25 days ago
በዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተጻፉ ሁለት አዳዲስ የሳይንስና ቴክኖሎጂ መጽሐፍት ተመረቁ
#ethiopia | የቀድሞው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዴኤታ እና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ አዴ፣ የወደፊቱን ዓለም በሳይንስና በቴክኖሎጂ የሚመለከቱ ሁለት አዳዲስ መጽሐፍትን ለንባብ አበቁ።
«Architecting the Future: A Blueprint for the Next Human Civilization» እና «Introduction to Astronautics: A Beginner's Guide» በሚል ርዕስ የቀረቡት መጽሐፍት፣ የወደፊቱን የሰው ልጅ ሥልጣኔ፣ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ሚና፣ እንዲሁም የጠፈር ሳይንስ እድሎችን በሰፊው የሚዳስሱ መሆናቸው ተገልጿል።
በመጽሐፍቱ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ዶ/ር ይሹሩን እንዳስታወቁት፣ «Architecting the Future» የሰው ልጅ ሕይወትን በፍጥነት እየቀየሩ ባሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል የወደፊቱን ዓለም በሰብዓዊ እሴቶች፣ በዘላቂነትና በራዕይ መገንባት ላይ ያተኩራል።
ሁለተኛው መጽሐፍ «Introduction to Astronautics» ደግሞ የጠፈር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለዕለት ተዕለት ኑሮ፣ ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለብሔራዊ ደህንነት ያለውን ፋይዳ በቀላል አቀራረብ በማስረዳት፣ በተለይም አፍሪካውያን ወጣቶች በጠፈር ኢኮኖሚ ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያበረታታል።
ደራሲው እንደገለጹት፣ ሁለቱ መጽሐፍት አንዱ የወደፊት ራዕይን ሲያስቀምጥ፣ ሌላው ደግሞ ያንን ራዕይ ለማሳካት የሚያስፈልጉ ሳይንሳዊና ቴክኖሎጂያዊ መሠረቶችን ያቀርባል።
መጽሐፍቱ ወጣቶችን ወደ STEM (ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ምህንድስናና ሂሳብ) ዘርፎች ለመሳብ፣ በኢትዮጵያ የምርምርና የፈጠራ ባህልን ለማጠናከር እንዲሁም ፖሊሲ አውጪዎች የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ እይታ እንዲኖራቸው በማገዝ ረገድ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopia #science #technology #innovation #spacescience #stem #booklaunch #getutemesgen #ጌጡተመስገን

2 months ago
በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ የሕይወት ተሞክሮ ላይ የሚያተኩር አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
#ethiopia | በአይናለም አዱኛ (ዶክተር) የተሰናዳውና በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወትና ተግዳሮቶች ላይ የሚያጠነጥነው "Walking Between Worlds: Letter to the Next Generation of the Ethiopian Diaspora" የተሰኘው መጽሐፍ በይፋ ተመርቋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከናወነው የገበያ ማቅረቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ታዋቂ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና በርካታ የክብር እንግዶች ታድመዋል።
በዕለቱም በምሁራንና በተሳታፊዎች አማካኝነት ስለ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ለአምስት አሥርት ዓመታት ገደማ (ከ38 ዓመታት በላይ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የኖሩት ደራሲዋ ዶክተር ዓይናለም አዱኛ፣ መጽሐፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ስለ አገራቸው በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውና የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በስደት ዓለም ያሳለፉትን የረጅም ጊዜ የሕይወት ተሞክሮና ገጠመኝ መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት ይህ መጽሐፍ ለሌሎች ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ዶክተር ዓይናለም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር ማከናወናቸውንና እንዲህ ዓይነቱ አበረታች ሥራ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ባለ 480 ገጽ ሆኖ ለንባብ መብቃቱ ታውቋል።
#diaspora #ethiopiandiaspora #booklaunch #aau #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
የመጽሐፍ ምረቃ ጥሪ
የደራሲ ማቴዎስ ገና (ዶ/ር) አዲስ መጽሐፍ ለምረቃ በቅቷል።
መጽሐፉ ለዘላቂ የፖለቲካ መረጋጋት እና ለማኅበራዊ ህይወት መሻሻል ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
የመጽሐፉ ርዕስ
"በረከት እና 'ርገማን በአንድ ብዕር ሲፈተሹ!!
የምረቃው መርሃ-ግብር
ቅዳሜ ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም.
ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡30
(በኢትዮጵያ አቆጣጠር)
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
ለዘላቂ የፖለቲካ መረጋጋት እና ለማህበራዊ ሕይወት መሻሻል!!
ሁላችሁም በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ እንድትታደሙ ጥሪ ቀርቧል።
ለምረቃው የቀረው 7 ቀናት ብቻ ነው!
#newbook #booklaunch #ethiopia #addisababa #የመጽሐፍምረቃ #ብሔራዊቴአትር #ማቴዎስጌታቸው #በረከትናርገማን

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ተመረቀ
*************************
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ የአረብኛው ትርጉም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በአቡ ዳቢ የተመረቀው ይህ መጽሐፍ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሁሉም አረብኛ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥትና ፍልስፍና እያራመደች የምትገኘውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የለውጥ እንቅስቃሴ ትልሞች በጥልቀት እንዲገነዘቡት ዓላማ ያደረገ ነው።
በመጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት” አረብኛ ትርጉም እውን መሆን በኢትዮጵያና በተቀረው የአረቡ ዓለም በኩል ያሉ የጋራ ጥቅሞችን አስተሳስሮ ለማስቀጠልና የጋራ ጥቅሞቻችንን ለማስጠቅ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሸክ ሻክቡት ቢን ናህያን አልናህያን፣ መጽሐፉ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረቡ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል የቆየውን ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገሪቱ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ታድመዋል።
በሰለሞን ኃይለኢየሱስ ከአቡዳቢ
#ethiopia #medemer #abiyahmed #uae #abudhabi #booklaunch #diplomacy

4 months ago
የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia |በኦቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላለፉት 48 ዓመታት የነበራቸውን የላቀ ልምድና የፈጠራ ሥራዎች የሚተርከው የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ተመርቋል።
በሀራ ኢቨንትስ አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኦቶሞቲቭ፣ ከኢነርጂ፣ ከአካዳሚክ እና ከመንግሥት የሥራ ዘርፎች የተወጣጡ ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህ መጽሐፍ ደራሲው በዘርፉ ያሳለፉትን ረጅም ዓመታት ጉዞ የሚዳስስ ሲሆን፣ በተለይም ስለ ወደፊቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ፣ ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ስለ ዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂዎች ጥልቅ ዕውቀትና ግንዛቤን የሚያካፍል መሆኑ ተገልጿል።
በምረቃው ወቅት በመስኩ ያሉ የኢንዱስትሪ መሪዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የታደሙ ሲሆን፣ ደራሲው ዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ ከመጽሐፉ ይዘት ባሻገር ካላቸው ሰፊ ልምድ በመነሳት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#theroadtodetroit #drashenafietsegaye #automotiveindustry #booklaunch #innovation #futuremobility #ethiopia #addisababa #technology #successstory

5 months ago
"መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም" (ኢሳ 34:16)
የብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አዲስ መጽሐፍ በሀዋሳ ይመረቃል
"የመሪነት ምስል"
#ethiopia | የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የሀዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ "የመሪነት ምስል" በሚል ርዕስ ያዘጋጁት አዲስ መጽሐፍ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
የምረቃው ዝርዝር መረጃ፦
መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ
ሀዋሳ በሚገኘው ሴንትራል ያማረች ሆቴል ትልቁ አዳራሽ
ታዳሚዎች፦ በዕለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እና የብፁዕነታቸው መንፈሳዊ ልጆች በተገኙበት ይከናወናል።
"መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም" (ኢሳ 34:16)
የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ፣ በሀዋሳና በአካባቢው የምትገኙ የጥበብ ወዳጆች ሁሉ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊና የዕውቀት ግብዣ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።
#getu #ethiopia #hawassa #orthodox #booklaunch #leadership #abuneyosef #sidama #church #የመሪነትምስል #አቡነዮሴፍ #መጽሐፍምረቃ #ሀዋሳ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ
የሳቪዮላው አሸናፊ ግርማ መጽሐፍ በድሬዳዋ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውና በልዩ የጨዋታ ስልቱ "ሳቪዮላ" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው የቀድሞው ድንቅ አማካይ አሸናፊ ግርማ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ከተማው ድሬዳዋ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአሸናፊ ግርማ እናት ወይዘሮ እህተ ወንድሙ ካሳዬ በምረቃው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በነገራችን ላይ
የአሸናፊ ግርማ አዋርድ በድሬ ተከናውኗል። በዚህ መሠረት
ለጥላሁን መገኒቾ (50,000 ብር)፣
ለፍቃዱ ተካ (25,000 ብር)፣
ለአህመድ ጁንድ (25,000 ብር) እና
ለፍስሐ በጋሻው (25,000 ብር) በክብር ተሸላሚ ሆነዋል።
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ በ350 ገጾች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ግርማ በምረቃው ላይ አስታውቋል።
አሸናፊ ግርማ ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሲሆን፣ በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ ሀገራችንን ወክሎ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል። በኢትዮጵያ ቡና ማሊያም ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መጽሐፍት ቤት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ በቀጣይም ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተገልጿል።
#getu #ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #diredawa #booklaunch #ethiopiancoffeefc #genenemekuria #libro #ethiopianlegend #አሸናፊግርማ #ሳቪዮላ #የኢትዮጵያእግርኳስ #ድሬዳዋ #መጽሐፍምርቃት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ያልተዘመሩላቸው የጥበብ ባለውለታዎች
የ1990ዎቹ የጥምር ሙያ ባለቤቶች ሲዘከሩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዓለም ውስጥ በዶክመንተሪ፣ በማስታወቂያ፣ በድራማ እና በፊልም ሥራዎች የበቁና የነቁ ትጉህ ሙያተኞች ነበሩ።
የ (Editing) ባለሙያዋ #ወይንሸት አዳሙ፣ ከአምስቱ ጉምቱ ባለሙያዎች ጋር በመሥራት ያገኘችውን ዕድልና ትምህርት በኩራት ታስታውሳለች። ሙያቸውን ብቻ ሳይሆን የሙያ ዲሲፕሊን፣ ትዕግሥት፣ ኃላፊነትና የተሟላ ሰው መሆንን የተማረችው ከእነርሱ እንደሆነ ትመሰክራለች።
የሙያ ባለውለታዎች ዝርዝር፦
ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ
ሰለሞን አበራ
ዘካርያስ ኃ/ማርያም (ነፍስ ይማር)
ፋንታሁን ኃ/ማርያም
ዘላለም ጌታሁን
የዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ልዩ የምስጋና ምሽት
እነነዚህን የሙያ ወንድሞች ዛሬ ለማስታወስ ምክንያት የሆነው፣ ትሁቱና ታታሪው ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተሰናዳ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ስለተዘጋጀለት ነው።
በዚሁ ዕለትም "ዝሃ" በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፉን አስመርቋል። ዳግማዊ ዝምተኛ ሰው ቢሆንም፣ ሥራዎቹ ግን ድምፅ አውጥተው ከፍ ብለው የሚደመጡ የጥበብ ውጤቶች ናቸው።
#ወይንሸት አዳሙ ለእነዚህ ባለሙያዎች ያላትን ክብርና ምስጋና ስትገልጽ፣ "ከቀዝቃዛው የራስ ዳሽን ተራራ እስከ ሐሩሩ የዳሎል በረሃ እየተጓዛችሁ የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የቱሪስት መስህቦችን በአማረ አቀራረብ አሳይታችሁናል። ስለማሕበራዊ ጉዳዮቻችን፣ ስለ አኗኗራችን፣ ስለባህሎቻችን ያስመለከታችሁንን ፈጽሞ አንዘነጋም" ብላለች።
ክብር በሕይወት ላሉት፣ ለተለየን ወንድማችንም ነፍስ ይማር።
#getu #ethiopia #art #documentary #theater #booklaunch #tribute #dagmawiamelework #ye1990ochubalemwyoch #ኪነጥበብ #ብሔራዊቴአትር #ዝሃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
5 months ago
📚 "ዮም"፦
በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆችና የወላጆቻቸው የጽናት መስታወት! ✨
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ሥር የሚኖሩ ልጆችን የማሳደግ ውጣ ውረድ፣ የወላጆች እሮሮ እና የጽናት ጉዞ እንደ መስታወት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል!
📖 ስለ መጽሐፉ፦
"ዮም" የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በአቶ ንሴብሆ ፍቅሬ እና በወ/ሮ ሳምራዊት ድንቁ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የራሳቸውን ልጅ በማሳደግ ሂደት ውስጥ ያለፉበትን ፈታኝ መንገድና መሰል ኢትዮጵያውያን ወላጆች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት ይዳስሳል።
🗓 የምረቃ ሥነ-ሥርዓት መርሃ-ግብር፦
ቀን፦ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ
ቦታ፦ ሀይሌ ግራንድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Haile Grand International Hotel)
🌟 የጥሪ መልዕክት፦
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ እርስዎም በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ በመገኘት በኦቲዝም ጥላ ሥር ላሉ ልጆችና ለሚደክሙ ወላጆቻቸው ድምፅ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
💰 ማሳሰቢያ፦
መጽሐፉ በዕለቱ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
"የኦቲዝም ልጆችን እና የወላጆቻቸውን የጽናት ጉዞ አብረን እንደግፍ!"
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ።
#ዮም #ኦቲዝም #autismawareness #ethiopia #booklaunch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📚 ደራሲ እና ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ በፍራንክፈርት! 🇩🇪🇪🇹
"ብዕር እና ባሩድ - የመጽሐፍ ምረቃ ዛሬ ይከናወናል
#ethiopia | በአሁኑ ሰዓት በሮም የሚገኘው ደራሲ አንዱአለም አራጌ፤ በቀጣይ ጉዞውን ወደ ጀርመን በማድረግ በጉጉት የሚጠበቀውን የመጽሐፍ ምረቃ በ ፍራንክፈርት (Frankfurt) ከተማ ሊያከናውን ቀጠሮ ይዟል።
ልዩ እንግዶች እና ተናጋሪዎች:
በዚህ ድምቀት ባለው መድረክ ላይ ታላላቅ የጥበብ እና የሀሳብ ሰዎች በክብር እንግድነት ተጋብዘው ንግግር ያደርጋሉ።
እነርሱም:-
🎙 አቶ ነጋሽ መሀመድ
🎙 ዶ/ር ይስማዕከ ወርቁ
🎙 አቶ ያሬድ ኃይለማርያም
መድረክ አጋፋሪ
መታሰቢያ ቀጸላ ናቸው።
ቀጠሮዎን ያስተካክሉ:
📅 ዛሬ ቅዳሜ፣ ፌብሩዋሪ 21 (Feb 21)
📍 ፍራንክፈርት፣ ጀርመን
በፍራንክፈርት እና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የጥበብ ወዳጆች፤ ይህንን ታላቅ ቀን እንዳያመልጥዎ ተጋብዛችኋል!
#andualemaragie #booklaunch #frankfurt #germany #ethiopia #literature #yismakeworku #negashmohammed #yaredhailemariyam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
በዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ የተጻፈው "ፍካሬ ትኩረት" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | በዲጂታል ዘመን የሰው ልጅ ትኩረትና ማንነት ላይ የሚያጠነጥነው የዶክተር አብዲበሺር ሰኢድ "ፍካሬ ትኩረት " የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አንጋፋው አርቲስት ሥዩም ተፈራ፣ የኢትዮጵያ ሠዓሊያን እና ቀራፂያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት አክሊሉ መንግሥቱን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ምሁራንና የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።
"ፍካሬ ትኩረት" የዲጂታል ዘመን ልማት፣ማንነት፣ እና ኃያልነት መበየኛ መጽሐፍ በአሁኑ ዘመን እንደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚቆጠር ሀብት መሆኑን መጽሐፉ ከዓለም አቀፍ እውነታ ጋር እያመሳከረ ይተነትናል።
መጽሐፉ በዲጂታል መሣሪያዎችና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት የሚሰረቀውን የሰው ልጅ አእምሯዊ ንቃት እንዴት መመለስ እንደሚቻል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያመላክታል።
✅ በዲጂታል ዘመን ውስጥ የማንነትን ጥያቄ በጥልቀት የሚዳስስ
✅ ለሀገራዊ ልማት አዳዲስ አቀራረቦችን የሚያቀርብ
✅ በትምህርት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያለውን ልምድ የሚያንጸባርቅ
✅ ለወጣቱ ትውልድ መሪ ሐሳብና ተግባራዊ መንገድ የሚያበረታታ መሆኑን ሒሳዊ ዳሰሳ ያቀረቡ ምሁራን እና ተወያዮች ገልጸዋል።
ዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ እና ጂኦግራፊ ትምህርት፤ የመጀመረያ ድግሪ የማስተርስ ድግሪ፤ በቱሪዝም እና ልማት ጥናት ከታላቁና አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በተጨማሪም ፣ ከሕንዱ ሀገር አቀፍ የኢንተርፔነርሺፕ ልማት ተቋም የድሕረ-ማስተርስ የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሬነር የአሰልጣኞች ስልጠና አግኝተዋል።
በተጨማሪም ከኬኒያው ሞይ ዩኒቨርሲቲ በድሕረ ማስተርስ የቱሪዝም አስተዳደር ስልጠና ፣ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ ምረቃ ዲፕሎማ በከፍተኛ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን ፣
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ፣የቱሪዝም፣ የእንተርፕሬነርሺፕ እና የድኅነት ቅነሳ ተመራማሪ ፣በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊና ሰብዓዊ ልማት ጥናቶች ኃላፊ ፣በታላቁ የአል-ነጃሺ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የቅርስና ቱሪዝም አመራር ጥናቶችን ሠርቷል።
በቱሪዝም፣ በኢንተርፕሬነርሺፕ፣ በምጣኔ ሀብት ዘርፎች የተለያዩ ጥናቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተመ
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገሮች ውስጥ የጥናት ምርምሮችንና የስልጠና ፕሮግራሞችን ያቀረበ ነው።
ከዚህ ቀደም ሲል የሴቶችን ትውልድ የማነጽ ሚና የሚዳስሰውንና በሦስት ቋንቋዎች(በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ) የታተመውን "Architects of The Ummah" የተሰኘ መጽሐፍ ከጓደኞቹ ጋር ለንባብ አብቅቷል።
በ7 ምዕራፎች ተቀንብቦ በ107 ገጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፣ በአሁኑ ወቅት በ320 ብር ለገበያ ቀርቧል። መጽሐፉ በተለይ በቴክኖሎጂ ተጽዕኖ ውስጥ ለሚገኘው ወጣት ትውልድና ለምሁራን ትልቅ ግንዛቤን እንደሚሰጥ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ከረመዳን ጾም በኃላ በሀረር የመጽሐፍ ምረቃና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።
#ethiopia #fikretukret #digitalage #identity #newbook #focus #mentalawareness #drabdibeshir #literature #addisababa #booklaunch #attentioneconomy

ሦስት የቤተክርስቲያን የዕውቀት መዛግብት በአንድ ላይ ተመረቁ
#ethiopia |የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕውቀት ምሶሶ የሆኑት፣ የ98 ዓመቱ ዕድሜ ባለጸጋ ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ እና መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ ያዘጋጇቸው ሦስት አዳዲስ መጽሐፍት ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በድምቀት ተመርቀዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ ለንባብ የበቁት መጽሐፍት በሁለቱ ሊቃውንት የተዘጋጁ ሲሆኑ፣ ይዘታቸውም የሚከተለው ነው፦
✅ ሦስቱ ሐዲሳት (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የቤተክርስቲያንን ጥልቅ ትርጓሜ ለትውልድ የሚያስተላልፍ።
✅ ሃይማኖተ አበው (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የሊቃውንቱን የዘመናት ዕውቀት የሰነቀ መሠረታዊ መጽሐፍ።
✅ የጸሎት መጽሐፍ Prayer Book - The Oriental Orthodox Church (በመጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ): በዓለም አቀፍ ቋንቋ የተዘጋጀ የጸሎት መጽሐፍ።
🔹ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ ከ50 በላይ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቁ አንጋፋ ሊቅ ናቸው። በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ልማት በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅነታቸው የሚታወቁት ሊቁ፤ በቅዳሴ፣ በቅኔና በሐዲሳት መጽሐፍት ትርጓሜ ያላቸውን ጥልቅ ዕውቀት ለትውልድ ለማሻገር በ98 ዓመት ዕድሜያቸውም በትጋት ላይ ይገኛሉ።
🔹መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ የቅኔና የሐዲሳት መምህር ሲሆኑ፣ እስካሁን 13 መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያንና ለሀገር አበርክተዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ መጽሐፍቱን የተመለከተ ሒሳዊ ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን፤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተክሌ ዝማሜ፣ የበገና መዝሙራት እና በልዩ የቅኔ ድግስ ታጅቦ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
#ethiopia #eotc (Ethiopian Orthodox Tewahedo Church) #booklaunch #ethiopianliterature #churchfathers #gheezliterature #religiousbooks

📚 ከ11 ዓመታት በፊት ዓለምን ያስደነገጠው የሊቢያው ግድያ... እሱ እንዴት ተረፈ?
#ethiopia | "ጓደኞቹ በISIS ሲያዙ እሱ እንዴት ቀረ? በእድል? በምክንያት? ወይስ በአጋጣሚ?"
ከ11 ዓመታት በፊት (ሚያዝያ 2007 ዓ.ም) አይኤስ (ISIS) በሊቢያ በረሃ በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸመው ዘግናኝ ግድያ መላው ዓለምን ያስቆጣና ልባችንን የሰበረ ክስተት ነበር።
ዛሬ፤ ከዚያ የሞት ቀጠና በመርፌ ቀዳዳ ሾልኮ የተረፈው ዳንኤል አብርሃ፤ ያንን አስፈሪ ጉዞ እና የጓደኞቹን ሰቆቃ "ሃያ ሦስት" በሚል መጽሐፍ አስፍሮታል።
ስለ መጽሐፉ:
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከአዲስ አበባ እስከ መተማ፣ ከሱዳን እስከ ሊቢያ በረሃ፣ እንዲሁም የባሕር ላይ ውጣ ውረድ በዝርዝር ተካቷል። ዳንኤል ጓደኞቹ ለሞት ሲነዱ እሱ እንዴት እንደተረፈ፣ የደላላዎቹን ሴራ እና የመጋዘኖቹን ጉስቁልና ቁልጭ አድርጎ አቅርቦታል።
ይህ በ262 ገጾች እና በ26 ምዕራፎች የተቀነበበ የጉዞ ማስታወሻ፤ በጋዜጠኛ ቢኒያም አቡራ አርታኢነት ተሰናድቶ ለንባብ በቅቷል።
ይህንን ታሪካዊ መጽሐፍ ዛሬ፣ አርብ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዋልያ መጻሕፍት (4 ኪሎ፣ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ኢክላስ ሕንጻ፣ 4ኛ ፎቅ) እየተመረቀ ነው።
የማይረሳ ታሪክ፣ የማይቀር ምርቃት!
#twentythree #booklaunch #danielabraha #libyasurvivor #truestory #waliabooks #ethiopia #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📚 ታሪክን የሚያረቅና ትውልድን የሚያነጽ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው! 🇪🇹
#ethiopia | "በአምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ የተፃፈው የከምባታ እና የሀዲያ ህዝቦች ታሪክ መጽሐፍ"
በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ረጅም ልምድ ባላቸው በአምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ የተዘጋጀውና የከምባታ እና ሀዲያ ህዝቦችን ታሪክ፣ አስተዳደር እና ባህላዊ ትስስር በጥልቀት የሚዳስሰው አዲስ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
የመጽሐፉ ልዩ ባህሪያት፡
✅ ታሪክን ወደኋላ ሄዶ በጥልቀት ይመረምራል፤ የተዛቡ ትርክቶችን ለማረቅ ፍቱን መድሃኒት ነው።
✅ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ምሁራን ጋር በመመካከር የተዘጋጀ የጥናት ውጤት ነው።
✅ የህዝቦችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ትስስር በማጉላት ለሀገር ግንባታ መንገድ ይጠቁማል።
የምርቃት መርሐ ግብር:
📅 ቀን: የፊታችን እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
clock ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ: ቦሌ አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ብሉ ስካይ ሆቴል
በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎች በሚታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ እርስዎም ተጋብዘዋል!
ታሪክን ከምንጩ እንጠጣ!
#ambassadortesfayehabiso #newbook #history #kembata #hadiya #ethiopianhistory #booklaunch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📚 "ሃያ ሦስት" - እውነተኛ የስደት ታሪክን የያዘ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው!
"ለሁሉም የመገናኛ ብዙኀን የተላለፈ ጥሪ"
#ethiopia | በዳንኤል አብርሃ የተዘጋጀውና የጸሐፊውን እውነተኛ የስደት ታሪክ እና ፈተና የሚተርከው "ሃያ ሶስት" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ፤ የፊታችን አርብ በድምቀት ይመረቃል።
በመሆኑም የመገናኛ ብዙኀን አካላት፣ የኪነ-ጥበብ ወዳጆች እና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በቦታው በመገኘት የዚህን ታሪክ ምስክር እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።
📅 ቀን: አርብ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም
አራት ኪሎ በሚገኘው ዋልያ መጽሐፍት አዳራሽ
clock ሰዓት: ከቀኑ 10:00 ጀምሮ
የስደት አለምን እውነታ እና የህይወት ትግልን በተለየ መንገድ የተሰነዳበትን ይህንን መጽሐፍ አብረን እንመርቅ!
📞 ለተጨማሪ መረጃ: 0928828448 / 0912675653
#twentythree #booklaunch #truestory #migration #ethiopianliterature #addisababa #events #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

"ጓደኞቹ በISIS ሲያዙ እሱ እንዴት ቀረ? በእድል? በምክንያት? ወይስ በአጋጣሚ?"
#ethiopia | ከአዲስ አበባ እስከ መተማ፣ ከሱዳን እስከ ሊቢያ በረሃ... የሞት እና የሽሽት ጉዞ!
"ሃያ ሦስት" የተሰኘው የዳንኤል አብርሃ አዲስ መጽሐፍ፤ በወቅቱ የነበረውን የሊቢያን ሰቆቃ፣ የደላላዎቹን ሴራ እና የመጋዘኖቹን ጉስቁልና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ
📖 ሰቆቃ እና ተአምር:
ጓደኞቹ ለሞት ሲነዱ፤ እሱ እንዴት ሊተርፍ ቻለ?
📖 የባሕር ላይ ውጣ ውረድ:
ሊቢያን አልፎ በጀልባ ለማቋረጥ ሲሞክር ምን ገጠመው?
📖 የአውሮፓ እውነት:
የከፈለው መስዋዕትነት የሚመጥን ካሳ በአውሮፓ አገኘ? ወይስ ሌላ ተጋድሎ?
ይህ መጽሐፍ ስለ እጣ-ፈንታ፣ ስለ ስኬት፣ ስለ ጽናት እና ተስፋ መቁረጥ አዲስ እይታን የሚሰጥ ነው።
የፊታችን አርብ ሁላችንም ተገኝተን እንመርቀው!
📅 ቀን: አርብ ጥር 22 ቀን 2018ዓ.ም
📍 ቦታ: ዋልያ መጻሕፍት (4 ኪሎ፣ ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ኢክላስ ሕንጻ፣ 4ኛ ፎቅ)
የማይረሳ ታሪክ፣ የማይቀር ምርቃት!
#twentythree #booklaunch #danielabraha #libya #survivalstory #ethiopianbooks #waliabooks #addisababa

"ወይኔ ብዙ ሰው ታድሟል፤ እግዚአብሔር ይስጣችሁ!"
- ብርቱካን ሚደቅሳ
#ethiopia | የቀድሞዋ የፖለቲካ ሰው እና የህግ ባለሙያ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ "መመለስ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸውን ትናንት ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም አስመረቁ።
በምርቃቱ ዕለት ፊታቸው በደስታ ሲያበራ የነበሩት ወይዘሮ ብርቱካን፤ አዳራሹን የሞላውን 821 ታዳሚ ሲመለከቱ በፈገግታ እና በመደነቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
292 ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ ለንባብ በመብቃቱ "እፎይ አልኩ" ሲሉ እፎይታቸውን ገልጸዋል።
የመጽሐፉ ይዘት እና አስተያየቶች፡-
በ34 አጫጭር እና ጣፋጭ ርዕሶች የተዋቀረው ይህ መጽሐፍ፤ በይኩኖአምላክ መዝገቡ እና በመሠረት አበጀ አርታኢነት የተዘጋጀ ነው።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኪነ-ጥበብ እና የስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች ስለ መጽሐፉ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡-
📚 ህይወት ተፈራ፣ መዓዛ ወርቁ፣ ቴዎድሮስ አጥላው እና ዳዊት ብርሃኑ መጽሐፉ የግድ መነበብ ያለበት መሆኑን በሙሉ አንደበታቸው መስክረዋል።
#birtukanmideksa #memeles #newbook #booklaunch #ethiopia

7 months ago
📚 ከሸገር – ሊቢያ – ዩኬ… 🌍
በሞት ⚰️ እና በህይወት 🌱 መካከል የተደረገ የህልውና ጉዞ!
✨ “ሃያ ሦስት” ✨
እንደ ወርቅ 🪙 በእሳት 🔥 የተፈተነ ወጣትነት!
⚔️ ከአይ-ኤስ-አይ-ኤስ (ISIS) እጅ ላለመግባት የተከፈለ መስዋዕትነት፣
🍞 ረሃብ፣ 💔 ክህደት፣ ⬇️ መውደቅ እና ⬆️ መነሳት…።
📖 የስደትን አስከፊነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ፣
❤️ ልብን ሰቅዞ የሚዘልቅ እውነተኛ የሕይወት ታሪክ
በሆነው “ሃያ ሦስት” መጽሐፍ ላይ ሰፍሯል።
🧭 ይህ መጽሐፍ ዝም ብሎ ታሪክ አይደለም፤
ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ያለፈ ወጣትነት፣
ነፍስን ለማቆየት የተደረገ የህይወት ውጣ ⬆️ ውረድ ⬇️ ነው።
🎓 የምረቃ ጥሪ! 🎉
ይህንን የፅናት 💪 እና የትግል ⚔️ ውጤት የሆነ መጽሐፍ
በጋራ 🤝 እንድንመረቅ ተጋብዛችኋል።
#️⃣ #hayasost #newbook 📘 #truestory 🧭 #migration 🌍 #survival 💪 #booklaunch 🎉 #addisababa 🏙️ #waliabookstore 📚
https://www.facebook.com/s...

📚 የዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው!
"ከእናት እቅፍ እስከ ልጅ ልጅ ምርኲዝ ትዝታዎቼ"
#ethiopia | የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር፣ የጄነራል ዊንጌት ብርቱ ተማሪ፣ በፈረንሳይ የህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና የ"ዕድገት በሕብረት" ዘመቻ ላይ አሻራቸውን ያኖሩት የ85 ዓመቱ አዛውርት ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው፤ የህይወት ታሪካቸው በደራሲ እና ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ አሰናኝነት ለመጽሐፍ በቅቷል።
የምረቃው ልዩ ድምቀቶች፡-
✨ የክብር መልዕክት: የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ክብርት ወይዘሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ ለባለታሪኩ ክብር የቪዲዮ መልዕክት ያስተላልፋሉ።
✨ ዶክመንተሪ: በሳቤህ ዞን እና በተወዳጅ ሚድያ የተዘጋጀ የ3 ሰዓት የድምፅ ዶክመንተሪ ይመረቃል።
✨ እንግዶች: ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ እና ሌሎች ታላላቅ ሰዎች ይገኛሉ፤ መጽሐፉን አቶ ደመላሽ አማረ ይዳስሱታል።
ይህንን በናይእግዚ ኅሩይ አርታኢነት እና በተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) አዘጋጅነት የተሰናዳውን የ350 ገጽ ታሪካዊ መጽሐፍ ለመታደም እርሶም ተጋብዘዋል።
📅 ቀን: ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም
⌚ ሰዓት: ከቀኑ 8:30 ጀምሮ
📍 ቦታ: ራስ መኮንን አዳራሽ (አ.አ.ዩ)
ኑ! የታላላቆችን ታሪክ እንስማ፤ እንማር!
#dryayehyirad #booklaunch #ethiopianhistory #biography #tewodajmedia #addisababa

Comments