5 hours ago
አምራች ኢንዱስትሪ፡ ከሥራ ዕድል ፈጠራ እስከ ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት
********************
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከሚያንቀሳቅሱ ዋና ዋና ምሰሶዎች አንዱ የሆነው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ገቢን በማሳደግና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ለኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ያለውን ሚና እያጠናከረ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንዱስትሪን “የኢኮኖሚ ልብ” በማለት ይገልጹታል። ሀገራችን የራሷን ምግብ፣ ልብስና መድኃኒት በበቂ ሁኔታ ማምረት ካልቻለች፤ የዜጎቿን ፍላጎት ለማሟላትና ኢኮኖሚያዊ ነፃነቷን ለማረጋገጥ ማኑፋክቸሪንግን በበቂ ደረጃ ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ያስገነዝባሉ።
በዚህ አቅጣጫ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታትና የኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም ለማሳደግ እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች መካከል የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው። በንቅናቄው ባለፉት 4 ዓመታት ከ3 ሺህ 500 በላይ አዳዲስ አምራቾች ወደ ዘርፉ መቀላቀላቸው ተገልጿል።
በሀዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የተጀመረው የሶላር ሴል ማምረት ሥራ የኢንዱስትሪው የምርት ስብጥርና የቴክኖሎጂ አቅም እየተስፋፋ መሆኑን ከሚያመላክቱ ማሳያዎች አንዱ ነው።
በግብርና ምርቶች ላይ እሴት መጨመርም የኢንዱስትሪው ሌላው ቁልፍ ትኩረት ነው። የኦሮሚያ ቡና ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማኅበር ምክትል ሥራ አስኪያጅ ምትኩ በቀለ፣ ቡናን በማቀነባበርና እሴት ጨምሮ በመላክ የሚገኘው ተጨማሪ ገቢ ለአርሶ አደሩ፣ ለሠራተኛውና ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ይናገራሉ።
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ፍፁም ከተማ፣ ከዚህ ቀደም አንዳንድ ምርቶችን ወደ ውጭ እየላኩ ተመሳሳይ ምርቶችን ከውጭ የማስገባት ሁኔታ እንደነበር በማስታወስ፣ አሁን ላይ ግን የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላትና የውጭ ምንዛሬን ለማዳን ለተኪ ምርቶች ትኩረት እንደተሰጠ ገልጸዋል። በ2018 ዓ.ም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወደ 30 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ ምርቶች ተመርተው ለሀገር ውስጥ ገበያ መቅረባቸውንም አስረድተዋል።
በሀገራችን ከሚገኙ 14 የኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል 11ዱ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞንነት ተሸጋግረዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፣ በፓርኮቹ ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ቁጥር ከ16 ወደ 320 በላይ አድጓል፤ ከ40 እስከ 50 ሚሊዮን ዶላር የነበረው ከፓርኮቹ የሚገኘው የወጪ ንግድ ገቢም ወደ 270 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል ይላሉ።
ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በወጪ ንግድና በተኪ ምርት ልማት የሚኖራቸው አስተዋጽኦ እየጨመረ ነው። ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችም ከጨርቃ ጨርቅና ከልብስ ምርት ባሻገር የሎጂስቲክስ፣ የቴክኖሎጂና የንግድ አገልግሎቶች በቅንጅት የሚሰሩባቸው ምህዳሮች እየሆኑ ነው።
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄና የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያከናውኗቸው ሥራዎች የሀገራችንን የማምረት አቅም ለማጠናከርና “ሜድ ኢን ኢትዮጵያ” የሚለውን መለያ በዓለም ገበያ ለማሳወቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #economy #industry #manufacturing #madeinethiopia #exporttrade #development #ebc

7 months ago
የኢትዮጵያ አረንጓዴ ወርቅ
10ኛው የሆርቲፍሎራ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ
#ethiopia | ዛሬ መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል የኢትዮጵያን የሆርቲካልቸር ዘርፍ ዕድገት የሚያሳይ ታላቅ ኤክስፖ በይፋ ተከፍቷል።
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዝግጅት ላይ ከ50 በላይ ሀገራት የተወከሉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት፦ ሆርቲካልቸር ከቡና በመቀጠል ለኢትዮጵያ ሁለተኛው ትልቅ የውጭ ምንዛሬ አስገኝ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አስገኝቷል።
ከአጠቃላይ የዘርፉ ገቢ 80 በመቶ የሚሆነው ከአበባ ኤክስፖርት የሚገኝ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ ላኪ ለመሆን በቅታለች።
ከ150 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኤግዚቢተሮች የተሳተፉ ሲሆን፣ አምራቾችን፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችንና ዓለም አቀፍ ገዢዎችን በአንድ መድረክ አገናኝቷል።
በፖሊሲና በመመሪያ ደረጃ እየተደረጉ ያሉ ማሻሻያዎች በፍራፍሬ፣ በአትክልትና በቅመማ ቅመም ኤክስፖርት ላይ አዲስ መነቃቃት ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኤክስፖው እስከ መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆይ በመሆኑ፣ የዘርፉን የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና የገበያ ትስስሮች ለመመልከት አዲስ ዓለም አቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል በመገኘት እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
#getu #ethiopia #hortiflora2026 #horticultureexpo #ethiopianflowers #agriculture #exporttrade #addisababa #economicgrowth #hortiflora #ሆርቲፍሎራ #አበባናአትክልት #ኤክስፖ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments