8 days ago
የመደመር አንቀጽ
ትዕይንታዊ ሀብቶቻችንም ለብዙ ዘመናት ባህላዊና ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ ሲከወኑ የኖሩ የኢትዮጵያ የቱሪስት መስሕቦች ናቸው። የሕዝቦችን ትውውቅና ትሥሥር ለሚያሳድጉ፣ ባህልንና ቅርስን ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ የዘመን መለወጫዎች፤ የጥምቀት፣ የኢሬቻ፥ የአረፋ፤ የአዊ የፈረሰኞች ትርዒት፣ ዓይነቶቹን የያዘ ነው። ከኪነ ጥበባዊ ቅርሶችም አኳያ ሀገራችን የሙዚቃ፣ የሥዕል፣ የቅርጻ ቅርጽ፣ ሀብታም ናት።
ኢትዮጵያ ከዋሻ ላይ ሥዕሎች ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ሥዕሎች ድረስ ከ5ሺ ዘመን የበለጠ የሥነ ሥዕል ታሪክ አላት። የተቀመረና በኖታ የተገለጠ ዜማ በማዘጋጀት ከዓለም ቀደምቶቹ ተራ የሚያሰልፋት የቅዱስ ያሬድ ዜማ ባለቤት ናት።
በየብሔረሰቡ ዘንድ ልዩ ልዩ የጭፈራ፣ የዜማ ስልትና የሙዚቃ መሣሪያዎች ይገኛሉ። ኢትዮጵያ በየአርኬዎሎጂው ቦታ ከተገኙት ቅርጻ ቅርጾች አንሥቶ በየብሔረሰቡ እስካሎት የቅርጽ ጥበቦች የተሞላች ናት።
የመደመር መንግስት
ገጽ 263
Ethiopian Broadcasting Corporation #medemer #ethiopia #አረፋ #መደመር #ኢትዮጵያ

9 days ago
የአፍርሶ የመጀመር የታሪክ ስብራት እንዴት ተገረሰሰ? ጀምሮ መጨረስ አዲሱ የኢትዮጵያ መለያ
#medemer #policycontinuity #ethiopiarising #gerd #infrastructuredevelopment
10 days ago
የጀመረችውን የምትጨርስ ታላቅ ሀገር
***
ትናንት በጥርጣሬ 'ይቻላል ወይ?' ተብለው የተጠየቁ የትልልቅ ሕልሞቻችን፣ ዛሬ የኢትዮጵያን የጽናት ቁመት ለዓለም የሚመሰክሩ ግዙፍ ማማዎች ሆነው በግርማ ሞገስ ቆመዋል። ይህ እንዴት ተቻለ? መልሱን በተከታዩ ማስፈንጠሪያ ያገኙታል ➡️ https://youtu.be/Pmr7GFRFo...
#medemer #policycontinuity #ethiopiarising #gerd
14 days ago
ምፅዓተ ጂኦ-ፖለቲካ እና የባሕር በር አጀንዳችን
****************
ዓለማችን ከአንድ ዋልታ ወደ ብዝኃ-ዓለማዊ ሥርዓት የኃይል ሽግግር እያደረገች ባለችበት በአሁኑ ዘመን፣ የጂኦ-ፖለቲካው ዐውሎ ነፋስ በድጋሚ እያንሰራራ ይገኛል።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃት በኋላ ተቀዛቅዞ የነበረው የኃያላን ሀገራት የእርስ በርስ የጂኦ-ፖለቲካዊ ሽኩቻ በማገርሸቱ፣ የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዳግም የዓለም አቀፍ ትኩረት ማዕከል ሆኗል።
ሀገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር እና የዓለም መሪ ለመሆን በሚያደርጉት ፉክክር፣ የዓለም ኃይል እና ሀብት የተከማቸባቸውን ቦታዎች ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥድፊያ "ምፅዓተ ጂኦ-ፖለቲካን" በይፋ አውጇል።
በአሁኑ ወቅት የኃያላኑ ግብግብ በተለይም የንግድ መስመሮችን እና ስትራቴጂያዊ የባሕር ሰርጦችን መቆጣጠር ላይ ያነጣጠረ ነው።
በታሪክ የምድርን ማዕከላዊ መሬት እና የባሕር ዳርቻን መቆጣጠር ዓለምን መቆጣጠር ነው የሚሉት የሀልፎርድ ማኪንደር እና የኒኮላስ ስፓይክማን ክላሲካል ፅንሰ-ሐሳቦች በድጋሚ የዓለም መድረክ ላይ ተግባራዊ እየሆኑ ይገኛሉ።
በዚህ ፉክክር መካከል ቀይ ባሕር፥ አፍሪካን፣ አውሮፓን እና እስያን የሚያገናኝ ድልድይ በመሆኑ የጂኦ-ፖለቲካ ፉክክር ማዕከል ሆኗል።
በዚህ ውስብስብ የጂኦ-ፖለቲካ ፍጥጫ ውስጥ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት ምሰሶነት ልዩ ትኩረት የሚሻ ነው። ትልቅ የሕዝብ ቁጥር ያላት እና በነፃነት ታሪኳ የምትታወቀው ኢትዮጵያ፣ በቀጣናው ፖለቲካ የላቀ አቅም ያላት ዋልታ ናት።
ይሁን እንጂ 97 በመቶ የሚጠጋ ምርቷን ለማስገባት በአንድ ሀገር ላይ ብቻ ጥገኛ መሆኗ፣ ሀገራችን በስትራቴጂያዊ የባሕር በር እጦት እንድትፈተን አድርጓታል።
ስለሆነም፣ ኢትዮጵያ ከታሪካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ገናንነቷ አኳያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበር አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የግድ ይላታል።
ስንት ሺሕ ኪሎሜትር አቋርጠው የመጡ የውጭ ኃይሎች አፍንጫችን ሥር ወታደራዊ የጦር ሰፈር በገነቡበት በዚህ ዘመን፣ ቀጣናዊ ዋልታ የሆነችው ሀገራችን የራሷን የባሕር ኃይል እና ወታደራዊ ቤዝ ለማደራጀት መመኘቷ ሉዓላዊ መብት ከመሆኑም ባሻገር ለቀጣናው ሰላም እና አንድነት መጠበቅ ወሳኝ እርምጃ ነው።
ከዚህ ሁሉ አዙሪት እና የኃያላን የእጅ አዙር ጦርነት ለመውጣት የሚያስችለው ስትራቴጂያዊ መንገድ "መደመር" ነው። ኢትዮጵያ ያላት ሰፊ ገበያ እና የውኃ ሀብት፣ የጎረቤት ሀገራት ካላቸው የባሕር በር ጋር ተቀናጅቶ አካባቢውን በጋራ የማልማት ትልቅ አቅም አለው።
የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በታሪክ፣ በባህል እና በሃይማኖት የተሣሠሩ ወንድማማች ሕዝቦች በመሆናቸው፣ አብሮነታቸውን ድንበር ሊገድበው አይገባም።
ጥላቻን አስወግዶ፣ ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ትሥሥር በመፍጠር፣ ወሰን ተሻጋሪ የንግድ ግንኙነትን ማጠናከር የውዴታ ግዴታ ነው።
የቀጣናው ሀገራት እርስ በርስ ከመጋጨት ይልቅ ቢተባበሩ እና የሌሎችን ኃይሎች ጣልቃ ገብነት በመረዳት ቢደጋገፉ፣ ቀጣናውን ከግጭት የፀዳ በማድረግ ወደ ላቀ ብልጽግና ማሸጋገር ይችላሉ።
የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም የሚረጋገጠውም ሆነ የቀጣናው ዕጣ ፈንታ ብሩህ የሚሆነው ይህ የትብብር እና የመደመር መንፈስ በተግባር ሲመነዘር ብቻ ነው።
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ebc #ethiopia #medemer #redsea #nationalinterest

15 days ago
ከሀገር ውስጥ ተቋማዊ ግንባታ እስከ ቀይ ባሕር ሕጋዊ መብት፤ አሰባሳቢው ሀገራዊ ትርክት
******************
ኢትዮጵያ በታሪኳ የብዙ ማንነቶችና የግዙፍ ታሪኮች ማህደር ብትሆንም፣ ላለፉት ዓመታት በፖለቲካው ምህዳር የነገሱት ትርክቶች እንደ አስተሳሳሪ ሳይሆን በሁለት ጎራ ተከፍለው ሀገራችንን ሲያዳክሙ ቆይተዋል።
ይህ በሁለት ጽንፎች መካከል የነበረ የጥላቻ ፖለቲካና የነጣጣይ ትርክቶች አዙሪት ግን አሁን በአዲሱ “የመደመር” እሳቤ ተሰብሯል። አዲሱ እሳቤ እነዚህን የቆዩ የፖለቲካ፣ የዴሞክራሲና የተቋማት ግንባታ ስብራቶች በመጠገን ሀገራዊ ህብርብሔራዊ አንድነትንና የጋራ ተስፋን ሰንቆ ብቅ ብሏል።
መደመር ያለፈውን ታሪክ በጭፍን ሳይቀበልና ሳይቃወም፣ መልካሙን ወርሶ ግድፈቶቹን ደግሞ ተምረንባቸው የምናልፍበት ድልድይ መሆኑን እና እሳቤው ከሀገር ውስጥ ፖለቲካ አልፎ የሀገራችንን ስልታዊ ጥቅሞች ማስከበር ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ምሁራን ገልጸዋል።
የታሪካዊ ጠላቶች ሴራ መነሻው ኢትዮጵያ በዓባይ እና በቀይ ባሕር ላይ ያላትን መብት ለማዳከም መሆኑን የጠቀሱት ምሁራኑ፣ የህዳሴ ግድብ በጸጥታ ኃይሎቻችን መስዋዕትነት የተገነባ የድላችን አምድ እንደሆነና የቀይ ባሕርን ህጋዊ መብት መጠየቅም የሉዓላዊነትና የህልውና ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲሱ ሀገራዊ ትርክት የውክልና ጦርነቶችን በመመከት ግጭትን ወደ ስምምነት፣ ልዩነትን ደግሞ ወደ ውበት እየቀየረ ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና ማማ የማውጣት ታሪካዊ ተልዕኮውን እያሳካ ይገኛል።
የመደመር እሳቤ የሀገራችንን ዘላቂ ስልታዊ ጥቅሞች፣ ተቋማዊ ብቃትንና የአህጉራዊ ፋይዳውን እንዴት እያስከበረ እንደሚገኝ የቀረበውን ሙሉ ማብራሪያና ሰፊ ትንታኔ አስተያየት መስጫው ውስጥ ያለውን ማስፈንጠሪያ ተጭነው ያንብቡ።
በላሉ ኢታላ
#ethiopia #medemer #nationalnarrative #redsea #africanunity #ethiopianbroadcastingcorporation

17 days ago
የመደመር አንቀጽ
...በሀገር ውስጥ ማግኘት የምንችላቸውን የግብአት ምርቶች ቅድሚያ እንሰጣለን። ከውጭ ማስገባት ያለብንን ደግሞ በሂደት እንተካለን። ማዳበሪያ የእርሻችን ወሳኝ ግብአት መሆኑ ይታወቃል። በዚህ ረገድ የሚፈጠሩ የጊዜ መዛባቶች ኪሣራቸው እጅግ ከባድ ነው። በመሆኑም የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን በከፍተኛ ደረጃ በማስፋፋት ከእኛ አልፎ ለሌሎች መሰል ሀገራትም ማዳበሪያ የምናቀርብበትን ዐቅም መገንባት ያስፈልጋል።
በመደመር መንግሥት የገጠር ልማታችን በአርሶና አርብቶ አደሩ ምርታማነት ላይ ብቻ የሚያተኩር አይደለም። አዳዲስ ገበያዎችን በመፍጠር የአርሶና የአርብቶ አደሩን ገቢ በማሳደግ ዙሪያ ይቃኛል። የገጠር ልማት የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የገበያ ትሥሥር እያጎለበተ መሄድና በገጠር የሥራ ፈጠራን ማስፋት አለበት።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 172
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc #ማዳበሪያ #ገጠር #መደመር #ዳንጎቴ #ጎዴ

18 days ago
የመደመር አንቀጽ
"የኢንዱስትሪ ጉዟችን የውስጥ ዐቅምን አሟጦ መጠቀምና አስፈላጊ ዐቅሞችን መገንባትን ማዕከል ያደረገ ነው። በዚህም የመጀመሪያው ጥቅል ግባችን በገቢ ንግድ (Import) ወደ ሀገራችን የሚጎርፉ ሸቀጦችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት አካሄድ ነው። የብዙ ጥሬ ዕቃዎች አምራች ብንሆንም፣ እነዚህን ግብዓቶች ተጠቅመው የሚሠሩ ምርቶችን መልሰን በውድ ዋጋ ከውጭ ሀገራት የምናስገባ ሀገር ነን።
ይህንን እውነታ ሥርዓት በያዘ መልኩ መቀየር እስካልቻልን ድረስ፣ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ኢንዱስትሪ መገንባት አንችልም። ሁለተኛው ጥቅል ግብ ደግሞ የወጪ ንግድ (Export) ቀጥታ ጥሬ ዕቃ ከመሸጥ አልፎ፣ ዕሴት የታከለባቸው ምርቶችን ማቅረብን፣ ከዚያም ሲያልፍ ያለቀላቸው ምርቶችን በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለተጠቃሚዎች ማቅረብን ዓላማ ያደረገ ነው።"
የመደመር መንግሥት
ገፅ 215
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ebc #መደመር #medemer #ኢንዱስትሪ

19 days ago
የመደመር አንቀጽ
የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ከሁሉም በላይ በፋብሪካ ምሕንድስናና በዲጂታል ቴክኖሎጂ የበቃ የሰው ኃይል ዝግጁነትን ይጠይቃል፡፡ ለዘርፉ የሚደረጉ ሥልጠናዎች ከተግባር ጋር የተያያዙ መሆን አለባቸው፡፡ እነርሱም ቴክኖሎጂን የማሸጋገር፣ የማለማመድና የመፍጠር፣ የመተርጎምና የመተግበር ክሂሎት ያለው የሰው ኃይል በማብቃት ላይ ማተኮር ይገባቸዋል።
ቴክኖሎጂ በአምራች ኢንዱስትሪው የነበረውን ምርት ለመተካት ይረዳል። አዲስ ምርት ለማምረት ወይም የነበረውን ለማዘመን ይችላል። በአዲስ የማምረት ሂደት ከፍተኛ ምርታማነት እንዲመዘገብ ያደርጋል። ተለጣጭነትንና የማምረት ሀቅምን በመገንባት የማምረት ወጪን ይቀንሳል። ጥራትና ጊዜን በመቀየር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ የዕሴት ጭማሪ ለማስገኘትና የተወዳደሪነትን ዐቅም ለማጎልበት ያግዛል።
የመደመር መንግስት
ገጽ 208/209
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ebc #መደመር #medemer

20 days ago
u12e8u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u1218u133du1210u134d u12e8u12d3u1228u1260u129b u1275u122du1309u121d u1260u12a0u1261u12f3u1262 u1270u1218u1228u1240
#medemer #ethiopiadiplomacy #abiyahmed #abudhabi #arabictranslation ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መጽሐፍ የዓረበኛ ትርጉም በአቡዳቢ ተመረቀ
#medemer #ethiopiadiplomacy #abiyahmed #abudhabi #arabictranslation
21 days ago
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ተመረቀ
*************************
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ የአረብኛው ትርጉም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በአቡ ዳቢ የተመረቀው ይህ መጽሐፍ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሁሉም አረብኛ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥትና ፍልስፍና እያራመደች የምትገኘውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የለውጥ እንቅስቃሴ ትልሞች በጥልቀት እንዲገነዘቡት ዓላማ ያደረገ ነው።
በመጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት” አረብኛ ትርጉም እውን መሆን በኢትዮጵያና በተቀረው የአረቡ ዓለም በኩል ያሉ የጋራ ጥቅሞችን አስተሳስሮ ለማስቀጠልና የጋራ ጥቅሞቻችንን ለማስጠቅ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሸክ ሻክቡት ቢን ናህያን አልናህያን፣ መጽሐፉ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረቡ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል የቆየውን ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገሪቱ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ታድመዋል።
በሰለሞን ኃይለኢየሱስ ከአቡዳቢ
#ethiopia #medemer #abiyahmed #uae #abudhabi #booklaunch #diplomacy

ትርክት ዓለምን የምንቃኝበት ዓይናችን ነው። በሕይወት ውስጥ የምንሰማቸው መረጃዎች፣ የሚገጥሙን ገጠመኞችና የምንኖርበት አካባቢ አስተሳሰብና ዕይታችንን በመቅረጽ የምንጋራውና የምንለያይበትን ትርክት ይሠራሉ። ይህም በማኅበረሰብ ውስጥ ራሳችንን የምንረዳበትን ሁኔታ ይፈጥራል። ከማኅበረሰብ ጋር ያለንን አንድነትና ልዩነት በዕዝነ ኅሊናችን ላይ ይቀርፃል። ትርክት አቅጣጫን ያመላክታል። የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመግባባትና በመረዳዳት ለጋራ ግብ የሚያሰልፍና የሚያሠማራ ገፊ ኃይል ነው። የትርክት ኃይል እንዳጠቃቀማችን ማኅበረሰባዊ ትሥሥርን ለማጠንከር አልያም ለግጭት ይውላል።
አዎንታዊ የትርክት ኃይል ፍጥነትንና ፈጠራን የማኅበረሰብ ዕሴት የማድረግ ዐቅም አለው። እንደዚያው ሁሉ አሉታዊ የትርክት ኃይልም ግጭትን ለመፍጠርና የማንነት ንግድ ክሂሎትን ለማዳበር ይውላል። ቅሬታዎችን እያባባሰ ግጭትን ይፈጥራል። ታሪካዊ ቅሬታን በማነሣሣት፣ አካባቢያዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን በዕኩይ መነጽር በማሳየት፣ የፖለቲካ ክሥተቶችን በአሉታ በመተርጎም፣ ተቋማዊ ደካማ አሠራሮችን ሕግጋት አድርጎ በማሳየትና የሀብት ክፍፍልን ሆን ተብሎ እንደተደረገ አድርጎ በማመላከት ቅሬታዎች ወደ ግጭት እንዲያመሩ ይደረጋል።
የመደመር መንግስት
ገጽ 342/343
Ethiopian Broadcasting Corporation #ኢትዮጵያ #ebc #narative #ebc #መደመር #ትርክት #medemer

23 days ago
የመደመር አንቀጽ
ለመበልጸግ የሚያስችል ዕምቅ ዐቅም የሀገራትን ልማት የሚያግዝ ሀብት ለማፍራት መነሻ ወረት ነው። የተፈጥሮ ሀብት፣ መልክአ ምድር፣ የሰው ኃይልና መሰል ጉዳዮች፤ በአጠቃላይ ለመልማት ያላቸው ምቹነትና ሀብት ለመፍጠር ያላቸው ዐቅም ስፋት ወይም ማነስ፤ ሀገራት ከድህነት ለመውጣት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በአንጻራዊነት ቀለል ያለና ረጅም ጊዜን የማይጠይቅ፤ አልያም ተጨማሪ ጥረቶችን የሚጠይቅና ፈታኝ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ወደፊት መጓዝ የምንችለው ዐቅሞችና ዕድሎች ከፍተኛውን ውጤት በሚያስገኙበት መንገድ ስንጠቀም በመሆኑ፤ ያሉንን ዕምቅ ዐቅሞች የምንጠቀምበትና ያጋጠሙንን ዕድሎች ወደ ውጤት የምንቀይርበትን መንገድ መቀየስ ትልቁ ጉዳይ ነው፡፡ ይሁንና የሀገራችን ኋላ መቅረት፤ ያሉንን ዕምቅ ዐቅሞች አለመጠቀማችንንና የሚያጋጥሙንን ዕድሎች ስናባክን መቆየታችንን የሚያሳይ ነው፡፡
የመደመር መንግሥት
ገጽ 16
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc

Sponsored by
Surafel
24 days ago
የመደመር አንጽ
“በእኔ በኩል ያልተሰለፈ፣በሌላው በኩል እንደተሰለፈ ይቆጠራል" በሚል አንድምታ የሚመራው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት፣ ድኾችን የበለጠ ያደኸያል። ባለጠጎችን ደግሞ ከልክ በላይ ያበለጽጋል። በዚህ ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ መድረክ የተያዘው የአዳጊ ሀገሮች ህልውና አደጋ ውስጥ ገብቷል። ከድህነት ለመላቀቅ የሚያደርጉት ጥረት በፖለቲካዊ ስልቶች በየጊዜው ይናጋባቸዋል። ዕድገታቸውን ወደ ተስፋ አስቆራጭ አዙሪት ይቀይርባቸዋል። ጉዟቸውን “አንድ ርምጃ ወደፊት፣ ሁለት ርምጃ ወደ ኋላ አድርጎታል፡፡ አዳጊ ሀገራት ከድህነት ለመውጣት የሚያደርጉት ትግል፣ በፖለቲካ ንግዱ ተጠልፎ መንገዱ ተዛብቷል። በዚህም ምክንያት እነዚህ ሀገራት የራሳቸውን ዕድል በራስ የመወሰን ትግል ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል።
የመደመር መንግስት
ገፅ 341
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #medemer #ethiopia

25 days ago
የመደመር አንቀጽ
የምንገኘው የዓለም ዋነኛ የንግድ ኮሪደር በሆነው ሥፍራ አካባቢ ነው። የቀይ ባሕር አካባቢ የምሥራቁንና የምዕራቡን ዓለም አገናኝ ወሽመጥ ነው። በመሆኑም የአፍሪካና እስያ መገናኛ ድልድይ ነን። ይህንን ግን ለዕድገታችን አላዋልነውም። እንደ ሲንጋፖር ያሉት ሀገራት አካባቢያቸው የሰጣቸውን ትሩፋት ተጠቅመው በልጽገዋል። አካባቢያቸው የሰጣቸውን ተጽዕኖ የመፍጠር ትሩፋት ለዕድገታቸው ግብአት ያደረጉ ሌሎችም በርካታ ሀገራት አሉ። ሀገራችን በአንጻሩ በአፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ለዕድገቷ ግብዐትነት በሚገባ አልተጠቀመችውም።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 53
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc #ቀይባሕር #የባሕርበር

26 days ago
የመደመር አንቀጽ
የመገናኛ ቴክኖሎጂም ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን ከመሰሉት መገናኛዎች እየተሻገረ ነው። ከአንድ ማዕከል ከሚመሩ መገናኛ ብዙኃን ወጥቶ የዘመኑ ዲጂታል ዓለም እያንዳንዱን ግለሰብ የመገናኛ ባለቤት አድርጎታል። የግለሰቦች መኖሪያ ቤትም ስቱዲዮ እንዲሆን አስችሏል። ዓለም በመረጃ ከመቼውም በላይ ተሣሥራለች። የተለያዩ መረጃዎችን ከአንዱ የዓለም ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ ማድረስ የጥቂት ደቂቃዎች ሥራ ሆኗል። አዳዲስ ድርጊቶች ያለ ምንም ፈቃድና ክልከላ በግለሰቦች እጅ በቀጥታ እስከ መሠራጨት ደርሰዋል። ከጅምላ ሥርጭት ወጥተው ግለሰቦች እንደየፍላጎታቸው የተቃኙ ዜናዎችን ማግኘት ጀምረዋል።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 16
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc
የመገናኛ ቴክኖሎጂም ጋዜጣ፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥንን ከመሰሉት መገናኛዎች እየተሻገረ ነው። ከአንድ ማዕከል ከሚመሩ መገናኛ ብዙኃን ወጥቶ የዘመኑ ዲጂታል ዓለም እያንዳንዱን ግለሰብ የመገናኛ ባለቤት አድርጎታል። የግለሰቦች መኖሪያ ቤትም ስቱዲዮ እንዲሆን አስችሏል። ዓለም በመረጃ ከመቼውም በላይ ተሣሥራለች። የተለያዩ መረጃዎችን ከአንዱ የዓለም ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ ማድረስ የጥቂት ደቂቃዎች ሥራ ሆኗል። አዳዲስ ድርጊቶች ያለ ምንም ፈቃድና ክልከላ በግለሰቦች እጅ በቀጥታ እስከ መሠራጨት ደርሰዋል። ከጅምላ ሥርጭት ወጥተው ግለሰቦች እንደየፍላጎታቸው የተቃኙ ዜናዎችን ማግኘት ጀምረዋል።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 16
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc
27 days ago
የመደመር አንቀጽ
የሀገር ደኅንነትና የመገናኛ ሥርዓቶችም በከፍተኛ ደረጃ ተቆራኝተዋል። ማኅበራዊ መገናኛ በሀገራት ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖም ከፍተኛ ሆኗል። የፈጠራና የሐሰት ወሬዎች ከየትኛውም የዓለም ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ በሰከንዶች እስከ ማስተላለፍ ተደርሷል። የዲጂታል ቴክኖሎጂና የማኅበራዊ መገናኛ ዕድገት እውነትን ከሐሰት አምታትቶታል። የጥልቅ ማመሳሰል (Deepfake) ዘመን እውነትና ሐሰት ልዩነቱ ጠፍቶ፤ የትርክት ፉክክር የሀገራትን ፖለቲካ መረጋጋት ነሥቶታል።
ቴክኖሎጂና ማኅበራዊ መገናኛ በሀገራት ፖለቲካ ውስጥ ተዋንያኑ ብዙ እንዲሆኑ አድርገዋል። አለመረጋጋትን መፍጠር ለሚፈልጉ ኃይሎች ድንበር ሳይሻገሩና ጦር ሳያዘምቱ የሀገራትን ፖለቲካ እንዲንጡ ዐቅም ሰጥቷቸዋል። ሀገራትን ለማውደምና ለማንበርከክ የሚደረግ ጦርነትም ሕንጻንና ከተማን ከማፍረስ ጭንቅላትን ወደ መስለብና ወደ ማፍረስ ማዕከሉን ቀይሯል። ጥይት ሳይተኩሱና ሕንጻ ሳያወድሙ፣ በማኅበራዊ መገናኛ የሚለቀቁ የሐሰት ወሬዎች፣ ሀገር ወደ ማፍረስ ተሸጋግረዋል።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 16
Ethiopian Broadcasting Corporation #abiyahmed #ethiopia #medemer #ebc #fakenews #deepfakes

28 days ago
የመደመር አንቀጽ
የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ብዙ ዓምዶች አሉት። አደጋን አስቀድሞ አይቶ ማስወገድ ወይም መከላከል አንዱ ነው። አደጋው ከመጣም አደጋውን ተቋቁሞ ማሳለፍ ሌላው ነው። አደጋው ጉዳት ካደረሰም በቶሎ ለማገገም የሚችል ኢኮኖሚን መገንባት ደግሞ ሌላው የማይበገር ኢኮኖሚ ጠባይ ነው።
የመደመር መንግሥት ኢኮኖሚውን የሚፈትኑ አደጋዎችን ማስጠም የሚችል ነው። ተለዋዋጭ ነገሮችን ይላመዳል፤ እንዲሁም ከአደጋ ቶሎ የሚያገግም ኢኮኖሚ መገንባት ትልቁ ትኩረቱና መገለጫው ነው።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 147
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc
የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ብዙ ዓምዶች አሉት። አደጋን አስቀድሞ አይቶ ማስወገድ ወይም መከላከል አንዱ ነው። አደጋው ከመጣም አደጋውን ተቋቁሞ ማሳለፍ ሌላው ነው። አደጋው ጉዳት ካደረሰም በቶሎ ለማገገም የሚችል ኢኮኖሚን መገንባት ደግሞ ሌላው የማይበገር ኢኮኖሚ ጠባይ ነው።
የመደመር መንግሥት ኢኮኖሚውን የሚፈትኑ አደጋዎችን ማስጠም የሚችል ነው። ተለዋዋጭ ነገሮችን ይላመዳል፤ እንዲሁም ከአደጋ ቶሎ የሚያገግም ኢኮኖሚ መገንባት ትልቁ ትኩረቱና መገለጫው ነው።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 147
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc
Sponsored by
Surafel
29 days ago
የመደመር አንቀጽ
የብሔራዊነት ትርክት በነጻነት፣ በእኩልነትና በወንድማማችነት/ እኅትማማችነት ላይ የተመሠረተ ነው። አቀራራቢ በሆነ ታሪክ ላይ ይገነባል። የትናንትን ብቻ ሳይሆን የዛሬ አብሮነትንና የነገ የጋራ ዕጣ ፈንታችንን የሚያመለክት ነው።
ወደ ሐሳብ ገበያ በምናደርገው ጉዞ ለፖለቲካ ገበያ በር የሚከፍቱ ያለፉ ስብራቶቻችንን ለመጠገንና መሻገር ያስፈልገናል።
ለሐሳብ ገበያ መሠረትን ለመጣልና ስብራቶችን ለመጠገን የሚያስችል ብሔራዊ መግባባትን የሚያመጣ ምክክር አስፈላጊ ነው።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 402/403
Ethiopian Broadcasting Corporation #medemer #ethiopia #patriots

1 month ago
የመደመር አንቀጽ
በኢንዱስትሪያዊነት ጉዞ ውስጥ፣ ዘመናዊ የአገልግሎት ዘርፍ ወሳኝ ምሰሶ በመሆን የኢንዱስትሪዎችን ስኬት ያረጋግጣል። ይህ ዘርፍ፣ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያቀርበው ድጋፍ እጅግ ከፍተኛ ነው። ያለው የብስለት ደረጃ የኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት ይወስናል፡፡ እንዲሁም የራሱም ብስለት በኢንዱስትሪያዊነት ፍጥነትና ጥራት ይወሰናል።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪያዊነት ስኬት፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ዘመናዊ አምራችነት በማሸጋገር ብቻ አይወሰንም። ከዚያም አልፎ ወደ ውስብስብና እጅግ ዘመናዊ ወደ ሆነ የአገልግሎት ዘርፍ ሽግግር በማድረግም ጭምር ሊረጋገጥ ይገባል። በአሁኑ ጊዜ ዝቅተኛ የዕሴት ጭማሪ በሚያመጡ ተግባራት ላይ ያተኮረውን የአገልግሎት ዘርፍ፣ ከፍተኛ የዕሴት ጭማሪ ወዳለው የቴክኖሎጂ ምጥቀትና ውስብስብነት ማሸጋገር ወሳኝ ነው።
የመደመር መንግስት
ገፅ 207
Ethiopian Broadcasting Corporation #industry #ethiopia #medemer

በአዲሱ ዘመን ዕሳቤ ከተሞች ለመኖሪያ ምቹ፣ ለንግድ ማሣለጫ፣ ለፈጠራና ለቢዝነስ መጀመሪያና መጎልበቻ፣ ለቱሪስት መዳረሻ ሆነው እንዲቆረቆሩ ማድረግ ያስፈልጋል።
እንዲሁም ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር የተሣሠሩና ገጠሩን ከከተማው በማቀናጀት የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን አስቻይ እንዲሆኑ ሊሠራ ይገባል።
ለዚህም አዲስ አበባና ሌሎች መካከለኛና አነስተኛ ከተሞችን የመሠረተ ልማት ችግሮቻቸውን መፍታት ይገባል። ያሉባቸውን የዕቅድና የአስተዳደር ፈተናዎች ማቃለል ያስፈልጋል።
የመጪውን ጊዜ ተግዳሮቶች ለመፍታትና ለመሻገር ደግሞ የላቀ ሐሳብ፣ ፈጠራና ፍጥነት ያለው ሥራ ይጠይቃል።
የመደመር መንግስት 234
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia Ethiopian Radio /የኢትዮጵያ ሬድዮ/ #corporation
#medemer #ethiopia #ebc #addisababa

5 months ago
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።
Sponsored by
Surafel
5 months ago
"መደመር" መተግበሪያ ተለቀቀ
#ethiopia | በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው መቅረባቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ።
መጻሕፍቱ ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከማገዛቸውም ባለፈ በውስጣቸው የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው ተብሏል።
መተግበሪያው ይፋ በሆነበት መድረክም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመደመር እሳቤ የተከናወኑ ተግባራት ያስመዘገቡት ተጨባጭ ውጤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢዎች እንደበት ተዳሰዋል። #nbc

6 months ago
የኢትዮጵያ"የሀይል ማስፋት" (Power Projection)፡በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የዲፕሎማሲ ጥረት...!
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ )
#ethiopia | በቅርቡ የተከናወነው በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት የG-20 የኢትዮጵያ ተሳትፎ እንዲሁም የማሌዥያና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት፣የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መንግስት እየተከተለው ያለውን የዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ "የሀይል ማስፋት"ስትራቴጂ ቁልፍ ማሳያዎች ናቸው።ይህ ስትራቴጂ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ተጽዕኖ በማስፋት፣ለሀገር ውስጥ ዕድገት የሚያስፈልገውን ሀብትና ዕውቀት ለመሳብ ያለመ መሆኑን ያሳያል።
🔴 የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዲፕሎማሲያዊ ራዕይ፦
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በዋናነት በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ (Economic Diplomacy) እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በማስፋት ላይ ያተኮረ ነው።ከዓለም ደቡብ (Global South) አገሮች በተለይም ከእስያ እና ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር አዲስና ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት መገንባት፤ በሁሉም ወገን የሀገርን መሰረታዊ ብሄራዊ ጥቅም ማስከበር እና ማረጋገጥ አጋርነትን ማስፋትን ያካትታል።
የ"ብልጽግና" ጽንሰ-ሀሳብ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች በሙሉ ከብልጽግና ራዕይ ጋር የተሳሰሩ ሲሆን፣ የውጭ ግንኙነት በዋናነት ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲያገለግል ለማድረግ ያለመ ነው።
🔴የቡድን ሀያ አባለ ሀገራት (G-20) ተሳትፎ፦የብዙ-ዋልታ ዓለምን (Multipolar World) መቀበል ኢትዮጵያ በG-20 ስብሰባ ላይ እንደ ልዩ እንግዳ መሳተፏ፣በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራው ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀንድ ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ተዋናይ አድርጎ ለማስቀመጥ ያለውን ጥረት ያሳያል።በዓለም የፋይናንስ እና የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ ማዕከላት ላይ ድምጽ እንዲኖራት ማድረግ።ክቡር ዶ/ር ዐቢይ በተደጋጋሚ እንደሚገልጹት፣ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኀብረት ዋና መስሪያቤት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን የአፍሪካን አጠቃላይ ጥቅም በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ በማንሳት፣ የሀይል ማስፋት ጥረቷን ከአህጉራዊ ሚናዋ ጋር አጣምራለች።
🔴 የእስያ መሪዎች ጉብኝት፦የቴክኖሎጂና የኢንቨስትመንት ድልድይ የማሌዥያ እና የሲንጋፖር መሪዎች ጉብኝት የዶ/ር ዐቢይ የዲፕሎማሲ ጥረት ዋነኛ መገለጫ ነው።ከእነዚህ ፈጣን ዕድገት ካላቸው የእስያ "ነብሮች" (Asian Tigers) ጋር ግንኙነት መፍጠር የኢትዮጵያን የመበልፀግ የማደግ ስትራቴጂ ለመደገፍ ወሳኝ ነው።
🖊እንደ መውጫ ስልታዊ ትኩረት የሀይል ማስፋት ትርጉም⁉️
ሲንጋፖር የላቀ የሎጅስቲክስ አስተዳደር፣ ዘመናዊ የከተማ ልማት (Smart City)፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልምድ ሽግግር፤ የኢትዮጵያን የባህር በር ፈተና ለመቅረፍ ዘመናዊ የንግድ መስመሮችን መገንባት እንደ አስረጅነት ይጠቀሳል ።( በሀገራችን በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልል ከተሞች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ይጠቀሳል ።
ማሌዥያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) በኤሌክትሮኒክስና በኢንዱስትሪ ዘርፍ መሳብ፣ የዘይትና ዘይት ነክ ምርቶች ንግድ በማጠናከር የኢኮኖሚ አጋርነትን እና የንግድ አጋሮች ማጎልበትን ያሳያል ።( Industrial Park Development cooperation ስር የሚከናወኑ የእውቀት እና የኢንዱስትሪ ሽግግር መጥቀስ ይቻላል ።)
🔴የማጣቀሻዎች (Reference )
1️⃣Abiy Ahmed (PhD). Medemer: A Collective Journey. (የዶ/ር ዐቢይ የፍልስፍና መሰረት ለዲፕሎማሲያዊ ስትራቴጂያቸው።)
2️⃣ Minister's Office. Official Press Releases on G20 and Bilateral Visits. (የጉብኝቶቹን ዓላማ እና የተደረጉትን ስምምነቶች ለመረዳት።)
3️⃣Think Tank Analysis. ISS, Chatham House or Brookings papers focused on Ethiopia's shift in foreign policy towards Asia and Global South engagement.
ይህ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የሀይል ማስፋት እቅድ በዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ኢኮኖሚን ማዕከል ባደረገ እና በብዙ-ዋልታ ትብብር ላይ በተመሰረተ ዘመናዊ ዲፕሎማሲ እየተመራ መሆኑን ያሳያል ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia 🇪🇹
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...