4 months ago
የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በባህርዳር ከተማ ሊካሄድ ነው
#ethiopia | የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ተነገረ።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በውድድሩ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ፣ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የቴክኒክ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው በማቅናት አስፈላጊውን ዝግጅት እያከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቋል።
ይህ የውድድር መድረክ በዋናነት አዳዲስ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራትና የውድድር እድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተገልጿል።
በዚሁ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ላይ የግል ተሳታፊዎችን ጨምሮ ከ6 የተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች እንደሚሳተፉ ታውቋል። በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ለሚያጠናቅቁ አትሌቶችም የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ተገልጿል።
ይህንን ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ተሳትፎ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ጊዜ አድነው እና አቶ መሐሪ ነጋሽ በጋራ የሰጡት ሲሆን፣ ውድድሩ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በቀጥታ ስርጭት ለተመልካች እንደሚተላለፍ ታውቋል።
#ethiopianathletics #bahirdar #streetrace #10krun #ethiopiansport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
"ኢትዮጵያ ታምርት" የጎዳና ላይ ሩጫ
ነገ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል
#ethiopia | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር "ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 4ኛው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ነገ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።
ዓላማው
የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅና በራስ አቅም የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለገበያ ማሳየት ነው።
ተሳታፊዎ
ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና በግል የሚወዳደሩ ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ።
የገንዘብ ሽልማት
በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፦
1ኛ፦ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር
2ኛ፦ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር
3ኛ፦ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር
ይሄ ሩጫ ተራ ስፖርታዊ ውድድር አይደለም፤ የኢኮኖሚ ነጻነታችንን የምናውጅበት መድረክ ነው። 'ኢትዮጵያ ታምርት' በሚል መሪ ቃል የምናደርገው ይሄ ንቅናቄ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህላችንን ያሳድጋል። ነገ መስቀል አደባባይ የሚገኙ 15 ሺህ ሯጮች የሀገራቸውን ምርት እየለበሱ ለሀገራዊ ብልጽግና እንደሚሮጡ ጥርጥር የለኝም።
ነገ መስቀል አደባባይ ለሀገር ምርትና ለጤና እንሮጣለን
#getu #ethiopiatamirt #industryethiopia #10krun #addisababaevents #localproduction #economicgrowth #ethiopianathletics #ኢትዮጵያታምርት #የጎዳናላይሩጫ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments