3 months ago
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ
የሳቪዮላው አሸናፊ ግርማ መጽሐፍ በድሬዳዋ ተመረቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ያሳረፈውና በልዩ የጨዋታ ስልቱ "ሳቪዮላ" የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው የቀድሞው ድንቅ አማካይ አሸናፊ ግርማ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ፣ ዛሬ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በትውልድ ከተማው ድሬዳዋ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአሸናፊ ግርማ እናት ወይዘሮ እህተ ወንድሙ ካሳዬ በምረቃው ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።
በነገራችን ላይ
የአሸናፊ ግርማ አዋርድ በድሬ ተከናውኗል። በዚህ መሠረት
ለጥላሁን መገኒቾ (50,000 ብር)፣
ለፍቃዱ ተካ (25,000 ብር)፣
ለአህመድ ጁንድ (25,000 ብር) እና
ለፍስሐ በጋሻው (25,000 ብር) በክብር ተሸላሚ ሆነዋል።
ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና + ካናዳ በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ በ350 ገጾች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ግርማ በምረቃው ላይ አስታውቋል።
አሸናፊ ግርማ ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ሲሆን፣ በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ ላይ ሀገራችንን ወክሎ አስደናቂ ብቃት አሳይቷል። በኢትዮጵያ ቡና ማሊያም ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መጽሐፍት ቤት ማግኘት የሚቻል ሲሆን፣ በቀጣይም ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተገልጿል።
#getu #ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #diredawa #booklaunch #ethiopiancoffeefc #genenemekuria #libro #ethiopianlegend #አሸናፊግርማ #ሳቪዮላ #የኢትዮጵያእግርኳስ #ድሬዳዋ #መጽሐፍምርቃት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
⚽️ የፍቅር ስጦታ ከሜዳው ባለውለታ፦
አሸናፊ ግርማ (ሳቪዮላ) ተተኪዎችን አበረታታ! 🇪🇹✨
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ስሙ በደማቁ የተጻፈው፣ የኢትዮጵያ ቡና እና የዋሊያዎቹ ድንቅ ኮከብ አሸናፊ ግርማ ዛሬ ማምሻውን በመስቀል ፍላወር 35 ሜዳ በመገኘት ለተስፋ ለስፖርት ቡድን አባላት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። አያይዞም ስፖርታዊ ልምዱን፤ ምክሩን አካፍሏል።
ስለ አሸናፊ ግርማ (ሳቪዮላ) በጥቂቱ፦
🏆 ድርብ ኮከብ፦
ሁለት ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ የተመረጠ የጥበብ ተምሳሌት።
🥇 የዋንጫ ባለቤት፦
ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የጥሎ ማለፍና የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን ያነሳ።
🇪🇹 ብሔራዊ ጀግና፦
በዋሊያዎቹ ማሊያ ሦስት የሴካፋ ዋንጫዎችን የሳመ ባለታሪክ።
📚 ባለታሪክ፦
የሕይወት ጉዞው "ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና" በተሰኘው መጽሐፉ በሰፊው ተተርኳል።
አሁኑኑ ኑሮውን በቶሮንቶ፣ ካናዳ 🇨🇦 ያደረገው አሹ፣ ወደ ሀገሩ ሲመጣ የወጣቶቹን ስፖርተኞች ተስፋ ለማለምለም ኳሶችና የተለያዩ የመለማመጃ ትጥቆችን በስጦታ አበርክቷል።
እናንት ያገሬ ልጆች
"መሥራት ጀግንነት ነው፤ ማድነቅ ደግሞ መሰልጠን ነው!" ለዚህ ድንቅ ባለሙያ ምስጋና ይገባዋል።
#ashenafigirma #saviola #ethiopianfootball #ethiopiancoffee #walias #sportsupport #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments