4 months ago
ከበረሃማነት ወደ ምድር ገነት፦
የአርሶ አደር አብነት ዴላሞ አስደናቂ የስኬት ጉዞ!
#ethiopia | በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የሚገኘው ወጣት አርሶ አደር አብነት ዴላሞ፣ ፈተናን ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር የግብርናን ትርጉም የቀየረ ብርቱ ወጣት ነው።
በአንድ ወቅት የገነባው ግዙፍ የውሃ ገንዳ ፈርሶ ንብረቱ ቢወድም፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ተነስቶ ዛሬ ለሀገር ሞዴል የሚሆን ስራ ሰርቷል።
የአብነት ስኬት ምንጮች፦
ተቀናጀ ግብርና፦ በ10 ሄክታር መሬት ላይ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የሌማት ትሩፋት፣ የቡናና ቅመማ ቅመም ልማትን በማቀናጀት ውጤታማ ሆኗል።
አግሮ-ቱሪዝም (Agro-Tourism)፦
ግቢውን በውብ አበቦችና ዛፎች አስጊጦ፣ ለተመራማሪዎችና ለእንግዶች የሚያገለግሉ ዘመናዊ መኝታ ቤቶችን፣ የስብሰባ አዳራሽና ሎጅ መሰል አገልግሎቶችን በመገንባት የገጠር ኮሪደር ልማትን በተግባር አሳይቷል።
ለ10 ወጣቶች በቋሚነት እንዲሁም እስከ 80 ለሚደርሱ ወጣቶች በጊዜያዊነት የስራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከ400 በላይ አርሶ አደሮችን በቴክኖሎጂና በምክር ይደግፋል።
በ50 ሄክታር መሬት ላይ ትልቅ የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚደረግበት የተቀናጀ የግብርና ማዕከል ለመገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በግንቦት 2017 ዓ.ም የአብነትን የስራ ቦታ ጎብኝተው፣ እንዲህ ያሉ ወጣቶች የሀገርን የብልጽግና ጉዞ ዕውን እንደሚያደርጉ መመስከራቸው ይታወሳል።
አዘጋጅ፡- ሰለሞን ደምሰው
ፎቶ፡- ጌታቸው ምትኩ
#getu #abnetdelamo #modelfarmer #agriculture #ethiopia #agriculturaltransformation #ከማምረትበላይ #beyondproduction #agrotourism #ethiopiaagriculture #greenlegacy #successstory #jobcreation #kembata #ethiopia #አርሶአደር #ስኬት #ግብርና #አረንጓዴአሻራ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
📚 ታሪክን የሚያረቅና ትውልድን የሚያነጽ አዲስ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው! 🇪🇹
#ethiopia | "በአምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ የተፃፈው የከምባታ እና የሀዲያ ህዝቦች ታሪክ መጽሐፍ"
በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ ረጅም ልምድ ባላቸው በአምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ የተዘጋጀውና የከምባታ እና ሀዲያ ህዝቦችን ታሪክ፣ አስተዳደር እና ባህላዊ ትስስር በጥልቀት የሚዳስሰው አዲስ መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
የመጽሐፉ ልዩ ባህሪያት፡
✅ ታሪክን ወደኋላ ሄዶ በጥልቀት ይመረምራል፤ የተዛቡ ትርክቶችን ለማረቅ ፍቱን መድሃኒት ነው።
✅ ከሀገር ውስጥና ከውጭ ምሁራን ጋር በመመካከር የተዘጋጀ የጥናት ውጤት ነው።
✅ የህዝቦችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ታሪካዊ ትስስር በማጉላት ለሀገር ግንባታ መንገድ ይጠቁማል።
የምርቃት መርሐ ግብር:
📅 ቀን: የፊታችን እሁድ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም
clock ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
📍 ቦታ: ቦሌ አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ብሉ ስካይ ሆቴል
በዕለቱ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ታዋቂ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን እና የሀገር ሽማግሌዎች በሚታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ እርስዎም ተጋብዘዋል!
ታሪክን ከምንጩ እንጠጣ!
#ambassadortesfayehabiso #newbook #history #kembata #hadiya #ethiopianhistory #booklaunch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
🛑 "በጎነትን አናሰናክል!"
- በሽንሺቾ ከተማ ለአቅመ ደካሞች የተዘጋጀው የገና ድጋፍ አደጋ ላይ ወደቀ!
ከወ/ሮ ብርቱኳን ፀጋዬ (ቡዬ) መታሰቢያ ፋውንዴሽን የተሰጠ መግለጫ
የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ "ቡዬ ፋውንዴሽን" (Buye Memorial Foundation) ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከሚገኙ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር፤ በሽንሺቾ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የገና ስጦታ እና ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ እንደነበረ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ፋውንዴሽኑ፡-
✅ ከ100 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሰንጋ በሬ ገዝቷል።
✅ ከ250 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን ጥሪ አድርጓል።
✅ ለዝግጅቱ የሚሆኑ ሌሎች ወጪዎችን አውጥቶ ዝግጅቱን አጠናቋል።
ነገር ግን የሽንሺቾ ከተማ አስተዳደር ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን በጎ ተግባር "በአዳራሽ መሰብሰብ አትችሉም" በማለት ከልክሏል! የሚገርመው ደግሞ አስተባባሪ ኮሚቴዎቹ "ከፈለጋችሁ ስጋውን በፌስታል/ፕላስቲክ እያዞራችሁ ስጡ" የሚል ምላሽ መሰጠቱ ነው።
በመሆኑም ከፋውንዴሽኑ መስራቾች፣ ደጋፊዎች እና ከማህበረሰቡ ለከተማው አስተዳደር የሚከተሉትን ጥያቄዎች እናቀርባለን፡-
1️⃣ ክብር የት ሄደ?
ሰፊና ምቹ የሆነ የከተማው ምክር ቤት አዳራሽ እያለ፣ እነዚህን አረጋውያን እና አቅመ ደካሞች በክብር ጋብዞ ማስተናገድ ሲቻል፣ ለምን በፌስታል እንዲዞር ተፈለገ?
2️⃣ ሞራላዊ ተጠያቂነትስ?
በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀን የድጋፍ መርሐ-ግብር ማስተጓጎል የሞራል ተጠያቂነት የለውም ወይ?
3️⃣ ተስፋን ማጨለም አይሆንም ወይ?
ከ250 በላይ ወገኖች ተስፋ አድርገው እና በጉጉት እየጠበቁ፣ ይህን መርሐ ግብር ማሰናከል ምን የሚሉት አሰራር ነው?
4️⃣ ጥሪ ለሚመለከታቸው አካላት!
የከምባታ ዞን ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሺንሽቾ ከተማ ማህበራዊ እና ዋስትና እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት፤ ይህን በጎ ስራ በማስተጓጎል እና ቦታ በመከልከል ዙሪያ ያለውን ጉዳይ በአስቸኳይ አይተው ማብራሪያ እንዲሰጡንና ለተቸገሩ ወገኖቻችን ፍትህ እንዲሰጥ እንጠይቃለን!
በጎ ስራን እናበረታታ ወይስ እናዳክም?
BUYE MEMORIAL FOUNDATION
(ወ/ሮ ብርቱኳን ፀጋዬ (ቡዬ) መታሰቢያ ፋውንዴሽን) #shinshicho #justice #charity #kembata #ethiopia #buyefoundation #genna -KWWMN የልማት ቲቢ
ታሕሣሥ 27፣ 2018
***
ይህንን ዘገባ ያጠናቀርነው የ"ቡዬ መታሰቢያ ፋውንዴሽን" (Buye Memorial Foundation) ያወጣውን መግለጫ መነሻ በማድረግ ነው። ጉዳዩን በተመለከተ ሚዛናዊ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን አካላት ለማነጋገር ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም ለጊዜው ልናገኛቸው አልቻልንም።
ሆኖም፣ የሚሰጡት ምላሽ ወይም ማብራሪያ ካለ ለማስተናገድ እና ለህዝብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን።

11 months ago
የአተካና ምሽት በዱራሜ
#ethiopia | በከምባታ የዘመን መለወጫ ‘‘መሳላ’’ በዓል ዋዜማ የሚከበረው የአተካና ስነ-ስርዓት በማህበረሰቡ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የመሳላ በዓል ሌላኛው ድምቀት ነው፡፡
በአካባቢው ባህል መሰረት ከእርድ ቀን አስቀድሞ የሚከበረው የእናቶች መሳላ በመባል የሚታወቀው የአተካና እራት የመብላት ስነ-ስርዓት በዱራሜ ከተማ በኡቱቢያ ወጋ አደባባይ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።
ይህ የአተካና ስነስርዓት የከምባታ እናቶች ለወራት ተጨንቀውና ተጠበው የሚያዘጋጁት የመሳላ በዓል አከባበር አንዱ አካል ነው።
የአዲስ ዓመት መግባትን ማብሰሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ይህ ስነ-ስርዓት፤ በቤተሰብ አባላትና ዘመድ ጎረቤት በጉጉት የሚጠበቅ ነው።
ከአተካና እራት ስነ-ስርዓት ቁጥሎ በጉጉት የሚጠበቀው የመሳላ ወይም የከምባታ ዘመን መለወጫ በዓል በነገው ዕለት ይከበራል።
በሲሳይ ደበበ
#ebc #ethiopia #kembata #መሳላ

Sponsored by
Surafel
Comments