15 days ago
በድሬደዋ ከተማ የትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክት ከፊል ርክክብ ተከናወነ
#ethiopia | የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ቤቶች ምገባ ፕሮግራም ያጋጥም የነበረውን የአቅርቦት መዘግየት ለመቅረፍ የሚያስችለውን የማዕከላዊ ማብሰያ ኩሽና ከፊል ግንባታ በይፋ ተረክቧል።
“ዘላቂ የትምህርት ቤት ምግብ በጀት ለተሻለ ትምህርት” በሚል መሪ ቃል የተገነባው ፕሮጀክቱን ያስረከበው የኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ምገባ ተነሳሽነት ሲሆን፣ በድሬዳዋ ከተማ ትምህርት ቢሮውና የኢትዮጵያ ትምህርት ቤት ምገባ ተነሳሽነት መካከል በተጠናቀቁና በቀሪ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል።
የምገባ ኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተመስገን፣ በከፊል በተረከቡት ፕሮጀክት ኤጀንሲው በሰባት ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን መመገብ መጀመሩን ገልጸዋል።
የፕሮጀክቱ አካል የሆነው የእርሻ ልማትም በርክክቡ የተካተተ ሲሆን፣ ለእርሻው የውኃና የኃይል አቅርቦት በአፋጣኝ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠቁሟል።
የድሬዳዋ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቡበከር አብዶሽ፣ ፕሮግራሙ በምግብ እጥረት የሚከሰተውን የትምህርት ማቋረጥ በመቀነስ ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን ለማስቀጠልም ከፕሮጀክቱ ገቢ በተጨማሪ ከአስተዳደሩና ከህብረተሰቡ ሀብት የማሰባሰብ ሥራ እንደሚከናወን አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ባለድርሻ አካላት በመልካ ጀብዱ ትምህርት ቤት በተግባር የተጀመረውን የተማሪዎች ምገባ ሂደት ተመልክተዋል።
#diredawa #schoolfeeding #ethiopia #education #schoolmeals #educationforall #esmi #unicef #sustainabledevelopment

2 months ago
3 months ago
በድሬዳዋ ከተማ 548 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ሊወጣ ነው
#ethiopia | የድሬዳዋ አስተዳደር በኢንዱስትሪ መንደር ሳይት ሶስት የገነባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች የባለቤትነት ዕጣ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ እንደሚያወጣ አስታወቀ።
የድሬዳዋ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኢማጅ አብደላ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጹት፣ በዕለቱ ለዕጣ የሚቀርቡት በአጠቃላይ 548 ቤቶች ሲሆኑ፣ መስፈርቱን አሟልተው የቆጠቡ ከ7,000 በላይ ቆጣቢዎች በሂደቱ ይሳተፋሉ ብለዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የዕጣ አወጣጡን ሂደት ሙሉ በሙሉ ግልጽና ተአማኒ ለማድረግ፣ ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አፕሊኬሽን እንደሚጠቀም አስታውቋል።
ዕጣው አወጣጥ ሂደትም ለሴቶች 30 በመቶ፣ ለመንግስት ሠራተኞች 20 በመቶ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች 2 በመቶ ቅድሚያ የሚሰጥበት አሠራር መዘርጋቱ ተጠቁሟል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በ2019 ዓ.ም. አራት ነጥብ አምስት ሄክታር መሬት ላይ "ሳይት አራት" የተሰኘ ዘመናዊ የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አቶ ኢማጅ አክለው ገልጸዋል።
#ድሬዳዋ #የጋራመኖሪያቤት #የቤትዕጣ #ኢትዮጵያ #ልማት #diredawa #ethiopia #housingdevelopment

4 months ago
የኢትዮጵያና የማላዊ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታቸውን በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀቁ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ከማላዊ አቻው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ግጥሚያ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል።
በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ በተጀመረው በዚህ ጨዋታ ለዋልያዎቹ ብቸኛዋን ግብ ቢኒያም በላይ ከመረብ ማገናኘት የቻለ ሲሆን የማላዊን የአቻነት ግብ ደግሞ አዴፖጁ ባባቱንዴ አስቆጥሯል።
በዋና አሰልጣኝ ዮሀንስ ሳህሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባሳለፍነው ቅዳሜ በተመሳሳይ በድሬዳዋ ስታዲየም ከማላዊ ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።
#walyas #football #diredawa #ethiopianfootball #malawi #friendlymatch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
4 months ago
የፍርድ ቤት መር አስማሚነት
ከባህላዊ እና ሃይማኖታዊ የሽምግልና ሥርዓት
#ethiopia | የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተግባራዊ እያደረገ ያለውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት አሰራር ይበልጥ ለማጎልበት እና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል የምክክር መድረክ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ተካሄደ።
በውይይቱ ላይ የድሬዳዋ ከተማ የባህል ሽማግሌዎች፣ የአባ ገዳዎች፣ የኡጋዞች እና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በፍርድ ቤት መር አስማሚነት ሥርዓት ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የፍትህ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በተለይም ድሬዳዋ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦችና ሃይማኖቶች መኖሪያ እንደመሆኗ፣ ዘመናዊውን የፍርድ ቤት መር አስማሚነት ከባህላዊ ሽምግልና እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር አቀናጅቶ መሄድ አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።
በምክክር መድረኩ ላይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፉአድ ኪያር እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ተገኝተዋል።
በቀጣይ ፍርድ ቤቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም፣ ለዘርፉ አዲስ ለሚቀላቀሉ አስማሚዎች የህግ እና የአሰራር ሥልጠና በመስጠት ወደ ተግባራዊ ትግበራ እንደሚገባ ታውቋል።
#ፍርድቤት #ፍትህ #ሽምግልና #ባህል #ሃይማኖት #ድሬዳዋ #ኢትዮጵያ #legal #mediation #culture #religion #diredawa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
የመኖሪያ ቤት እጥረትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቅረፍ ይሠራል፦ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
**************
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ላለፉት ቀናት በድሬዳዋ ባካሄዳቸው የተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች የ50ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓሉን አጠቃልሏል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር፣ ኮርፖሬሽኑ የወርቅ እዮቤልዩውን ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በድሬዳዋ በተለያዩ መርሀ ግብሮች በማክበሩ አመስግነዋል።
ድሬዳዋ ከለውጡ ወዲህ ሰላምና አንድነቷን አስጠብቃ በማስቀጠል የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ፋይዳ ያላቸው የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኗን ገልጸዋል።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዚህ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ አንስተዋል።
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኃይለብርሃን ዜና፣ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 8 ዓመታት ዕድሜና ልምዱን የሚመጥኑ ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ገቢውን ከ30 እጥፍ በላይ አሳድጓል ብለዋል።
በቀጣይም አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የመኖሪያ ቤት እጥረትን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቅረፍ ይሠራል ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወጠነውን 1.5 ሚሊዮን ቤቶች የመገንባት ዕቅድ በውጤታማነት ለመተግበር በትኩረት እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የኮርፖራሽኑ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ እውነቱ ወርቅነህ፣ ኮርፖሬሽኑ ካጋጠመው ውድቀት በመነሳት ባለፉት 8 ዓመታት ባከናወናቸው የለውጥ ሥራዎች የቤቶች ግንባታ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል መሆን ችሏል ብለዋል።
ኮርፖሬሽኑ የወርቅ እዮቤልዩ በዓሉን ከአዲስ አበባ በመቀጠል ከግንቦት 10 እስከ 17 በድሬዳዋ በተለያዩ መርሐ ግብሮች ሲያከብር ቆይቶ ነው በዛሬው ዕለት አጠቃልሏል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#ethiopia #housingcorporation #50years #goldenjubilee #diredawa #ebc

ፌደራል ፖሊስ ምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በድሬዳዋ ከተማ ተመረቀ
*************
በምስራቅ ኢትዮጵያ ያለውን የሰላምና ደህንነት ስራ ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዘው የፌደራል ፖሊስ ምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
ለተለያዩ የፀጥታና የደህንነት ሥራ እንቅስቃሴዎች ምቹ ተደርጎ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ይህ ማዕከል የፖሊስ አባላት ማዘዣ ጣቢያዎችን፣ ዶርሚተሪዎችን፣ ዘመናዊ ቢሮዎችን፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን እና የጤና ማዕከልን ያካተተ ነው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ድሬዳዋን ጨምሮ አካባቢው የታላቋ ኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚስተናገድበት ስትራቴጂካዊ ቀጣና መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም የማዕከሉ በዚህ ሥፍራ መገንባት አሸባሪዎችን እና ፀረ-ሰላም ኃይሎችን ቀድሞ በመቆጣጠር ሰላምና ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ እንዲሁም በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ነጻ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ጠቅላይ አዛዡ አክለውም፣ ማዕከሉ የወንጀል ምርመራ ኃይልን ለማጠናከርና የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የፌደራል ፖሊስ በሁሉም የሀገራችን ማዕዘናት ላይ መሰል ዘመናዊ ማዕከሎችን በመገንባት ለሰላም መረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አጽንኦትም ሰጥተዋል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር በበኩላቸው፣ የሀገር ሰላምና ደህንነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ዜጎች በነፃነት ወጥተው እንዲገቡ የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ የሌሎች የፀጥታ አካላት ሚና ከፍተኛ እና የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ከንቲባ ከድር ጁሀር አዲስ የተገነባው የፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ከድሬዳዋ ከተማ ባለፈ አጠቃላይ ለምስራቁ የሀገራችን ክፍል ደህንነት መረጋገጥና ለህዝቡ አስተማማኝ ከለላ ለመስጠት ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ እንደሆነ ገልጸዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ
#diredawa #federalpolice #peaceandsecurity #ethiopia #ethiopianbroadcastingcorporation

6 months ago
ከምሥራቋ ፈርጥ ድሬዳዋ
የበዓል መልዕክት ከከንቲባዋ ጋር
#ethiopia | "የበረሀዋ ንግሥት" ተብላ በምትጠራውና የፍቅር ከተማ በሆነችው ድሬዳዋ፣ ከከተማዋ ከንቲባ ጋር ከአቶ ከድር ጁሃር ቆንጆና ፍሬያማ ጊዜን አሳልፈናል።
ድሬዳዋ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦችና እምነቶች መገናኛ እንደመሆኗ፣ የበዓል ድባቧም የተለየና ማራኪ ነው። ይህ ቆይታችንም ለከተማዋ ያለንን ክብርና ፍቅር የገለጽንበት ነበር።
መልካም የፋሲካ በዓል!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከድሬዳዋ ምድር የተላከ የሠላም፣ የፍቅርና የደስታ የበዓል መልዕክት ይድረሳችሁ።
ድሬ የፍቅር ከተማ፣ በዓሉ የደስታ ይሁንላችሁ!
#getu #diredawa #ethiopia #mayorofdiredawa #easterethiopia #travelethiopia #cityoflove #holidayvibes #easter2026 #ድሬዳዋ #ፋሲካ #በዓል #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

📌 በድሬዳዋ (በትንሿ ኢትዮጵያ)
#ethiopia | የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (CAF) ቀደም ብሎ ጨዋታው በዝግ ስቴዲየም እንዲካሄድ አስተላልፎት የነበረውን ውሳኔ በማሻሻል፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የሚያደርገውን የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ደጋፊዎች እንዲታደሙት ፈቅዷል።
ዋና ዋና ነጥቦች፡
እስከ 10,000 የሚደርሱ የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊዎች ስቴዲየም በመገኘት ቡድናቸውን ማበረታታት ይችላሉ።
መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.በንግሥት ሳባ (ድሬዳዋ) ስቴዲየም።
መላው የድሬዳዋ እና የአካባቢው ነዋሪ ስቴዲየም በመገኘት ለሀገሩ ያለውን ፍቅር የሚገልጽበት አጋጣሚ ተፈጥሯል።የደጋፊው ድምፅ ለዋልያዎቹ ትልቅ ጉልበት እንደሚሆን ይታመናል።
ድል ለዋልያዎቹ ፤ ድል ለኢትዮጵያ ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #walias #caf #diredawa #afcon2027 #ethiopianfootball #ድሬዳዋ #ኢትዮጵያ
Sponsored by
Surafel
7 months ago
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ
የሳቪዮላው አሸናፊ ግርማ መጽሐፍ በድሬዳዋ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውና በልዩ የጨዋታ ስልቱ "ሳቪዮላ" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው የቀድሞው ድንቅ አማካይ አሸናፊ ግርማ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ከተማው ድሬዳዋ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአሸናፊ ግርማ እናት ወይዘሮ እህተ ወንድሙ ካሳዬ በምረቃው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በነገራችን ላይ
የአሸናፊ ግርማ አዋርድ በድሬ ተከናውኗል። በዚህ መሠረት
ለጥላሁን መገኒቾ (50,000 ብር)፣
ለፍቃዱ ተካ (25,000 ብር)፣
ለአህመድ ጁንድ (25,000 ብር) እና
ለፍስሐ በጋሻው (25,000 ብር) በክብር ተሸላሚ ሆነዋል።
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ በ350 ገጾች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ግርማ በምረቃው ላይ አስታውቋል።
አሸናፊ ግርማ ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሲሆን፣ በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ ሀገራችንን ወክሎ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል። በኢትዮጵያ ቡና ማሊያም ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መጽሐፍት ቤት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ በቀጣይም ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተገልጿል።
#getu #ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #diredawa #booklaunch #ethiopiancoffeefc #genenemekuria #libro #ethiopianlegend #አሸናፊግርማ #ሳቪዮላ #የኢትዮጵያእግርኳስ #ድሬዳዋ #መጽሐፍምርቃት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

8 months ago
በድሬደዋ ለታዳጊዎችና ለቀድሞ ኮከቦች የተደረገ ድንቅ የስፖርት ድጋፍ! 🏟✨
#ethiopia | የእግር ኳስ መፍለቂያ በሆነችው ድሬደዋ ከተማ ለሚገኙ ታዳጊዎችና ለቀድሞ ታዋቂ ተጫዋቾች የሚያበረታታ የትጥቅ ድጋፍ ተደረገ።
የድጋፉ ዝርዝር፦
🏃♂️ ለታዳጊዎች፦
በከተማዋ በዘጠኙም ቀበሌዎች ለሚገኙ ከ13 ዓመት በታች (U-13) ታዳጊ እግር ኳስ ተጫዋቾች የተደረገው ይህ ድጋፍ፣ ነገ ለሀገር የሚተርፉ ኮከቦችን ለማፍራት ትልቅ እገዛ ያደርጋል።
የድጋፉ አስተባባሪዎች፦
ይህ በጎ ተግባር በከተማዋ ስፖርትን ለማሳደግ በሚተጋው በአሸናፊ ግርማ እና በዋናው (Wana) የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት ትብብር የተከናወነ ነው።
እንዲህ ያሉ አገር በቀል ድርጅቶችና ስፖርተኞች ለታዳጊዎች የሚያደርጉት ድጋፍ ሊበረታታ ይገባል።
ድሬደዋ ዳግም ለሀገር የሚተርፉ ስፖርተኞችን የምታፈራበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!
#diredawa #ethiopianfootball #wanasport #grassrootsfootball #ashenafigirma #sportsupport #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🎷 በአንጋፋው አሊ ቢራ ስም የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሊቋቋም ነው! 🎵
#ethiopia | "የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ60 ዓመታት የጥበብ ንጉስ ታሪካዊ ክብር ሊሰጥ ነው"
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፤ ከ260 በላይ የሙዚቃ ሥራዎችን ለኢትዮጵያ እና ለዓለም ያበረከተውን አንጋፋ ድምፃዊ፣ የዜማ ደራሲ እና አቀናባሪ ዶ/ር አሊ ቢራን ለመዘከር በስሙ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ለማቋቋም ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የሙዚቃ ትምህርት ቤቱ ዓላማ፡-
1️⃣ የድሬዳዋን የኪነ-ጥበብ ጸጋ መጠቀም፣
2️⃣ የአሊ ቢራን ዘመን አይሽሬ ውርስ ለትውልድ ማሸጋገር፣
3️⃣ የተለያዩ የሙዚቃ ጥበቦችን እና የአካባቢውን ባህል መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችን መስጠት ነው።
አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያከናወነ ሲሆን፤ የቦርዱ ውሳኔ በትምህርት ሚኒስቴር ሲጸድቅ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገልጿል።
ለአሊ ቢራ ይህ ይነስበታል እንጂ አይበዛበትም! 👏
አዲስ ዘመን (በነፃነት አለሙ)
#alibirra #diredawauniversity #musicschool #ethiopianmusic #legend #art #diredawa

9 months ago
የፍቅር ድልድይ ከቤልጂየም ወደ ድሬዳዋ!
❤️
#ethiopia | የኢትዮ-ቤልጂየም ማኅበር ለህጻናት ማቆያ ማዕከል የ500 ሺህ ብር የገና ስጦታ አበረከተ
የኢትዮ-ቤልጂየም ማኅበር (Ethio-Belgium Association) ለድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህጻናት ማቆያ ማዕከል ግምታቸው 500 ሺህ ብር የሚያወጣ የገና በዓል ስጦታ አበርክቷል።
ስጦታውን የተረከቡት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ "የሚሰጡ እጆች ሁልጊዜም የተባረኩ ናቸው" በማለት፣ ድጋፉ በገና ዋዜማ መከናወኑ ወላጅና አሳዳጊ ለሌላቸው ህጻናት በዓሉን ልዩ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል።
🎁 የተበረከቱት ቁሳቁሶች፦
✅ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣
✅ የኤሌክትሪክ ምድጃ (ኦቭን)፣
✅ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣
✅ ዳይፐር እና አልባሳት ናቸው።
"ሁለት አገሮችን በልብ የሚያገናኝ ድልድይ"
የኢትዮ-ቤልጂየም ማኀበር መሥራችና ዳይሬክተር፣ የድሬዳዋ ተወላጅ የሆነችው ሞዴል ፈቲያ መሐመድ፤ ስለ ድጋፉ ፋይዳ እና ስለ ከተማዋ ጥልቅ መልዕክት አስተላልፋለች፡-
"ዛሬ ይህን ድጋፍ በድሬዳዋ ከተማ ማቅረባችን ለእኛ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው። ድሬዳዋ የልዩነት እና የአብሮነት ከተማ ናት፤ ዛሬ ደግሞ የፍቅር እና የተስፋ መድረክ ሆናለች። ...
... ይህ ድጋፍ ለልጆቻችን ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ እና በቤልጂየም መካከል ያለውን የሰውነት፣ የፍቅር እና የእርስ በእርስ መተሳሰብ የሚያጠናክር ድልድይ ነው። ማኅበራችን ሁለት አገሮችን በርቀት ሳይሆን በልብ የሚያገናኝ ድርጅት ነው። ዛሬ በድሬዳዋ ያየነው ፍቅር፣ በቤልጂየም የተጀመረ ነው፤ ይህም ፍቅር ድንበር እንደሌለው ያሳያል።"
ሞዴል ፈቲያ አያይዛም "ልብስ ማልበስ" ስላለው ትልቅ ትርጉም እንዲህ ብላለች፡-
"ልጅን ልብስ ማልበስ ማለት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ለእነርሱ የሚተላለፈው መልዕክት ታላቅ ነው። 'ታይተሃል፣ ተወዳጅ ነህ፣ ክብር አለህ!' የሚል ትርጉም ይይዛል። ልጆች ሲለብሱ ልባቸውም ይሞላል፤ ዓይናቸውም ተስፋ ያበራል። እኛ ልጆቻችንን ስንንከባከብ፣ የነገ ኢትዮጵያን እየተንከባከብን ነው።"
መልካም የገና በዓል! 🎄
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#diredawa #charity #ethiobelgiumassociation #lovehasnoborders #bridgeoflove #genna #ethiopia #hope

1 year ago
ፎቶ ተከስተብርሃን
አቶ ተከስተብርሃን ያዘው ይባላሉ። የጉርሱም ከተማ የመጀመሪያው ፎቶግራፈር ናቸው። "ፎቶ ተከስተ ብርሃን" በሚል መጠሪያ በመላው ጉርሱም ይታወቃሉ።ፎቶ ተከስተን የማያቅ የጉርሱም ሰው የለም ማለት ይቻላል ። ስማቸው ከጉርሱም ከተማ ጋር በተደጋጋሚ ይነሳል።
አቶ ተከሰተብርሃን ትውልዳቸው ግራዋ ከተማ ነው። በልጅነታቸው ጉርሱም አክስታቸው ጋር ይመላለሱ እንደነበር ይናገራሉ።ጉጋዴን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ላይ ሰርተዋል ።
ከ1967 ዓም ጀምሮ ፎቶግራፍ ማንሳት የጀመሩ ሲሆን ለረጅም አመታት በዚህ ሞያ አገልግለዋል። በ1969 ዓም ጉርሱም ከተማ ጠቅልለው እንደገቡ የሚናገሩት አቶ ተከሰተ እስከ 1983 ማለትም ለአስራ አራት አመታት ያህል በዚህ ሞያ ጉርሱም ከተማ ላይ ሰርተዋል ።
ስለ ካሜራቸው ጠይቀናቸው ... እንዲህ አሉን ...
" ጉርሱም ከተማ ባዶ እጄን ነው የመጣሁት ካሜራ አልነበረኝም, በግዜ ውድ የነበረ ሰአት ነበረኝ እርሱ ሸጬ ካሜራ ገዛው ፎቶ ማንሳት ጀመርኩ “ አሉን
ከፎቶግራፍ ስራ ቀጥሎ ሌሎች ስራዎችን ይሰሩ እንደነበር አጫውተውናል።
አቶ ተከስተ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው። ዛሬም ኑራቸው ጉርሱም ከተማ ነው። እንደዚህ ቀደሙ ተሯሩጠው መስራት የሚችሉ አይመስሉም። የመጨረሻ ልጃቸው ማየት የተሳናት ነች።
ወደ ቤታቸው ጓራ ብለን ባለቤታቸውን እና ሴት ልጃቸውን ጠየቅ አደረግን ከመንገድም የመጨረሻ ወንድ ልጃቸውን አስተዋወቁን።
ድጋፍ እንደሚፈልጉ ለመረዳት ጊዜ አልወሰደብንም እርሷቸውም ትንሽ ጠቋም አደረጉን። እኛም እንደተስፈኛ ፎቶግራፈርነታችን በግሩፕችን ስም ( Bored Cellphone ) የተወሰነ ብር ሰብሰብ አድርገን በሞያቸው ለሰጡት አገልግሎት አመስግነን ቀበል አደረግናቸው።
መረቁን...
"ለካስ ሰው አለኝ ... ሀገራችሁን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ። ለወግ ለማዕረግ ያብቃችሁ። ተባረኩ"
እንቧ ባይናቸው ግጥም ብሎ ነበር። ተመሰጋግን ስልክ ተቀብለን እንደምደውል ቃል ገብተን ተለያየን።
የጉርሱም ናፍቆት ይቀጥላል ...
Via: Mastewal Eyasu
.#kundudo #diredawa #bcaatour #tecno #camon40 #tecnoai #7yearsofboredcellphone

Comments