Logo
Getu Temesgen
📚 የዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው የህይወት ታሪክ መጽሐፍ ሊመረቅ ነው!

​"ከእናት እቅፍ እስከ ልጅ ልጅ ምርኲዝ ትዝታዎቼ"
#ethiopia | ​የቀድሞ የትምህርት ሚኒስትር፣ የጄነራል ዊንጌት ብርቱ ተማሪ፣ በፈረንሳይ የህክምና ትምህርታቸውን የተከታተሉ እና የ"ዕድገት በሕብረት" ዘመቻ ላይ አሻራቸውን ያኖሩት የ85 ዓመቱ አዛውርት ዶ/ር ያየህይራድ ቅጣው፤ የህይወት ታሪካቸው በደራሲ እና ጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ አሰናኝነት ለመጽሐፍ በቅቷል።

​የምረቃው ልዩ ድምቀቶች፡-
✨ የክብር መልዕክት: የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ክብርት ወይዘሮ ሣህለወርቅ ዘውዴ ለባለታሪኩ ክብር የቪዲዮ መልዕክት ያስተላልፋሉ።

✨ ዶክመንተሪ: በሳቤህ ዞን እና በተወዳጅ ሚድያ የተዘጋጀ የ3 ሰዓት የድምፅ ዶክመንተሪ ይመረቃል።

✨ እንግዶች: ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ እና ሌሎች ታላላቅ ሰዎች ይገኛሉ፤ መጽሐፉን አቶ ደመላሽ አማረ ይዳስሱታል።

​ይህንን በናይእግዚ ኅሩይ አርታኢነት እና በተወዳጅ ሚድያ (ዕዝራ እጅጉ) አዘጋጅነት የተሰናዳውን የ350 ገጽ ታሪካዊ መጽሐፍ ለመታደም እርሶም ተጋብዘዋል።

​📅 ቀን: ቅዳሜ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም
⌚ ሰዓት: ከቀኑ 8:30 ጀምሮ
📍 ቦታ: ራስ መኮንን አዳራሽ (አ.አ.ዩ)

​ኑ! የታላላቆችን ታሪክ እንስማ፤ እንማር!

​#dryayehyirad #booklaunch #ethiopianhistory #biography #tewodajmedia #addisababa

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.