1 day ago
በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞች የጋምቤላን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያረጋገጡ ነው፦ ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ
**********************
በጋምቤላ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የደን እና የፍራፍሬ ችግኞች የማህበረሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እያሳደጉ እንደሚገኙ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሯ ይህንን ያብራሩት በዛሬው ዕለት ከፍተኛ የክልል አመራሮች እና በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ተሳትፎ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘውን ታሪካዊ ግብ ለማሳካት፣ የጋምቤላ ክልል ማህበረሰብም ከማለዳው ጀምሮ በነቃ ተሳትፎ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ ያላቸውን የደንና የፍራፍሬ ችግኞች በመትከል ላይ ይገኛል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ መርሃ ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ሰባት ዓመታት በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተከናወኑ ተግባራት የደን ሽፋኑ እንዲጨምር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በተለይም የተተከሉ የፍራፍሬ ችግኞች ለቤት ውስጥ ምግብነት ከመዋል አልፈው ለገበያ በመቅረብ ላይ እንደሚገኙ የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሯ፣ ይህም የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል።
በቀጣይም በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ የደንና የፍራፍሬ ችግኞችን በስፋት የመትከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ችግኝ የመትከል እና የመንከባከብ ባህል በሚገባ እየዳበረ በመምጣቱ፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም የታቀደውን ግብ በማሳካት የላቀ ስኬት ይመዘገባል ተብሎ በከፍተኛ ተስፋ ይጠበቃል።
በሚፍታህ አብዱልቃድር
#greenlegacy #gambella #ethiopia #treeplanting #climateaction

የጤናው ዘርፍ የአረንጓዴ አሻራ ተሳትፎ
📌 ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል
#ethiopia | በሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ሰራተኞች ከኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት ከገፈርሳ ጉጄ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር በዛሬ እለት በገፈርሳ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ዳርቻ ከ30 ሺህ በላይ ችግኞች በዛሬው እለት ተተክለዋል።
በሸገር ከተማ በገፈርሳ ጉጄ አካባቢ በተካሄደው በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ላይ የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የየደረጃው የአካባቢው አመራሮች እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና የማህበረሰብ ክፍሎች ከማለዳው 1 ሰዓት ጀምሮ በመገኘት ችግኝ ተክለዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ አረንጓዴ አሻራ እና የጤና ዘርፍ የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። ችግኝ ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለህብረተሰብ ጤና፣ ለንጹህ አየር እና ለምግብ ዋስትና ማሻሻያ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በተለይም ለአዲስ አበባ እና ለአካባቢው ህዝብ የንጹህ ውሃ ምንጭ የሆነውን የገፈርሳ አካባቢን መንከባከብ የሁላችንም ህብረ-ብሄራዊ ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በዕለቱ በቦታው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትሯ ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ አካባቢዋን ለመጠበቅ የምታደርገው ጥረት በንግግር ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ መሆኑን አብራርተዋል።
በዕለቱ ሚኒስቴሩ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ከ30 ሺህ በላይ ችግኞችን የተከለ ሲሆን፣ በክረምቱ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ-ግብር ደግሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 250 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እና ከ20 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ነጻ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትሯ፣ የጤና ባለሙያዎች እና መላው የሀገራችን ህዝብ ቀኑ ሳያልቅ እና ጀምበር ሳትጠልቅ የድርሻቸውን ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ኩነት አካል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
ከችግኝ ተከላው መርሐግብር ባሻገር የኢትዮጵያ የአካል ድጋፍ አገልግሎት በሸገር ከተማ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
በጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ministryofhealth #treeplanting
#climateaction #publichealth
#environmentalhealth #gefersa #cleanenvironment #greenethiopia
#communitysupport

Sponsored by
Surafel
3 days ago
800 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር ኢትዮጵያ ለዓለም የምታሳየው ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ
************************
ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን ዘመነ-ተሻጋሪ ተጽዕኖ ለመቋቋም፣ የተጎዱ መሬቶችን ለማደስ እና የዜጎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወት ለማሻሻል ያለመ ሀገራዊ ራዕይ ሰንቃ በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።
የዚሁ ዘላቂ ጥረት አካል የሆነውና በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ፣ ሀገራችን ለአረንጓዴ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዳግም በተግባር የሚያስመሰክር ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።
ይህ ዘመቻ ተራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ብቻ ሳይሆን፣ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ ልብና በአንድ ዓላማ በመነሳት የሚያደርጉት የተቀናጀ አቅምና አንድነት ማሳያ እንዲሁም የተፈጥሮ ሚዛንን ለመመለስ የተደረገ ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
በዚህ ታሪካዊ ቀን ከሚተከሉት ችግኞች መካከል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ዘይቱን ያሉ ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ተክሎች ይገኙበታል።
እነዚህ የፍራፍሬ ዛፎች የምግብ አቅርቦትን ከማሳደግ ባሻገር ለገበሬዎች የገቢ ምንጭ በመሆን የገጠር ኢኮኖሚን ለማጠናከር በከፍተኛ ሁኔታ ያግዛሉ።
በተጨማሪም የደን ሽፋን መጨመር የአፈር መሸርሸርን ከመከላከል ባለፈ የከርሰ ምድር ውሃ እንዲጎለብት ያደርጋል፤ ታላላቅ የኃይል ማመንጫ ግድቦች እና የመስኖ መሠረተ ልማቶች በደለል እንዳይሞሉ በመከላከል የአገልግሎት ዘመናቸውን ያራዝማል።
የአካባቢ ሙቀትን በመቀነስና የዝናብ ዘይቤን በማስተካከልም ለግብርናው ዘርፍ የተሻለ እና አስተማማኝ ሁኔታ ይፈጥራል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የነገዋን አረንጓዴ፣ በምግብ ራሷን የቻለች እና የተፈጥሮ ሀብቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጣለ ጠንካራ መሠረት ነው።
ዛሬ በትጋት መሬት የሚይዘው እያንዳንዱ ችግኝ የነገው የኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ፣ አረንጓዴ ተፈጥሮ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተላለፍ ታሪካዊ አሻራ ደማቅ መገለጫ ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#greenlegacy #ethiopia #climateaction #treeplanting #sustainability

4 days ago
በቢሾፍቱ ከተማ ከአምስት ሺህ በላይ ችግኞች ተተከሉ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከጤና ሚኒስቴር እና ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር «ጤናማ ምግብ ለአስተማማኝ ህይወት፣ አረንጓዴ ልማት ለነገ ትውልድ!» በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ አድራጎት የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የባለሥልጣኑ ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን የኮፕ 32 (COP 32) አየር ንብረት ጉባኤን ከማገዝ ባሻገር አገር በቀል፣ ፍራፍሬ እና ለመድኃኒትነት የሚውሉ ተክሎችን በመትከል የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተከናውነዋል።
በዕለቱም ከሰባት ነጥብ አንድ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ከምግብነት ባለፈ ለመድኃኒትነት ጭምር የሚጠቅሙ እንደ ማንጎ እና አቮካዶ ያሉ ከአምስት ሺህ በላይ ችግኞች ተተክለዋል።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሄራን ገርባ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችን አቅም ለማሳደግ እና የጥሬ ዕቃ አቅርቦትን በራስ አቅም ለመሸፈን በምታደርገው ጥረት ውስጥ የመድኃኒትነት እጽዋትን መንከባከብ ትልቅ ድርሻ አለው።
ችግኞችን ከመትከል ባለፈ ለዕድገታቸው ተገቢውን ቋሚ እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሯ፣ ይህንን አረንጓዴ ልማት ከምርምርና ከኢንዱስትሪ ጋር በማስተሳሰር የሀገር ውስጥ መድኃኒት ማምረት አቅምን ለማጠናከር እንደሚያግዝ አስገንዝበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው፣ የጤና ሴክተሩ በበጎ ፈቃደኝነት መርሃ ግብሩ አጠቃላይ ከሁለት መቶ ኃምሳ ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን አንስተዋል።
ከአዲስ አበባ እስከ ቢሾፍቱ ባለው የፍጥነት መንገድ ዳርቻ የተጀመረው ይህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከአንድ ዓመት በኋላ ከፍተኛ የእጽዋት ሽፋን እንደሚፈጥር ጠቁመው፣ የተተከሉትን ችግኞች በባለቤትነት ስሜት በመንከባከብ ለታለመለት ዓላማ ማብቃት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷ከበደ መክብብ
#greenlegacyethiopia#ethiopia
#bishoftu #climateaction #healthylife
#cop32 #healthsector #treeplanting

Comments