5 months ago
ካፒታል የቁጠባና ብድር ማህበር በቤቴል አዲስ ቅርንጫፍ ከፈተ
#ethiopia | ካፒታል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት፣ በቤቴል አካባቢ አዲስ ቅርንጫፉን በድምቀት መርቆ ሥራ አስጀምሯል።
ይህ አዲስ ቅርንጫፍ በተለይ የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የቁጠባና የብድር አማራጮችን ለደንበኞች ለማቅረብ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በምረቃው ወቅት የተገኙት የማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ
አቶ ደረጀ መኮንን ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ ያለው ስኬት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ አዲሱ ቅርንጫፍ የአባላትን የፋይናንስ ፍላጎት በቅርበት ለመፍታት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አረጋግጠዋል።
የካፒታል የቁጠባና ብድር ማህበር ሥራ አስኪያጅ
አቶ ጅሬኛ ነገሬ ቅርንጫፉ ለአካባቢው ነዋሪዎችና አባላት ቀላልና ተመጣጣኝ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት፣ በግለሰቦችና በአካባቢው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የማህበሩ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen
#capitalsacco #ethiopianfinance #bethelbranch #savingandcredit #interestfreebanking #economicgrowth #getutemesgen

Comments