8 days ago
የሞተው ሕያው የሆነበት ማሩ ከዋሻ የሚፈስበት አስደናቂው ስፍራ
♦️ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
#ethiopia | በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ምስራቅ በለሳ ወረዳ፣ ጎጋ ቀበሌ የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ የቀደመ ታሪኩን ፣ የተፈጥሮ ግርማውንና ታአምራት በአንድ ላይ የያዘ ድንቅ መንፈሳዊ ስፍራ ነው።
አባቶች እንደሚያስረዱት የስፍራው የቀደመ መጠሪያ "ዛጅር ማኤል" ይሰኝ ነበር። ይህ ስም "ዛጅር" ማለት ውሃ በደረቅ አለት ላይ ፈንጥቆ የሚወጣበትን አቅጣጫ ሲያመላክት፣ "ማ" ዋሻውን፣ "ኤል" ደግሞ የሰማይ አምላክን በመወከል እግዚአብሔር በድንቅ ሁኔታ በደረቅ አለት ላይ ውሃ የፈነጠቀበት ስፍራ መሆኑን ይናገራሉ።
የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የስብከተ ወንጌል ኃላፊ እና ጸኃፊ አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚገልጹት፣ የቦታው ተአምራዊ ጉዞ በይፋ ጎልቶ መታየት የጀመረው በ2013 ዓ.ም የጸበል አገልግሎት ሲጀመር ነው።
በተለይም የስፍራውን ስም ከአዲሱ ስያሜ ጋር ያያዘው ታዓምር በዚሁ ዘመን ተከስቷል። ከገዳሙ 12 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ በምትገኘው ዙ ሐሙሲት ከተማ አቅራቢያ የምትኖር አንዲት ሴት በጽኑ ታማ ወደ ህክምና ከተወሰደች በኋላ በቃሬዛ ላይ እያለች ህይወቷ ያልፋል።
በወቅቱ የጸበሉ አስተዳዳሪ የነበሩት አባት እና ሌሎች ካህናት አስከሬኑን ይዘው በመንገድ ላይ ሳሉ የእግዚአብሔርን ኃይል በማመን ቅዱስ ጸበሉን አፍሰው ረጩባት። በዚያው ቅጽበት የሞተችው ሴት ትንፋሽ ተመልሶላት ተነሳች፤ ሙሉ ፈውስ አግኝታም ድንቅ ምስክርነቷን ሰጠች።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጸበሉ "ሙት አንሳ" የሚለውን ስያሜ አገኘ። በኋላም ከዋሻው በላይ ከሚንጠበጠበው ማር ጋር ተያይዞ "ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል እና ቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም" ተብሎ መጠራት ጀመረ።
የገዳሙ መነኮሳት እንደሚናገሩት በዋሻው ጣሪያ ላይ ለዘመናት ሳይቆረጥ የቆየ ልዩ ማር ይገኛል። ይህ ማር በተለያዩ ጊዜያት በራዕይ "ተቆርጦ ለምእመናን ፈውስ ይሁን" የሚል መልእክት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም፣ የቦታው ገደላማና አስፈሪ አቀማመጥ ማንም እንዲደፍረው አላደረገም።
ቆየት ብሎ መነኮሳቱ በጸሎትና በምህላ ሲገቡ ንቡ ቦታውን ለቆ ይወጣል። ማሩ አሁን ላይ እየተቆረጠ ለበርካታ ድውያናትና ምእመናን ዘላቂ ፈውስን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ዛሬ ለቁጥር በርካታ የሆኑ መነኮሳት የሚኖሩበት ይህ ታላቅ ገዳም የተመሰረተው በአንድ አባት መንፈሳዊ ታዛዥነትና ጽናት ነው። አባ ብርሃነ ሠላም እንደሚያስረዱት፣ በ2009 ዓመተ ምህረት ግንቦት 21 ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ አባ ብርሃነ ማርያም ከድዊ አንሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ሲሄዱ በፊታቸው የተለየ ብርሃን እየመራቸው
ቦታው ይደርሳሉ።
ያን ብርሃን እየተከተሉ የሶስት ሰዓት መንገድ በእግር ተጉዘው አሁን ገዳሙ በሚገኝበት ስፍራ ሲደርሱ ብርሃኑ ተሰወረባቸው። በወቅቱ ምንም ዓይነት መኖሪያ ቤትና መጠለያ በሌለበት፣ የክረምቱ ዝናብና ቅዝቃዜ በበዛበት ወቅት አባታችን በእርጥብ ዋሻ ውስጥ ማደር ጀመሩ።
እግዚአብሔርም በቸርነቱ የሚያድሩበትን ስፍራ ደረቅ በማድረግ ጠበቃቸው፤ የዕለት ምግባቸውንም የአካባቢው ህዝብና ጸበልተኞች እያመጡ ያቀርቡላቸው ነበር።
የአባታችንን ትምህርትና ተአምራዊ ፈውሱን ያዩ በርካታ መንፈሳውያን ልጆች በየጊዜው ወደ ስፍራው በመምጣታቸው የምናኔ ሀሳብ በብዙዎች ህሊና ውስጥ ሰረፀ። አባ ብርሃነ ሠላም አያይዘው እንደሚገልጹት፣ በ2011 ዓመተ ምህረት በአካባቢው ሰበካ ጉባኤ ድጋፍ የተገዙ በሬዎችን በመጠቀም መሬት ማረስና የጋራ ኑሮ ተጀመረ። በ2013 ዓመተ ምህረት የመነኮሳቱ ቁጥር ከመቶ በላይ በመድረሱ የአካባቢው ህዝብና ካህናት ተመካክረው ቦታ በመስጠታቸው ትንሽ መቃኞ ተሠርቶ ታቦተ ሚካኤል ገባ።
በመጨረሻም በ2014 ዓመተ ምህረት መስከረም 29 ቀን በማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቡጽዕ አቡነ ዮሐንስ አባታዊ ቡራኬና ውሳኔ ገዳም የመሆን ሙሉ ክብሩንና ስያሜውን አገኘ።
ይህን መንፈሳዊና ታሪካዊ ገዳም የሚገኘው ከአዲስ አበባ
በሰሜን አቅጣጫ 667 ኪሎ ሜትር፣ ከባህርዳር ከተማ 183 ኪሎ ሜትር፣ ከዞኑ ጎንደር ከተማ በአዲስ ዘመን - እብናት -ጎሃላ 192 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከጎንደር ማክሰኚት- አረባያ -ጎሃላ 119 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም፤ በአባቶችና በእናቶች ጸሎትና በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ እስከ ዛሬ የቆየ፣ ለትውልድ የሚተርፍ ታላቅ መንፈሳዊ አደራ ነው።
ይህ ገዳም ከተመሠረተበት ጊዜ አንሥቶ በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ዛሬ ላይ ደርሷል። ከሰሞኑን በገዳሙና በአካባቢው በመዘዋወር እየተከናወኑ ያሉትን የልማት ሥራዎች ተመልክተናል፤ የተመለከትነውንም በተከታታይ ክፍሎች እናቀርብላችኋለን።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#mutansa #ethiopianmonastery #gondarethiopia #ethiopianorthodox #spiritualjourney

2 months ago
ካናዳ : አንጋፋዋ ዘማሪት አዲስ ለማ የዝማሬ አልበም አስመረቀች
#ethiopia | ታዋቂዋ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ዘማሪት አዲስ ለማ በአዲስ አበባ ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ በሚገኘው ታላቁ የቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአገልግሎት ያደገች ሲሆን ይህ ደብር በርካታ ታዋቂ ዘማርያንን በማፍራት የሚታወቅ ታሪካዊ ቦታ ነው።
ዘማሪት አዲስ ወደ ውጭ ሀገር ከመጓዟ በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ በነበራት ሰፊ አገልግሎት ከፍተኛ አክብሮትን ያተረፈች ሲሆን በተለይም ለምኝ ድንግል ለምኝ፣ በመከራ ፅና፣ ምድረ ቀራንዮ እና ተነሺ ኢትዮጵያ የተሰኙት ዝማሬዎቿ ሁልጊዜ በምእመናን ልብ ውስጥ የሚታወሱ ተወዳጅ ሥራዎቿ ናቸው።
ከሀገር ወጥታ በደቡብ አፍሪካ በኩል አድርጋ በምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት አገልግሎቷን የቀጠለችው ዘማሪት አዲስ ለማ፣ በቅርቡ ካጋጠማት አስከፊ የመኪና አደጋ በተአምር ተርፋ ዛሬ ላይ አዲስ የዝማሬ አልበሟን በበርካታ ወንድሞችና እህቶች ታጅባ በደማቅ ሁኔታ አስመርቃለች።
በአገልግሎቷ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን በደግነቷ የምትታወቀው ዘማሪት አዲስ፣ ከዚህ አዲስ አልበም ምርቃት የሚገኘውን ገቢ ሙሉ በሙሉ በካናዳ ካልጋሪ ለሚገኘው የደብረ ፀሐይ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሕንፃ ግዢ እንዲሆን በስጦታ አበርክታለች።
ይህ በጎ ተግባር በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያተረፈ ሲሆን ለአገልጋይዋም መልካም ምኞቶች እየቀረቡላት ይገኛል።
#mezmur #orthodox #ethiopianorthodox #canada #calgary #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

3 months ago
ከግማሽ ክፍለ ዘመን ( ከ 50 ዓመታት ) በላይ በታማኝነት ያገለገሉት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
#rthiopia | በቦሬ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንደ ጽኑ ዋርካ በመሆን ለሃምሳ ዓመታት ያህል ያለመታከትና በታላቅ ፍቅር ሕዝበ ክርስቲያንን ሲያገለግሉ የኖሩት ታላቁ አባት መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተስፋ ማርያም ሕይወታቸው አልፏል።
አባታችን ለምዕመናን የእምነት ምሰሶ እና የትሕትና ትልቅ አርአያ ነበሩ።
በቅዱስ ሥፍራው ያሳለፏቸው ረጅም ዘመናት ለሥልጣን ወይም ለምድራዊ ዝና ሳይሆን ለእውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት የተሰጡ ነበሩ።
ማንኛውንም ዓይነት ፈተናና የሕይወት መከራ ሳይበግራቸው እምነታቸውን ጠብቀው ሐዋርያዊ ሩጫቸውን በድል አጠናቀዋል።
አባታችን በ1977 ዓ.ም መልአከ ገነት የሚለውን የማዕረግ ስም ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በብፁዕ አቡነ በርተሎሚዎስ አቅራቢነት አግኝተዋል።
ታላቁ አባት በቀድሞው የሲዳሞ ክፍለ ሀገር ውስጥ በይርጋዓለም፣ በጀምጀም፣ በሻኪሶ፣ በነጌሌ ቦረና፣ በዲላ፣ በይርጋጨፌ፣ በአለታ ወንዶ፣ በቦሬ ቅድስት ማርያም እና በይርባ ሙዳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሳይቀሩ ቅዱስ ወንጌልን በመስበክና የሰንበት ትምህርት ቤቶችን በማደራጀት ከልጅነት እስከ እውቀት የደከሙ ታላቅ ሐዋርያ ነበሩ።
ለቤተ ክርስቲያን ካበረከቷቸውና ሁልጊዜም በታሪክ ከሚታወሱት ተግባሮቻቸው መካከል
አንደኛው ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ያሳዩት ጽናትና ታማኝነት ሲሆን፣ ቅዱስ ስፍራውን ሳይለቁ በቅድስና መኖር የሚቻለው በእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን በተግባር አሳይተዋል።
ሁለተኛው ዕድሜያቸው ቢገፋም መንፈሳቸው እየታደሰ ለምዕመናን መጽናናትና ለአገልግሎት ራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው ነው።
ሦስተኛው ደግሞ ያከናወኑት መንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ያለ ምንም ምድራዊ ጥቅም፣ በቅንነትና በንጹሕ ልብ የተመራ መሆኑ ነው።
በአሁኑ ወቅት አባታችን ከዚህ ዓለም ድካምና መከራ አርፈው ወደማያልፈው የቅዱሳን ማረፊያ ተሻግረዋል።
ምንም እንኳ የአካል መለያየታቸው፣ ያሳደገን፣ የመከረንና ያስተማረን ጣፋጭ ምክራቸውን ማጣታችን ልብን የሚነካ ቢሆንም፣ የሠሩት መልካም ሥራ ግን ሁልጊዜም ሕያው ሆኖ ይኖራል።
ያገለገሏት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ ክርስቲያኑ የአባታችንን ጸሎትና በረከት እንዲያገኙ እየተመኘን፣ ለእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የቦሬ ከተማና የገጠር ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።
#church #ethiopianorthodox #christianity #memorial #bore #sidamo #orthodox #faith #clergy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

የቤተ መቅደስ ግንባታን ለማጠናቀቅ
የቀረበ የክብር እና የባህር ጥሪ
#ethiopia | በመሪ እያዩ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን እየተከናወነ የሚገኘውን የሕንጻ ቤተ መቅደስ ግንባታ ዳር ለማድረስ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል።
ግንባታውን ለማስቀጠል የታቀደው ይህ የባህር እና የክብር ጥሪ ግንቦት 8 እና 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በዕለቱ በተዘጋጀው ባህር ላይ በመገኘት ማዕድ እየተቆረሰ ለቤተ ክርስቲያኑ ግንባታ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል።
ምዕመናን በዚህ የበረከት ተካፋይ እንዲሆኑ የቤተ ክርስቲያኑ የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ
+251947980166
+251912 609 000
+251911241074
ድጋፍ ለማድረግ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
1000321686854
በአባይ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
0505
አድራሻ ፡-
በመሪ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ከ 40 በ 60 ኮንዶሚኒየም በታች እና በዞን 2 አያት መኖሪያ ቤቶች
#ethiopianorthodox #churchbuilding #spiritualcall #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓት ተከናወነ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት እና የአፋን ኦሮሞ ቴሌቪዥን ጣቢያ የበላይ ኃላፊ እንዲሁም የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም (ወይዘሮ አምሳለ ወርቅ ማሞ) በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
እማሆይ አስካለ ማርያም በ1933 ዓም በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መምህር አገር ቦሰቄ በተባለ ሥፍራ ከአባታቸው አቶ ማሞ ወልደየስና ከእናታቸው ወይዘሮ አጸደ በየነ ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በአካባቢያቸው በሚገኝ ትምህርት ቤት የመሠረተ ትምህርት እውቀትን ገብይተዋል።
በ1948 ዓም ከአባ ክንፈ ሚካኤል (አቶ ጌታነህ የኋላሸት) ጋር ትዳር በመመሥረት ስድስት ወንዶችና ሁለት ሴቶችን በድምሩ ስምንት ልጆችን ወልደው በሃይማኖትና በሥነ ምግባር ኮትኩተው አሳድገዋል።
ሟች እናት ለስምንት ልጆች እናት ከመሆናቸውም ባለፈ ለ38 የልጅ ልጆች፣ ለ20 የልጅ ልጆች ልጆች እንዲሁም ለ4 ቅም አያት ለመሆን የበቁ የልጅ ጸጋ የበዛላቸው እናት ነበሩ።
በሰው ዘንድ እጅግ የተወደዱ፣ ትሑት፣ እንግዳ ተቀባይና ለችግረኞች ሩኅሩኅ በመሆናቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ነበራቸው።
የትዳር አጋራቸው ካረፉ በኋላ ቀሪ ሕይወታቸውን በጾም፣ በጸሎትና በትህርምት በመምራት አምላካቸውን ሲያገለግሉ ቆይተው ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓም በ85 ዓመታቸው አርፈዋል።
የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በሉሜ ሞጆ ወረዳ ኤጀሬ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተሸኝተዋል።
#orthodoxtewahedo #eotc #abunemathewos #mojjo #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

ከመቃብር በላይ የሚውል መልካም ስም
በአሰላ የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ!
#ethiopia | ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አንድ ታሪካዊ ክስተት ተከናውኗል።
በሀገርና በቤተክርስቲያን ዘንድ እጅግ የሚከበሩትና "መጋቤ በረከት" የሚል ማዕረግ የተሰጣቸው የታላቁ አባት የመጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ የመታሰቢያ ህንፃ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
የልጆች ስጦታ፦
እኚህ ታላቅ አባት ካረፉ አንድ ዓመት ሲሞላቸው ልጆቻቸው ከአባታቸው የተረከቡትን በጎነት ለታሪክ እንዲተርፍ ከ62 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን ባለ ሁለት ወለል ሙዚየም ገንብተው ለምረቃ አብቅተዋል።
"ጊዳድ" መጽሐፍ፦
የአባታቸውን የህይወት ጉዞ፣ የንግድ ስኬትና የቤተሰብ አመራር ጥበብ የሚዳስሰው "ጊዳድ" የተሰኘው መጽሐፍ በጸሐፊ ሌሊሳ ኢድሪስ ተዘጋጅቶ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ለንባብ በቅቷል።
ታሪካዊ ምስክርነት፦
ሙዚየሙ የአባቱን መልካም ስራዎች የሚገልጹ ፎቶግራፎች፣ ቁሳቁሶችና መረጃዎችን የያዘ ሲሆን፤ አዳራሽና ቢሮዎችንም ያካተተ ዘመናዊ ህንፃ ነው።
መጋቤ በረከት ግርማ ደምሴ (1949 - 2017 ዓ.ም)
በአርሲ ዞን ተወልደው በንግዱ ዓለም ስኬታማ የነበሩ ሲሆን፤ አምስት ልጆችን በስነ-ምግባር አሳድገው ለሀገር ያበቁ ታላቅ አባት ናቸው።
በቤተክርስቲያን ግንባታ፣ በማህበራዊ ልማትና በሽምግልና ስራቸው "የቱሩፋት አበጋዝ" ተብለው ይወደሳሉ።
እውነትን በመናገርና ችግረኞችን በመርዳት የሚታወቁት እኚህ አባት፣ በ68 ዓመታቸው ሚያዚያ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ማረፋቸው ይታወሳል።
ሀብት ለራስ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለታሪክና ለወገን ሲተርፍ ትልቅ ትርጉም ይኖረዋል። የመጋቤ በረከት ግርማ ልጆች ለአባታቸው ያደረጉት ይህ ተግባር፣ ማንኛውም ሰው በህይወት ዘመኑ የሚዘራው በጎነት እንዲህ በክብር እንደሚታጨድ ማሳያ ነው። አሰላ ዛሬ የአንድ ብርቱ አባት ታሪክ ህያው ሆኖ ሲታደስ ውላለች!
መልካም ስራ ከመቃብር በላይ ይውላል!
#getu #megabebereketgirma #asella #legacy #gidatbook #ethiopianhistory #ethiopianorthodox #arsi #inspiration #መጋቤበረከትግርማ #አሰላ #ታሪክ #ጊዳድ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

በሞቱ ህይወትን የሰጠን በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ያወጀልንን የአባታችንን የመድኃኔዓለምን ቤት ከመፍረስ እንታደግ! 🙏✨
የወደቀውን ለማቅናት፣ የፈረሰውን ለመጠገን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን እንረባረብ!
ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ፣ ምንጣፍ እንዲሁም ንዋየቅድሳቱ በመሉ ከጥቅም ውጪ ሆኗል የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ መቅደሱም ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።
አባቶችም በተማፅኖ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸውን እርዱን እያሉ ከፊታችን ቆመዋል!
ስለ እኛ በቀራንዮ አደባባይ ስጋውን የቆረሰው ፣ደሙን ያፈሰሰውና የእሾህ አክሊል የደፋው በትንሳኤው ትንሳኤያችንን ያወጀልን መድኃኔዓለም፣ ዛሬ የእኛን እጅ ይፈልጋል። ከ 200 ብር ጀምረን የአቅማችንን በመለገስ ይህንን ታሪካዊ መቅደስ ከመፍረስ እንታደግ።
የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - CBE)፦
🏦 1000756255626
(መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤ/ክ)
📞 ለበለጠ መረጃ
+251-920-950007
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
እባካችሁ ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
#getu #medhanealem #savethechurch #northshewa #ethiopianorthodox #humanitariancall #heritageconservation #ethiopia #የመድኃኔዓለምቤት #ሰሜንሸዋ #ቤተክርስቲያን #ጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
4 months ago

ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።

ዛሬ ስቅለቱን እያሰብን የበረከት ስራ እንስራ የአባታችንን መድኃኔዓለምን ቤት ከመፍረስ እንታደግ! 🙏✨
የወደቀውን ለማቅናት፣ የፈረሰውን ለመጠገን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን እንረባረብ!
ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።
እንዴት መርዳት እንችላለን?
ስለ እኛ በቀራንዮ አደባባይ ስጋውን የቆረሰው ፣ደሙን ያፈሰሰውና የእሾህ አክሊል የደፋው መድኃኔዓለም፣ ዛሬ የእኛን እጅ ይፈልጋል። ከ 200 ብር ጀምረን የአቅማችንን በመለገስ ይህንን ታሪካዊ መቅደስ ከመፍረስ እንታደግ።
የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - CBE)፦
🏦 1000756255626
(መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤ/ክ)
📞 ለበለጠ መረጃ
+251-920-950007
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
እባካችሁ ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
#getu #medhanealem #savethechurch #northshewa #ethiopianorthodox #humanitariancall #heritageconservation #ethiopia #የመድኃኔዓለምቤት #ሰሜንሸዋ #ቤተክርስቲያን #ጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
4 months ago
ጸሎተ ሐሙስ
የትሕትናና የአዲስ ኪዳን ብስራት
ዛሬ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ "ጸሎተ ሐሙስ" ወይም "ሕጽበተ እግር" ተብሎ የሚታሰበው ታላቅ ዕለት ነው። ይህ ቀን ስድስት የተለያዩ መጠሪያዎችና ጥልቅ ትርጉሞች አሉት፦
ጸሎተ ሐሙስ
ጌታ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጸለየበት በመሆኑ።
ሕጽበተ እግር
የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትሕትናን ያስተማረበት።
ምሴተ ሐሙስ
የጌታ እራት ወይም ቅዱስ ቁርባን የተመሰረተበት።
የነጻነት ሐሙስ
የሰው ልጅ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣቱ የታወጀበት።
የአዲስ ኪዳን ሐሙስ
የጥላው (የብሉይ ኪዳን) አልፎ የእውነቱ (የአዲስ ኪዳን) መሥዋዕት የተጀመረበት።
የአይሁድ ፋሲካ
አይሁድ የመሻገሪያ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ዕለት።
"እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።" (ዮሐ 13:14)
#getu #holythursday #maundythursday #humility #ethiopianorthodox #passionweek #lastsupper #newcovenant #ሕማማት #ጸሎተሐሙስ #ሕጽበተእግር #ትሕትና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የ አባታችን መድኃኔዓለምን ቤት ከመፍረስ እንታደግ! 🙏✨
የወደቀውን ለማቅናት፣ የፈረሰውን ለመጠገን ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን እንረባረብ!
ከ60 አመት በላይ ያስቆጠረው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ የሚገኘው መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ዛሬ በከባድ ችግር ላይ ይገኛል። ከእድሜ ብዛት የተነሳ የቤተ መቅደሱ ቋሚ ምሰሶዎች በምስጥ ተበልተው፣ ጣሪያውም በማፍሰሱ ምክንያት የአባታችን የመድኃኔዓለም ማደሪያ ሊወድቅ ጥቂት ቀርቶታል።
እንዴት መርዳት እንችላለን?
ስለ እኛ ስጋውን የቆረሰውና ደሙን ያፈሰሰው መድኃኔዓለም፣ ዛሬ የእኛን እጅ ይፈልጋል። ከ 200 ብር ጀምረን የአቅማችንን በመለገስ ይህንን ታሪካዊ መቅደስ ከመፍረስ እንታደግ።
የባንክ አካውንት (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - CBE)፦
1000756255626
(መለጥ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤ/ክ)
📞 ለበለጠ መረጃ
+251-920-950007
(እባክዎን የክርስትና ስምዎን በቴሌግራም ወይም በዋትሳፕ በዚሁ ስልክ ይላኩላቸው በፀሎት ያስቧችኋል)
እባካችሁ ሼር (Share) በማድረግ ድምፅ ሁኑልኝ! 🙏⛪
#getu #medhanealem #savethechurch #northshewa #ethiopianorthodox #humanitariancall #heritageconservation #ethiopia #የመድኃኔዓለምቤት #ሰሜንሸዋ #ቤተክርስቲያን #ጥሪ #ጌጡተመስገን #getutemesgen
4 months ago
የአባታችንን ሕይወት እንታደግ
ለመልአከ ሕይወት ቀሲስ የወርቅእሸት ገላው አስቸኳይ ጥሪ! ✨
#ethiopia | በልደታ ለማርያም ደብር ለረጅም ዘመናት በቅዳሴ፣ በተአምረ ማርያም ንባብና በንስሐ አባትነት ሲያገለግሉ የኖሩት መልአከ ሕይወት ቀሲስ የወርቅእሸት ገላው በአሁኑ ወቅት በከባድ ሕመም ላይ ይገኛሉ።
በአፋቸው ውስጥ በወጣች ቁስል ምክንያት ለሕይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። በሀገር ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የሕክምና ተቋማት ክትትል ቢያደርጉላቸውም፣ ሕመሙ እየተባባሰ በመሄዱ አሁን ወደ ውጭ ሀገር ሄደው እንዲታከሙ በሐኪሞች ተወስኗል።
ለሕክምናው 5,000,000 (አምስት ሚሊዮን) ብር ተጠይቋል። ይህንን የካህን አቅማቸው ስለማይችል የእኛን ርብርብ ይሻሉ።
አባታችን ድነው ወደ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ፣ አቅማችን የፈቀደውን በማድረግና መረጃውን Share በማድረግ ለደጋጎች እንዲደርስ እናድርግ።
🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)፦ 1000004007682
(ወርቅሸት ገላው) 📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0946655003 / 0911571123
የካህን በረከት በቤት ይሞላልና ለአባታችን ደራሽ እንሁን!
#getu #helppriestworkeshet #lidetamariam #ethiopianorthodox #emergencyaid #medicalfund #spiritualfather #addisababa #churchservice #ቀሲስወርቅእሸትገላው #የእርዳታጥሪ #ልደታለማርያም #በረከት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የትንሳኤ በዓል አስመልክቶ ወደ እየሩሳሌም ታቅዶ የነበረው መንፈሳዊ ጉዞ ተራዘመ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ሃይማኖታዊ ጉዞ አዘጋጅ ድርጅቶች ማህበር ለ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል ወደ እየሩሳሌም ታቅዶ የነበረው መንፈሳዊ ጉዞ መራዘሙን ማህበሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ማህበሩ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ በታሪክ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ባለቤትነት የሚመሩ ከስድስት በላይ ገዳማት የሚገኙባት ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም፣ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን የምታስተናግድ ታላቅ የሃይማኖት ስፍራ ብትሆንም አሁን ላይ ባለው ወቅታዊ ሁኔታ የጉዞ መርሃ ግብሩ ላይ ለውጥ ለማድረግ መገደዱን ገልጿል።
ለዘንድሮው የትንሳኤ በዓል ጉዞ በርካታ ምዕመናን አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቀውና የቪዛ ሂደታቸውን ጨርሰው የነበረ ቢሆንም፣ በእስራኤልና በአካባቢው ባለው ወቅታዊ ግጭትና የሰላም እጥረት ምክንያት የአየር ክልል መዘጋትና የበረራዎች መስተጓጎል በመፈጠሩ ጉዞው ለምዕመናን ደህንነት ሲባል እንዲራዘም ተወስኗል።
ማህበሩ ይህንን ውሳኔ ያስተላለፈው ምዕመናን ያለ ምንም ስጋት ሃይማኖታዊ ስርአታቸውን መፈጸም የሚችሉበት አስተማማኝ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑን ገልጾ፣ በቅርብ ክትትል ሁኔታዎችን እያጠና መሆኑንም ጠቁሟል።
በመሆኑም አሁን ያለው ስጋት ተወግዶና በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም መስፈኑ ሲረጋገጥ፣ በግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለሚከበረው በዓለ እርገት ጉዞው የሚከናወን መሆኑን ማህበሩ ገልጿል።
ምዕመናን በትግስትና በጸሎት ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ እንዲጠባበቁ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፣ ማህበሩም ቀጣይ ጉዞዎችን በተመለከተ መረጃዎችን ተከታትሎ ለተጓዦች እንደሚያሳውቅ ገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#jerusalempilgrimage #ethiopianorthodox #pilgrimageupdate #faithjourney #holyland #ethiopia #spiritualtravel #newsupdate

የቅዱስ ጊዮርጊስና የቅድስት አርሴማን ቤተ መቅደስ አብረን እንፈጽም! ⛪✨
በሰሚት ቀሬ ምስራቀ ፀሐይ የሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሕንጻ ግንባታ ከተጀመረ 8 ዓመታትን አስቆጥሯል።
በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ከ70 ሺህ በላይ አባወራና እማወራ የሚኖርበት በመሆኑና አሁን ያለው ቤተ ክርስቲያን እጅግ ጠባብ በመሆኑ፣ አዲሱን ሕንጻ አጠናቆ ማስመረቅ የጊዜ የማይሰጠው ተግባር ሆኗል።
የግንባታው ሁኔታ
ጅማሬ
በመስከረም 2010 ዓ.ም በ50,000 ብር ካፒታል ተጀመረ።
አሁን ያለበት ደረጃ
የፊኒሺንግ (የማጠናቀቂያ) ሥራ ላይ ይገኛል።
ዕቅድ
የፊታችን ሚያዝያ 23 ቀን 2019 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ለማስመረቅ ታቅዷል።
እንዴት መርዳት ይቻላል?
የሰማዕታቱን ቤት አብረን ለመፈጸም በሚከተሉት የባንክ አካውንቶችና የክፍያ አማራጮች አቅማችን የፈቀደውን በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንሁን፦
🔹 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000200637268
🔹 አሃዱ ባንክ፦ 0073908710901
🔹 አባይ ባንክ፦ 2306
🔹 ቴሌብር (Telebirr)፦ 0945230023
በእግዚአብሔር ቤት የሚተከል ለዘላለም ይለመልማል።
ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የድርሻችንን እንወጣ!
#getu #summitqere #stgeorge #starsema #churchconstruction #ethiopianorthodox #donationdrive #addisababa #spiritualgrowth #ቅዱስጊዮርጊስ #ቅድስትአርሴማ #ቤተክርስቲያን #ሰሚት #አዲስአበባ
5 months ago
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወጣቶች ቤተሰቦች የ4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከቱ
#ethiopia | በጥምቀት በዓል ዕለት ታቦት በሰረገላ ሲያጅቡ በደረሰ የኤሌክትሪክ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ አራት ወጣቶች ቤተሰቦችና ለተረፈው አንድ ወጣት፣ ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ።
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ በኮዬ ፈጬ ደብረ ፀሐይ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናኛን ሰጥተዋል።
አደጋው በደረሰ ወቅት በሀገረ ስብከቱ በተዋቀረ የ10 አባላት ኮሚቴ አማካኝነት በንግድና በአቢሲኒያ ባንኮች በተሰበሰበው ገንዘብ መሠረት፦
* ለሦስት ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 1 ሚሊዮን ብር፤
* በሕይወት ለተረፈው ወጣትና ለሌሎቹ ቤተሰቦች እንደየጉዳት መጠኑ ከ300 ሺህ እስከ 700 ሺህ ብር፤
* ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ለተወሰኑት የሥራ ዕድልና የእህል ድጋፍ ተበርክቷል።
"ታማኝ አገልጋዮች ነበሩ"
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዕለቱ ባስተላለፉት የማጽናኛ ትምህርት፣ ወጣቶቹ እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የደረሰ አገልግሎት ማበርከታቸውን ገልጸዋል።
ከሳምንቱ "ገብር ኄር" (ታማኝ አገልጋይ) ስያሜ ጋር በማያያዝም፣ ቤተሰቦቻቸው በእምነት እንዲጸኑና እንዳያዝኑ አበረታተዋል።
ለሟች ወጣቶች በደብሩ መታሰቢያ ሐውልት የቆመላቸው ሲሆን፣ ብፁዕነታቸው ይህን የተቀናጀ የድጋፍ ሥራ ላከናወኑት ኮሚቴዎችና የሰበካ ጉባኤ አባላት ምስጋና አቅርበው መርሐ ግብሩን በጸሎት አጠናቀዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #የኢትዮጵያኦርቶዶክስተዋሕዶቤተክርስቲያን #ብፁዕአቡነሳዊሮስ #ኮዬፈጬ #ሰብአዊድጋፍ #ተዋሕዶ #ethiopianorthodox

6 months ago
የዐቢይ ጾም የበረከት ጥሪ
ቅድስት ሃናን አብረን እንገንባ!
#ethiopia | ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የደብረ ደናግል ቅድስት ሃና ካቴድራል በ 837 ዓ.ም የተመሰረተች ቢሆንም፣ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች።
ይህንን የተጀመረውን የልማት ስራ ዳር ለማድረስና የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ ታላቅ መንፈሳዊ ጥሪ ቀርቦላችኋል።
🗓 የዝግጅቱ ዝርዝር፦
ቀን፡ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም (እሁድ)
ሰዓት፡ ከጠዋቱ 7:30 ጀምሮ
ቦታ፡ አዲስ አበባ፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ-ክርስቲያን
✨ የዕለቱ መርሃ-ግብር፦
በዕለቱ የትምህርተ ወንጌል ስርጭት እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ተዘጋጅቷል።
በዚህ የተቀደሰ ተግባር ላይ በመገኘት የአገልግሎቱ ደጋፊና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ በቅድስት እናታችን በቅድስት ሃና ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
💰 ድጋፍ ለማድረግ
📍 የባንክ አካውንት፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)
📍 የአካውንት ቁጥር፡ 1000709139634
አዘጋጅ፡ የአዲስ አበባ አስተባባሪ ኮሚቴ
"እኛም ለቤታችን፣ እኛም ለእናታችን!"
#ethiopianorthodox #tewahedo #sthanna #spiritualgathers #addisababa #churchdevelopment #orthodoxtewahedo #ethiopia #faith #donation

⛪️ የታላቁ የማን እንደ አባ አቡነ ያሳይ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም የታሪክ ዶክመንተሪ ምረቃ! 🌿✨
"አባ አትማረኝ" የተባሉት ቅዱስ አባት ዋሻና አጽም የሚገኝበት ጥንታዊው ገዳም!
በቅድሚያ እንኳን ለ2018 ዓ.ም የዐቢይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ!
በጣና ሀይቅ ዙሪያ የሚገኘውና በ1326 ዓ.ም በጻድቁ አቡነ ያሳይ የተመሠረተው ይህ ጥንታዊ ገዳም፤ የብዙ ቅዱሳን ታሪክና ድንቅ ቅርሶች መገኛ ነው። የገዳሙን ታሪክና በውስጡ ያሉትን መንፈሳዊ ሀብቶች ለምእመናን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀው አጭር ዶክመንተሪ በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
መርሐ ግብሩ፦
🗓 ቀን፦ ቅዳሜ፣ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ (4ኛ ፎቅ)
በዕለቱ፦
✅ የገዳሙ ታሪክ ዶክመንተሪ ይመረቃል፤
✅ የእመቤታችን እና የአቡነ ያሳይ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ (በተለይ ለሴቶች አገልግሎት የሚውል) እንዲሁም የልማት ሥራዎች ፍኖተ ካርታ ይፋ ይደረጋል፤
✅ ብፁዓን አባቶች፣ መምህራንና ዘማርያን ይገኛሉ።
በአካል ተገኝተው የገዳሙን በረከት ይካፈሉ፤ በገዳሙ ስም የተላለፈውን መንፈሳዊ ጥሪ ይቀበሉ!
ድጋፍ ለማድረግ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000731553134
📞 ስልክ፦
0918240454 / 0906632367 / 0921612653
አምላከ አቡነ ያሳይ ኢትዮጵያን ይባርክ!
#abuneyasay #tana #ethiopianorthodox #documentary #spirituality #addisababa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

⛪️የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎች በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተመረቁ! ✨
#ethiopia | "ይህ ሥራ የምዕመናን አንድነትና ለቤተክርስቲያን ያላቸው ፍቅር ውጤት ነው" - ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ሲከናወኑ የቆዩ የልማት ሥራዎች ተጠናቀው ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።
በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ፣ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፤ የተሰራው የልማት ስራ ለአገልግሎት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለሌሎች አድባራትም ትልቅ ምሳሌ መሆኑን መስክረዋል።
የስኬቱ ሚስጥር:
እነዚህ የልማት ሥራዎች ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ድረስ በምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የሞራል ተነሳሽነት የተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።
በእለቱም ለልማቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እና ለደብሩ ምዕመናን እንኳን ደስ አላችሁ!
#eotc #straphael #gulele #churchdevelopment #abunehiryakos #addisababa #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

7 months ago
🌿 የቃና ዘገሊላ በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር በድምቀት እየተከበረ ነው!
#ethiopia | "ውሃውን ወደ ወይን የለወጠበት ተአምር በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት እየተዘከረ ነው"
የጥምቀት በዓል ማሳረጊያ የሆነው የቃና ዘገሊላ በዓል በጎንደር ከተማ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
የበዓሉ ድባብ:
በዓሉ በተለይ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በልዩ ክብር የሚከበር ሲሆን፤ የዕለቱን ታላቅነት የሚዘክሩ ያሬዳዊ ወረቦችና ጣፋጭ የቤተክርስቲያን መዝሙራት በሊቃውንቱ እየቀረቡ ነው።
የአባቶች ቡራኬ:
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፤ ከበርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና የሃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ለህዝቡ ትምህርት እና ቡራኬ ሰጥተዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በቦታው ተገኝተው በረከቱን እየተካፈሉ ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!
#kanazegelila #gondar #eotc #timket #ethiopianorthodox #abuneyohannes #celebration

የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ሥላሴ ዓመታዊ በዓል ተከበረ
📌 ቤተክርስቲያኑ ሁለገብ እድሳት እንዲደረግለት ጥሪ ቀረበ
#ethiopia | በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ የሚገኘውና በኪነ-ህንፃ ጥበቡ የሚታወቀው የንግሥተ አድባራት ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ ክብረ በዓል ዛሬ ጥር 7 ቀን በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አብነ ዮሐንስ፣ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ ምዕመናን ተገኝተዋል።
ደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በታላቁ ንጉሥ ዐፄ ኢያሱ (አድያም ሰገድ) የንግሥና ዘመን (1674-1698 ዓ.ም) የተገነባ መሆኑ ይታወቃል።
የኪነ-ህንፃ ባለሙያው፦ ቤተክርስቲያኑ በታዋቂው ባለሙያ ገብረ ሥላሴ አማካኝነት በኖኅ መርከብ ቅርፅ የተገነባ ነው።
በንጹህ ኖራና በተጠረቡ ድንጋዮች የተገነባ ሲሆን፣ የህንፃው ቅርፅ ምዕመናንን ከኃጢአት ማዕበል ጠብቃ ለሰማያዊ ክብር የምታበቃ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ተደርጎ ይወሰዳል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁትንና የቤተክርስቲያኑን ጣሪያና ግድግዳ ያጌጡትን ድንቅ ሥዕላት የሳሉት ባህታዊ አባ ኃይለ መስቀል ወልዱ እንደሆኑ በታሪክ ተመዝግቧል።
ቤተክርስቲያኑ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና የኢትዮጵያ የጥበብና የሃይማኖት መታወቂያ ቢሆንም፣ ላለፉት በርካታ ዓመታት ምንም ዓይነት እድሳት ሳይደረግለት መቆየቱ ተገልጿል።
በበዓሉ ላይ የተገኙት ብጹዕ አብነ ዮሐንስ እንደገለጹት፤ ይህንን ታሪካዊ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍና ከጉዳት ለመታደግ ሁለገብ እድሳት ማድረግ አሁን ላይ የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በዚህ የአለም ቅርስ በሆነው ቤተክርስቲያን ጥገና ላይ በእውቀት በገንዘብ በጉልበት እንዲሳተፉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ጌትነት ተመስገን
#debreberhanselassie #gondar #ethiopianorthodox #gondarethiopia #ደብረብርሃንሥላሴ #ጎንደር #ኢትዮጵያ #ተዋህዶ #ቅድስትሥላሴ

Comments