5 months ago
ያልተዘመሩላቸው የጥበብ ባለውለታዎች
የ1990ዎቹ የጥምር ሙያ ባለቤቶች ሲዘከሩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዓለም ውስጥ በዶክመንተሪ፣ በማስታወቂያ፣ በድራማ እና በፊልም ሥራዎች የበቁና የነቁ ትጉህ ሙያተኞች ነበሩ።
የ (Editing) ባለሙያዋ #ወይንሸት አዳሙ፣ ከአምስቱ ጉምቱ ባለሙያዎች ጋር በመሥራት ያገኘችውን ዕድልና ትምህርት በኩራት ታስታውሳለች። ሙያቸውን ብቻ ሳይሆን የሙያ ዲሲፕሊን፣ ትዕግሥት፣ ኃላፊነትና የተሟላ ሰው መሆንን የተማረችው ከእነርሱ እንደሆነ ትመሰክራለች።
የሙያ ባለውለታዎች ዝርዝር፦
ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ
ሰለሞን አበራ
ዘካርያስ ኃ/ማርያም (ነፍስ ይማር)
ፋንታሁን ኃ/ማርያም
ዘላለም ጌታሁን
የዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ልዩ የምስጋና ምሽት
እነነዚህን የሙያ ወንድሞች ዛሬ ለማስታወስ ምክንያት የሆነው፣ ትሁቱና ታታሪው ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተሰናዳ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ስለተዘጋጀለት ነው።
በዚሁ ዕለትም "ዝሃ" በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፉን አስመርቋል። ዳግማዊ ዝምተኛ ሰው ቢሆንም፣ ሥራዎቹ ግን ድምፅ አውጥተው ከፍ ብለው የሚደመጡ የጥበብ ውጤቶች ናቸው።
#ወይንሸት አዳሙ ለእነዚህ ባለሙያዎች ያላትን ክብርና ምስጋና ስትገልጽ፣ "ከቀዝቃዛው የራስ ዳሽን ተራራ እስከ ሐሩሩ የዳሎል በረሃ እየተጓዛችሁ የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የቱሪስት መስህቦችን በአማረ አቀራረብ አሳይታችሁናል። ስለማሕበራዊ ጉዳዮቻችን፣ ስለ አኗኗራችን፣ ስለባህሎቻችን ያስመለከታችሁንን ፈጽሞ አንዘነጋም" ብላለች።
ክብር በሕይወት ላሉት፣ ለተለየን ወንድማችንም ነፍስ ይማር።
#getu #ethiopia #art #documentary #theater #booklaunch #tribute #dagmawiamelework #ye1990ochubalemwyoch #ኪነጥበብ #ብሔራዊቴአትር #ዝሃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

🎭 አንጋፋው የጥበብ ሰው ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ሊመሰገን ነው
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ላለፉት 40 ዓመታት በድርሰት፣ በዝግጅትና በትወና ዘርፍ የማይተካ አሻራውን ያሳረፈው አንጋፋው ባለሙያ ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ፣ የሙያ ባልደረቦቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት ታላቅ የምስጋና መርሃ-ግብር ሊደረግለት ነው።
የመርሐ-ግብሩ ዝርዝር መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የምስጋና ምሽቱ ቀጠሮ
ርዕስ፦ "ስሙ አተ"
ቀን፦ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ
ቦታ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር
አዘጋጅ፦ ሔኖክ የእታገኝ ልጅ
ስለ ተመጋስኙ ዳግማዊ አመለወርቅ (ዓመል)
ልደት፦
በ1960 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ አብነት (ጠጅ ሳር ሰፈር) ተወለደ።
የሙያ ዘመን፦
40 ዓመታትን በጥበብ ዓለም አሳልፏል።
ስራዎቹ፦
ከ500 በላይ ዶክመንተሪዎችንና ከ1,000 በላይ ማስታወቂያዎችንተ፤ጀ። በመስራት ድንቅ ብቃቱን አስመስክሯል።
"ዓመል" የተሰኘ የቴሌቪዥን ድራማ፣ "የቃቄ ውርዶዎት" እና "ከመጋረጃ ጀርባ" የተሰኙ ዝነኛ ቴአትሮችን ጨምሮ ከ40 በላይ በመድረክ ቴአትሮች ላይ ተሳትፏል።
ለ17 ዓመታት ያህል ስክሪፕት በመጻፍና በፊልም ስራዎች ላይም የራሱን አሻራ አኑሯል።
✨ በምሽቱ ምን ይጠበቃል?
በዚህ የክብር ምሽት ላይ ተመጋኙን የሚመጥኑ ልዩ ልዩ የጥበብ ዝግጅቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ዳግማዊ ለኢትዮጵያ ኪነ-ጥበብ ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ እውቅና ይሰጠዋል።
ዛሬም ድረስ ለሙያው ያለውን መሰጠት እያሳየ የሚገኘው ዳግማዊ፣ በብዙ ወጣት ባለሙያዎች ዘንድ እንደ አርአያ የሚጠቀስ ስብዕና ባለቤት ነው።
እንኳን ደስ አለህ ዳግማዊ!
ጥበብ ትክበር!
#ዳግማዊአመለወርቅ #ዓመል #ብሔራዊቴአትር #ኢትዮጵያ #ኪነጥበብ #ስሙአተ #artethiopia #dagmawiamelework #getu #temesgen #getuts emesgen #ጌጡ #ተመስገን #ጌጡተመስገን

Comments