33 mins. ago
ሳንቲም ፔይ እና የቅን ልቦች የ2018 የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ምርጫን በጋራ ለማካሄድ ተስማሙ
#fastmereja I ሳንቲም ፔይ እና የቅን ልቦች ድርጅት በቅርቡ የሚካሄደውን የ2018 የቅን ልቦች የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የህዝብ ምርጫ በጋራ ለማከናወን የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረገው ይህ ስምምነት የህዝብ ምርጫ ሂደቱን በዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመደገፍ ግልጽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል። የሳንቲም ፔይ የክፍያ እና የዲጂታል መሰረተ ልማት የምርጫውን የመምረጫ ግልጽነትና ፍጥነት ከፍ እንደሚያደርገው ከተፈረመው ስምምነት ለመረዳት ተችሏል።

4 hours ago
የሐምሌ ወር «የቅን ልቦች» አሸናፊዎች ታወቁ፡ ዶክተር ኖ እና ባለጫማው የክብሩ ባለቤት ሆኑ
በሐምሌ ወር የማህበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪነት የተዘጋጀው «የቅን ልቦች» ሽልማት ለዶክተር ኖ እና ለባለጫማው መሰጠቱ ተገለጸ። ሁለቱ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በወሩ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ ባከናወኗቸው በጎ አድራጎቶች እና ህብረተሰብን ባነቃቁ ስራዎቻቸው የበርካታ ተከታታዮችን ድጋፍ በማግኘት አሸናፊ መሆናቸው ተረጋግጧል።

21 hours ago
የሴዶ እና የጆኒ ታላቅ የMMA ፍልሚያ ነሐሴ 21 ይካሄዳል!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የማርሻል አርትስ እና የቦክስ ስፖርት ታሪክ ያልተነካውን እምቅ አቅም ለዓለም ለማሳየትና ስፖርቱን ለወጣቶች የቋሚ ገቢ ምንጭ ለማድረግ ያለመው ''አድዋ ፋይት ናይት 2" (ETFC 002) ታላቅ የውድድር ምሽት ነሀሴ 21 እንደሚካሄድ በዛሬዉ እለት ተገለፀ።
ነሀሴ 21 በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ በስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ ትኩረትን የሳበው እና በጉጉት የሚጠበቀው ዋና ፍልሚያ (Main Event) በጆኒ (Johnny) እና በሴዶ (Sedo) መካከል የሚደረገው ድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ግጥሚያ እንደሆነ ተገልጿል።
ዛሬ በተሰጠው የጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ተወዳዳሪዎች በፊት ለፊት ፍጥጫ (Face-to face) የተገናኙ ሲሆን እርስ በእርስ ያቀረቧቸው የተፎካካሪነት እና የስነ-ልቦና የበላይነት የመውሰጃ አስተያየቶች በስፍራው የነበረውን ስሜት ያጋገሉት ሲሆን፣ ሁለቱም ስፖርተኞች ለነሐሴ 21ዱ ታላቅ ፍልሚያ ያላቸውን ከፍተኛ ዝግጁነትና የማሸነፍ በራስ መተማመን አሳይተዋል።
የውድድሩ አዘጋጅና የስዊት ቦክስ መስራች እና ስራ አ አቶ ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው፣ ETFC 002 የቀደመው ETFC 001 ከተካሄደበት ፍጥነትና ሁኔታ በተሻለ መልኩ በከፍተኛ ደረጃ ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
አዘጋጆቹ ለፕሮግራሙ መዘገየት ይቅርታ በመጠየቅ፣በተወዳዳሪዎቹ የስነ-ምግባር ጥንካሬ ላይ ሙሉ እምነት እንዳላቸውና ስፖርተኞቹ ሀገራቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ ማስጠራት የሚችሉ መሆናቸውን አብራርተዋል።
በምሽቱ 11 የተመረጡ ፍልሚያዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ 4 የቦክስ (Boxing) 4 የኤምኤምኤ (MMA) 3 የሙአይ ታይ (Muay Thai) ፍልሚያዎች ናቸው።
በዝግጅቱ ላይ የሴቶች ተሳትፎ ልዩ ቦታ የተሰጠው ሲሆን፣ አትሌት አብስላት እና ዛራ በተወዳዳሪነት የሚሳተፉ ሲሆን በቀጣዩ «አድዋ ፋይት ናይት 003» ውድድር ላይ ደግሞ የሴት ተወዳዳሪዎች ቁጥር እንዲጨምርና ሰፊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።
በሌላ በኩል፣ በቀደሙት ዝግጅቶች የነበረውን የመቀመጫ መደራረብ ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የተሰራ ሲሆን በዚህም ተመልካቾች ትኬት በሚቆርጡበት ወቅት ቀጥታ የመቀመጫ ቦታቸውን (Seat) መርጠው እንዲይዙ እንደሚደረግም ነዉ የተገለፀዉ።
አዘጋጆቹ እንዳብራሩት፣ በቅርቡ በሚካሄዱት ETFC-003 እና ETFC-004 የውድድር መድረኮች ላይ የሀገር ውስጥ ስፖርተኞች ከውጭ ሀገር ተወዳዳሪዎች ጋር እንዲጋጠሙ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን ይህም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እንደ ኡሲክ (Usyk) ያሉ ታዋቂ የዓለም አቀፍ ቦክስ ውድድሮችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማዘጋጀት ለተያዘው ታላቅ ዕቅድ መንገድ የሚከፍት ነው ተብሏል።
ይህ ዝግጅት በአድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ፣ የስፖርት አመራሮች እንዲሁም አጋር ድርጅቶች አስተዋጽኦ የሚካሄድ ሲሆን፣ የስፖርት አፍቃሪያን የነሐሴ 21ዱን የሴዶ እና ጆኒ ፍልሚያ በከፍተኛ ጉጉት በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
📷 ከበደ መክብብ

23 hours ago
🚨 አፋልጉኝ 🚨
ታዳጊ አልዓዛር ጌታቸው የ14 ዓመት ታዳጊ ሲሆን፣ ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሚኖርበት ሐያት 49 ኮንዶሚኒየም እንደወጣ እስከ አሁን አልተመለሰም።
ያያችሁት ወይም ያለበትን ቦታ የምታውቁ አባካችሁ በሚከተሉት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ለቤተሰቦቹ ጥቆማ በመስጠት ተባበሩ፡
📞 0911793976
📞 0991693268

“ታሪክ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም-የነፍስ መገለጥ እንጂ”
ጋዜጠኛ ዮናስ አየለ እንደጻፈው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሚኮ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳምጬ እንደጨረስኩ በቃለ ምልልሱ በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ ጎልተው ከወጡ ዋና ዋና ጭብጦች መካከል አንዱ ነገረ ታሪክ እንደሆነ ተሰምቶኛል፡፡ ታሪክ-የሀገር ውስጥና የውጭ፤ የሩቅና የቅርብ ዘመን! ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያንጸባረቁትን ሚዛናዊና አምክኖአዊ የታሪክ እይታና ድምዳሜያቸውን አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ የአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ ዘመን እንግሊዛዊ የታሪክ ጸሐፊና ፖለቲከኛ ሎርድ አክተን “History is not a burden on the memory but an illumination of the soul” ብሎ ሲጽፍ “ታሪክ የነፍስ መገለጥ እንጂ በትዝታ ላይ የተጫነ ሸክም አይደለም” ማለቱ ነበር፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ አንኳር ጉዳዮች እስከዛሬ ድረስ በሀገራችን የታሪክ አጻጻፍ(Historiography) እና በሕዝባዊ ትርክቶቻችን(በሚዲያዎችን ጭምር) በሚገባቸው ልክ ያልተወሱ፤ ቢወሱም ፈራ ተባ እየተባሉ የሚጠቀሱ፤ አለፍሲልም ባልተገባ የፖለቲካ እይታ ደንቃራ ተደርገው የተወሰዱ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of the history) ሆነው የኖሩ ስብራቶቻችን ነበሩ፡፡ ከነዚህ ቁልፍ ጉዳዮች መካከል ዋነኛዎቹ አንዱ የሕዝቦች ትስስር እና መስተጋብር ታሪክ ሲሆን ሌላኛው በአገረ መንግስት ምሥረታ ውስጥ የሸዋ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚናን የተመለከቱት ናቸው፡፡
በመጀመሪያ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በኩታ ገጠም ቀዬዎቻቸው እና የታሪክ እድል በፈጠረላቸው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የባህል አጋጣሚዎች እንደሌሎች ማህበረሰቦች ሁሉ መጋባት መዋለዳቸው፤መተሳሰር መዋሀዳቸው ሀቅ የመሆኑን ያህል የታሪክ ጥናት እና የትርክቶቻችን ማጠንጠኛ አለመሆናቸው ይታወቃል፡፡ ከዚህ በባሰ ሁኔታ ደግሞ በነገሥታቱ መካከል የነበረው የፖለቲካ ጋብቻና የመሪዎቻችን ማህበራዊ መሠረት ጉዳይ ነውር እስኪመስል በእውነታው ልክ ሳይጠናና፣ሳይነገርለት ዘመናት አልፈዋል ፡፡ በሌላ በኩል በሸዋና አካባቢው ለረዥም ዘመን የኖሩ ሕዝቦች በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት የተጫወቱት ሚናና የሚጋሩት ቀደምት የሥልጣኔ ባለቤትነት (ታሪክ ሰሪነት-Agency) ግጥምጥሞሽ በሀገር መሪ ደረጃ መወሳታቸው እጅግ ጉልህ ፋይዳ ያለው ጉዳይ ነው ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው ያነሷቸው የታሪክ እውነታዎች ያለጥርጥር ታሪካችንንና የታሪክ ምልከታችንን ደጋግመን መመርምር እንዳለብን የሚያስገነዝቡና የወገንተኝነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ሃይማኖታዊ የታሪክ ምንጮች እንኳን የተቀመጡ ገሃድ እውነታዎች ናቸው፡፡ መመርመር ለሚፈልግ አጥኚ እነዚህ የታሪክ እውነታዎች በየነገሥታቱ ዜና መዋዕሎች (የዐጼ አምደ ጽዮን፣ ዐጼ ሱስንዮስ፣የዐጼ ገላውዲዮስ፣ የዐጼ ሠርጸ ድንግል ወዘተ)፤ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የታሪከ ነገሥት ቅጂዎች፣ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ አውሮፓውያን ተጓዦችና ጸሐፊያን (ፍራንስስኮ አልቫሬዝ፣ ፔድሮ ፔዝ፣ ማኑኤል አልሜዳ፣ ጄሮኒሞ ሎቦ፣ ጀምስ ብሩስ፣ ኮንቲ ሮሲኒ ወዘተ ) መዝግበው በተውልን ሰነዶች ሰፍረው የምናገኛቸው፤ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ ቱባ መረጃዎች ናቸው፡፡
ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተወልን የጽሑፍ ሰነድና ሌሎች ሀገርኛ የቃል መረጃ ምንጮች ዐፄ ልብነድንግል(1498-1532 ዓ.ም.) እንደ መሪ የአማራና የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ምናልባትም የሌሎች ሕዝቦችም ማህበራዊ ዳራ የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት እንደሆኑ የሚያስረዱ ሲሆን አልቫሬዝ የንጉሱ የእናት ወንድም የነበሩት አጎታቸው ዶሪ ባህረ ነጋሽ ኦሮሞ እንደነበሩና ባህረ ነጋሽ ዶሪ ሲሞቱ ሥልጣኑ በቀጥታ ወደልጃቸው ቡሎ መሸጋገሩን ጭምር በአይኑ ያየውን ጽፏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በትኩረት መታየት የሚገባው ጉዳይ ስለዐጼ ልብነ ድንግል የጦር አዛዦች የተነገሩ የቃል መረጃዎች ናቸወ፡፡ ከእነዚህ መካከል የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት የቦረንትቻ ባሕል ያውቅ እንደነበር በተክለጻዲቅ መኩሪያ መጻፉና ከዐጼ ልብነድንግል የጦር አዛዦች አንዱ የነበረው ቱሉ ደገልሀን በመራው ከኢማም አሕመድ ጋር የተካሄደ ጦርነት የዐጼው ጦር ሲያፈገፍግ ንጉሠ ነገሥቱ “ሁሉም ቢፈራ ቱሉ እንዴት ፈራ? ” ማለታቸው ስለሠራዊታቸው ሥብጥር የሚነግረን ነገር አለ፡፡
ኦቶማን ቱርኮችን እና የዘመኑ ተላላኪዎቻቸውን ለመዋጋት የንጉሠ ነገሥቱ ሠራዊት አንድ አካል ሆነው እስከ ኤርትራ ድረስ ዘምተው ስለነበሩ የኦሮሞ ተዋጊዎች ተጋድሎ የዐጼ ሠርጸድንግል(1542-1590 ዓ.ም.) ዜና መዋእል በግልጽ አስፍሯል፡፡ እነዚህ የኦሮሞና የሌሎች ሕዝቦች ተወላጅ ወታደሮች ትግራይ እንጢጮ አካባቢ ያካሄዱትን አውደ ውጊያ ዜና መዋዕሉ ይተርካል፡፡ ለመንግሥታቸውና ለሀገራቸው እስከባሕር ጠረፍ ድረስ ዘምተው ዋጋ መክፈላቸውም ተመዝግቧል፡፡ የዐጼ ሱስንዮስ(1607-1632 ዓ.ም.) ዜና መዋእል እና በዘመኑ ኢትዮጵያ መጥተው የነበሩ የአውሮፓ(የፖርቱጋል) ተጓዦች የጻፏቸው የመረጃ ምንጮች ንጉሠ ነገሥቱ ግንደበረት፣ሐምቦና አካባቢው ቤታቸው እንደነበር፤ አጎታቸው ለማሞ እንደሚባል፣ ወላጅ እናታቸው(ሐመልማል ወርቅ) የአዛዥ ኩሎ ልጅ የነበረች፤ የዚሁ የሐመልማል ወርቅ ጎሳ ተወላጅ የሆነ ቡኮ የተባለ ኦሮሞና ሠራዊቱ ለአባይ ቅርብ የሆነች ምዕራብ ሸዋ ላይ ዐጼ ሱስንዮስ ሲያገኙት የነበረውን ደስታና የፍቅሩን ጽናት ዜና መዋዕሉ ሳይሰስት ጽፎታል፡፡ ዐጼ ፋሲል(ከ1632 እስከ 1667 ዓ.ም.) አባቱ ሱስንዮስ እናቱ የወሎ ቃሉ ሰው(እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ የሚል ስም የተሰጣት) እንደሆነች የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1620ዎቹ ዓመታት ጀምሮ በኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ፖርቱጋላዊ ቄስ ጄሮኒሞ ሎቦ ስለዐጼ ፋሲል እናትና ኦሮሞ ዘመዶቻቸው በአይን ምስክርነት የሚያውቀውን ጽፏል፡፡ የእቴጌ ሥልጣን ሞገሳ አያት ስለብዝሀ ሃይማኖት አስፈላጊነት የነበራቸውን ግልጽ ፖሊሲ ጭምር ሎቦ ዘግቦታል፡፡ የዐጼ በካፋ(1721-1730 ዓ.ም.) እና የዐጼ ኢዮአስ(1747-1761 ዓ.ም.) ጎንደር መቼም ለሕዝቦች ውህደትና ትስስር ጥሩ ማሳያ ነበረች፡፡ የየጁ ኦሮሞ ገዢ የነበረው የአሚቶ ሴት ልጅ ዝነኛዋ ውቢት ልጇ ዐጼ አዮአስ ነበር፡፡ ኢዮአስ ከኦሮሞ አጎቱ ከደጃች ሉቦ ጋር ሥልጣኑን በጎንደር እንዴት እንዳጸና፤ የቤተ መንግሥቱም የሥራ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ እንደነበረ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕልና በጀምስ ብሩስ ቅጽ ሁለት መጽሀፍ የተመዘገቡ የታሪክ መረጃዎች ያስረዱናል፡፡
መነሻውን ወሎ በማድረግ ጎንደር ጸንቶ የኖረው የየጁ ሥርወ መንግሥት(ወረ ሼኮች) መሥራቾች የመርሳው አባ ጌትዬ፣ የልጃቸው ጓንጉል አባ ሴሩ እንዲሁም የልጅ ልጃቸው የራስ አሊ ጓንጉል(አሊ ትልቁ) ታሪክ በኢዮአስ ዜና መዋዕል፣ በጀምስ ብሩስ መጽሐፍና በሌሎች በርካታ ሰነዶች ታሪካቸው ተዘግቧል፡፡ በኋላ ላይ በሽፈራው በቀለ(ፕሮፌሰር) እና ሞላ ትኩዬ የቀረቡ ጥልቅ ጥናቶች ይህን እውነት በዝርዝር ያስረዱናል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው እንደጠቀሱት የእነዚህ መሪዎች የፖለቲካ ጋብቻ ታሪክ የሚያሳየን በሄዱበት አገር ሁሉ የሕዝቦች ትሥሥር እና የፖለቲካ ጋብቻ የኖረ ታሪካችን እና የጉልበታችን ምንጭ እንደነበረ ነው፡፡ በዳግማዊ ዐጼ ቴዎድሮስ ዘመን የተጻፉ የታሪክ ሰነዶች የወሎዋ ገዢ ወርቂቱ ወዳጆ(የማመዶች ሥርወ መንግሥት መሪ የኢማም አሊ አባ ቡላ ባለቤት) ንጉሥ ምኒልክ ከመቅደላ እስር ቤት እንዲያመልጡ ያደረጉ፤ አጃቢ ሠራዊት አሰማርተው ምኒልክን እስከሸዋ የሸኙ እንደነበሩ በዋናነት ከጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ ታሪከ ዘመን ዘ ዳግማዊ ምኒልክ ዜና መዋዕል እና በመቅደላ አምባ እስር ላይ የነበሩ አውሮፓውያን ከጻፏቸው መረጃዎች እንረዳለን፡፡
ሥልጣኔዎቻችን ሁሉ ተደምረን ያሳካናቸው እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው አንስተዋል፡፡ የዐድዋ ዘመቻና ድሉ ለዚህ አንዱ ማሳያ እንደሆነ ተጨባጭ የታሪክ ምንጮች ያስረዱናል፡፡ በ1888 ዓ.ም. ለዓድዋ ዘመቻ ከመላው ኢትዮጵያ የተመመው ሠረዊት ወፍላ ላይ የነበረው ሠልፍ የንጉሠ ነገሥቱ ዜና መዋዕል እንኳን እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ “የመኳንንቱ የጦር መሣሪያ፣ወርቁ፣ ጣፋ፣ ብሩ፣ ሙጣው፣ ጫሜው፣ ሎሚታውና ኩፊታው፣ ከሌቻው፣ ወርቅ ለምዱ እንደጸሐይ ሲያበራ ዋለ፡፡” እንደጸሐይ የበራውን ሕብረ ባሕልና ሕብረ ማንነት ትርክቶቻችን በልኩ አጉልተው ያውቃሉ?
ሸዋና አካባቢው(ወሎን ጨምሮ) እንደ አንድ ጂዞ ስትራቴጂ ሥፍራ የሕዝቦች ውህደትና ትስስር መሠረት ሆኖት የመልክዓ ምድር መገኛው ለግብርና እና ለውጭ ንግድ የተመቸ በመሆኑ በኢትዮጵያ አገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ ውስጥ ቁልፍ ቦታ ይዞ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው መግቢያ አስታውሰውናል፡፡ ሸዋና አካባቢው ከመንግሥታት ምስረታ ጋር በተገናኘ ከዘጠነኛው አንስቶ እስካሁን ያለው ረዥም የታሪክ ጉዞ በርግጥም ሊነገር፣ ሊተነተን የአደባባይ ትርክት አካል ሊደረግ የሚገባው እውነት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሸዋ ሡልጣኔት ምስረታ( እ.አ..አ.896 ዓ.ም.) እስከ ዓድዋ ድል(1888 ዓ.ም.) ሥላወሷቸው የአርጎባ(የወላስማ/ወሊ አስማ ሥርወ መንግሥት)፣ የአማራ(ሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት)፣ ኦሮሞ(ቱለማው በተለይ)፣ወርጂ፣ ጉራጌ፣ ጋፋት፣ ወዘተ ሕዝቦች ትስስርም ይሁን የፖለቲካ ጋብቻ የተመለከተ ታሪክ ከበቂ በላይ የታሪክ ማስረጃ ምንጮች ቢኖሩንም በታሪክ ግርዶሹ ምክንያት የወል ትርክት አካል መሆን አልቻለም፡፡
ኤንሪኮ ቼሩሊ ከሐረር አግኝቶ ያሳተመው በአረብኛ የተጻፈው የሸዋ ሡልጣኔት ዜና መዋዕል እንደሚያመለክተው ሡልጣኔቱን እ.አ.አ. በ896/7 የመሰረቱት የማህዙሚ ጎሳ አባላት ናቸው፡፡ መንግሥታቸውም ከ9ኛው እስከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በተከታታይ በገዙ አሥራ አራት ሱልጣኖች እንደጸና የታሪክ መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ የሸዋ ሙስሊም ሡልጣኔቱ መቀመጫ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምሥራቅ 70 ኪሎ ሜትር ላይ የምትገኝ ወለላ የተባለች ሥፍራ እንደነበረች የጆርጅ ደብሊው ቢ ሀንቲንግፎርድ(1989) ጥናት ያመለክታል፡፡ የማህዙሚ ሥርወ መንግሥት ከመጨረሻዎቹ መሪዎች አንዱ የነበረው ሡልጣን ድልመራህ ወርጂዎች የይኖሩበት በነበረው አካባቢ በ1270ዎቹ በነበረ የርስ በርስ ጦርነት ድል ሳይቀናው ሲቀር ሕይወቱን ለማትረፍ ዐጼ(የአማራ ገዥ?) እንደሄደ ይህው የአረብኛ ዜና መዋእል ያስረዳል፡፡ የማህዙሚዎች የሸዋ ሡልጣኔት የተተካው በዋናነት የአርጎባዎች አገር በሆነው ይፋት(ዊፋት) ላይ በወላስማዎች ነበር፡፡ ወላስማዎች ከአጎራባቾቻው ጋር እየተጋቡ፣ እየተስማሙም እየተጋጩም የይፋት ሡልጣኔትን ከ13ኛው እስከ 15ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ እስከ ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ጠረፍ እንዳስተዳደሩ ስፍር ቁጥር የሌለው የሰነድ( የኢብን ካልዱን ተማሪ የነበረው አል ማቅሪዚ ጽሑፍ- ኪታብ አል ኢልማም)፣ የአርኪዮሎጂና የቃል መረጃ ምንጮች አሉ፡፡
መነሻውን ሰሜን ሸዋ እና ደቡብ ወሎ ያደረገው የክርስቲያኑ ሰሎሞናዊ ሥርወ መንግሥት በአካባቢው ያሉ ሕዝቦች ተዋህደው ከ13ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በጋራ የመሠረቱት እንደሆነ አያጠያይቅም፡፡ አማራዎች፤ አርጎባዎች፣ ወርጂዎች፣ ጋፋቶች፣ ጉራጌዎች እና ኦሮሞዎች፣ አፋሮች፣ ሐረሪዎች ወዘተ በዚህ የሸዋ መንግሥታት የተጽዕኖ ምህዳር(Orbit) ውስጥ እንደሚገኙ ዜና መዋእሎች፣ የሃይማኖት ሰነዶች፣ የአርኪዮሎጂ ማስረጃዎች ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩ የቃል መረጃ ምንጮች ያመለክታሉ፡፡ ለምሳሌ ታደሠ ታምራት(ፕሮፌሠር) ከ13ኛው እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያንና መንግሥትን ግንኙነት ታሪክ ባጠኑበት መጽሐፋቸው የገላንና ያያ ሰዎች ሸዋ ውስጥ በ13ኛው ክፍለ ዘመን በኦዳ ዛፍ (ኮቢል የሚባል ዋርካ) ሥር ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይፈጽሙ እንደነበር ገድለ አቡነ ቀውስጦስን ጠቅሰው ጽፈዋል(ገጽ 184)፡፡ ሸዋ የባለ ብዙ ማንነት ሕዝቦች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር በ16ኛው ክፍለ ዘመን የተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች ላይ መረጃ የተወልን መነኩሴው አባ ባህሪይ እንደገለጸው “ሸዋ የመንግሥት ሀገር ነች” (ገጽ 130)፡፡ በየዘመናቱ ከሸዋ የተነሱ የፖለቲካ ኃይሎች፣ ፈረሰኛ ሠራዊታቸውን ይዘው በሰሜን እስከ ኤርትራ(በዐጼ ሠርጸ ድንግል ዘመን- የኤርትራዋ ባሬንቱ የዚህ የታሪክ ሂደት ውርስ አይደለችም ማለት አይቻልም፡፡) በምሥራቅ እስከ ዘይላ(ከዐጼ አምደጽዮን እስከ ገላውዲዮስ ዘመን)፣ በምዕራብ እስከ ሱዳን ፋዞግሊ(ዐጼ ሱስንዮስ ዘመን) በደቡብ እስከ ሞያሌ ተንቀሳቅሰው በአገረ መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫተዋል፡፡
እነዚህ የሸዋ እና አካባቢው ሕዝቦችና ገዢዎች ትልቁን ንቅናቄያቸውን ያደረጉት ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዐጼ ምኒልክና ራስ ጎበና ዳጬ የቱለማ ኦሮሞ፤ የሸዋ አማራ እና የሌሎችም ውህድ የሆነ ጦራቸውን አዝምተው ወሎ ወግተው ወረኢሉን የመንሥታቸው መቀመጫ ያደረጉት አርሲ፣ወለጋ፣ከሐረር ከመዝመታቸው በፊት ነበር፡፡ የመጫ ኦሮሞ ተወላጁን የጎጃሙን ንጉስ ተክለሃይማኖት(አዳል ተሰማ) በቱለማው መሪ ራስ ጎበና ዳጪ እምባቦ ላይ ያስገበሩት የጂኦ ፖለቲካዊ እና የሕዝቦች ትስስር እድሎች ጉልበት ፈጥሮላቸው፤ ኃይል አጎናጽፏቸው እንጂ በአጋጣሚ አይደለም፡፡ በርግጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፖለቲካችን ደንቃራነት የፈጠረውን የታሪክ ግርዶሽ ያሸነፉ ፋና ወጊ ጥናቾች መውጣት ጀምረዋል፡፡ አንዱ “Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia(1855-1913)” በሚል ርዕስ በብሪያን ጀምስ ዬትስ(2002) በኤሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ ከተጠናው እጅግ ጠቃሚ የዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናት ሲሆን ሌላው የደቻሳ አበበ(ዶ/ር) ጎበና ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ ምልልሳቸው የዘመናዊት ኢትዮጵያን እውን መሆን ያለ ምኒልክና ያለ ጎበና እንደማይታሰብ ሲጠቅሱ ይህንን እውነታ ማጉላታቸው ይመስለኛል፡፡
የሕዝቦች ትስስርና የፖለቲካ ጋብቻ በአማራና በኦሮሞ ሕዝብ መስተጋብር ብቻ የታጠረ አልነበረም-ሊሆንም አይችልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ሥልጣኔ መጋመዱ ረቂቅ ነው፡፡ ከጥንታዊ አክሱም ዘመን ጀምሮ በዝነኞቹ የአክሱም መቃብር ሀውልቶች እና በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ከምናገኛቸው የኪነ ሕንጻ ትእምርቶች(Symbols) መካከል የውሸት በሮች (False Doors) እና የውሸት መስኮቶች(False windows) የሙታን መንፈስ(ኤከራ) መመላለሻ እንደሆኑ በጥናት የተረጋገጠ ነው (ቢትራይስ ፕሌይን Annales d'Éthiopie 1965) ፡፡ ይህ የኤከራዎች መመላለስና የመነጋገር ባህል እና እምነት ከደቡባዊ ግብጽ አንስቶ እስከ ሰሜን ኬንያ ድረስ በሚኖሩ የኩሽ ሕዝቦች በሰፊው የሚታወቅ ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ልምምድ ነው፡፡
ሌላው በልኩ ያልተጠና እና በትርክቶቻችን ውስጥ ትኩረት ያልተሰጠው በሕዝቦች መካከል ያለ ሥልጣኔ ትስስር ታሪክ የእያንዳዱን የዛግዌ ነገሥታት የሥልጣን ዘመናትን የተመለከተ ነው፡፡ ከታሪክ ነገሥት፣ ከልዩ ልዩ ዜና መዋዕሎች፣ ከፖርቱጋል ተጓዦች(ፓኤዝና አልሜዳ) ከብሪቲሽ ሙዝየም እንዲሁም ከኮንቲ ሮሲኒ የተገኙት ምንጮች የሚረጋግጡት የሁሉም የዛግዌ ዐጼዎች( ከአንድ ሁለቱ በስተቀር) የሥልጣን ዘመን 40፤40 ዓመታት ነበር፡፡ ይህ ጉዳይ በኦሮሞ የገዳ ሥርዓት የአንድ ትውልድ የሥልጣን ዑደት ጋር አንድ አይነት የሆነው በአጋጣሚ ነው ወይስ ዛግዌዎች እና ኦሮሞዎች የኩሽ ሕዝቦች በመሆናቸው ቀዳሚ ከሆነው የጋራ ሥልጣኔያቸው የሚቀዳ የአስተዳደር ሥርዓት ነው? እነዚህስ ሀቆች የወል ትርክቶቻችን መመሆን አለመቻላቸው በፖለቲካ ደንቃራነት የተፈጠረ የታሪክ ግርዶሽ(eclipse of history) እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል? በላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና እና በሸዋ በሚገኘው የአዳዲ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ኪነሕንጻ መካከል ያለው ፍጹም ተመሳሳይነት ምንጩ ምንድነው? ሊጠና፣ ሊነገር ልንማርበት ይገባል፡፡
በርግጥም ታሪካችን ትዝታችን ላይ የተጫነ ሸክም ሳይሆን የነፍስ መገለጥ ነው የሚያሰኘው የሕዝቦች ትሥሥር፣ ውህደት የሥልጣኔ መጋራትና መወራረስ ታሪክ መታወቁ መንፈስን ሃርነት ማውጣቱ ይመስለኛል፡፡

1 day ago
ከሞጃና ወደራ ወረዳ አስተዳደር ምክርቤት የተሰጠ የሀዘን መግለጫ
በታላቋ ገዳም በጻድቃኔ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ገዳም ድንገት በተከሰተ ርዕደ መሬትና የመሬት መንሸራተት አደጋ የ14 ሰው ሕይወት አለፈ።
በመሬት መንሸራተቱ የ14 ምዕመናን ሂወት ሲያልፍ በ5 ሰው ላይ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በ2 ሰዎች ላይ መለስተኛ ጉዳት በመድረሱ የወረዳዉ አስተዳደር ምክርቤት መሪር ኀዘኑን ገልፆል ።
የወረዳዉ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሀን ተስፈ ጨምሮ የወረዳ አስተባባሪ አመራርና የፀጥታ አመራሩ እቦታዉ ላይ በመገኘት ነፍስ በማዳን እርብርቡ ላይ ሁለተናዊ ድጋፍ አድርገዋል።
የህክምና ባለሙያዎች የአካባቢዉ ማህበረሰብ በቦታዉ ላይ በመገኘት የተጎዱ ወገኖችን የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ብርቱ ትግል አድርገዋል።
ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ቀሌምንጦስ በስፍራው የተገኙ ሲሆን ለሞቱ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ለተጎዱት ጸሎት ላዘኑ ወገኖቻችን የማጽናኛ ትምህርተ ወንጌልና አባታዊ ቃለ በረከት በመስጠት ላይ ይገኛሉ ።

በጅማ ዞን «ተስፋን እንትከል» በሚል መርህ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ
#fastmereja I በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን፣ ሰቃ ወረዳ ቡዬ ቀጨማ ቀበሌ ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም «ተስፋን እንትከል» በሚል መርህ የመላው ኢትዮጵያውያንን ጥሪ ያቀናጀ ታላቅ የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል። ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በተያዘው አገራዊ ግብ መሠረት የተከናወነ ሲሆን፣ የአረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ረገድ የትውልድ ሀላፊነትን ለመወጣት ያለመ አገራዊ ጥረት አካል እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ ሀገር አቀፍ አቅጣጫን መሠረት ያደረገ ታላቅ መርሃ ግብር በግሪን ዌቭ አሊያንስ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት፣ ከኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ለዝግጅቱ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ ስነ-ስርዓት ላይ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ከታደሙት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መካከል የግብርና ሚኒስቴር ደኤታ ዶክተር ኢፋ ሙለታ፣ የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቲጃኒ ናስር፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ደኤታ ነፊሳ አልመሃዲ፣ የግሪን ዌቭ አሊያንስ መስራች አምባሳደር ሚካኤል ነጋሳ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መልካሙ ዴሲሳ ይገኙበታል።
በተጨማሪም የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች እና የቲክቶክ ይዘት ፈጣሪዎች በስፍራው በመገኘት አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፍ ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል።
መርሃ ግብሩ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤን ለማጠናከር እና የወደፊት ትውልድን የወደፊት እጣ ፈንታ በተግባር ለመገንባት ያለመ መሆኑን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

አባይ ሆምስ ሪል እስቴት ኪንግስ ሬዚደንስ የተሰኘውን ሁለተኛ ፕሮጀክቱን በይፋ አስጀመረ
አባይ ሆምስ ሪል እስቴት ቄራ-ጎተራ አካበቢ የሚገነባውን ሁለተኛ ፕሮጀክቱን ሀምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. በይፋ አስጀምሯል።
ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ፊት ለፊት በሚገኘው የሽያጭ ቢሮ ብቅ በማለት የዚህ ፕሮጀክት ቀዳሚ ባለቤት ይሁኑ።

Sponsored by
Surafel
2 days ago
በጅማ ዞን ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ የተለያዩ እንግዶች ጅማ ገቡ!
በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን ሰቃ ወረዳ በቡዬ ቀጨማ ቀበሌ ነገ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄደውና ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ የቀረበበት የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠጠናቀቁ ተገለጸ። በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በተያዘው ግብ መሠረት የሚከናወነው ይህ መርሃ-ግብር፤ አረንጓዴ አሻራን በማሳረፍ ረገድ የትውልድ ሀላፊነትን ለመወጣት ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ይህ ሀገር አቀፍ አቅጣጫን መሠረት ያደረገ ታላቅ መርሃ-ግብር በግሪን ዌቭ አሊያንስ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት፣ ከኢፌድሪ ግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዘጋጅነት የቀረበ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ አስፈላጊውን ቴክኒካል ድጋፍ በማድረግ ተሳትፏል።።
ለዝግጅቱ ስኬት በጅማ ከተማ የደረሱ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ቲክቶክሮች እና የጥሪው ተጋባዦች በዞኑ እና በከተማ አስተዳደሩ፣ በአባ ገዳዎች፣ በሀደ ሲንቄዎች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ነገ በሚካሄደው በዚህ ታሪካዊ ኹነት ህብረተሰቡ በነቃ ሁኔታ እንዲሳተፍ አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል።

የእናንተ የሐምሌ ወር የቅን ልቦች የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪ ማነው ?
1.ባለጫማው
2.ዶክተር ኖ
3.ማራኪ ወግ
4. ወቸው ጉድ
5.ቲክቫህ ኢትዮጲያ
6.ቴዲ ሀዋሳ
ድምፃችሁን
በ0908089108
0908089408 ቴክስት ብቻ አድርጉ
1.ባለጫማው
2.ዶክተር ኖ
3.ማራኪ ወግ
4. ወቸው ጉድ
5.ቲክቫህ ኢትዮጲያ
6.ቴዲ ሀዋሳ
ድምፃችሁን
በ0908089108
0908089408 ቴክስት ብቻ አድርጉ
2 days ago
የአቡነ ሀብተ ማርያም ምልጃ እና ረድኤት አይለየን🙏
በምጽዋትና በስገድት የምትጋደለው እናቱ ዮስቴና ሀብቷን ሁሉ ለድሆች ሰጥታ ለምናኔ ወደ በረኃ ሄደች።
በዚያ ያገኘችው ባሕታዊም በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሰች፡፡ የአባቱ የትውልድ ሀገር የራውዕይ በምትባል ሀገር ሲሆን ከዚህች የተባረከች ሴት ጋር ተጋባ። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች፣ በሕግ ተወስና በጾም፣ በጸሎት፣ የምትተጋ ነበረች።
ከጥቂት ጊዜያት በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። በሕገ እግዚአብሔር አንጸው አሳደጉት። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።
አንድ ቀን የአባቱ በጎቹን ሲጠብቅ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለ፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። እርሱ ግን በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዝናም ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ የሀብተ ማርያምን በትሩን በጉልበት ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅ ሎ አዋለው። እረኞቹም ሀብተ ማርያምን ሲለምኑት፣ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ስር ወደቀ፡፡ በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሶ ታላቅ ተጋድሎ ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ 500 ጊዜ ይሰግዳል።
እህልም መቅመስን ትቶ የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም ያከፍላል። በሌሊትም ቁሞ በማደር በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ አሥነሳውና ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት መጻፉን ነገረው፡፡ ስለ ድንግልናው፣ ስለ ምናኔው፣ ስለ ፍጹም ምንኲስናው፣ አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። የቅዱስ ማቴዎስንና የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ሲያነብ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ ሰጠው፡፡
የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል ሲያነብም ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ ሰጠውና ቃል ኪዳን ገባለት። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶች ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክት ሁሉ እየተደሰቱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያምን “ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል” አሉት። ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። በኅዳር 26 ቀን ነፍሱ ከሥጋው በሰላም ተለየች።
ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት። ገዳማውያን የዓለምን ክብር ንቀው ሔደዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውን እንደግፍ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
· አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ፦ የሰዎች ህመም የሚሰማቸው፣ ተስፋን በተግባር የሚተረጉሙት ስራ ፈጣሪ
“Life’s most persistent and urgent question is, 'What are you doing for others?'”
(የህይወት ዘወተር እና አጣዳፊው ጥያቄ፦ ‘ለሌሎች ሰዎች ምን እያደረግክ ነው?’ የሚለው ነው።)
— ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር
በማህበረሰብ ውስጥ የሚታዩ ክፍተቶችን አይቶ ከመቆጨት ይልቅ የመፍትሔ አካል ለመሆን መነሳት የትልልቅ ሰዎች መለያ ባህሪይ ነው። በትውልደ ኢትዮጵያዊው ስራ ፈጣሪ አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ዘንድም የሚታየው ይህ ህያው እውነት ነው፤ ጥበብን፣ የበጎ አድራጎት መንፈስን እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን በማስተሳሰር በሀገራችን ልዩ የለውጥ አሻራ በማስቀመጥ ላይ ይገኛሉ።
የተድላ አምቡላንስ መወለድ፦
የህይወት አድን አገልግሎት ራዕይ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በሀገራችን በህክምና ትራንስፖርት ዘርፍ ያለውን ትልቅ ክፍተት በጥናት በመረዳት ነው "ተድላ አምቡላንስን" ወደ ስራ ያስገቡት። በተለይም አካል ጉዳተኞች፣ የአእምሮ ዕድገት ውስንነት (ኦቲዝም) ያለባቸው፣ የዳያሊሲስ ህመምተኞች እና አረጋውያን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚያጋጥማቸውን የእንቅስቃሴ እና የትራንስፖርት እንግልት በመመልከት፣ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የድንገተኛ እና ድንገተኛ ያልሆነ የህክምና መጓጓዣ አገልግሎት እንዲመሰረት አድርገዋል።
ድርጅቱ ከንግድ ስራ በላይ የማህበረሰብ አለኝታነትን መርሁ በማድረግ፦
· ደረጃቸውን የጠበቁ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ያቀረበ፣
· በገንዘብም ሆነ በአገልግሎት ደረጃ አቅም የሌላቸውን ለመደገፍ የተጋ፣
· ለሁሉ አቀፍ ተደራሽነትና ለዜጎች ክብር የቆመ ተቋም ሆኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
“The best way to find yourself is to lose yourself in the service of others.”
(ራስህን ለማግኘት የሚቻለው የተሻለው መንገድ በሌሎች አገልግሎት ውስጥ ራስህን ስትሰጥ ነው።)
— ማሃትማ ጋንዲ
“ማንም የላት”፦
ጥበብ ለሰብአዊነት እና ለማህበራዊ ንቅናቄ
አቶ ሳሚ ከስራ ፈጣሪነታቸው ባሻገር፣ ጥበብ ለማህበራዊ ለውጥ ያላትን ትልቅ ሀይል በመረዳት ከ1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ “ማንም የላት” የተሰኘውን ታሪካዊ የኅብረት ዜማ ፕሮዲዩስ አድርገዋል።
ይህ ስራ በግጥም ናትናኤል ግርማቸው፣ በዜማ አህመድ ተሾመ (ዲንቢ)፣ በቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) እንዲሁም በዳይሬክቲንግ ነፃዓለም አብዲ የተቃኘ ሲሆን፤ ድምፃውያን ማስተዋል እያዩ፣ ሄዋን ገብረወልድ፣ ሀና ግርማ እና አብርሃም በላይነህ (ሻላዬ) ድምፃቸውን ሰጥተውበታል። ከ50 በላይ የሙያ አጋሮች የተሳተፉበት ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ ህብረተሰቡን ስሜታዊ ጉዳት ውስጥ ሳይከት በደማቅ ቅንብር የችግሩን አሳሳቢነትና የለውጥ አስፈላጊነት ያሳያል።
አካል ጉዳተኝነት የችግር ምንጭ ሳይሆን፣ እንደ ማህበረሰብ የፈጠርነው የመዳረሻ እና የትራንስፖርት እጥረት ዋናው ክፍተት መሆኑን ማሳወቅ ነው። “ማንም የላት” የሚለውን ስሜት “እኛ አለንላት!”በሚል አዎንታዊ ምላሽ ለመተካት ያለመ ማህበራዊ ንቅናቄ ነው።
አቶ ሳሚ ካህሳይ እና ድርጅታቸው ተድላ አምቡላንስ ቃላቸውን በተግባር በማስመስከር፤ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ በተደረገ ስነ-ስርዓት፦የሙዚቃ ቪዲዮውን ገቢ፦ በሰይፉ ኦን ኢቢኤስ (Seifu on EBS) የዩቲዩብ ቻናል ተለቆ የሚሰበሰበው ሙሉ ገቢ ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማዕከል እንዲሆን አስረክበው ነበር።
በርካታ ዊልቸሮች፣ ዘይት፣ ላርጎ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለመቄዶንያ መስራች ለዶ/ር ቢንያም በለጠ በአካል አስረክበዋል።
ተድላ አምቡላንስ ለማንኛውም ሰዓት ለመቄዶንያ ማዕከል ነፃ የአምቡላንስ አገልግሎት ለመስጠት በይፋ ቃል ገብተዋል።
የአቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ህልም በዋና ከተማው አዲስ አበባ ብቻ የተገደበ አይደለም። በክልሎች፣ በገጠራማ አካባቢዎች እና ክፍለ ሀገራት የሚኖሩ፣ አማራጭ ያጡ ዜጎች ዘንድ ይሄው ዘመናዊና የተከበረ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲደርስ ከመንግስት እና ከተለያዩ አካላት ጋር በትስስር ለመስራት አቅደዋል።
“No one has ever become poor by giving.”
(መስጠት ማንም ሰው ደሃ አያደርግም።)
— አን ፍራንክ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ በስራ ፈጠራቸው ሀገራዊ ክፍተትን የደፈኑ፣ በጥበብ ስራቸው የማህበረሰብ ህሊናን ያነቁ፣ በበጎ አድራጎታቸው ደግሞ የብዙዎችን እምባ ያበሱ የዘመናችን አርአያ ናቸው።
ተድላ አምቡላንስ “ሕይወትን ለማስቀጠል እየመጣን ነው!” በሚለው መሪ ቃሉ፣ የብዙዎችን ህይወት የመታደግ እና ተስፋ የመንዛት ታላቅ ሀገራዊ አገልግሎቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
መደምደሚያ
አቶ ሳሚ ካህሳይ ተድላ ከ 27 ዓመታት ሰድት በኋላ አገር ቤት መጥተዋል። የእናት ሀገር ኢትዮጵያ ጥሪ ተቀብለው "እናቴ፤ ኢትዮጵያ ሆይ ! - ስደተኛው ልጅሽ ከ27 ዓመታት በኋላ መጥቷል! - ደስ ይበልሽ!"
የሀገር ጥሪን የመለሰ የዲያስፖራ ተሳትፎ፦ ህልምን በሀገር ላይ መተርጎም እንደነሳሚ ነው።
“Ask not what your country can do for you — ask what you can do for your country.”*
(ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን፣ እኔ ለሀገሬ ምን አደረግሁ ብለህ ጠይቅ።)
— ጆን ኤፍ. ኬኔዲ
አቶ ሳሚ ካህሳይ በምዕራቡ ዓለም (በአሜሪካ) ያካበቱትን የሙያ ልምድ፣ እውቀትና ሀብት ይዘው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በህክምናና በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩት በምክንያት ነው። መንግስትና የሀገር ጥሪ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ያቀረቡትን ጥሪ መሰረት በማድረግ፣ በውጭ ሀገር ያዩትን ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥና ህልማቸውን በሀገራቸው ምድር ላይ ተግባራዊ አድርገዋል።
ይህ እርምጃቸው ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ሲሆን፤ ሌሎች በውጭ ሀገር የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንም በየተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ መጥተው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ትልቅ ማነቃቂያና መንገድ ጠራጊ አርአያ የሚሆን ነው።
እናንት ያገሬ ልጆች
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ ጀግንነት ነው!
ለሥራቸው፤ ለሰበአዊነታቸው እጅ እንነሳለን!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
"ሕይወትን ማዳን፤ የመጀመሪያ ቅድሚያችን!"
– ተድላ አንቡላንስ
📞 ለአስቸኳይ ጥሪዎች 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት ዝግጁ
☎️ +251 985 585 888
📞 8558
የማኅበራዊ ሚዲያ ሊንኮች ናቸው - ይከተሉን፦
Facebook: fb.com/Tedlaambulance
Instagram: instagram.com/tedlaambulance
Telegram: t.me/tedlaambulanceservice
TikTok: tiktok.com/tedlaambulance

3 days ago
«ገነርስ» የተሰኘው የአርሰናል ደጋፊዎች ማህበር በይፋ ስራ ጀመረ!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የሚገኙ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ክለብ የአርሰናል ደጋፊዎችን በአንድ ማህበር ስር በማሰባሰብ በኢኮኖሚ፣ በሙያ እና በማህበራዊ ዘርፎች ለማስተሳሰር ያለመው «ገነርስ» የተሰኘ ማህበር በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታወቀ።
ማህበሩ በይፋ ሥራ መጀመሩን ባበሰረበት መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ የማህበሩ ዋና ዓላማ የስፖርት ደጋፊነትን ከተለመደው ስፖርታዊ መዝናናት ባሻገር፣ ለአባላቱ ተጨባጭ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ወደ ሚያስገኙ ዕድሎች ማሸጋገር መሆኑ ተገልጿል።
የ«ገነርስ» ማህበር ዋነኛ ትኩረት ደጋፊዎችን በአንድ ሁለንተናዊ መድረክ ስር ማገናኘት ሲሆን፣ ለዚህም ስኬት ከመንግስታዊ እና ከግል ተቋማት ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነቶችን ለመመስረት ማቀዱ ተጠቅሷል።
በተለይም የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለአባላት የሙያ ክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠናዎች፣ የሥራ ዕድሎች እና የንግድ አማራጮች እንደሚመቻቹ የተገለፀ ሲሆን አባላት እርስ በእርስ እንዲቀራረቡ እና ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ የአባልነት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ጠንካራ የማህበረሰብ መድረክ ለመገንባት መታቀዱ ይፋ ሆኗል።
በተጨማሪም ማህበሩ አባላቱን የሚያዝናኑ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን የሚያጋሩ እና ትምህርታዊ ይዘት ያላቸውን የዲጂታል ሚዲያ ውጤቶች በማዘጋጀት የማህበረሰብ ትስስሩን ይበልጥ ለማጠናከር ማቀዱ በመድረኩ ላይ ተመላክቷል።
«ገነርስ» ማህበር በኢትዮጵያ የስፖርት ደጋፊነት ባህል ላይ አዲስ አሠራር በማስተዋወቅ፣ ደጋፊዎች ስፖርታዊ ፍቅራቸውን ወደ የጋራ ዕድገት እና ማህበራዊ ተፅዕኖ የሚቀይሩበትን አቅጣጫ እንደሚያመቻች ይጠበቃል።

አሜሪካ የቪዛ ዋስትና ክፍያን ቋሚ አደረገች፣ ተጓዦች እስከ 20 ሺህ ዶላር ይጠየቃሉ!
#fastmereja I የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች 30 የአፍሪካ ሀገራት ጨምሮ የ50 ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሪቱ ለንግድና ለጉብኝት (B1/B2) ቪዛ ሲያመልክቱ እስከ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የቪዛ ዋስትና (Visa Bond) ማስያዝ የሚያስገድደውን መመሪያ በቋሚነት ማጽደቁን አስታወቀ።
ቀን፦ ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም. (August 1, 2026)
እንደ አዲሱ መመሪያ አሰራር፣ ተጓዦች የተሰጣቸውን የቪዛ ጊዜ ሳያሳልፉ እና የሀገሪቱን ህግ አክብረው ከተመለሱ ያስያዙት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። ነገር ግን ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የሚቆዩ ወይም የቪዛ ደንብ የሚጥሱ ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ተገልጻል።
ይህ አሰራር ቀደም ሲል ለሙከራ ትግበራ ተዘርግቶ የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባደረገው ግምገማ ከቪዛ ጊዜ በላይ የመቆየት ችግርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ በቋሚነት ስራ ላይ እንዲውል ተወስኗል። የቆንስላ ክፍሎች እንደ አመልካቾቹ ሁኔታ ከ10 ሺህ፣ 15 ሺህ እስከ 20 ሺህ ዶላር የሚደርስ ገንዘብ በዋስትና መልክ እንዲያዝ የመወሰን ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ መመሪያ ውስጥ የተካተቱት የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ቤኒን፣ ቦትስዋና፣ ቡሩንዲ፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኮትዲቯር፣ ጅቡቲ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳው፣ ሌሶቶ፣ ማላዊ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞሪሸስ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ሴኔጋል፣ ሲሼልስ፣ ታንዛኒያ፣ ቶጎ፣ ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እርምጃው የህገ-ወጥ ስደተኞችን ቁጥር እና የቪዛ ጊዜ ማለፍን ለመግታት ያለመ ነው ሲሉ ቢገልጹም፣ የስደት ህግ አዋቂዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ግን አሰራሩ ህጋዊ ተጓዦችን እንደሚያሰናክልና ከፍተኛ የፋይናንስ ጫና እንደሚፈጥር በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

በጎሮ ጉሊት አካባቢ መንገድ ላይ ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋዎች እየደረሱ መሆናቸው ተገለጸ
#fastmereja I በጎሮ ጉሊት አካባቢ በሚገኘው የአስፋልት መንገድ ላይ በተደጋጋሚ በሚከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ምክንያት የሰው ህይወት አልፎ በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። ነዋሪዎቹ የሚመለከተው አካል በአስቸኳይ በፍጥነት መቀነሻ (Speed Breaker) በመስራት የሰዎችን ህይወት እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።
በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ አንዲት የአካባቢው ነዋሪ በስሜት ውስጥ ሆና እያለቀሰች እንደገለጸችው፤ ጉዳዩ ምንም ዓይነት ድራማ ወይም ማጋነን የሌለበትና በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች በሙሉ የሚያውቁት እውነተኛ ስቃይ ነው ብላለች። ነዋሪዋ ወደ ሰፈሩ ከገባችበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተደጋጋሚ ጊዜያት አስቃቂ የመኪና አደጋዎች ሲከሰቱ መመልከቷን ተናግራለች።
አደጋው በየጊዜው የበርካታ ወገኖችን ህይወት እየቀጠፈና አካል እያጎደለ የሚገኝ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም የሚመለከታቸው አካላት በአስፋልቱ ላይ ፍጥነት መቀነሻ በመስራት ተጨማሪ አደጋዎችን እንዲከላከሉ ተጠይቋል። በተጨማሪም ህብረተሰቡና አሽከርካሪዎች በአካባቢው በሚያሽከረክሩበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪዋን አስተላልፋለች።

ጄጄ ግሩፕ በኡራኤል ባለ 12 ወለል ህንፃ ግንባታ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ አስጀመረ!
#fastmereja :- በኮንስትራክሽን እና ሪል እስቴት ዘርፍ የተሰማራው ጄጄ ግሩፕ (JJ Group)፣ በኡራኤል አደባባይ አካባቢ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቅ ባለ 12 ወለል ባለብዙ አገልግሎት ህንፃ ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን በዛሬዉ እለት አስታወቀ።
ህንፃው ለንግድ፣ ለቢሮ እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ሲሆን እስከ ሁለት የከርሰ-ምድር (Basement) እና 12 ወለሎችን (G + 12) የያዘው ይህ ህንፃ፣ ከ10 እስከ 47 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ከ60 እስከ 70 የሚደርሱ የንግድ ሱቆች፣ በ4ኛው ወለል ላይ የተዘጋጁ የቢሮ ቦታዎች እንዲሁም 31 ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።
ህንፃው ለተረጋጋ የመኖሪያ alalar™ ሲባል ለንግድና ለመኖሪያ ክፍሎቹ የተለያየ መግቢያና መውጫ እንዲኖረው ተደርጎ የተዋቀረ እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጀበል ጀማል እንደገለፁት ድርጅታቸው ባለፉት 13 ዓመታት በዘርፉ በነበረው ልምድ ከ4ዐ በላይ ህንፃዎችንና ፋብሪካዎችን ገንብቶ ማስረከቡን ጠቁመው፣ በቅርቡ ይፋ የሚሆነው የሪል እስቴት አዋጅና ደንብ የገዢዎችንና የአልሚዎችን መብት የሚያስከብር መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለጻ፣ የንግድ ሱቆቹን በ8 ወራት፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶቹን ደግሞ በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለደንበኞች ለማስረከብ ማቀዱንም ገልፀዋል።
አቶ ጀበል አክለውም "ገንዘብ በዝግ አካውንት ተቀምጦ በስራው እድገት ልክ በባንክና በባለሙያ እየተረጋገጠ የሚለቀቅበት አሰራር መዘርጋቱ በዘርፉ ላይ ታማኝነትን ይፈጥራል" ብለዋል።
በተጨማሪም የፕሮጀክቱን መበሰር ምክንያት በማድረግ በቅድመ-ሽያጭ (Pre-sale) ደረጃ 10 አፓርትመንቶች ብቻ በልዩ ቅናሽ ለገዢዎች መቅረባቸው ተገልጿል።

ሐምሌ 30 ደረሰ! የደረጃ ‘’ለ’’ ግብር ከፋዮች የመጨረሻው ቀን
ስናስታውሶ!!
ራስዎንና ድርጅቶን ከቅጣትና አላስፈላጊ ውጣ ውረድ ይታደጉእያልን ከአክብሮት ጭምር ነው!!
ሐምሌ 30 ከመጠናቀቁ በፊት ግብሮን አጠናቀው በመክፈልጥንቅቅ ያለ የዜግነት ግዴታዎን የተወጡ መሆኑን ያረጋግጡ፡፡
ለአዲስ አበባ ከተማ ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የድርሻዎንማበርከትዎን እያስተዋሉ ደስ ይሰኙ፡፡
የደረጃ ‘’ለ’’ ግብር ከፋይ ሆነው ከሐምሌ 30 በፊትየሚጠበቅብዎትን ግብር ሲከፍሉ፡
አንድም ከቅጣትና አላስፈላጊ ውጣ ውረድ ይድናሉ
እንደገናም ለከተማዋ ዕድገት ግዴታውን እንደተወጣ ዜጋኩራትን ይኮራሉ፡፡
ቢኮሩም ይገባዎታል፡
የግብር ግዴታዎን ከሐምሌ 30 በፊት ተወጥተዋልና፡፡
3 days ago
3 days ago
የቅዱሳን ይርጋለም እህት ሩት ይርጋለም የፖሊስን እርምጃ አደነቀች
#fastmereja I በቅርቡ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወቷ ያለፈው የቅዱሳን ይርጋለም እህት ሩት ይርጋለም፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው ፈጣንና የተቀናጀ ክትትል የተሰማትን ከፍተኛ ምስጋና ገለጸች።
ሩት በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈችው መልዕክት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ባደረገው የጠበቀ ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ሳይበተኑ እና ልብሳቸውንም ሳይቀይሩ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጻለች። ይህ ክስተት የአንድ ቤተሰብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ህብረተሰብ ጉዳይ መሆኑን ያመለከተችው ሩት፣ መሰል አስቃቂ ድርጊቶች በሌሎች ቤተሰቦች ላይ እንዳይደገሙ ሲባል ለቅዱሳን ትክክለኛና ተመጣጣኝ ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቃለች።
ህዝቡም ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረትና ያሳየውን አጋርነት በማመስገን፣ ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ህዝቡ ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪዋን አስተላልፋለች።

4 days ago
ሼፍ ሄኖክ ዘርይሁን የምስራቅ አፍሪካ ሼፎች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ
📌 ኢትዮጵያ የ2027ቱን አህጉራዊ ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ ተወሰነ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሼፎች ማህበር ፕሬዝዳንት ሼፍ ሄኖክ ዘርይሁን የምስራቅ አፍሪካ ሼፎች ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ። በደቡብ አፍሪካ እና በስዋቲኒ በተካሄደው የ2026 የአፍሪካ ሼፎች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉት ሼፍ ሄኖክ ይህን ከፍተኛ ኃላፊነት ከመጨበጣቸውም በላይ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የ2027ቱን የመላው አፍሪካ የሼፎች ፌስቲቫል በጋራ እንድታዘጋጅ ውሳኔ ተላላፏል።
በደቡብ አፍሪካ እና በስዋቲኒ አስተናጋጅነት በተካሄደው በዚህ አህጉራዊ መድረክ የአፍሪካ የምግብ ግብአቶች፣ የአዘገጃጀት እና የአመጋገብ ታሪክ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን፣ ዘርፉን የሚያጎለብቱ የተለያዩ አለም አቀፋዊ ስልጠናዎችም ተሰጥተዋል። ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ የተፈጥሮ የምግብ ግብአቶች እና ሀብታም የአመጋገብ ባህል ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ሀገሪቱ ያላትን እምቅ ሀብት ለመላው አለም ለማስተዋወቅና በገበያ ላይ በማቅረብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንድታገኝ ትልቅ መንገድ የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ተከትሎ ኢትዮጵያ የ2027ቱን አህጉራዊ የሼፎች ፌስቲቫል እንድታዘጋጅ መመረጧ በምግብ ቱሪዝም እና በባህል ልውውጥ ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን፣ የሀገሪቱን ገጽታ በበጎ መልኩ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ይታመናል።

በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚታዩ የክህሎትና የመዋቅር ችግሮችን ለመቅረፍ አዲስ የጋራ ስምምነት ተደረገ!
#fastmereja :-በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሚታዩ መዋቅራዊና የክህሎት ችግሮችን ለመቅረፍ የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የአባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ በጋራ ለመስራት በዛሬዉ እለት ተፈራረሙ።
በአዲሱ አስተዳደራዊ መዋቅር ስር የሚገኙትን ብሔራዊ ቴአትር፣ ሀገርፍቅር ቴአትር፣ የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም (ባህል አዳራሽ)፣ ራስ ቴአትር እና የሕፃናትና ወጣቶች ቴአትርን የሚያስተዳድረው ተቋሙ፤ ከግል ዘርፍ አጋሮች ጋር አብሮ ለመሥራት ባቀደው መሠረት ይፋዊ ስምምነቱን አድርጓል።
በስምምነቱ መሠረት የአስተዳደሩን የዘመናት የታሪክና የልምድ ክምችት ከአካዳሚው ዘመናዊና ፈጠራ የታከለበት የአሰልጠና ዘዴ ጋር በማዋሃድ በቴአትር፣ በሙዚቃ፣ በፊልምና ተዛማጅ የኪነ-ጥበብ ዘርፎች ሰፊ ስልጠናዎች በጋራ እንደሚሰጡ ተገልጿል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ወግ የሚያንፀባርቁ ጥበባዊ ሁነቶችንና ትላልቅ ፕሮዳክሽኖችን በጋራ በማዘጋጀት ለሕዝብ ለማቅረብ፣ እንዲሁም ከግጥም ምሽቶች እስከ ታላላቅ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሎች ድረስ ያሉ መድረኮችን ለማስፋፋት መታቀዱም ነዉ የተገለፀዉ።
የአባ ለታ አክቲንግ አካዳሚ ዋና መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሌንጮ ፍቅሩ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት እንደገለጹት፤ አካዳሚው ከተመሠረተበት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በርካታ ወጣትና ህጻናት
ተማሪዎችን አብቅቶ ያስመረቀ ሲሆን፣ በተለይም በልጆች አክቲንግ ዘርፍ አበራች አስተዋጽኦ አበርክቷል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ሌንጮ አክለው እንደገለጹት፣ አካዳሚው እስካሁን በነበረው ጉዞ የቦታ፣ የሎኬሽን እና የትወና ቁሳቁሶች (Props) እጥረት ዋና ዋና ማነቆዎች እንደነበሩበት አስታውሰዋል።
ሆኖም ከአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ጋር የተደረገው ይህ ይፋዊ ስምምነት እነዚህን የሎጅስቲክስና የቦታ ችግሮች በዘላቂነት በመቅረፍ፣ የሰለጠኑ አዳዲስ ከዋክብትን ወደ ታሪካዊ የቴአትር መድረኮች ለማውጣት ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

🎤ድምፃዊ ፀሐዬ በፀሐይ ተሸለመ!
📚ንባብ ለሕይወት በድምቀት ተከፍቷል
ሐሙስ ሐምሌ 23/2018 በኤግዚቢሽን ማዕከል ጥቁር እንግዳ መድረኩን ተቆጣጠረው።
ተወዳጅ ድምፃዊ ፀሐዬ ዮሐንስ በንባብ ለሕይወት የመጻሕፍት አውደርዕይ ላይ ተገኝቶ ዘመን ተሻጋሪ ሙዚቃውን "ማንበብና መጻፍ"ን በልዩ ብቃት በመጫወት ታዳሚዎችን በደስታ ብዛት ከመቀመጫቸው አስነስቷል። ልጆችም አብረውት አዚመዋል።
በኢትዮጵያ ሴት ደራሲያን ታሪክ በረዥም ልቦለድ ዘርፍ ፋና ወጊ የሆነችው "ፀሐይ መላኩ" ለአርቲስቱ የምስጋና ሰርተፊኬት በክብር አብርክታለች።
ንባብ ለሕይወት እስከ ሐምሌ 26/2018 በኤግዚቢሽን ማዕከል ይቀጥላል።

ይህን መልዕክት ከማንም ሰው ጋር አታገናኙብኝ ሲል ድምጻዊ ማሚላ ሉቃስ መልዕክት አስተላልፏል
"ያደረጉብንን እና ያስደረጉብንን ነገር ለኢትዮዽያ ህዝብ በአደባባይ ቀርበን ሁሉን ብንናገር፣ አይደለም በሰርጋቸዉ በቀብራቸዉ ቀን እናት እና አባታቸዉ ብቻ አልቅሰዉ እንዲሸኟቸዉ አድርገን እናሰቀራቸዉ ነበር ግን God…"

"ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለትዳራችሁ፣ ለልጆቻችሁ፣ ለመላው ቤተሰባችሁ እግዚአብሔር የበዛ ሰላም፣ ጤና፣ ጥበብና በረከት ይስጥ። ዘመናችሁ በጌታ ፊት የተባረከ፣ በደስታ የተሞላ፣ በስኬትና በፀጋ የሚታጀብ ይሁን። እግዚአብሔር በሁሉም መንገዳችሁ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ ቤታችሁንም በሰላሙና በበረከቱ ይሙላ። አሜን።" ነብይ ኢዩ ጩፋ
Sponsored by
Surafel
4 days ago
"ደህና ነኝ!" ሊመረቅ ነው!
የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ “ደህና ነኝ - እግዚአብሔር ይመስገን” የተሰኘ መንፈ-ሳይንሳዊ መፅሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2/2018 ዓም ፣ ቅዳሜ ጠዋት 4፡00 ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ አሁን በትውልዱም ፣ በሐገራችንም የገባውን የጭንቀት ፣ የፍርሃት ፣ የባዶነት ስሜት ፣ የተስፋ መቁረጥ ፣ የካንሰር ፣ የስኳር ፣ ስትሮክና መሰል በሽታዎች ጥቃትን በዕውቀት ያክማል፡፡ በራስ ኩነኔ ፣ በሱሰኝነት ፣ በገንዘብ እጦት ወዘተ (ብቻ) ሕይወትም ኑሮም ለከበዳት ነፍስ አስገራሚ ምስጢራትን ይበታትናል፡፡ ፀሐፊው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ፣ በመኖርና መሞት መካከል ከተፋለመባቸው የ12 ዓመታት የሕይወት ጦርነት አሸናፊነት ውስጥ “ደህና ነኝ ፤ እግዚአብሔር ይመስገን!” መጽሐፍ ተወልዳለች።
በምረቃው ዕለት ታላላቅ እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን መርሀ ግብሩንም የሚያዋዙ የጥበብ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

አንድ ቀን ቀረው! አባይ ሆምስ ሪል እስቴት ሀምሌ 25 በአዲስ ነገር! እጅግ የሚያተርፉበትን እድል ለመጠቀም ከቀዳሚዎቹ መካከል እንዲሆኑ ሀምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ሜክሲኮ ጠማማ ፎቅ ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው ቢሮው ከጠዋቱ 3፡30 ጀምሮ ልዩ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር አዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል።
አባይ ሆምስ ሪል እስቴት
ጊዜው የአባይ ነው!
https://web.facebook.com/p...
አባይ ሆምስ ሪል እስቴት
ጊዜው የአባይ ነው!
https://web.facebook.com/p...
4 days ago
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ከአማራ ክልል ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ
#fastmereja | የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽህፈት ቤት በባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ታሪክ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተፈራርመዋል።
ይህ አዲስ የትብብር ስምምነት ቀደም ሲል በባለሙያዎች ደረጃ በተናጠል ይደረጉ የነበሩ የቴአትርና ሙዚቃ ዝግጅቶችን ወደ ተደራጀና ተቋማዊ አጋርነት የሚያሸጋግር ሲሆን፣ ሀገራዊ የታሪክና የባህል እሴቶችን ለአዲሱ ትውልድ በተሻለ ጥራትና ተደራሽነት ለማስተላለፍ ያለመ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ተደራሽነቱን ለማስፋትና ህዝባዊነቱን ለማፅናት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጋር የሚደርጋቸው ስትራቴጂካዊ ጥረቶች አካል የሆነው ይህ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ፣ በአማራ ክልል ባህል ኪነ-ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽህፈት ቤት የተዘጋጀው "እንዛታ" የተሰኘው ትውፊታዊ ቴአትር ጥሪ ለተደረገላቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና እንግዶች ቀርቧል።

Comments