Logo
EBC
የኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ከዛሬ ጥረት እስከ ነገው ብሩህ ተስፋ
*************

የዘንድሮው የሠርቶ አደሮች ቀን በኢትዮጵያ ሲከበር ሀገራችን የሰው ኃይሏን ወደ ምርታማነት ለመቀየር እያከናወነች ያለችው መጠነ-ሰፊ ተግባር ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያሳየ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት የተመዘገበው የ9.2 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት በበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ ወደ 10.2 በመቶ ይደርሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ ስኬት ለዜጎች አስተማማኝ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እንደ የጀርባ አጥንት ያገለግላል።

በተለይም የኢንዱስትሪው ዘርፍ የ13.2 በመቶ እና የግብርናው ዘርፍ የ7.9 በመቶ ዕድገት ማስመዝገባቸው ለቋሚና ለጊዜያዊ የሥራ ዕድል ትልቅ ዕድል ፈጥሯል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ እና የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ደግሞ ወጣቶች በቤታቸው ሆነው ለዓለም አቀፍ ገበያ እንዲሠሩ አዲስ በር ከፍቷል።

እንደ ኮሪደር ልማት ያሉ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው።

በሌላ በኩል በሕጋዊ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸው የመንግሥትን መዋቅራዊ ሪፎርም ውጤታማነት ያሳያል።

የስታርትአፕ አዋጅ መጽደቅና የብድር አቅርቦት ማሻሻያዎች ተዳምረው ኢትዮጵያን ሰፊ የሥራ ዕድል እየተፈጠረባት ያለች የነገዋ ብሩህ ሀገር እየሆነች ነው።

ሙሉ መረጃውን ለማንበብ በአስተያየት መስጫው ውስጥ ያለውን ሊንክ ይመልከቱ 🔗👇

በለሚ ታደሰ
#ethiopia #jobcreation #economicgrowth #digitalethiopia #laborday #homegrowneconomy

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.