23 days ago
የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ አድጓል
**********************
የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ ጭማሪ በማሳየት መጠኑ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ ማደጉን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ አስታውቋል።
ኮሚቴው ከ7ኛ ስብሰባው በኋላ በሰጠው መግለጫ እንዳብራራው፥ በሐምሌ ወር 2016 ተግባራዊ ከተደረገው ሁሉን አቀፍ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ማግስት ሀገራችን በአጠቃላይ የውጭ ኢኮኖሚ ሚዛን ትርፍ ማስመዝገብ ችላለች።
ይህም ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው ጉድለት አንፃር ሲታይ ዘርፉ ከፍተኛ መሻሻል ላይ መሆኑን ያመላክታል።
አጠቃላይ የማሻሻያ እርምጃዎቹ የውጭ ገበያ ተወዳዳሪነትን እና የውጭ ምንዛሪ ገቢን በማሳደግ የውጭ ኢኮኖሚ ዘርፉን ዘላቂነት እያረጋገጡ መሆኑ ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የሸቀጦች ወጪ ንግድ ገቢ በሶስት እጥፍ ማደግ፣ እንዲሁም በግለሰቦች እና በመንግሥት የሃዋላ ፍሰት ላይ የታየው አበረታች መሻሻል የሸቀጦች ገቢ ንግድ መጨመርን በከፊል እንዲያካክስ ረድቶታል።
በዚህም የተነሳ በ2016 በጀት ዓመት 6.2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሶ የነበረው የሂሳብ ሚዛን ጉድለት በ2018 በጀት ዓመት ወደ 1.8 ቢሊዮን ዶላር በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ መቻሉ በመግለጫው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው የካፒታል ሂሳብ ትርፍ ለአጠቃላይ የክፍያ ሚዛኑ መሻሻል የጎላ አስተዋፅዖ ማበርከቱ ተገልጿል።
ኮሚቴው የዓለም አቀፉን የገንዘብ ድርጅት (IMF) የሐምሌ 2018 ትንበያ ዋቢ በማድረግ እንደገመገመው፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ግጭት ቀደም ሲል ሲጠበቅ የነበረው የተረጋጋ የዓለም ኢኮኖሚ አቅጣጫ እንዲዛባ አድርጓል።
በመሆኑም ዓለም አቀፍ ዕድገት በ2026 ወደ 3.0 በመቶ እንደሚቀንስ እና በ2027 ደግሞ መጠነኛ መሻሻል በማሳየት 3.4 በመቶ እንደሚሆን ተተንብዮአል።
በተመሳሳይ፣ አጠቃላይ የዓለም የዋጋ ግሽበት በ2026 ወደ 4.7 በመቶ ጭማሪ ካሳየ በኋላ በ2027 ወደ 3.9 በመቶ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ቢሆንም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአለመረጋጋት ስጋቶች አሁንም ድረስ መቀጠላቸውን ኮሚቴው አስገንዝቧል።
#ethiopia #ebc #nationalbankofethiopia #foreignexchange #economicreform #macroeconomics #exportgrowth #imf #globaleconomy

24 days ago
የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ጤናማ እና የተረጋጋ ሆኗል - የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ
***************
የኢትዮጵያ ባንክ ዘርፍ የተረጋጋ መሆኑን እንዲሁም የመሠረታዊ ገንዘብ ዕድገት መረጋጋት ማሳየቱን የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡
የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ በሀገራችን ያለው የመሠረታዊ ገንዘብ ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የወለድ በተመለከተ የአጭር ጊዜ የወለድ ተመኖች ከፍተኛ መሻሻል ማሳየታቸውን እና ከማስቀመጫ ወለድ ውጭ ያሉት በሙሉ ከዜሮ በላይ መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡
በግንቦት ወር 2018 የሁሉም የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነዶች አማካይ የወለድ ምጣኔ እና የ91 ቀን የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ አማካይ የወለድ ምጣኔ በቅደም ተከተል 12.3 እና 11 በመቶ በመሆን ካለፈው ዓመት ቅናሽ አሳይተዋል፡፡
ይሁን እንጂ በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ገበያ በተለይ በአጭር ጊዜ ሰነዶች ላይ ወደ 667.8 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ከፍተኛ የተጨማሪ ፍላጎት ተመዝግቧል፡፡
የኢንቨስትመንት ባንኮች ተሳትፎ መጨመር ገበያውን ይበልጥ እንዳሰፋው ነው ኮሚቴው በመግለጫው የጠቀሰው፡፡
ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበት የ7-ቀን የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ አማካይ የወለድ ምጣኔ በመጋቢት ወር 2018 ከነበረው 18.0 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በግንቦት ወር 2018 ወደ 14.6 በመቶ ደርሷል፡፡
በዚህም የባንክ ለባንክ የገንዘብ ገበያ አጠቃላይ የግብይት መጠንም 3 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ተገልጿል፡፡
በአጠቃላይ የባንክና የፋይናንስ ዘርፉ በቂ ካፒታል ያለው እና የተበላሸ ብድር መጠኑ ዝቅተኛ በመሆኑ ጤናማ እና የተረጋጋ ሆኖ መቀጠሉን ኮሚቴው አረጋግጧል፡፡
ለዚህ አዎንታዊ አፈፃፀም የአጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ ክምችት ማደግ እና የብድር ተመላሽ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡
የባንኮችን ጤናማነት በይበልጥ ከሚያሳዩት አንዱ የሆነው የግል ባንኮች የብድር እና የተቀማጭ ሂሳብ ምጣኔ በ2016 ከነበረው 90.3 በመቶ በ2018 ወደ 72.7 በመቶ ዝቅ ማለቱ፣ የባንኮች የገንዘብ አስተዳደር አቅም በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን እንደሚያሳይ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡
#ethiopia #ebc #nationalbankofethiopia #bankingsector #financialstability #monetarypolicy #economicgrowth #treasurybills

4 months ago
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማስጠንቀቂያ
ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ ወንጀል ነው!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊ መንገድ የገንዘብ ማስተላለፍ ፈቃድ ያላቸውን 23 ድርጅቶች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ባንኩ ፈቃድ በሌላቸው መንገዶች ገንዘብ መላክም ሆነ መቀበል በሕግ እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ፈቃድ ያላቸው ዋና ዋና ድርጅቶች ዝርዝር፦
✅ አቢሲኒያ ረሚት (Abyssinia Remit)
✅ አፍሪካ ኤክስቼንጅ (Africa Exchange)
✅ አላንሳሪ ኤክስቼንጅ (Alansari Exchange)
✅ አሪፍ ረሚት (Arif Remit)
✅ ብር-ሊንክ ረሚታንስ (Birr-Link Remittance)
✅ ቦሌ አትላንቲክ ኢንተርናሽናል (Bole Atlantic)
✅ ቦቲም መኒ ቴክኖሎጂ (Botim Money Technology)
✅ ካሽ ኤክስፕረስ (Cash Express)
✅ ደሃብሽል (Dahabshiil)
✅ ኢትዮ ሶሊሽንስ (Ethio Solutions) ... እና ሌሎችም (በድምሩ 23 ድርጅቶች)።
ፈቃድ በሌላቸው ድርጅቶች ገንዘብ መላክ በ "ሕገ-ወጥ መንገድ በተገኘ ገንዘብ" (Money Laundering) እንደመሳተፍ የሚቆጠር ከባድ ወንጀል ነው።
በሕገ-ወጥ ዝውውር ላይ የሚገኙ ገንዘቦች በመንግሥት የመወረስ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
ሕገ-ወጥ ዝውውር የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት በማዳከም የኑሮ ውድነት እንዲባባስ ያደርጋል።
በውጭ የምትኖሩ ወገኖቻችንም ሆናችሁ እዚህ ሀገር ውስጥ ገንዘብ የምትቀበሉ፣ ራሳችሁን ከሕግ ተጠያቂነት ለመጠበቅና ለሀገራችሁ ዕድገት የበኩላችሁን ለመወጣት ሁልጊዜም ሕጋዊ የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶችን ብቻ ተጠቀሙ።
#getu #nationalbankofethiopia #remittanceethiopia #legalmoneytransfer #moneylaunderingawareness #ethiopiaeconomy #dahabshiil #abyssiniaremit #arifremit #financeethiopia #ብሔራዊባንክ #ገንዘብዝውውር #ሕጋዊ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
የሰባት ወራት አፈጻጸም የዓምናውን ሙሉ ዓመት በለጠ
#ethiopia | በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ ብቻ ከ50 ኩንታል በላይ ወርቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ መደረጉ ተመላከተ።
ይህ አፈጻጸም የ2017 ሙሉ በጀት ዓመትን አጠቃላይ ምርት (47 ኩንታል) በሰባት ወራት ውስጥ መብለጥ የቻለ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።
የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ናስር መሀመድ እንደገለጹት፣ ለዚህ ስኬት መገኘት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* ጥብቅ የሕግ ማዕቀፍ፡ በዘርፉ ላይ የተዘረጋው ጠንካራ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት።
* ሕጋዊነትን ማስፈን፡ አምራቾችና አቅራቢዎች በሕጋዊ ፈቃድ እንዲንቀሳቀሱ መደረጉ።
* የአሠራር ማሻሻያ፡ ወርቅ በሕጋዊ መንገድ ተገዝቶ ለባንክ የሚቀርብበት ቀልጣፋ ሥርዓት መዘርጋቱ።
* አስተማማኝ ሰላም፡ በክልሉ መንግሥትና በጸጥታ አካላት ቅንጅት የተፈጠረው አንጻራዊ ሰላም ለምርቱ በሕጋዊ መስመር መቅረብ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ።
ክልሉ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በአጠቃላይ 70 ኩንታል ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማቅረብ አቅዶ በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝም ታውቋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #benishangulgumuz #mining #goldproduction #economy #nationalbankofethiopia #development

6 months ago
💵 የብሔራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ፦ የውጭ ምንዛሬ ማጭበርበርን ለመከላከል ወሳኝ እርምጃ ተባለ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁሉም ባንኮች ለገቢ ዕቃዎች የብድር ሰነድ (LC) ሲፈቅዱ፣ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚያወጣውን የተመን ዋጋ (Customs Valuation) እንደ መነሻ እንዲጠቀሙ ግዴታ ጥሏል። ይህ መመሪያ በገቢ ንግድ ሽፋን የሚደረገውን ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ለመግታት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
📉 የሀብት ሽሽቱ አስከፊነት
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ "ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ" የተባለውን ተቋም መረጃ በመጥቀስ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በገቢ ንግድ ማጭበርበር ምክንያት ብቻ በዓመት በአማካኝ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች። ነጋዴዎች የዕቃዎችን ዋጋ አጋንኖ በማቅረብ (Over-invoicing) የውጭ ምንዛሬን ወደ ውጭ እንደሚያሸሹም ባለሙያው አመልክተዋል።
🔍 አዲሱ አሰራር ምን ይፈይዳል?
እንደ ዶክተር ቆስጠንጢኖስ ገለጻ፣ አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ዘመን የዕቃዎች ዓለም አቀፍ ዋጋ በግልጽ የሚታወቅ በመሆኑ፣ የጉምሩክን ተመን መጠቀም ለማጭበርበር የሚሞክሩ አካላትን ዕድል ያጠባል።
በሌላ በኩል የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ዶክተር ሞላ አለማየሁ መመሪያውን ቢደግፉም፣ ስጋታቸውን እንዲህ ገልጸዋል፦
* የቴክኖሎጂ አስፈላጊነት፦ አሰራሩ ውጤታማ እንዲሆን ግልጽ በሆነ ቴክኖሎጂ መደገፍ አለበት።
* ቢሮክራሲን መከላከል፦ ዘርፉ ለብልሹ አሰራር የተጋለጠ በመሆኑ፣ ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል ካልተደረገበት ሌላ የቢሮክራሲ ጫና ሊፈጥር ይችላል።
💡 መፍትሔው
የሀገሪቱ የንግድ ሚዛን አሁንም በገቢ ንግድ ላይ ያጋደለ በመሆኑ፣ ይህ አሰራር ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ከተደረገ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለማዳን ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ባለሙያዎቹ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #nationalbankofethiopia #economy #importexport #foreigncurrency #financereform #customs #businessnews

Sponsored by
Surafel
10 months ago
#nationalbankofethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ስብሰባውን አድርጎ የገንዘብ ፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች ለቦርድ አቅርቦ ማስወሰኑም የብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።
ምን ወሰነ ?
1ኛ. የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ተመን (National Bank Rate) አሁን ባለበት 15 በመቶ እንዲቆይ ፤ ብሔራዊ ባንክ ለሚሰጣቸው የተቀማጭ ሂሳብ አገልግሎት (standing deposit facility) እና የብድር አገልግሎት (standing lending facility) የሚከፈሉ የወለድ ተመኖች ባሉበት እንዲቀጥሉ፣ እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ምጣኔ በነበረበት እንዲቆይ ተወስኗል፡፡
2ኛ. በመስከረም ወር ላይ ሊነሣ ይችላል ተብሎ የተገመተዉ የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያን ሙሉ ለሙሉ ሳይነሳ ገደቡ ለጊዜው ከ18 በመቶ ወደ 24 በመቶ ከፍ እንዲል ተወስኗል፡፡
3ኛ. ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱ በሚፈለገው ልክ እንዲሆን ለማስቻል እንደ አስፈላጊነቱ ገበያ-መር የሆነ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎችን በተናጠልም ሆነ በቅንጅት በቀጣይነት የሚጠቀም እንደሆነ ተገልጿል። እነዚህ የገንዘብ ፖሊሲ መሣሪያዎች፦
- የብሔራዊ ባንክ የወለድ ተመን፤
- ከባንኮች ጋር የሚደረግ የገንዘብ ግብይት (Open Market Operations)
- የውጭ ምንዛሬ ገበያ (foreign exchange interventions) እንዲሁም ባንኮች በብሔራዊ ባንክ የሚያስቀምጡት የግዴታ መጠባበቂያ ምጣኔ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።
የኮሚቴው ስብሰባ ታህሳስ ወር 2018 እንዲሆን ተወስኗል፡፡
(ሙኩ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
tikvahethiopia

Comments