
በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች የተተገበረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የእግር መንገዶችን፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን እና የዘመናዊ ከተማ መሠረተ ልማቶችን በጥበብ በማቀናጀት የከተማ መሬት አጠቃቀምን ሙሉ ለሙሉ አዘምኗል።
በተመሳሳይ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋናችንን ወደ 23.6 በመቶ ማሳደግ የተቻለ ሲሆን፣ ይህም ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ አበርክቶው ከፍተኛ ዕውቅና አስገኝቷል።
በዲጂታል ዘርፍ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂ ጠንካራ መሠረት በመጣል ለ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ዕቅድ መድረኩን አመቻችቷል።
የበርካታ ሚሊዮን ዜጎችን የዕለት ተለት እንቅስቃሴ እያዘመነ የሚገኘው የፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣ እንዲሁም የቴሌብር፣ የ5ጂ አገልግሎት እና የኢ-ኮመርስ ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችንን በከፍተኛ ደረጃ እያፋጠኑት ይገኛሉ።
ከተወሳሰቡ ፖለቲካዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ወጥተን በማዕከላዊው የመደመር መስመር ላይ በመቆም ታሪካችንን በድል አድራጊነት እየጻፍን እንገኛለን።
እውን የሆኑት እጅግ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እና ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ጋር ዳግም የተገነባው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የማትበገር እና በዘላቂ ብልጽግና ጎዳና ላይ የምትገኝ መሆኗን በተጨባጭ ያረጋግጣሉ።
በቀጣይም ይህ የጸና የለውጥ ጉዞ ለዜጎቻችን የላቀ የኑሮ ደረጃን የሚያረጋግጥ፣ እንዲሁም ለቀጣናው የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ትስስር ማዕከልነታችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ይሆናል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #economicreform #digitalethiopia #greenlegacy #gerd #brics #ebc

ነዋሪዎችን ማዕከል ያደረገ ሰው-ተኮር የከተማ ልማት
********************
ከተሞች የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ ሕይወት እና የዘመናዊነት መስታወቶች ናቸው።
የአንድ ከተማ ዕድገት በተገነቡ ሕንፃዎች፣ በተስፋፉ መንገዶች እና በተጨመሩ የንግድ ማዕከላት ብዛት ብቻ አይለካም።
እውነተኛ የከተማ ልማት የሚገለጸው ነዋሪዎች ንጹህ፣ አረንጓዴ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ለኑሮ ምቹ በሆነ አካባቢ መኖር ሲችሉ ነው።
አዲስ አበባ በፍጥነት እያደገች ያለች የአፍሪካ መዲና እንደመሆኗ፣ ይህን ዕድገቷን ከሥነ-ምህዳር ጥበቃ እና ከሕዝብ ምቾት ጋር ማጣጣም ወሳኝ ጉዳይ ነው።
በዚህ መነሻ የከተማዋ የኮሪደር ልማት ከመንገድ ግንባታ ባሻገር የመዲናዋን ገጽታ እና የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል ያለመ ሰፊ የከተማ ለውጥ አቅጣጫ ሆኖ በትግበራ ላይ ይገኛል።
የከተማ ውበት በሰው ሠራሽ ግንባታዎች ብቻ አይፈጠርም፤ ዛፎች፣ መናፈሻዎች፣ ክፍት ቦታዎች እና የወንዝ ዳርቻዎችም የመዲናዋ ተፈጥሯዊ ውበት ናቸው።
እነዚህ አረንጓዴ ስፍራዎች ለነዋሪዎች መዝናኛ እና ማረፊያ ከመሆናቸው ባሻገር፣ ለከተማዋ ንጹህ አየር እና የተሻለ ከባቢን ፈጥረዋል።
ከዚህ በተጓዳኝ የሕዝብ ቦታዎችን መጠበቅ፣ ቆሻሻን በአግባቡ መያዝ እና ንብረቶችን መንከባከብም የከተማ ስልጣኔን የሚያሳዩ ተግባራት ናቸው።
ይህ ኃላፊነት ደግሞ የከተማዋ አስተዳደር ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዱ ነዋሪ የውዴታ ግዴታ ነው።
የከተማ ልማት ሌላው መሠረታዊ ጉዳይ፣ ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ አካባቢን መፍጠር ነው።
በዚህ ረገድ አካል ጉዳተኞችን ጭምር ታሳቢ ያደረጉ ሰፊ እና ምቹ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መሄጃዎች እና የሕዝብ መዝናኛዎች የመዲናዋ ልማት ሰውን ያማከለ እንዲሆን አድርገዋል።
ይህ የልማት አቅጣጫ የመደመር እሳቤን በተግባር ያሳየ ሕያው ምስክር ነው። ልማትን ከሥነ-ምህዳር፣ ዘመናዊነትን ከታሪክ፣ የመንግሥትን ሚና ከነዋሪዎች ተሳትፎ ጋር በማስተሳሰር የተሟላ የከተማ ለውጥ ማምጣት ተችሏል።
በዚህ መልኩ የኮሪደር ልማቱ ከመንገድ እና ሕንፃ ግንባታ ባሻገር ሰውን፣ ተፈጥሮን እና ልማትን በአንድ ማዕቀፍ የማበልፀግ ውጤታማ አቅጣጫን ተከትሏል።
የአዲስ አበባ የነገ ገጽታ ዛሬ በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ይወሰናል። ዛሬ የሚተከሉ ዛፎች፣ የሚጠበቁ የተፈጥሮ ሀብቶች እና የሚገነቡ ሰው-ተኮር መሠረተ ልማቶች ለትውልድ የሚተላለፉ ዘላቂ የከተማ ቅርሶች ናቸው።
አዲስ አበባን ማልማት ማለት የሕንፃዎችን እና የመንገዶችን ቁጥር መጨመር ብቻ ሳይሆን፤ ተፈጥሮን የምትጠብቅ እና ለኑሮ የምትመች ጽዱ ዘመናዊት ከተማን መገንባት ማለት ነው።
ንጹህ፣ አረንጓዴ እና ለነዋሪዎች ምቹ የሆነች ዘመናዊት አዲስ አበባን እውን ማድረግ ደግሞ ከከተማ ውበት ባሻገር የትውልዶች የተሻለ ሕይወት እና የዘላቂ ልማት ዋስትና ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #addisababa #urbancorridor #greenlegacy #cleancity #ebc

2 months ago
u12e8u12a2u1275u12eeu1335u12eb u12e8u1273u12f3u123d u1283u12edu120d u12a0u1265u12eeu1275
#ethiopia #renewableenergy #gerd #greenlegacy #electricvehicles ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል አብዮት
#ethiopia #renewableenergy #gerd #greenlegacy #electricvehicles
Sponsored by
Surafel
2 months ago
u12d3u1208u121d u12a5u12cdu1245u1293 u12e8u1230u1320u12cd u1225u122b
#ethiopia #pmabiyahmed #greenlegacy #cleanenergy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዓለም እውቅና የሰጠው ሥራ
#ethiopia #pmabiyahmed #greenlegacy #cleanenergy
2 months ago
ያለ ውጭ እርዳታ 48 ቢሊዮን ችግኞች፦ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ስኬት | Green Legacy Ethiopia
**************** #greenlegacy #ethiopia #climateaction #48billionseedlings
2 months ago
አረንጓዴ ዐሻራ፡- የኢትዮጵያውያን የሕብረትና የፅናት ህያው ሐውልት
**************************
ኢትዮጵያውያን በጋራ ስንቆም የሚያስቆመን ምድራዊ ኃይል እንደሌለ የቀደመው ታሪካችን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በዓድዋ ጦርነት በአንድ ልብ ተሰልፈን ቅኝ ግዛትን ድል እንደነሳነው እና ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የሀገራዊ ቁርጠኝነት ምልክት አድርገን እንደገነባነው ሁሉ፣ ዛሬ ደግሞ በተፈጥሮ ጥበቃ ታሪክ አዲስ ሀገራዊ ገድል እየፈጸምን እንገኛለን።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት በ2011 ዓ.ም የተጀመረው ታላቁ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ በሕብረትና በፅናት ከተጓዝን ሁለንተናዊ ለውጥን በተግባር ማምጣት እንደምንችል ያረጋገጠ ደማቅ የስኬት ማሳያ ሆኗል።
ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ እስከ 56 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን በመትከል የሀገራችንን የደን ሽፋን ከ17.2 ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።
በቅርቡም "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያውያን በድጋሚ ዓለምን ያስደመመ ታላቅ የአንድነት ድል አስመዝግበዋል።
ይህ ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከአርሶ አደር እስከ ከተሜው የተሳተፈበት ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ የተራቆቱ መሬቶችን ከማገገም ባሻገር፤ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያና ቡና ያሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በማካተት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የኢኮኖሚ አቅምን ለመገንባት ትልቅ መሰረት ጥሏል።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ጥበቃና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እያስመዘገበችው ያለው ይህ አስደናቂ ስኬት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተፈጥሮ እንክብካቤ ተምሳሌት እንድትሆን አድርጓታል።
ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ቀጣዩን ታላቅ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) እንድታስተናግድ ታሪካዊ ኃላፊነት ተጥሎባታል።
የተተከሉትን ችግኞች በተከታታይ መንከባከብና ማሳደግ የነገ ሀገራዊ ፅናታችንን የሚያረጋግጥ በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ይህን ኃላፊነት በመወጣት ለቀጣዩ ትውልድ የበለጸገችና ያሸበረቀች ኢትዮጵያን በሕብረት ሊያወርስ ይገባል።
በብሌን ደምበሎ
#greenlegacy #ethiopia #climateaction #planthope #cop32 #ebc

የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ፤ የሕዝባዊ ትብብርና የብሔራዊ መግባባት አዲስ የለውጥ ማዕበል
**********************
የተፈጥሮ አካባቢን መንከባከብና የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል ከዓለም አቀፍ አጀንዳነቱ ባሻገር፣ በኢትዮጵያ ማኅበራዊና ባህላዊ እሴቶች ላይ አዲስ ምዕራፍ እየከፈተ ይገኛል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት በሀገራዊ ጥሪ የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር፣ ዛሬ በቀላሉ ዛፍ የመትከል ዘመቻ መሆኑ አብቅቶ የሕዝባዊ ባህል አካል እና የብሔራዊ መግባባት ትልቅ መድረክ ለመሆን በቅቷል።
ይህ በየዓመቱ የሚካሄደው መርሐ ግብር በመላው ኢትዮጵያ አዲስ የማኅበረሰብ እንቅስቃሴን የፈጠረ ሲሆን፣ ዕድሜ፣ ጾታ፣ የትምህርት ደረጃ እና የኑሮ ሁኔታ ሳይለያያቸው ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ለጋራ ዓላማ እንዲሰለፉ አድርጓቸዋል።
በአረንጓዴ ዐሻራ የሚተከለው ችግኝ "ሀገር የጋራችን ናት" የሚለውን እውነት በተግባር ያሳያል።
ከአንድ ክልል የተዘጋጁ ችግኞች ወደ ሌላ ክልል እየተጓጓዙ ሲተከሉም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን እና ወንድማማችነትን ይበልጥ ያጠናክራሉ።
የአረንጓዴ ዐሻራ ስኬት በሚተከሉት ችግኞች ብዛት ብቻ ሳይሆን በሚሰጠው ዘላቂ ጥቅምም ይለካል።
የአፈር መሸርሸርን በመከላከልና የውሃ ሀብትን በማደስ ለግብርናው ክፍለ-ኢኮኖሚ ዋስትና እየሆነ ይገኛል።
በተጨማሪም የፍራፍሬ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች በመተከላቸው የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና የዜጎችን ገቢ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው።
መርሐ ግብሩ ከአካባቢ ጥበቃ አልፎ የሀገራዊ አንድነትና የሕዝቦች አዎንታዊ ግንኙነት መገለጫ ሆኗል።
የተተከሉት ችግኞች ጸድቀው ለፍሬ እንዲበቁ ማድረግ የሁላችንም ዘላቂ ኃላፊነት ሲሆን፣ ሀገር በልማት፤ ማኅበረሰብ ደግሞ በመግባባትና በአንድነት አረንጓዴ ሆኖ ይበቅላል።
በአድማሱ አራጋው
#greenlegacy #ethiopia #climateaction #environmentalprotection #nationalunity #ebc

ከአፈር ጥበቃ እስከ ቀጠናዊ ዲፕሎማሲያዊ ስኬት፡ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ ያስመዘገባቸው 10 ታሪካዊ እመርታዎች
*******************
ወደ አረንጓዴ ምድር የምታደርገውን ጉዞ በፅናት ያፋጠነችው ኢትዮጵያ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊ ተጽዕኖዎችን የመቋቋም አቅሟን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ተራ የዛፍ ተከላ ዘመቻ ሳይሆን፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ የምግብ ዋስትናን፣ የማክሮ ኢኮኖሚ እመርታን እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ የበላይነትን ያጣመረ ሀገር በቀል ስትራቴጂካዊ ተአምር ነው።
ለመሆኑ ይህ መርሐ ግብር ኢትዮጵያን በምን ዓይነት አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ አስገብቷታል? 10ን ዐበይት የአረንጓዴ ዐሻራ ውጤቶች እንመልከት፡-
✅ከዕቅድ በላይ የተመዘገበ ግዙፍ የቁጥር እመርታ
በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት ሲጀመር የተያዘው እቅድ 4 ቢሊዮን ችግኞችን መትከል የነበረ ቢሆንም፣ በሕዝባዊ ንቅናቄው 4.7 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል ነበር ታሪካዊው ዘመቻ የተከፈተው።
ከዚህ ጠንካራ መነሻ በመነሳትም እስከ 2018 ዓ.ም ባሉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ ወደ 56 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን መሬት በማስያዝ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ አስደናቂ ተሞክሮ ማበርከት ተችሏል።
✅በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የክትትል እና የጽድቅ መጠን ጥራት
የተተከሉት ችግኞች ዝም ብለው የሚተው ሳይሆን በጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS)፣ በጂፒኤስ (GPS) እና በሳተላይት ምስሎች ታግዘው የሚመሩ በመሆናቸው እያንዳንዱን እድገት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መከታተል ተችሏል።
በዚህም ዘመናዊ አሠራር ምክንያት የተተከሉት ችግኞች የመጽደቅ መጠን 84 በመቶ መድረሱ በዳታ ተረጋግጧል።
✅የዓለምን ትኩረት የሳበው የአንድ ቀን የታሪክ ሪከርድ
ሐምሌ 2018 ዓ.ም በተካሄደው ሀገር አቀፍ ዘመቻ ከ26.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በአንድ ጀምበር በመሳተፍ በ12 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን ተክለዋል።
ይህ ክንውን በ2017 ዓ.ም ተይዞ የነበረውን የ714 ሚሊዮን ሪከርድ በአዲስ መልክ የሰበረ ታሪካዊ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
✅የሥነ-ምህዳር መታደስ እና የደን ሽፋን ማደግ
በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ ብቻ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ከተሰሩት ግዙፍ አረንጓዴ ስራዎች በኋላ አሁን ላይ ወደ 23.6 በመቶ እና ከዚያ በላይ አድጓል።
ይህም ከ297 ሚሊዮን ቶን በላይ ካርቦን ዳይኦክሳይድ በመምጠጥ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
✅የመሬት ሀብትን የመጠበቅ እና የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ደኅንነት
ከመርሐ ግብሩ ትግበራ በፊት በየዓመቱ ይሸረሸር የነበረው 1.9 ቢሊዮን ሜትሪክ ቶን አፈር እና ደለል አሁን በተሰራው የተፈጥሮ ጥበቃ ምክንያት ወደ 208 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
ይህም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውኃ አካላት በደለል ከመሞላት አደጋ የተጠበቁበት ታላቅ ስኬት ነው።
✅ሰፊ አረንጓዴ የሥራ ዕድል እና የማህበራዊ ፍትሕ ማረጋገጫ
በመላው ኢትዮጵያ ከተቋቋሙት 120 ሺህ በላይ የችግኝ ጣቢያዎች ጋር ተያይዞ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ አረንጓዴ የሥራ ዕድሎች ተፈጥረዋል።
ከነዚህ ተጠቃሚዎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ወጣቶች በመሆናቸው ሥራ አጥነትን በመቀነስ ረገድ የላቀ ማኅበራዊ ፍትሕን አረጋግጧል።
✅የጥምር ደን ግብርና እና የምግብ ዋስትና እውን መሆን
ከተተከሉት አጠቃላይ ችግኞች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ተክሎች ናቸው።
አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ፖም፣ ሻይ እና ቡናን የመሳሰሉ ተክሎች በስፋት መተከላቸው የዜጎችን የዕለት ተዕለት ገቢ ከማሳደግ ባለፈ የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ እያረጋገጠ ነው።
✅የማክሮ ኢኮኖሚ እመርታ እና የኤክስፖርት ንግድ ዕድገት
በመርሐ ግብሩ የተገኘው ምርት በ2011 ዓ.ም 246 ሺህ ቶን የነበረውን የቡና ኤክስፖርት መጠን በ2017/18 በጀት ዓመት ወደ 469 ሺህ ቶን አሳድጎታል።
በተጨማሪም የፍራፍሬ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ኢትዮጵያ በአቮካዶ ኤክስፖርት ከአፍሪካ የሁለተኛ ደረጃን እንድትይዝ አስችሏታል።
✅ሕዝባዊ ባህል እና ብሔራዊ መግባባት
በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በነቃ ሁኔታ በዘመቻው ይሳተፋሉ። ይህ ሰፊ ህዝባዊ ጥምረት የአካባቢ ጥበቃን ከመንግስት ፖሊሲነት ባለፈ ወደ ጠንካራ የህዝብ የዘወትር ባህልነት እና ብሔራዊ መግባባት የቀየረ አዲስ ማህበራዊ እሴት ሆኗል።
✅የረጅም ጊዜ ራዕይ እና የቀጠናዊ ዲፕሎማሲ የበላይነት
ኢትዮጵያ እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ 65 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ይዛ እየሠራች ሲሆን፣ ይህም በ2027 ለምታስተናግደው 32ኛው የዓለም አቀፍ የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ትልቅ ድልድይ ነው።
ከዚህም በተጨማሪ ለጎረቤት ሀገራት እንደ ጂቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን በማካፈል ቀጠናዊ ወንድማማችነትን እና ዲፕሎማሲን በተጨባጭ እያጠናከረች ትገኛለች።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከቀሊል የዛፍ ተከላ ዘመቻ አልፎ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን፣ የምግብ ዋስትናን፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬን እና የዲፕሎማሲ አቅምን በአንድ ላይ ያቀናጀ አህጉራዊ የመልማት ሞዴል ነው።
ይህ ታላቅ እንቅስቃሴ ኢትዮጵያ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያበረከተችው ዘላቂ የአረንጓዴ ህይወት ስጦታ ነው።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #greenlegacy #climateaction #sustainability #plantingourfuture

ፈተናን ወደ ዕድል፡ የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በተጨባጭ ስኬቶች ሲመዘን
************************
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያጋጠሟት ሁለገብ ፈተናዎች ሳይበግሯት ትኩረቷን በታላላቅ የልማት ውጥኖች እና በኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ላይ በማድረግ አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ከፍታለች።
ሀገራችን በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋ የተያያዘችው የብልፅግና ጎዳና ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በመሳሰሉ ግዙፍ መሠረተ ልማቶች እና በሚታዩ ተጨባጭ ስኬቶች የታጀበ ሆኗል።
እየተተገበረ ያለው የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ሥርዓትን ጨምሮ በኢኮኖሚው ዘርፍ የተወሰዱት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት መስፋፋት እና የፋይናንስ ተዳራሽነት ሀገራዊ ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ።
በተለይም በዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አማካኝነት በርካታ የሕዝብ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ እንዲደገፉ መደረጉ፤ የሥራ ቅልጥፍናን ከማሳደጉም በላይ የዜጎችን እንግልት በእጅጉ ቀንሷል።
በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት፣ የኤርፖርቶች ማስፋፊያ፣ የትራንስፖርት መሠረተ ልማቶች እንዲሁም 'የገበታ ለትውልድ' የቱሪዝም መዳረሻዎች ዘመናዊና ማራኪ ሀገራዊ ገጽታን በመፍጠር ረገድ ፈጣን ለውጥ አምጥተዋል።
በሌላ በኩልም በግብርናው ዘርፍ በበጋ ስንዴ ልማትና በምርት ስብጥር የተመዘገቡት አበረታች ስኬቶች፣ ሀገራችንን በምግብ ራስን ወደ መቻል ምዕራፍ በፍጥነት እያሸጋገሯት ይገኛሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የበጎ ፈቃድ ሥራዎችና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች መተከላቸው፤ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለምግብ ዋስትና እና ለዘላቂ የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ ትልቅ መሠረት ጥሏል።
ከፈተናዎች ባሻገር የታዩት እነዚህ የልማት ስኬቶች ኢትዮጵያን ነገ ይበልጥ ተስፋማ የሚያደርጉ ናቸው። የተጀመሩት ታላላቅ የልማት እንቅስቃሴዎችና የሕዝቡ ንቁ ተሳትፎ ተጠናክረው ሲቀጥሉ፣ ሀገራችን የያዘችውን የብልፅግና ራዕይ በተሟላ ሁኔታ እንደምታሳካ የተጣለውን ጠንካራ መሠረት ማየት በቂ ማረጋገጫ ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #digitalethiopia #economicgrowth #macroeconomics #greenlegacy #infrastructure

u12d3u1208u121du1295 u12ebu1235u1308u1228u1218u12cd u12a0u123bu122bu127du1295
#cleanenergy #greenlegacy #ethiopia ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዓለምን ያስገረመው አሻራችን
#cleanenergy #greenlegacy #ethiopia
2 months ago
ዓለም ያልቻለውን ኢትዮጵያ አደረገችው | የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ዓለም አቀፋዊ ፋይዳ
#ebcdotstream #greenlegacy #globalclimateaction #ethiopianforest
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

ኢትዮጵያ ለዓለም ያስተማረችው አዲስ ታሪክ
****************
ትላንት በመላው ኢትዮጵያ በተካሄደው ታሪካዊ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ በ12 ሰዓታት ውስጥ ለመትከል ካቀደችው 800 ሚሊዮን ችግኝ 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ የዓለም አቀፍ ሥነ ምህዳር ጥበቃ ታሪክ አስመዝግባለች።
ከማለዳው ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የመትከያ ስፍራዎች ወጣቶች፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት እና ታዋቂ ግለሰቦች በተገኙበት የተካሄደው ይህ ታላቅ ሕዝባዊ ንቅናቄ ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው ተፈጥሮአዊ ህልውና እና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ምድር ያላቸውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጡበት ሆኗል።
ኢትዮጵያ ካቀደችው በላይ 805 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ባስመዘገበችው በዚህ ታላቅ ስኬት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጠንካራ መልእክቶችን አስተላልፋለች።
የአየር ንብረት መዛባትን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በመግለጫዎች እና በኮንፈረንሶች ብቻ ሳይሆን በተግባር መሬት ላይ በሚወርዱ ግዙፍ ሕዝባዊ ሥራዎች መመራት እንዳለበት በተግባር የተደገፈ መሪነቷን አሳይታለች።
በሌላ በኩል ሀገራችን የራሷን የደን ሽፋን ከማሳደግ እና የደረቁ የውኃ አካላትን ከመመለስ ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በማካፈል በቀጣናው አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።
ኢትዮጵያ በራሷ አቅም እና በሕዝቧ ንቅናቄ ትልቅ ሀገራዊ ሀላፊነቷን መወጣቷን በመግለጽ የበለፀጉ ሀገራት እና የዓለም አቀፍ አካባቢ ጥበቃ ተቋማት ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል የገቡትን የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ ቃል በተግባር እንዲወጡ በድፍረት እንድትሞግት ትልቅ የዲፕሎማሲ ሞራል እና አቅም ፈጥሮላታል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጣለባትን እምነት የሚያጸና ሲሆን፣ ሀገራችን በታላላቅ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ በዘርፉ ያላትን የላቀ የሞራል ልዕልና እና ተደማጭነት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዳግም ያስመሰከረ ነው።
የተመዘገበው 805 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ስኬት የዛሬን የተፈጥሮ ቁስል እያከመ፣ የነገዋን ኢትዮጵያ እና የዓለምን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ በተግባር የተጻፈ ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ምዕራፍ ነው።
በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #ebc #ebcdotstream #greenlegacy #planthope #climateresilience #ethiopiarising

በአንድ ጀንበር 805.3 ሚሊዮን ችግኝ ተተክሏል #greenlegacy #ethiopia #greeneconomy #environmentalprotection #agroforestry #ethiopiannews #climateaction
2 months ago
ለትውልድ የምናወርሰው ህያው ቅርስ
#ethiopia #greenlegacy #planting800million #digitalaudit #geospatialtechnology
Sponsored by
Surafel
2 months ago
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች የጋምቤላን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
**********************
በጋምቤላ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የደን እና የፍራፍሬ ችግኞች የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ እንደሚገኙ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሯ ይህንን ያብራሩት በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የክልል አመራሮች እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘውን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት፣ የጋምቤላ ክልል ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ በነቃ ተሳትፎ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ ያላቸውን የደንና የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ላይ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ተግባራት የደን ሽፋኑ እንዲጨምር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በተለይም የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለቤት ውስጥ ምግብነት ከመዋል አልፈው ለገበያ በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ይህም የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት የመትከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ባህል በሚገባ እየዳበረ በመምጣቱ፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የታቀደውን ግብ በማሳካት የላቀ ስኬት ይመዘገባል ተብሎ በከፍተኛ ተስፋ ይጠበቃል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#greenlegacy #gambella #ethiopia #treeplanting #climateaction

u1260u12a0u1295u12f5 u1300u121du1260u122d u12e8800 u121au120au12eeu1295 u127du130du129d u1270u12a8u120b - u1270u1235u134bu1295 u12a5u1295u1275u12a8u120d
#ethiopia #greenlegacy ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ - ተስፋን እንትከል
#ethiopia #greenlegacy
2 months ago
u1208u120du1306u127bu127du1295 u1218u1220u1228u1275 u12a5u12e8u1270u12a8u120du1295 u1290u12cd
#greenlegacy #ethiopia #ebc ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ለልጆቻችን መሠረት እየተከልን ነው
#greenlegacy #ethiopia #ebc
2 months ago
#ethiopia | "ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለመሬት አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች፡፡"
- የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር
እናት አለም መለሰ
***
በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተዘጋጀው ታሪካዊ ሀገራዊ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ
ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 800 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ያቀደችውን ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ጀምራለች።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በሰጡት መግለጫ፣ መላው ኢትዮጵያውያን የተጎሳቀለችውን ምድር ለመመለስና ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ አሻራ ለማኖር በአንድነት መነሳታቸውን ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ፣ “ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብለው ለምድር አደራ ይሰጣሉ፤ ምድርም የተሰጣትን አደራ እጥፍ አድርጋ ትመልሳለች” በማለት የሕዝቡን የአንድነት መንፈስና ለተፈጥሮ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል።
በ“ኑ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው የዘንድሮው ዘመቻ፣ በመደመር መርህ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በንቃት እንዲሳተፉና 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ቀን የመትከል ግብ እንዲሳካ ጥሪ ቀርቧል።
መርሐ ግብሩ ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም. እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ሁሉም ክልሎችና የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፎ በሰፊው እንደሚከናወን ተገልጿል።
ይህ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአካባቢ ጥበቃ፣ የደን ሽፋን መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለማስረከብ ከሚደረጉ ሀገራዊ ጥረቶች መካከል ቁልፍ ተነሳሽነት መሆኑ ተጠቅሷል።
#አረንጓዴአሻራ #greenlegacy #ethiopia #planttrees #climateaction #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments