Logo
Getu Temesgen
በዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ የተጻፈው "ፍካሬ ትኩረት" የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | በዲጂታል ዘመን የሰው ልጅ ትኩረትና ማንነት ላይ የሚያጠነጥነው የዶክተር አብዲበሺር ሰኢድ "ፍካሬ ትኩረት " የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ባሳለፍነው ቅዳሜ በብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ አንጋፋው አርቲስት ሥዩም ተፈራ፣ የኢትዮጵያ ሠዓሊያን እና ቀራፂያን ማኅበር ፕሬዚዳንት አርቲስት አክሊሉ መንግሥቱን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ምሁራንና የጥበብ አፍቃሪያን ተገኝተዋል።

"ፍካሬ ትኩረት" የዲጂታል ዘመን ልማት፣ማንነት፣ እና ኃያልነት መበየኛ መጽሐፍ በአሁኑ ዘመን እንደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የሚቆጠር ሀብት መሆኑን መጽሐፉ ከዓለም አቀፍ እውነታ ጋር እያመሳከረ ይተነትናል።

መጽሐፉ በዲጂታል መሣሪያዎችና በማኅበራዊ ትስስር ገጾች አማካኝነት የሚሰረቀውን የሰው ልጅ አእምሯዊ ንቃት እንዴት መመለስ እንደሚቻል የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ያመላክታል።

✅ በዲጂታል ዘመን ውስጥ የማንነትን ጥያቄ በጥልቀት የሚዳስስ
✅ ለሀገራዊ ልማት አዳዲስ አቀራረቦችን የሚያቀርብ
✅ በትምህርት፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያለውን ልምድ የሚያንጸባርቅ
✅ ለወጣቱ ትውልድ መሪ ሐሳብና ተግባራዊ መንገድ የሚያበረታታ መሆኑን ሒሳዊ ዳሰሳ ያቀረቡ ምሁራን እና ተወያዮች ገልጸዋል።

ዶ/ር አብዲበሺር ሰኢድ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ እና ጂኦግራፊ ትምህርት፤ የመጀመረያ ድግሪ የማስተርስ ድግሪ፤ በቱሪዝም እና ልማት ጥናት ከታላቁና አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የፍልስፍና ዶክትሬት ዲግሪ ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በተጨማሪም ፣ ከሕንዱ ሀገር አቀፍ የኢንተርፔነርሺፕ ልማት ተቋም የድሕረ-ማስተርስ የዓለም አቀፍ የኢንተርፕሬነር የአሰልጣኞች ስልጠና አግኝተዋል።

በተጨማሪም ከኬኒያው ሞይ ዩኒቨርሲቲ በድሕረ ማስተርስ የቱሪዝም አስተዳደር ስልጠና ፣ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ ምረቃ ዲፕሎማ በከፍተኛ ትምህርት የማስተማር ሥነ ዘዴ ስልጠናዎችን የወሰዱ ሲሆን ፣
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ፣የቱሪዝም፣ የእንተርፕሬነርሺፕ እና የድኅነት ቅነሳ ተመራማሪ ፣በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊና ሰብዓዊ ልማት ጥናቶች ኃላፊ ፣በታላቁ የአል-ነጃሺ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት የቅርስና ቱሪዝም አመራር ጥናቶችን ሠርቷል።

በቱሪዝም፣ በኢንተርፕሬነርሺፕ፣ በምጣኔ ሀብት ዘርፎች የተለያዩ ጥናቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ያሳተመ
በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሕንድ እና ሌሎች ሀገሮች ውስጥ የጥናት ምርምሮችንና የስልጠና ፕሮግራሞችን ያቀረበ ነው።

ከዚህ ቀደም ሲል የሴቶችን ትውልድ የማነጽ ሚና የሚዳስሰውንና በሦስት ቋንቋዎች(በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ) የታተመውን "Architects of The Ummah" የተሰኘ መጽሐፍ ከጓደኞቹ ጋር ለንባብ አብቅቷል።

በ7 ምዕራፎች ተቀንብቦ በ107 ገጾች የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ፣ በአሁኑ ወቅት በ320 ብር ለገበያ ቀርቧል። መጽሐፉ በተለይ በቴክኖሎጂ ተጽዕኖ ውስጥ ለሚገኘው ወጣት ትውልድና ለምሁራን ትልቅ ግንዛቤን እንደሚሰጥ በምረቃው መርሐግብር ላይ ተገልጿል።
ከረመዳን ጾም በኃላ በሀረር የመጽሐፍ ምረቃና የፊርማ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል።
#ethiopia #fikretukret #digitalage #identity #newbook #focus #mentalawareness #drabdibeshir #literature #addisababa #booklaunch #attentioneconomy

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.