1 month ago
አረንጓዴ ዐሻራ ከተጀመረ ወዲህ የዝናብ መጠን በመጨመሩ በዓመት እስከ 5 ጊዜ ማምረት እየተቻለ ነው - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
************************
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል።
መርሐ ግብሩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) አስጀምረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከተጀመረ ወዲህ የክልሉ የደን ሽፋን በመጨመሩ፣ የመሬቱ ለምነትና ውሃ የመያዝ አቅምም እያደገ መምጣቱን አንስተዋል።
በክልሉ ከዚህ ቀደም በዓመት አንዴ ወይም ሁለቴ ብቻ ይመረት እንደነር ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ አሁን የዝናብ መጠን በመጨመሩ በዓመት እስከ አምስት ጊዜ ማምረት እየተቻለ ነው ብለዋል።
የመሬት ለምነት እየተሻሻለ በመምጣቱም የግብርና ምርታማነት መጨመሩ ተገልጿል።
አሁን ላይ የክልሉ ሕዝብ ችግኝ መትከልን ባህሉ እያደረገ በመምጣቱ፣ በዘመቻ ብቻ ሳይሆን አመቺ በሆኑ ወቅቶች ሁሉ እየተከለ እንደሚገኝ ተገልጿል።
እስከ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም የክልሉ ሕዝብ በነቂስ በመውጣት የተለያዩ ችግኞችን እንዲተክል በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ መልዕክት ተላልፏል።
በአስማረ ብርሃኑ
#ethiopia #climateaction #environmentalprotection #greenlegacy #centralethiopia #ebc

2 months ago
ቤተ ጉራጌ
እዣ : የኢንቨስትመንት ፀሐይ እየወጣላት ነው
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው አዲስ የብረት ማምረቻ ፋብሪካ በይፋ ተመረቀ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የብረት ማምረቻ ፋብሪካ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ባለሀብቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል።
የሀሮት ሪልስቴት እህት ኩባንያ የሆነው ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር መሥራችና ባለቤት አቶ ሰኢድ ኑሩ እንደተናገሩት "ቪታ ሳሉቲ የጣልያንኛ ቃል ሲሆን ሰላማዊ ሕይወት የሚል ትርጉም ይዟል። ሰላማዊ ሕይወት በቤተ ጉራጌ - ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ኢትዮጵያ መልካም ምኞት ለመግለጥ ነው። የቤተ ጉራጌ አኗኗርም ለማመላከት ነው ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ የሚገኘውንና የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ የሆነውን ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር ፋብሪካን በዛሬው ዕለት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
አያይዘውም "ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ የግል ባለሀብቱ ሚና የላቀ ነው!" ሲሉ አወድሰዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ፋብሪካ ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ የካፒታል ወጪ የተገነባ ሲሆን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተለያዩ መጠንና ቅርጽ ያላቸው የትቦላሬና የላሜራ ብረት 22 ምርቶችን በከፍተኛ ጥራት የማምረት አቅም አለው።
አቶ ሰኢድ ኑሩ ንግግር "ይህ ፕሮጀክት ከህልም ወደ እውነት፣ ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ነው። ሀገራት የሚበለጽጉት በተፈጥሮ ሀብታቸው ብቻ ሳይሆን ራዕይን ወደ ተግባር በሚቀይሩ ባለሀብቶችና በሥራ ፈጣሪ ዜጎች ነው!" ብለዋል።
አቶ ሰኢድ አያይዘውም የቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ከህልም ወደ እውነት ከሀሳብ ወደ ተግባር የተቀየረ ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው። ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ያድናል ሲሉ አብስረዋል።
ኢንጂነር ናሆም መገርሣ በ5,000 ካሬ ላይ የሚገኘው ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት ለ123 ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ለበርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችም ተዘዋዋሪ የስራ ዕድሎችን በማመቻቸት ለቀጣናው የኢኮኖሚ እድገት የጎላ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።
የቪታ ሳሉቲ ማኒፋክቸሪንግ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ፋብሪካው በዞኑ የመጀመሪያው የብረት ፋብሪካ መሆኑን አስረድተዋል።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች ጥራታቸውን የጠበቁ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በመገንባትና በማስረከብ ከሚታወቀው የሀሮት ሪል እስቴት ጋር እህት ኩባንያ ነው።
ሀሮት ሪል እስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለህብረተሰቡ በማቅረቡ የኢትዮ ህይ 2025 የሪል እስቴት አዋርድ አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።
የፋብሪካው አመራሮች ለዚህ ስኬት መገኘት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱት የክልልና የዞን የስራ ኃላፊዎች፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ለቲናው አበባ ልማት አክሲዮን ማህበር፣ ለባለሙያዎች እንዲሁም ለቤተሰቦቻቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
የሀሮት ሪል ስቴት የማርኬቲንግ ኃላፊ ፋንትሽ ሸዋ እንደገለጹት፤ ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የሀሮት ሪል ስቴት እህት ኩባንያ ነው። ተቋሙ ከተመሰረተ 4ኛ ዓመቱን እያከበረ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ ድርጅቱ ለደንበኞቹ በገባው ቃል መሠረት በቦሌ ቡልቡላ ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶች በይፋ አስረክቧል።
በተጨማሪም ከሁለት ወር እስከ አንድ ዓመት ባለው አጭር ጊዜ ውስጥ በመስቀል ፍላወር፣ በሀያት ፈረስ ቤት እና በቦሌ ቡልቡላ አካባቢዎች የሚገነቡ ተጨማሪ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች እንደሚያስረክብ አስታውቀዋል።
ሀሮት ሪል ስቴት በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያላቸውን ቤቶች ለገበያ በማቅረቡ በፈረንጆቹ 2025 በተካሄደው የኢትዮ ሪል ስቴት ሽልማት መርሃ ግብር ላይ በጥራትና በዋጋ አቅርቦት የአሸናፊነት ክብርን ያገኘ ድርጅት መሆኑ አብራርታለች።
ቪታ ሳሉቲ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በኢንዱስትሪ፣ በኮንስትራክሽን፣ በሆቴልና በሌሎች የልማት ዘርፎች ላይ ኢንቨስትመንቱን ይበልጥ በማስፋፋት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ጉዞ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
ባለሃብቱ አቶ ሰኢድ ይህ ስኬት የአንድ ሰው ጥረትና ውጤት ብቻ አይደለም። ከጀርባው ብዙ እጆች፣ ብዙ ዱአዎች እና ጸሎቶች፣ ብዙ ምክሮች ያሉበት ነው። በዚህ መሠረት ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ ለኢንቨስትመንት ቢሮ፣ ለጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለቲናው አበባ ልማት አ/ማሀበር ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ ለባለሙያዎች እና ለሠራተኞቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ሰኢድ የትምህርት ሕይወታቸውን እንዳጠናቀቁ በቀጥታ የተቀላቀሉት የንግዱን ዓለም ሲሆን፣ መጀመሪያ ላይ በመኪና መለዋወጫ ንግድ በመሰማራትና በመቀጠልም ወደ አስመጪና ላኪነት ዘርፍ በመሸጋገር ረጅም ዓመታትን አሳልፈዋል። በሂደትም የንግድ ሥራቸውን በማስፋት የጀመሩት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ገና በጅማሮው ከፍተኛ የምስጋና ሽልማትና ዕውቅናን ሊያጎናጽፋቸው ችሏል። ባለሀብቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ ዘርፍ በስፋት በመግባት ላይ ይገኛሉ።
በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴያቸው ውስጥ ያጋጠማቸው የአስተዳደር ፈተና ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ሰይድ ሲመልሱ፣ ምንም ዓይነት ችግር እንዳልገጠማቸው በአጽንኦት ተናግረዋል። በአካባቢው የሚገኙ ከላይ እስከ ታች ያሉ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የአስተዳደር አካላት አንድ ባለሀብት እውነተኛ አልሚ መሆኑን ከተረዱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ሰይድ፣ ለእሳቸውም የተደረገላቸውን ተገቢውን ድጋፍና ትብብር በሙሉ አመስግነዋል።
የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ
"በዞናችን ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሀብቶች ሁሉ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ዝግጁ ነን፣ በቁርጠኝነትም እንሠራለን! ... ዛሬ ኑ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው ፦ "የጉራጌ ማህበረሰብ በሀገሪቱ በሁሉም አካባቢዎች ከተሞችን በማልማትና ጠንካራ የንግድ ሥርዓት በመዘርጋት የሚታወቅ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ባለሀብቶች ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው በልማት እየሳተፉ መሆኑ እጅግ ያስደስታል። ይህ ፋብሪካ የሀገር ሀብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል። ሌሎች ባለሀብቶችም በክልሉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።"ለአገርና ለሕዝብ መልዕክታቸውን አሰምተዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፕሬዝዳንት ዶክተር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እና የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አባስ መሀመድን ጨምሮ በርካታ የአመራር አካላት ተገኝተዋል።
"Vita, saluti, peace, life" blends Italian and English expressions of well-being, translating roughly to "life, greetings, peace, and life." This combination evokes a deep desire for a harmonious, healthy existence filled with good energy and wellness.
#manufacturing #factoryinauguration #centralethiopia #guragezone #investment #harotrealestate #vitasaluti #economicgrowth #realestate #housing #bolebulbula #homeownership #ethiopianbusiness #ኢንቨስትመንት #ሪልስቴት #ኢንዱስትሪ #ልማት #የሥራዕድል #ቢዝነስ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
በቡታጅራ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች በርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ተመረቁ
***************************
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ በአጭር ጊዜ በጥራት ግንባታቸው የተጠናቀቁ ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት እነዚህ ፕሮጀክቶች ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን፣ ለቀጣይ ሥራዎች ውጤታማነት ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ፣ የከተማዋን ልማትና ዕድገት እንዲሁም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርጉ መሆናቸው ተገልጿል።
በርዕሰ መስተዳድሩ ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁት የልማት ፕሮጀክቶች መካከል የ 8 ነጥብ 35 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት፣ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክት፣ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የማኅበረሰብ አቀፍ የሕዝብ መድኃኒት መደብር፣ የልጆች መዝናኛ ማዕከል፣ ሴራና ባህል ቤት፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት፣ የዋናው መንገድ ስማርት ፖል እንዲሁም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህም በተጨማሪ በከተማዋ በቀጣይ ለሚገነቡ የጤና ጣቢያ እና የስታዲየም ግንባታ ማስጀመሪያ የሚሆን የመሠረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ የቡታጅራ ከተማን ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው።
ከተማዋን አሁን በተጀመረው ፍጥነት ማሳደግ ከተቻለ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማዕከል እንደምትሆን ጽኑ እምነታቸውን የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ቡታጅራ በብዝሃነት የደመቀች ከተማ መሆኗን ተከትሎ የሰላም ተምሳሌት በማድረግ ለመኖሪያ፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ እንድትሆን መሥራትና የከተማውን ገቢ አሟጦ በመጠቀም የልማት ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምረቃ መርሃ-ግብሩ ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ፣ የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙስጠፋ ሐሰን፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤልን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞን፣ የከተማና የወረዳ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
#ethiopia #butajira #development #centralethiopia #regionalnews

4 months ago
የሀምበሪቾ 777 ደረጃ የተራራ ላይ ውድድር! 🏃♂️💨
ሀምበሪቾ 777 ተራራ ብቻ አይደለም፤ የታታሪነታችንና የጥንካሬያችን አርማ ነው!" በሚል መሪ ቃል፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የሚገኘው ድንቁ የሀምበሪቾ ተራራ፣ ታላቅና ታሪካዊ የተራራ ላይ የደረጃ ውድድር ሊያስተናግድ ቀጠሮ ተይዟል።
ይህ ውድድር የሰው ልጅ ጽናትና የተፈጥሮ ውበት የሚገናኙበት፣ የከምባታ ህዝብ ኩራት ለዓለም የሚታይበት ልዩ መድረክ ነው!
ፈታኙ የ777 ደረጃዎች ጉዞ፦
ተወዳዳሪዎች ከተራራው ግርጌ ካለው ለምለሙ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ ተነስተው፣ የ 777ቱን አስደናቂ ደረጃዎች በመርገጥ የተራራውን አናት ቀድመው ለመርገጥ ብቃታቸውን ይፈትናሉ። ይህ በአፍሪካ ደረጃ ለየት ያለ የከፍታ ሩጫ (Vertical Race) ተሞክሮን ይሰጣል።
ዳጎስ ያለና አበረታች ሽልማት፦
ለጽናታቸው አሸናፊዎች (ለወንድም ለሴትም) ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ማራኪ የገንዘብ ሽልማት፣ የክብር ሜዳሊያና የምስክር ወረቀት ተዘጋጅቷል።
የኪነ-ጥበብና የባህል ድግስ፦
በተራራው አናት ላይ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የባህል ቡድኖች፣ የከምባታ ባህላዊ ጭፈራዎች፣ አልባሳትና የጥበብ ስራዎች ለታዳሚው በድምቀት ይቀርባሉ።
የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ስህበት፦
ውድድሩ ሀምበሪቾን በዓለም አቀፍ የስፖርት ቱሪዝም ካርታ ላይ ለማስፈርና አካባቢውን ለኢንቨስትመንት ምቹ የማድረግ ሰፊ ራዕይ ሰንቋል።
👕 የውድድሩ ቲሸርቶችና ምዝገባ፦
ልዩ ዲዛይን ያላቸው ቲሸርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተዘጋጅተዋል። ቲሸርቶቹን በመግዛት የውድድሩ ተሳታፊ መሆን ይቻላል።
ቲሸርቶቹን ከዛሬ ጀምሮ በሁሉም የዞኑ ከተሞች በሚገኙ መሸጫ ጣቢያዎች ያገኛሉ!
የዕለቱ መርሃ-ግብር መረጃ፦
ቀን፦ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም
መነሻ ቦታ፦ ፋርሲ ገበራንቾ ሜዳ (ከተራራው ግርጌ)
መድረሻ ቦታ፦ የሀምበሪቾ ተራራ አናት (777ኛው ደረጃ)
አድራሻ፦ ዱራሜ ከተማ፣ ከምባታ ዞን
ኑ!
የታሪክ አካል ይሁኑ! Betty Event Organizer (ቤቲ ፕሮሞሺን) ከከምባታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ይህንን ዝግጅት በላቀ ጥራት አሰናድተው ይጠብቁዎታል።
📞 ለበለጠ መረጃ፣
ለምዝገባና ለቲሸርት ትዕዛዝ በዚህ ስልክ ይደውሉ፦ 0902917695
ሀምበሪቾ 777 -
ወደ የከፍታ የምንወጣበት፣ ኩራታችንን ለዓለም የምናሳይበት!
#hambericho777 #hamberichostairsrace #777stepchallenge #mounthambericho #durame #kambata #centralethiopia #visitethiopia #mountainrace #bettyevents #athleticsethiopia #ethiopia #ሀምበሪቾ777 #ደረጃሩጫ #ከምባታ #ዱራሜ #ቱሪዝም #ጌጡተመስገን #getutemesgen #getu

6 months ago
🚧 የ1.3 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት! የቱሉቦሎ-ኬላ አስፋልት መንገድ ተመረቀ
"የዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረውና ሁለት ክልሎችን የሚያስተሳስረው መንገድ ለአገልግሎት በቃ"
#ethiopia | የኦሮሚያ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችን የሚያገናኘው የ80 ኪሎ ሜትር የቱሉቦሎ-ኬላ አስፋልት መንገድ በከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተመርቆ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ፕሮጀክቱ
🛣 ርዝመትና ደረጃ:
80 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን እና በአስፓልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ።
💰 ወጪ:
1.3 ቢሊዮን ብር (ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መንግስት የተሸፈነ)።
🏗 ገንቢ እና አማካሪ:
በቻይናው "ሁናን ሁንዳ" የተገነባ ሲሆን፤ በሀገር በቀሉ "የተባበሩት የምኅንድስና አማካሪዎች" ቁጥጥር የተደረገበት።
የመንገዱ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ:
ይህ መንገድ የአካባቢውን ማህበረሰብ የልማት ጥያቄ ከመመለሱም በላይ፤ የአዲስ አበባ-ቡታጅራ-ሆሳዕና እና የአዲስ አበባ-ወልቂጤ-ጅማ መስመሮችን በማገናኘት ለትራንስፖርት እና ለገበያ ትስስር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል።
#infrastructure #roadproject #ethiopia #tulubolo #kela #development #oromia #centralethiopia

Sponsored by
Surafel
Comments