15 days ago
የኢትዮጵያ አዲሱ የጤና ሉዓላዊነት እና የታሪክ ሽግግር | የምሥራቅ አፍሪካ የጤና ቱሪዝም ማዕከልነት እና የጤናው ዘርፍ ስኬቶች | Ethiopia | Health #healthsovereignty #digitalethiopia2030 #healthtourism
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

1 month ago
የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
#ethiopia | ባሌ፣ ሮቤ - የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ የመዳረሻ ልማት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሽግግር፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገለጹ።
በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia's Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል አበይት ርዕስ ሚኒስትሩ “የመዳረሻ ልማት ብሔራዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ንግግር፣ መዳረሻዎች የቱሪዝም መስህቦች ብቻ ሳይሆኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የኢንቨስትመንት ማዕከላት፣ የማህበራዊ ለውጥ መድረኮች እና የብሔራዊ ማንነት መገለጫዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።
እንደ ዶ/ር አብርሃም ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞቿ ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ፣ ኢንቨስትመንት ለመሳብ፣ መሠረተ ልማትን ለማዘመን እና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር እየሰራች ሲሆን፣ የመዳረሻ ልማት እነዚህን ግቦች በተግባር የሚያሳካ ስትራቴጂ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሶፍ ኦማር ዋሻዎች፣ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ዋንጪ፣ ሐረር፣ ሐዋሳ ሐይቅ፣ ጣና ሐይቅ፣ ገራልታ እና አርባምንጭን ጨምሮ የኢትዮጵያ መዳረሻዎች ጎብኚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ ተመራማሪዎችን እና ፈጣሪዎችን ከዓለም ዙሪያ ለመሳብ ትልቅ አቅም እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ዶ/ር አብርሃም የመዳረሻ ልማት በትራንስፖርት፣ ሎጂስቲክስ፣ ግብርና፣ ሪል እስቴት፣ መስተንግዶ እና አገልግሎት ዘርፎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን እንደሚያነቃቃ ገልጸው፣ በተለይም ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያን ጨምሮ በትስስር እና መሠረተ ልማት ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች የቱሪዝም፣ የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የሪል እስቴት ዕድሎችን እንደሚያሰፉ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የልማት አጋሮች፣ የግሉ ዘርፍ ባለሀብቶች እና የአካባቢ ማህበረሰቦች በመዳረሻ ልማት ዘርፍ በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው፣ የኢትዮጵያ መዳረሻዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የኢንቨስትመንትና የፈጠራ ማዕከላት ማድረግ እንደሚቻል አስገንዝበዋል።
#ethiopia #destinationdevelopment #tourism #investment #economicgrowth #getutemesgen #ethiopia #bale #tourism #getutemesgen #ጌጡተመስገን #artificialintelligence #digitalethiopia2030 #mwu

ኢትዮጵያ በ2030 በኃላፊነት በተመራ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ተቋማዊ ብቃቷን ማጠናከር አለባት ተባለ
ሮቤ፣ ባሌ – ሰኔ 15፣ 2018 ዓ.ም.
#ethiopia | ኢትዮጵያ በ2030 የቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ዘርፍ ተወዳዳሪ ለመሆን ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባሻገር ጠንካራ ተቋማዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ብቃት እና የዲጂታል ሥርዓት ግንባታ ላይ ማተኮር እንዳለባት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ገለጹ።
ዶ/ር አብዮት ይህን ያሉት በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ላይ “The Responsible AI Revolution: Building Ethiopia's Institutional Edge in Tourism and Hospitality by 2030” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ቁልፍ ንግግር ነው።
እንደ አማካሪው ገለጻ፣ ኢትዮጵያ በዲጂታል ሽግግር ጉዞዋ ከዜሮ እየተነሳች አይደለችም። ባለፉት ሰባት ዓመታት በቴሌኮም ሪፎርም፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በዲጂታል መታወቂያ፣ በክፍያ ሥርዓቶችና በመንግሥት አገልግሎቶች ዘርፍ ጉልህ እድገቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም. የተጀመረው “Digital Ethiopia 2030” የተሰኘው ብሔራዊ ስትራቴጂ ሁሉም ዜጎች በዲጂታል ኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ እኩል ዕድል እንዲያገኙ እና የዲጂታል አገልግሎቶች በእምነትና በደህንነት እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም አብራርተዋል።
ዶ/ር አብዮት እንዳሉት፣ የቱሪዝም ዘርፉ ከዲጂታል ለውጥ በፍጥነት ተጠቃሚ ሊሆን ከሚችሉ ዘርፎች አንዱ ሲሆን፣ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የቱሪዝም መድረኮች፣ የዲጂታል ትኬትና ክፍያ ሥርዓቶች፣ የጎብኚዎች ፍሰት ትንተና እና የተቀናጀ የቱሪዝም መረጃ ሥርዓት ለዘርፉ አዲስ ዕድሎችን እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል።
በንግግራቸው የ“MESOB” የተባለውን የተቀናጀ የመንግሥት አገልግሎት መድረክ በአርአያነት ያነሱት አማካሪው፣ ቱሪስቶች ኢትዮጵያን እንደ አንድ የጉዞ ልምድ እንጂ እንደ ተለያዩ ተቋማት እንደማያዩ ገልጸው፣ የቱሪዝም መረጃ፣ የሆቴል አገልግሎቶች፣ የመጓጓዣ አማራጮች፣ የክፍያ ሥርዓቶችና የደህንነት መረጃዎች በአንድ የተቀናጀ ሥርዓት መሰጠት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ለዚህም የቴክኖሎጂ፣ የሂደት እና የሰው ኃይል ሦስት ዋና ምሰሶዎች በአንድነት መሠራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ብሮድባንድ ግንኙነት፣ ዲጂታል መድረኮች፣ የመረጃ አስተዳደር፣ የAI ሥነ-ምግባር መመሪያዎች እና የሰው ኃይል ብቃት በጋራ ሲጠናከሩ ብቻ ዘላቂ ለውጥ እንደሚመጣ አስገንዝበዋል።
አማካሪው ኢትዮጵያ በ“5 Million Ethiopian Coders” መርሃ ግብር ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በኮዲንግ፣ በዳታ ትንተናና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ክህሎቶች ማሠልጠን መቻሏ ለዘርፉ ጠንካራ የሰው ኃይል መሠረት እየፈጠረች መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ በ2030 የኢትዮጵያ ስኬት የሚለካው በተጠቀመችባቸው የAI መሣሪያዎች ብዛት ሳይሆን በዩኒቨርሲቲዎች የተሻሻሉ ሥርዓተ ትምህርቶች፣ በተቋማት የመረጃ ጥራት፣ በዲጂታል ብቃት፣ በግላዊነት ጥበቃ እና በሕዝብ እምነት ላይ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ኮንፈረንሱ በመዳ ዋላቡ ዩኒቨርሲቲ በቱሪዝምና ሆስፒታሊቲ ትምህርት ዘርፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚያመጣውን ዕድልና ተግዳሮት መወያየት ቀጥሏል።
#ethiopia #bale #tourism #getutemesgen #ጌጡተመስገን #artificialintelligence #digitalethiopia2030 #mwu

3 months ago
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ''የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት'' በተሰኘው ሀገራዊ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ለሚመዘገበው ዕድገት መሠረት የሚሆን የሉዓላዊ ዲጂታል መሠረተ ልማት እየገነባች መሆኗን ገልጸዋል።
#artificialintelligence #digitalethiopia2030 #ethiopiantechnology #datasovereignty
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
#artificialintelligence #digitalethiopia2030 #ethiopiantechnology #datasovereignty
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
4 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም "teleSign" የተሰኘውን የዲጂታል ፊርማ መድረክ በይፋ አስጀመረ
#ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፍትህ ሚኒስቴር እና ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ጋር በመተባበር "teleSign" የተሰኘ አዲስ የዲጂታል ፊርማ መድረክ በይፋ ወደ ሥራ አስገብቷል።
ይህ ዘመናዊ መድረክ የመንግስት ተቋማት የአሰራር ስርዓታቸውን ወደ ዲጂታል በመቀየር ለዜጎች ቀልጣፋ፣ ግልፅና ወረቀት አልባ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ሲሆን፣ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ራዕይን ለማሳካት የሚደረገውን ጉዞ በእጅጉ ያፋጥነዋል።
ቴክኖሎጂው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዘ የማንነት ማረጋገጫ (Liveness Detection) ስርዓትን የሚጠቀም በመሆኑ፣ የሰነድ መጭበርበርንና ስርቆትን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ አስተማማኝነትን ያረጋግጣል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ፣ መድረኩ በተለይ በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያለውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፣ ቀደም ሲል ዳያስፖራው የውክልና ሥልጣንና ሌሎች የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎቶችን ለማግኘት በአካል ኤምባሲዎች መገኘት ይገደድ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ግን ይህ "ድንበር የለሽ ቴክኖሎጂ" ዜጎች ባሉበት ሆነው በደቂቃዎች ውስጥ ጉዳያቸውን እንዲያስፈጽሙ በማድረግ እንግልትንና ወጪን በእጅጉ ይቀንሳል።
የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ በላይሁን ይርጋ በበኩላቸው፣ የዲጂታል ፊርማው በሀገሪቱ የዲጂታል ፊርማ አዋጅ መሠረት ሙሉ የሕግ ከላላና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። የአሰራር ስርዓቱን ከሰው ንክኪ ነፃ ማድረጉ በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀሚድ ኪኒሶ እንደገለፁት ፣ ከተቋሙ ባህላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊ ዲጂታል ሽግግር የተደረገ ወሳኝ እርምጃ መሆኑንና ከብሔራዊ መታወቂያ (Fayda) ጋር መገናኘቱ ማንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ፣ ኩባንያቸው ከግንኙነት አገልግሎት አቅራቢነት ወደ ዲጂታል አገልግሎት አቅራቢነት እያደረገ ያለውን ስኬታማ ሽግግር አውስተዋል።
የቴሌሳይን መድረክ የላቀ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና የቴሌብር (telebirr) ክፍያ ሥርዓትን በማቀናጀት ለተቋማትም ሆነ ለግለሰቦች ደህንነቱ የተጠበቀና ፈጣን ዲጂታል ምህዳር እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
ተገልጋዮች ይህንን አገልግሎት በቴሌሳይን መተግበሪያ (teleSign App)፣ በድረ-ገፅ ወይም በQR ኮድ አማካኝነት በቀላሉ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የዲጂታል ኢኮኖሚ ባለቤት እንድትሆን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiotelecom #telesign #digitalethiopia2030 #digitalsignature #telebirr #techinnovation #ethiopiadigitaltransformation

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለሦስት ተቋማት በውክልና ተሰጠ
#ethiopia | የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት (ICS) የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ፣ የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባዎችን በውክልና እንዲሰጡ ከተመረጡ የመንግሥት ተቋማት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ።
🤝 ውክልና የተሰጣቸው ተቋማት፦
አገልግሎቱ በአዲሱ አዋጅ መሰረት የሚከተሉትን ተቋማት በውክልና መርጧል፦
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፦ እስከ ወረዳ በሚገኙ መዋቅሮች የሲቪል እና የቤተሰብ ምዝገባ ስራዎችን በሙሉ በውክልና ያከናውናል።
የጤና ሚኒስቴር፦ በተመረጡ ወሳኝ ኩነቶች (እንደ ልደት) ላይ የማሳወቅና የምዝገባ ሂደቶችን ያመቻቻል።
የመከላከያ ሚኒስቴር፦ በተቋሙ ስር ያሉ ወሳኝ ኩነቶችን የማሳወቅ ፈቃድ ተሰጥቶታል።
🚀 "ዲጂታል ምዝገባ ለዲጂታል ኢትዮጵያ"
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንደገለጹት፣ ይህ የምዝገባ ሥርዓት ዘመናዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ለሀገራዊ ፖሊሲ ቀረፃ ወሳኝ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ፦
ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በተበለጸገ አዲስ ሶፍትዌር አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል።
ምዝገባው ለዲጂታል ማንነት መታወቂያ (Digital ID) እና ለ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ስኬት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።
#ethiopia #immigration #civilregistration #digitalidentity #digitalethiopia2030 #ics #publicservice #addisababa

Comments