Logo
EBC
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በዓለም ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ነው - የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
*************************

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ2017 በጀት ዓመት የ9.2 በመቶ ዕድገት አስመዝግቧል፤ ይህም በዓለም ላይ ፈጣን ዕድገት ካስመዘገቡ ኢኮኖሚዎች አንዱ ያደርገዋል ብሏል።

‎ያለፉት ዓመታት እውነታ በግልጽ እንደሚያሳየው፣ የመንግሥት ቃል የተስፋ ቃል ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም የተከናወኑት ውጤት ተኮር ተግባራት እና የተመዘገቡት ውጤቶች በተጨባጭ የሚታዩ ናቸው ብሏል።

ይህን መነቃቃት መሠረት በማድረግ የኢኮኖሚ ዕድገቱ በ2018 በጀት ዓመት 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢኮኖሚ ዕድገቱ ግብርና፣ ኢንዱስትሪና አገልግሎት ዘርፎችን ያካተተና ሰፊ መሠረት ያለው ሲሆን፣ በሂደት ግን ኢንዱስትሪው የዕድገቱ ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እየወጣ ይገኛል።

ይህም መንግሥት ለማኑፋክቸሪንግ፣ ለኢንዱስትሪ ልማት፣ ለዕሴት ጭመራና ለውጭ ገበያ ተኮር ምርቶች የሰጠውን ቀጣይነት ያለው ትኩረት የሚያሳይ እንደሆነ መግለጫው ያትታል።

‎እነዚህ ውጤቶች እንዲሁ ግምቶች ብቻ ሳይሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ አፈጻጸም የግምገማ ሥርዓት አማካኝነት ክትትል የሚደረግባቸው የተጠያቂነትና የታቀደ አመራር ፍሬዎች ሲሆኑ፣ በዚህም አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ከ2016 ዓ.ም ወዲህ የ100 በመቶ ገደማ ጭማሪ በማሳየት 20 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

የዋጋ ግሽበትም ወደ ታች ማሽቆልቆሉን በመቀጠል አሁን ላይ ወደ አንድ አሐዝ ደረጃ እየተቃረበ ይገኛል፤ ይህም በቅርብ ዓመታት ውስጥ በቤተሰቦችና በንግዶች ላይ ከባድ ጫና ፈጥሮ ከነበረው ባለ ሁለት አሐዝ የዋጋ ግሽበት አንጻር ትልቅ መሻሻል ነው።

ይህ ስኬት የተመዘገበው ዓለም አቀፍ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች ስትራቴጂያዊ ቁሳቁሶችን ገበያ ያናጋው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረትን ጨምሮ ውጫዊ ጫናዎች ባሉበት ወቅት ነው።

‎የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ከተጀመረ ወዲህ መንግሥት ከውጭ ምንጮች ምንም ዓይነት አዲስ የንግድ ብድር ስምምነት ያላደረገ ሲሆን፣ ይህም የሀገራችንን የብድር ዕዳ ጫና በከፍተኛ ሁኔታ አቅልሎታል።

ከእነዚህ ቁጥሮች በስተጀርባ ኢትዮጵያውያን በዓይናቸው የሚያዩትና በእጃቸው የሚዳስሱት ተጨባጭ ለውጥ አለ።
#ethiopia #pmoethiopia #economicgrowth #homegrowneconomicreform #ebc

20 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.