ያልተዘመሩላቸው የጥበብ ባለውለታዎች
የ1990ዎቹ የጥምር ሙያ ባለቤቶች ሲዘከሩ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ዓለም ውስጥ በዶክመንተሪ፣ በማስታወቂያ፣ በድራማ እና በፊልም ሥራዎች የበቁና የነቁ ትጉህ ሙያተኞች ነበሩ።
የ (Editing) ባለሙያዋ #ወይንሸት አዳሙ፣ ከአምስቱ ጉምቱ ባለሙያዎች ጋር በመሥራት ያገኘችውን ዕድልና ትምህርት በኩራት ታስታውሳለች። ሙያቸውን ብቻ ሳይሆን የሙያ ዲሲፕሊን፣ ትዕግሥት፣ ኃላፊነትና የተሟላ ሰው መሆንን የተማረችው ከእነርሱ እንደሆነ ትመሰክራለች።
የሙያ ባለውለታዎች ዝርዝር፦
ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ
ሰለሞን አበራ
ዘካርያስ ኃ/ማርያም (ነፍስ ይማር)
ፋንታሁን ኃ/ማርያም
ዘላለም ጌታሁን
የዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ ልዩ የምስጋና ምሽት
እነነዚህን የሙያ ወንድሞች ዛሬ ለማስታወስ ምክንያት የሆነው፣ ትሁቱና ታታሪው ዳግማዊ አመለወርቅ ፈይሳ በመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተሰናዳ ደማቅ ሥነ ሥርዓት ልዩ የምስጋና ፕሮግራም ስለተዘጋጀለት ነው።
በዚሁ ዕለትም "ዝሃ" በሚል ርዕስ ያሳተመውን መጽሐፉን አስመርቋል። ዳግማዊ ዝምተኛ ሰው ቢሆንም፣ ሥራዎቹ ግን ድምፅ አውጥተው ከፍ ብለው የሚደመጡ የጥበብ ውጤቶች ናቸው።
#ወይንሸት አዳሙ ለእነዚህ ባለሙያዎች ያላትን ክብርና ምስጋና ስትገልጽ፣ "ከቀዝቃዛው የራስ ዳሽን ተራራ እስከ ሐሩሩ የዳሎል በረሃ እየተጓዛችሁ የተፈጥሮ ጸጋዎችንና የቱሪስት መስህቦችን በአማረ አቀራረብ አሳይታችሁናል። ስለማሕበራዊ ጉዳዮቻችን፣ ስለ አኗኗራችን፣ ስለባህሎቻችን ያስመለከታችሁንን ፈጽሞ አንዘነጋም" ብላለች።
ክብር በሕይወት ላሉት፣ ለተለየን ወንድማችንም ነፍስ ይማር።
#getu #ethiopia #art #documentary #theater #booklaunch #tribute #dagmawiamelework #ye1990ochubalemwyoch #ኪነጥበብ #ብሔራዊቴአትር #ዝሃ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

3 months ago