1 month ago
ከራስ አገዝነት ወደ እሴት ሰንሰለት - የኢትዮጵያ ግብርና የ5 ዓመታት የለውጥ ጉዞ
***********************
ከ2012 እስከ 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የታየው ለውጥ በኢኮኖሚ ታሪካችን ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የሚይዝ መዋቅራዊ ሽግግር ነው።
ዘርፉ ከኋላ ቀር የአመራረት ዘዴ በመላቀቅ ምርታማነቱ ወደተሻሻለ እና እሴት ወደሚጨምር የንግድ ሥርዓት እየተሸጋገረ ይገኛል።
ይህ ሽግግር የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት እና ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ጋር ጠንካራ መስተጋብር በመፍጠር ታይቶ የማይታወቅ ስኬት አስመዝግቧል።
በምርት ዕድገት እና ኮሜርሻላይዜሽን ረገድ፣ በ2012 ዓ.ም 44 ሚሊዮን ቶን የነበረው አጠቃላይ የግብርና ምርት መጠን፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 150 ሚሊዮን ቶን ከፍ ብሏል።
ይህ ከ3 እጥፍ በላይ የሆነ ዕድገት የተገኘው የኩታ ገጠም እርሻ ሥርዓትን በመተግበር እና ሙሉ የግብርና ጥቅሎችን በመጠቀም ነው።
በሌማት ትሩፋት መርሐ ግብርም፣ በ2012 ዓ.ም 48 ሺህ ቶን የነበረው የዶሮ ሥጋ ምርት፣ በ2017 ዓ.ም ወደ 190 ሺህ ቶን በማደግ የ296 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
በተጓዳኝም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ 48 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከልና 12.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግም በማድረግ የደን ሽፋንን ከ17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ከፍ ማድረግ ተችሏል።
የገቢ ምርትን ከመተካት አኳያ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራች ሀገር ለመሆን በቅታለች። ሙሉ በሙሉ በስንዴ ምርት ራስን በመቻል የገቢ ምርትን ያስቀረች ሲሆን፣ በብቅል ገብስ እና በሩዝ የተደረገው ጥረትም አስተማማኝ አቅርቦት ፈጥሯል።
በወጪ ንግድ በኩል፣ በቡና ልማት የተከናወኑ ሥራዎች ምርቱን ወደ 1 ሚሊዮን ቶን እንዲጠጋ በማድረግ በ2017 ዓ.ም ብቻ 2.65 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ አስገኝተዋል።
የግብርና ወጪ ንግድም እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ወደ ውጭ የመላክ አቅም በመገንባቱ፣ ገቢው በ2014 ዓ.ም 3 ቢሊዮን ዶላር ሊደርስ ችሏል።
ግብርና ለጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 34 በመቶ አስተዋፅኦ እያደረገ ሲሆን፣ ለሀገር ውስጥ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች 70 በመቶ የሚሆነውን ጥሬ ዕቃ ያቀርባል።
ይህን የግብርና እና የኢንዱስትሪ ትስስር ይበልጥ ለማቀናጀት በክልሎች የተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ትልቅ ሚና አላቸው።
እስከ አሁን ከ344 ሺህ በላይ አነስተኛ አርሶ አደሮች እና ከ60 በላይ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ከእነዚህ ፓርኮች ጋር ተሳስረዋል።
ለእነዚህ ስኬቶች መሠረታዊው ምክንያት መንግሥት የቀረፀው አዲሱ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ነው። ፖሊሲው የግሉ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።
በተወሰደው የታክስ ማሻሻያ እርምጃ ከ1 ሺህ በላይ አስመጪዎች ወደ 1.2 ሚሊዮን የሚጠጉ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን አስገብተዋል።
እነዚህ የግብርና ግብዓቶች እና መሣሪያዎች ደግሞ ከግብር ነጻ ሆነው እንዲገቡ ዕድል ተፈጥሯል። ይህም 37 በመቶ የሚሆነው የአነስተኛ አርሶ አደሮች ማሳ በቴክኖሎጂ እንዲታረስ አስችሏል።
የ8028 ድምፅ-መር የግብርና ማማከር አገልግሎት እና የገጠር ዲጂታል ኪዮስኮችም አርሶ አደሩ ጠቃሚ ቴክኖሎጂን እና የገበያ መረጃን በቀላሉ እንዲያገኝ አስችለውታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #agriculture #agroindustry #valueaddition #economicgrowth #ebc

Comments