12 days ago
#eotc
#ደመራ2019
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ2019 ዓ/ም ደመራን በዓል አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፋለች።
ቤተክርስቲያኗ እንደተለመደው ሁሉ ልጆቿ የደመራ በዓልን ለማክበር ሲመጡ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የሆነውንና የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ተለይታ የምትታወቅበትን #ነጭ_ልብስ ለብሰው እንዲገኙ መልዕክት አስተላልፋለች።
ከሥርዓት የወጡና ልዩነትን የሚፈጥሩ አለባበሶችን ማስወገድ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥታ ገልጻለች።
በተለይም የዚህ ዓመት በዓለ መስቀል የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ሣልሳዊ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በተገኙበት የሚከበር በመሆን የተለየ ድምቀት ይሰጠዋል ተብሏል። ከዚህም በላይ በዓሉ ዓለም አቀፋዊ ትኩረት እንዲያገኝ ያደርገዋል።
በመሆኑም መላው ምዕመኑ ፦
- አለባበሱ ፣
- ዝማሬው ፣
- አጠቃላይ እንቅስቃሴው ሁሉ በሥርዓት የሚከናወንና ሰላምን የሚሰብክ ሊሆን እንደሚገባ ቤተክርስቲያኗ መልዕክት አስተላልፋለች።
የመስቀል ደመራ ማክበሪያ ሥፍራዎች አካባቢ ፍተሽ ስለሚኖርም ምዕመኑ ቀድሞ አውቆ ተባባሪ እንዲሆን አደራ ብላለች።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ መስቀል አደባባይን ጨምሮ ከ2,657 በላይ በሆኑ ቦታዎች ላይ ደመራ ተደምሮ በዓሉ እንደሚከበር ተነግሯል።
በመላው ሀገሪቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች ይከበራል።
ፎቶ ፦ ፋይል
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

1 month ago
ተባባሪ ፕ/ር ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ(ዶ/ር) የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በመመረቃቸው ልዩ የደስታና የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ፣ የቦርድና የሴኔት አባላት ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ለደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለተባባሪ ፕሮፌሰር ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) ልዩ የደስታና የምስጋና መርሃ ግብር አካሄዱ።
ይህ ታላቅ መርሃ ግብር የተዘጋጀው ብፁዕነታቸው በሰሜን አሜሪካ ከሚገኘው ሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አመራር ዘርፍ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ መዐርግ በማጠናቀቃቸው ምክንያት ነው።
በበዓሉ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ምክትል ፕሬዚደንት መልአከ ኃይል አባ ጽጌ ደንግል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላላፊ ሲሆኑ ይህ ስኬት የአንድ ሰው የትምህርት ውጤት ብቻ ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያኒቱና ለሚመጣው ትውልድ የሚተላለፍ የታላቅ ተስፋና የእውቀት ምንጭ መሆኑን ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የብፁዕነታቸውን የትምህርትና የአገልግሎት ጉዞ የሚያስረዳ "ፍኖተ ሕይወት" መጽሔት፣ "ከአሜሪካ እስከ ጂንካ" የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም እና የዩኒቨርሲቲውን ታሪካዊ እድገት የሚያሳይ ዐውደ ርዕይ ለታዳሚዎች ቀርቧል።
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ በበኩላቸው የብፁዕነታቸውን የመመረቂያ ጥናት ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን ጥናቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዐውድ ውስጥ አገልጋይ መሪነትን፣ የሥራ ተነሣሽነትን እና መንፈሳዊነትን ያቀናጀና የቤተክርስቲያኗን መንፈሳዊ ተልዕኮ መሰረት ያደረገ ትልቅ የምርምር አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን አብራርተዋል።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ በተደረገላቸው አቀባበል የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፣ የተገኘው ውጤት የቤተክርስቲያኒቱ የጋራ ስኬት መሆኑን በመጥቀስ ለተማሪዎች ውጤታማነት ግልጽ ዓላማ፣ ጽናት፣ የጊዜ አጠቃቀም፣ ትክክለኛ የጥናት ስልትና የማኅበራዊ ሕይወት ድጋፍ ወሳኝ መሆናቸውን አበክረው ተናግረዋል።
የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስም ባስተላለፉት አባታዊ መልእክት፣ ብፁዕነታቸው ሀገር በቀል እውቀትን ከዘመናዊ ዓለም አቀፍ እውቀት ጋር አጣጥመው በመያዝ ዘመኑን የዋጀ እረኝነትን በተግባር ያሳዩ ታላቅ አርአያ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በኹነቱ በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
(EOTC -TV)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
በምእመናን እና በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተዘግታ የቆየችውን ቤ/ክ ዳግም ለመክፈት ውይይት ተደረገ
#ethiopia | ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የግሪክ አምባሳደር አንቶኒዮስ ስጉሮፖሎስን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
የውይይቱ ዋና ትኩረት በግሪክ አቴንስ ከተማ የምትገኘውና ከ40 ዓመታት በላይ አገልግሎት ስትሰጥ የነበረችው የቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበት ሁኔታና ወደ አገልግሎት የምትመለስበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነው።
ይህች ታሪካዊ ቤተክርስቲያን በምእመናን እና በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በሀገሪቱ የሃይማኖት ሚኒስቴር ትእዛዝ አገልግሎቷ ተቋርጦ የተዘጋች ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንደገና ተከፍታ አገልግሎት የምትጀምርበት አካሄድ ተመክሮበታል።
ቤተክርስቲያኗ በስደት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባለፈ ባህልና እምነትን ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መጠጊያ ለመሆን የምታደርገው በጎ አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ፣ የተፈጠረው ችግር ተፈትቶ አገልግሎቱ በፍጥነት እንዲቀጥል ጥረት እየተደረገ ይገኛል።
EOTC BSA

5 months ago
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ያስገነባው 1B+G+10 ሕንጻ በቅዱስ ፓትርያርኩ ቡራኬ ተመረቀ።
በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመት የተጀመረው በ480 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሁለገብ ሕንፃ በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት ዘመነ ሢመት ተጠናቆ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ተባርኮ ተመረቀ።
EOTC

ዘገባው የEOTC ነው

ቅዱስ ሲኖዶስ ውዝግብ ያስነሳውን መጽሐፍ አገደ
#fastmereja I የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው የአምስተኛ ቀን ውሎው "ዋልድባ አብረንታት ገዳምን ይወቁ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ በየትኛውም አህጉረ ስብከት እንዳይሰራጭ አገደ። የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል (ረ/ፕ) ለ EOTCTV በሰጡት ማብራሪያ መጽሐፉ በእምነት አስተምህሮ ላይ ጉድለት ያለበትና ለክፍፍል የሚዳርግ ነው ተብሏል።
ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ የቀረበው መጽሐፍ በቤተክርስቲያኗ የሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ፤ "እመቤታችን ከሰማይ እንደወረደች አድርጎ የሚያሳይ፣ የምሥጢራተ ቤተክርስቲያንን ቁጥር የሚያፋልስና ለመነኩሴ የማይገባ ስድብና ትችት የበዛበት" መሆኑ ተገልጿል። በዚህም ምክንያት መጽሐፉ እንዲወገዝ በሊቃውንቱ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ምልዓተ ጉባኤው ተመልክቶታል።
ይሁን እንጂ ሲኖዶሱ መጽሐፉን ከማገድ ባለፈ፣ የሊቃውንት ጉባኤ የጽሑፉን ባለቤትነትና ጸሐፊውን ለይቶ ባለማቅረቡ ጉዳዩ በድጋሚ ተጣርቶ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲቀርብ መርቷል። እስከዚያው ድረስ ግን የገዳሙ አባቶች በሰላምና በፍቅር እንዲቆዩና መጽሐፉም ከሥርጭት ውጪ እንዲሆን ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

''ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው''
📌መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
#ethiopia | በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን!
ብፁዕ ኣቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ ኣስኪያጅ፤
ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፤
ብፁዕ ኣቡነ ሕርያቆስ
የኣዲስ ኣበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣
በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)።
የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤
ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎኣል፤
ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሓፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው፤
ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ ኣከናውኖታል፤
በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ኣስታረቀ፤
ለዚህም ነው ተበዳይ እሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እሱ፣ ኣስታራቂ እሱ፣ ታራቂ እሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለኛ ግር የሚል ቢመስልም ለሱ ቀላል ነበረ።
በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በኣንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ሽፍታ “ዛሬውኑ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “ኣባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ ኣደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ ኣማሕፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው።
ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው፤
እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ ኣድኖናል” ብለን በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፣ እሱም “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” ብሎ የሚያረጋጋን በመሰቀሉ ይህንን ውጤት ስላስገኘልን ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረ ሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር ኣንድ ተልእኮ ነው፤
ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በኣስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የኣንድነት ምስጢር ነው፤
እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ ኣሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት ኣይኖርም ነበር፤
ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮኣችንን በኣግባቡ ኣለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሳሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል።
ይሁንና ኣሁንም ሕዝቡን ወደ ኣንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤
ሃገርን በኃላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም ኣማራጭ ሓሳብ ኣለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልኂቃነ ሃገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም ኣትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ ኣይደለምና፣
የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ ኣዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በኣንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሃብትን ማግኘት፣ የእምነት ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው።
ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም፤
ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው ኣማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን ኣይበጅም እንላለን።
በመጨረሻም፦
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ ኣምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የረክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን!!!
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሓት ለእግዚአብሔር፤
አሜን!!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤
ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
ኣዲስ ኣበባ - ኢትዮጵያ
EOTC TV

የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓት ተከናወነ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት እና የአፋን ኦሮሞ ቴሌቪዥን ጣቢያ የበላይ ኃላፊ እንዲሁም የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት የብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ወላጅ እናት እማሆይ አስካለ ማርያም (ወይዘሮ አምሳለ ወርቅ ማሞ) በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
እማሆይ አስካለ ማርያም በ1933 ዓም በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ መምህር አገር ቦሰቄ በተባለ ሥፍራ ከአባታቸው አቶ ማሞ ወልደየስና ከእናታቸው ወይዘሮ አጸደ በየነ ተወለዱ።
ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስም በአካባቢያቸው በሚገኝ ትምህርት ቤት የመሠረተ ትምህርት እውቀትን ገብይተዋል።
በ1948 ዓም ከአባ ክንፈ ሚካኤል (አቶ ጌታነህ የኋላሸት) ጋር ትዳር በመመሥረት ስድስት ወንዶችና ሁለት ሴቶችን በድምሩ ስምንት ልጆችን ወልደው በሃይማኖትና በሥነ ምግባር ኮትኩተው አሳድገዋል።
ሟች እናት ለስምንት ልጆች እናት ከመሆናቸውም ባለፈ ለ38 የልጅ ልጆች፣ ለ20 የልጅ ልጆች ልጆች እንዲሁም ለ4 ቅም አያት ለመሆን የበቁ የልጅ ጸጋ የበዛላቸው እናት ነበሩ።
በሰው ዘንድ እጅግ የተወደዱ፣ ትሑት፣ እንግዳ ተቀባይና ለችግረኞች ሩኅሩኅ በመሆናቸው በአካባቢው ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ ስም ነበራቸው።
የትዳር አጋራቸው ካረፉ በኋላ ቀሪ ሕይወታቸውን በጾም፣ በጸሎትና በትህርምት በመምራት አምላካቸውን ሲያገለግሉ ቆይተው ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓም በ85 ዓመታቸው አርፈዋል።
የሥርዓተ ቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በሉሜ ሞጆ ወረዳ ኤጀሬ ደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን ጨምሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና በርካታ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
እንዲሁም የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያ ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተሸኝተዋል።
#orthodoxtewahedo #eotc #abunemathewos #mojjo #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
የሕጽበተ እግር እና የጸሎተ ሐሙስ ሥነ ሥርዓት በድምቀት ተከናወነ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ትሕትና በማሰብና የጸሎተ ሐሙስን በዓል በማስመልከት በመላው አገሪቱ በሚገኙ አድባራትና ገዳማት በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተከብሯል።
በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተከናወነው በዚሁ ታላቅ መርሐ ግብር ላይ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በተገኙበት የሕጽበተ እግር ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል።
በዕለቱም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት እግራቸውን በማጠብ ያሳየውን ፍጹም ትሕትና ለማዘከር ብፁዕነታቸው የካህናትንና የዲያቆናትን እግር በውኃና በወይራ ቅጠል አጥበዋል።
ከመታጠቡ ሥነ ሥርዓት ጎን ለጎንም የዕለቱን ትርጉምና የድኅነት ጉዞ የሚያዘክሩ የጸሎት፣ የምህላና የስግደት መርሐ ግብሮች ሲከናወኑ ውለዋል።
በካቴድራሉ የተሰበሰቡ ምእመናንም የሕጽበተ እግሩን ሥርዓትና የማዕድ ምስጢር የታሰበበትን ቅዳሴ በመከታተል በዓሉን በጸሎት አሳልፈዋል።
በተለይም በዚህ ዕለት የሚፈጸመው ሥርዓተ ሕጽበትና የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት አማናዊው የኪዳን መሠረት የተጣለበት መሆኑን በማሰብ፣ ካህናቱና ምእመናኑ በጾምና በጸሎት ተወስነው ለትንሣኤው በዓል መንፈሳዊ ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 EOTC

7 months ago
የመልካም ሰዎች መጉደል ለቤተ ክርስቲያን ነገ ያሳስባል"
- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ በነበረው የወንጌል አገልግሎቱ የሚታወቀው የወጣት መምህር ዘለዓለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የቀብር ሥነ-ሥርዓት በአሁኑ ሰዓት በታላቁ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀትና ሐዘን እየተከናወነ ይገኛል።
ከመስቀል አደባባይ የጀመረውና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን የታደሙበት ይሄው የሽኝት መርሃ ግብር፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎችና ከፍተኛ የሃይማኖት አባቶች ታጅቦ ቀጥሏል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ በመምህሩ ድንገተኛ ሕልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸዋል። በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ አማካኝነት ለታዳሚው በንባብ በተሰማው የቅዱስነታቸው መልእክት ላይ የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተጠቅሰዋል፦
* መምህር ዘለዓለም በመንፈሳዊ ሕይወቱና በትጋቱ ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ተስፋ የነበረው፣ ወንጌልን ለማድረስ በገጠርም በከተማም የደከመ አባት መሆኑ ተገልጿል።
* "በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም በሰማይ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን" (2ቆሮ. 5፡1) የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በመጥቀስ መጽናናትን አስተላልፈዋል።
* ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ውስጥ ሃይማኖትን ወይም ማንነትን መሠረት በማድረግ በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ምእመናን ላይ የሚደርሰው ጥቃት ልባቸውን በትካዜ ውስጥ እንደከተተው ሳይጠቅሱ አላለፉም።
መምህር ዘለዓለም ወንድሙ በሰሜን አሜሪካ ለአገልግሎት በሄደበት ወቅት ባጋጠመው ሕመም ከዚህ ዓለም በሥጋ መለየቱ ከፍተኛ ድንጋጤ የፈጠረ ቢሆንም፣ "ያለዋጋ የተቀበለውን የእግዚአብሔር ቃል ለምእመናን በማስተማር አደራውን በሚገባ ተወጥቷል" ሲሉ ቅዱስ ፓትርያርኩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም፣ ሁሉን የሚችል አምላክ ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ መጽናናትን እንዲሰጥ፣ ለቤተ ክርስቲያንም ተተኪ አገልጋዮችን እንዲያዘጋጅ አባታዊ ጸሎታቸውን አድርገዋል።
"ለአገልጋዩ ወልደ ሰማዕት ነፍስ እረፍተ መንግሥተ ሰማያትን እንመኛለን!"

#ethiopia | በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ በነበረው የወንጌል አገልግሎቱ የሚታወቀው የወጣት መምህር ዘለዓለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የቀብር ሥነ-ሥርዓት በአሁኑ ሰዓት በታላቁ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ድምቀትና ሐዘን እየተከናወነ ይገኛል።

Sponsored by
Surafel
7 months ago
ud83dude4f u12e8u1273u122au12ad u1270u1233u1273u134au1293 u12e8u1260u1228u12a8u1275 u1270u12abu134bu12ed u12edu1201u1291! ud83cuddfaud83cuddf8
u2014 u12a8u1296u1285u1270 u121du1225u122bu1245 u12aau12f3u1290 u121du1215u1228u1275 u1264u1270 u12adu122du1235u1272u12ebu1295 u12e8u1240u1228u1260 u1325u122a
#ethiopia | u1260u12cbu123du1295u130du1270u1295 u12f2u1232u1293 u12a0u12abu1263u1262u12cd u12e8u121au1308u1298u12cd u12e8u1296u1285u1270 u121du1225u122bu1245 u12aau12f3u1290 u121du1215u1228u1275 u1264u1270 u12adu122du1235u1272u12ebu1295u1363 u1260u1245u122du1261 u12e8u1308u12dbu12cdu1295u1293 13 u12a4u12a8u122d (Acres) u1235u134bu1275 u12ebu1208u12cdu1295 u12e8u1240u12f5u121eu12cdu1295 u12e8u12acu121bu122du1275 (K-mart) u130du12d9u134d u12edu12deu1273 u12c8u12f0 u1218u1295u1348u1233u12cau1293 u121bu1205u1260u122bu12ca u12a0u1308u120du130du120eu1275 u121bu12d5u12a8u120du1290u1275 u1208u1218u1208u12c8u1325 u1273u120bu1245 u12e8u1308u1262 u121bu1230u1263u1230u1262u12eb u1218u122du1203-u130du1265u122d u12a0u12d8u130bu1305u1277u120du1362
u12edu1205 u1355u122eu1300u12adu1275 u1260u121du12d5u122bu1261 u12d3u1208u121d u1208u121au1296u1229 u12a6u122du1276u12f6u12adu1233u12cdu12ebu1295u1293 u1208u120du1306u127bu1278u12cd u12d8u1218u1291u1295 u12e8u12cbu1300u1293 u1203u12edu121bu1296u1273u12ca u12a5u1234u1275u1295 u12e8u1320u1260u1240 u1275u12cdu120du12f5 u1208u121bu134du122bu1275 u1273u1235u1266 u12e8u1270u12d8u130bu1300 u130du12d9u134d u1270u124bu121d u1290u12cdu1362
u12e8u1355u122eu1300u12adu1271 u12cbu1293 u12cbu1293 u12a0u12abu120bu1275
* u1264u1270 u1218u1245u12f0u1235u1366
u1260u12a0u1295u12f5 u130au12dc u12a82,000 u1260u120bu12ed u121du12d5u1218u1293u1295u1295 u1218u12ebu12dd u12e8u121au127du120d u12d8u1218u1293u12cau1293 u1230u134a u1264u1270 u1218u1245u12f0u1235 u130du1295u1263u1273u1362
* u12d8u1218u1293u12ca u1275u121du1205u122du1275 u1264u1275u1366
u120du1306u127bu127du1295 u12a8u1263u1205u120bu12cau1293 u1203u12edu121bu1296u1273u12ca u12a5u1234u1276u127bu127du1295 u12abu1348u1290u1308u1321 u12a0u1235u1270u1233u1230u1266u127d u1270u1320u1265u1240u12cd u1260u12a5u12cdu1240u1275u1293 u1260u1235u1290-u121du130du1263u122d u12e8u121au1273u1290u1339u1260u1275 u1275u121du1205u122du1275 u1264u1275u1362
* u12e8u1245u12f1u1235 u12ebu122cu12f5 u1218u1295u1348u1233u12ca u12e8u12d5u12cdu1240u1275 u121bu12d5u12a8u120du1366
u12a5u1235u12a8 u1218u1295u1348u1233u12ca u12aeu120cu1305 u12a5u1295u12f2u12ebu12f5u130d u1273u1235u1266 u12e8u1270u1218u1220u1228u1270u1293 u1208u12a0u1283u1275 u12a0u1265u12ebu1270 u12adu122du1235u1272u12ebu1293u1275 u132du121du122d u12a0u1245u121d u12e8u121au1206u1295 u12e8u1270u12f0u122bu1300 u12e8u121du122du121du122du1293 u12e8u1275u121du1205u122du1275 u121bu12d5u12a8u120du1362
* u1218u1220u1228u1270 u120du121bu1275u1366
u12a8800 u1260u120bu12ed u1218u12aau1293 u121bu1246u121au12eb (Parking) u12ebu1208u12cdu1293 u1260u1218u1200u120d u12a8u1270u121b u12e8u121au1308u129d u1230u134a u12edu12deu1273u1362
ud83dudcc5 u12e8u1240u1325u1273 u1235u122du132du1275 u12e8u1308u1262 u121bu1230u1263u1230u1262u12eb (Livestream Fundraising)
u12edu1205u1295u1295 u1273u122au12abu12cau1293 u1218u1295u1348u1233u12ca u1270u124bu121d u12f3u122d u1208u121bu12f5u1228u1235 u1260u12d3u1208u121d u12d9u122au12eb u12e8u121au1308u1299 u12a6u122du1276u12f6u12adu1233u12cdu12ebu1295 u1201u1209 u1260u1308u1295u12d8u1263u1278u12cdu1363 u1260u12d5u12cdu1240u1273u1278u12cdu1293 u1260u1338u120eu1273u1278u12cd u12a5u1295u12f2u1233u1270u1349 u1325u122a u1240u122du1267u120du1362
* u1218u130bu1262u1275 12 u12a5u1293 13 u1240u1295 2018 u12d3.u121d
(March 21 & 22, 2026)
* u1208u1201u1208u1275 u1240u1293u1275 u12e8u121au1246u12ed u12e8u1240u1325u1273 u1235u122du132du1275 u12e8u1308u1262 u121bu1230u1263u1230u1262u12ebu1362
ud83dudcde u1208u1270u1328u121bu122a u1218u1228u1303u1293 u12f5u130bu134d
* u12a0u12f5u122bu123bu1366
6509 Riggs Road Hyattsville, MD 20782
* u1235u120du12adu1366 301-559-4656
* u12f5u1228-u1308u133du1366 WWW.HMKMEOTC.ORG
\
7 months ago
ማንም ኢትዮጵያዊ የፈለገውን ሀይማኖት እምነት የመከተል የማምለክ መብት
የኢፊድሪ ህገመንግስት
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690
መግቢያ #ethiopia | ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ በኢትዮጵያ ያሉ ሀይማኖቶች እኩል መብት ደረጃ በህገመንግስቱ እደል የተሰጣቸው በመሆኑ በእኩልነት ህገመንግስታዊ የእኩልነት መብታቸውን ተጠቅመው የፈለጉትን ሀይማኖት የመከተል የማምለክ መብት እንዳላቸው በህገመንግስቱ አንቀጽ 27 ላይ ተደንግጎ የተቀመጠ ነው። እኛም በዚህ ጽሁፍ ማንም ሰው የፈለገውን ሀይማኖት በግልም ሆነ በአንድነት ሆኖ የማምለክ መብት አለው ሲባል እስከ ምን ድረስ ነው የሚለውን እንመለከታለን።
1. ማንም ሰው
ማንም ሰው ማለት ዘር፣ብሔር በአመለካከት ልዩነት ሳይለይ በፈለገው ሀይማኖት በግሉም ሆነ በቡድን ሆኖ የማምለክ መብት አለው ለማለት ተፈልጎ ነው።
2. የሀይማኖቶች እኩልነት
ሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሀይማኖቶች ሙስሊም፣ክርስትያኑ በሙሉ ህገመንግስቱ በፈቀደላቸው ወይም በሰጣቸው እድል መሠረት በየትኛው ቦታ ሆነው ፈጣሪያቸውን እንደ የእምነታቸው ስረአታቸው ማምለክ ይችላሉ።
3. ከመንግሥት ምን ይጠበቃል?
መንግስት የእኩልነት መብት የማረጋገጥ ግዴታ አለበት። ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩልነት የማምለክ ስረአታቸውን እድል እንዲጠቀሙ እኩል ምቹ ሁኔታን መጠበቅ አለበት። አንዱን ሀይማኖት አስበልጦ ሌላውን ሀይማኖት አሳንሶ ሳይሆን ሁሉንም ሀይማኖቶች በእኩል የማየት ግዴታ ያለበት ሲሆን ይህም ህገመንግስታዊ ነው።
4. መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ ናቸው
በህገመንግስቱ አንቀጽ 11 መሠረት መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ መሆናቸውንና አንዱ በአንዱ ጣልቃ በመግባት ስልጣንና አካሄዳቸውን ሊሻማ ሊወስድ ሊያውክ ሌላ ተጽእኖ ሊወስድ፣አላግባብ ሊያስር፣ሊገድል ሌላም አላስፈላጊ ተጽእኖ ከማድረግ ከመቆጠብ ማንም ሀይማኖት በፈለገው ሀይማኖት የማምለክ ሊጠብቅ የመንግስት ግዴታ ሲሆን የሀይማኖት ተቋምም በመንግሥት አሰራር ስልጣን ውስት በመግባት መንግስት በሚሰራው ስራ ላይ ጣልቃ ከመግባት መቆጣብ በህገመንግስቱ የተቀመጠ ግዴታ ነው።
5. ከሀይማኖቶች ምን ይጠበቃል?
ሀይማኖቶች የራሳቸውን እምነት ስረአታቸው በሚፈቅድላቸው መሠረት ሲያካሂዱ የሌላውን ሰው እምነት፣የዜጎችን መብት የመንግስትን ህልውና የሚፈታተን ከተሰጣቸው የመብት ወሰን ሳያልፉ እምነታቸውን የማምለክ ስረአታችን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል።
6. አሁን ላይ የእምነት ተከታዮች የማምለክ መብት ተጨባጭ ሁኔታ ምን ይመስላል?
አሁን ላይ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ እና በታወቁ ዜናዎች እንደምንሰማው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ልጆች በተደጋጋሚ ለሞት የተዳረጉ ሲሆን በተለይም ካህናት፣ቄስ፣ምእመናን ከዚህ በፊት እንደተከሰተው አሁንም በአርሲ የተከሰተ ሲሆን በድጋሚም በወሎ በተመሳሳይ የኦርቶዶክስ ልጆች በጥይት የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ህይወታቸው ያለፈ እንዲሁም በርካታ የቆሰሉ እንዳሉም ተገንዝበናል፤ ይህ ኢ ህገመንግስታዊ ድርጊት ነው።
7. የመንግስት ህግ የማስከበር ኃላፊነት እና ግዴታ
ሀይማኖቶች በህገመንግስት የተሰጣቸውን መብት በመጠቀም ስረአቱ በሚፈቅድላቸው ልክ ሊያመልኩ ሊከተሉ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህ እንዲሆን ከስጋት ተጠብቀው የመኖር መብታቸው ተረጋግጦ የፈለጉትን ሀይማኖት ስረአት እንዲከተሉ መንግስት የሰላም ጸጥታ ድህንነት ስራ ሊያስጠብቅ ያስፈልጋል።
ከዚህም ባለፈ ዜጎቹ ሲሞቱ የማንኛውም ሀይማኖት ተከታይ ቢሆን ለደረሰባቸው ሞት ዜጎቹ እንደ መሆኑ መጠን ተገቢውን ክብር በመስጠት እውቅና ሊሰጥ ይገባል። ይህ አለመሆኑ የመንግስት ኀላፊነት ተጠያቂነትን የሚያስከትል በመሆኑ እና ከዲሞክራሲያዊ ስረአተ መንግስት አካሄድ ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ይህን በአንክሮ በመመልከት ሊያስተካክል ይገባዋል።
8. የህግ ምክር
ሀይማኖቶች በህገመንግስቱ አንቀጽ 11፥25፥27 ላይ በተሰጣቸው የማምለክ መብት መሰረት ሀይማኖታቸው በሚፈቅድላቸው ስረአት መሠረት ማምለክ የሚችሉ ሲሆን ይህንን መንግስት የማስጠበቅ ግዴታ አለበት። ሀይማኖቶችም ይህ መብታቸው ሲጠበቅላቸው በተነጻጻሪ የሌላውን መብቶችን ባከበረ መልኩ ስረአታቸውን ሊፈጽሙ ያስፈልጋል።
ማጣቀሻ/References/
የኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 11፥25፥27
የዩቲዮብ ገጽ
/ eotctv
➽ የፌስ ቡክ ገጽ
/ eotctvchannel
➽የቴሌግራም ገጽ
https://t.me/eotctvcha...
➽ የቲክ ቶክ ገጽ
https://vm.tiktok.com/...
➽ የዩቲዮብ ገጽ Eotc tv 2
• EOTC TV 2 |
➽የትዊተር ገጽ
/ eotct
➽የኢንስታግራም ገጽ
https://www.instagram....
https://t.me/Fantahunlawye...
https://www.facebook.com

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ 13ኛው በዓለ ሢመት ዛሬ በድምቀት ይከበራል
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስድስተኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ ወደ መንበረ ፓትርያርክነቱ የመጡበት 13ኛው ዓመት የሢመት በዓል ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
በአዲስ አበባ በሚገኘው በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚከናወነው በዚህ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት ላይ፦
* ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
* የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣
* ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣
* ዲፕሎማቶችና በርካታ ምዕመናን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል
በዕለቱ የቅዱስነታቸውን የ13 ዓመታት ጉዞና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደራዊና መንፈሳዊ አገልግሎቶች ላይ ያከናወኗቸው ተግባራት የሚዘከሩ ሲሆን፣ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ መርሐ ግብሮችም ይከናወናሉ።
ቅዱስነታቸው በ2005 ዓ.ም ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #አቡነ_ማትያስ #በዓለ_ሢመት #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤተክርስቲያን #መንበረ_ጸባዖት #eotc #abunemathias #ethiopia

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት "ድረ-ገጽ" ይፋ ሆነ
#ethiopia | የቅዱስ ፓትርያርኩን “ሐዋርያዊ አገልግሎት ፤ አባታዊ ትምህርት ፤ ወቅታዊ መረጃዎችና ታሪካዊ ሰነዶችን” የሚያቀርብ ድረ-ገጽ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ይፋ ተደረገ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ፤ የቅዱስነታቸውን የዕለት ከዕለት ሐዋርያዊ ተግባራት አባታዊ መመሪያዎች፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን እና የቤተክርስቲያኒቱን ዘመናዊና ታሪካዊ ክንውኖች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽ የሚያደርግ አዲስ ድረ-ገጽ በይፋ ሥራ ማስጀመሩን አስታወቀ።
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት eotcp.org በሚል አድራሻ ይፋ ያደረገው ይህ ዲጂታል መድረክ፤ ከመደበኛ የዜና ማሰራጫነት ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊና መንፈሳዊ መረጃዎች በአንድ ማዕከል አደራጅቶ የያዘ “ዲጂታል መረጃ ማዕከል” ሆኖ ያገለግላል፡፡
ይህ አዲስ ድረ-ገጽ ከመንበረ ፓትርያርክ የሚወጡ ይፋዊ መግለጫዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች ለምዕመናን የሚደርሱበት አማራጭም ይሆናል ተብሏል፡፡
በድረ-ገጹ የቅዱስ ሲኖዶስ ዓመታዊ ጉባኤያት ውጤቶችና መመሪያዎች ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ የሚቀመጡ በመሆናቸው መረጃዎችን ከወሬና ከግምት ባለፈ በቀጥታ ከምንጩ ለማግኘት እንደሚያስችል ተጠቁሟል፡፡
የብፁዕ ወቅዱስፓትርያርኩን ዕለታዊ ክንውኖችና አባታዊ ትምህርቶችንም ድረ-ገጹ ሠፊ ሽፋን ሰጥቷቸዋል።
በዚህም በድረ-ገጹ “ቃለ በረከት” በሚለው ክፍል ሥር የቅዱስነታቸው መንፈሳዊ መመሪያዎች በጽሑፍ ተቀምጠው የሚገኙ ሲሆን፣ “ዜና መዋዕል” በሚሰኘው ገጽ ደግሞ የፓትርያርኩን ታሪካዊ ጉዞዎችና ዓበይት ኩነቶች በዝርዝር ማግኘት የሚያስችል ነው፡፡
ይህም ምዕመናን ስለ ብፁዓን ወቅዱሳን አባቶቻቸው ሐዋርያዊ አገልግሎት ወቅታዊና ተአማኒ መረጃ እንዲኖራቸው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተመልክቷል።
የቅዱስ ፓትርያርኩ ሐዋርያዊ አገልግሎት የቤተክርስቲያናችን ታሪክ አካል እንደመሆኑ በሁለት ዋና ዋና ዘርፎች ተከፍሎም በዚሁ ድረ-ገጽ ቀርቧል።
የሀገር ውስጥ አገልግሎቶችን በተመለከተም በአህጉረ ስብከት የሚደረጉ ጉብኝቶችና በዓላት አከባበር በስፋት የሚዘገብበት ሲሆን ፣ የውጭ አህጉር ሐዋርያዊ ጉዞዎች ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ተጽዕኖና የወንጌል ሥርጭት በሚወክል መልኩ የሚሰፍርበት ይሆናል ተብሏል፡፡
ከመረጃ ሥርጭት ባለፈ ድረ-ገጹ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ራሱን ለዘመናዊ የመረጃ ፍሰት ክፍት ማድረጉን የሚያሳዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችንም አካቷል።
በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች የተዘጋጀው ይህ ድረ-ገጽ ፣ ከተለያዩ ማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ጋር ቀጥተኛ ትስስር ያለው በመሆኑ ምእመናን መረጃዎችን ዘመኑን በዋጀ መልኩ እንዲያገኙ ያግዛል።
በተጨማሪም በስልክ፣ በኢሜይልና በፖስታ ሣጥን ቁጥር አማካኝነት ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሚደረግበት “ያግኙን” የሚሰኝ የግንኙነት መስመርም በድረ-ገጹ በግልጽ ተቀምጧል።
በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት በኩል ይፋ የሆነው ይህ ዲጂታል መድረክ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ያሏትን ሠፊ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ለዓለም ለማስተዋወቅና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው፡፡
ድረ-ገጹ ይፋ መሆኑን አስመልክተው መረጃ የሰጡን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፀሐፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ ድረ-ገጹ እውን እንዲሆን በሃገር ውስጥና በባህር ማዶ የሚገኙ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች በብር እስከ 400 ሺህ የሚገመት በሙያቸው እና በሌሎችም መልኮች አስተዋጾ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
የቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናንና መረጃ ፈላጊዎች eotcp.org በመግባት ትክክለኛውንና ይፋዊውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መረጃዎች እንዲከታተሉም የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፀሐፊ መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ኃይለ ገብርኤል ነጋሽ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በምሥራቅ አርሲ የተደገመው ሰቆቃ፡ የንጹሐን ደም በገዛ ቀያቸው ፈሰሰ!
በምሥራቅ አርሲ ዞን መርቲ አቦምሳ ወረዳ፣ ፈረቀሳ ቀበሌ ውስጥ የካቲት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሊቱን በታጣቂዎች በተፈጸመ አረመኔያዊ ጥቃት፣ የንጹሐን ዜጎች ሕይወት በግፍ መነጠቁ ተሰማ። ይህ ጥቃት ሰላማዊ አርሶ አደሮችን ኢላማ ያደረገ ሲሆን፣ በአካባቢው ነዋሪዎችና በሃይማኖት ተቋማት ዘንድ ትልቅ ድንጋጤንና መሪር ሐዘንን ጥሎ አልፏል።
የጥቃቱ ሰለባዎችና የደረሰው ውድመት
ጥቃቱ ማንነትንና እምነትን መሠረት ባደረገ መልኩ የተፈጸመ ሲሆን ሦስት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች እና አንድ ሙስሊም ወንድማችን በታጣቂዎቹ በግፍ ተገድለዋል።
ከ10 በላይ የሚሆኑ የኦርቶዶክሳውያን አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች የእህል ጎተራዎች እና ከብቶች ሙሉ በሙሉ በእሳት እንዲጋዩ ተደርጓል።
የሶማሌ እና የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሣዕ በደረሰው አሰቃቂ ድርጊት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸው ለሚመለከተው የመንግሥት አካል የሚከተለውን ጥብቅ ጥሪ አስተላልፈዋል፦
"መንግሥት በእነዚህ ሕገ-ወጥ ታጣቂዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን ኃላፊነቱን በአስቸኳይ እንዲወጣ እንጠይቃለን።"
ይህ ሰላማዊ ሰዎችንና የሃይማኖት ተከታዮችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል። ለተገደሉት ወገኖቻችን መታሰቢያ ይሆን ዘንድ እንዲሁም መሰል ግፎች በዝምታ እንዳይታለፉ ይህንን መረጃ በማጋራት የንጹሐን ድምፅ እንሁን።
ምንጭ፦ EOTC TV

8 months ago
በሃዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች እንድረስላቸው! 💔🙏
"ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ" (ሮሜ 12:15)
#ethiopia | በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ አካባቢ በሚገኘው የኮየ ፈንታ ደብረ ፀሐይ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በበዓለ ጥምቀት ዕለት በአሳዛኝ የኤሌክትሪክ አደጋ አራት ወጣት አስተባባሪዎችን ማጣታችን ይታወሳል።
እነዚህ ወጣቶች በበዓሉ ድምቀት ሰረገላ በማዘጋጀት እና በማጓጓዝ ላይ እንዳሉ በኤሌክትሪክ ንኪኪ በተከሰተ አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ማህበረሰቡን በእጅጉ አሳዝኗል።
ይህ ክስተት የወጣቶቹን ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል። በተለይም፦
ከሟቾች መካከል የአቶ አበበ ተፈራ ባለቤት የ9 ወር ነፍሰ ጡር መሆናቸውና ልጆቻቸውም አሁን ካሉበት ቤት በኪራይ ምክንያት እንዲወጡ መደረጋቸው፤
የሟች አቶ ፍቃዱ ተክለየስ ቤተሰቦች የሚመገቡት የሌላቸው 5 ቤተሰቦች በችግር ላይ መውደቃቸው፤
ሌላኛው ሟች አቶ ሄሮጳ ማሞ የቤተሰቡ አስተዳዳሪና ብቸኛ ደጋፊ በመሆኑ ቤተሰቡ በከፍተኛ ሃዘንና ችግር ውስጥ መገኘቱ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል።
ስለሆነም እነዚህን የተቸገሩ ቤተሰቦች ለመርዳት ከጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ የካቲት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
ለተጎጂ ቤተሰቦች ተብሎ በተከፈተው የጋራ የባንክ አካውንት ድጋፍዎን ማድረግ ይችላሉ፦
💰 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000742754247
💰 አቢሲኒያ ባንክ፦ 249319147
የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሚደረገው የቀጥታ ስርጭት ላይ በመሳተፍና ይህን መልዕክት ለሌሎች በማጋራት የድርሻዎን እንዲወጡ በትህትና እንጠይቃለን።
ፈጣሪ ለሟቾች መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን!
#emergencyappeal #charityethiopia #supportfamilies #humanitarianaid #eotc #communitysupport #ethiopiahelp

ሦስት የቤተክርስቲያን የዕውቀት መዛግብት በአንድ ላይ ተመረቁ
#ethiopia |የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕውቀት ምሶሶ የሆኑት፣ የ98 ዓመቱ ዕድሜ ባለጸጋ ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ እና መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ ያዘጋጇቸው ሦስት አዳዲስ መጽሐፍት ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በድምቀት ተመርቀዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ ለንባብ የበቁት መጽሐፍት በሁለቱ ሊቃውንት የተዘጋጁ ሲሆኑ፣ ይዘታቸውም የሚከተለው ነው፦
✅ ሦስቱ ሐዲሳት (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የቤተክርስቲያንን ጥልቅ ትርጓሜ ለትውልድ የሚያስተላልፍ።
✅ ሃይማኖተ አበው (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የሊቃውንቱን የዘመናት ዕውቀት የሰነቀ መሠረታዊ መጽሐፍ።
✅ የጸሎት መጽሐፍ Prayer Book - The Oriental Orthodox Church (በመጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ): በዓለም አቀፍ ቋንቋ የተዘጋጀ የጸሎት መጽሐፍ።
🔹ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ ከ50 በላይ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቁ አንጋፋ ሊቅ ናቸው። በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ልማት በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅነታቸው የሚታወቁት ሊቁ፤ በቅዳሴ፣ በቅኔና በሐዲሳት መጽሐፍት ትርጓሜ ያላቸውን ጥልቅ ዕውቀት ለትውልድ ለማሻገር በ98 ዓመት ዕድሜያቸውም በትጋት ላይ ይገኛሉ።
🔹መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ የቅኔና የሐዲሳት መምህር ሲሆኑ፣ እስካሁን 13 መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያንና ለሀገር አበርክተዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ መጽሐፍቱን የተመለከተ ሒሳዊ ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን፤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተክሌ ዝማሜ፣ የበገና መዝሙራት እና በልዩ የቅኔ ድግስ ታጅቦ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
#ethiopia #eotc (Ethiopian Orthodox Tewahedo Church) #booklaunch #ethiopianliterature #churchfathers #gheezliterature #religiousbooks

⛪️የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን የልማት ሥራዎች በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተመረቁ! ✨
#ethiopia | "ይህ ሥራ የምዕመናን አንድነትና ለቤተክርስቲያን ያላቸው ፍቅር ውጤት ነው" - ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጉለሌ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ሲከናወኑ የቆዩ የልማት ሥራዎች ተጠናቀው ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል።
በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ፣ የሀድያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፤ የተሰራው የልማት ስራ ለአገልግሎት ምቹ ሁኔታን ከመፍጠሩም በላይ ለሌሎች አድባራትም ትልቅ ምሳሌ መሆኑን መስክረዋል።
የስኬቱ ሚስጥር:
እነዚህ የልማት ሥራዎች ከጅምሩ እስከ ፍፃሜው ድረስ በምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና የሞራል ተነሳሽነት የተከናወኑ መሆናቸው ተገልጿል።
በእለቱም ለልማቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
ለቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች እና ለደብሩ ምዕመናን እንኳን ደስ አላችሁ!
#eotc #straphael #gulele #churchdevelopment #abunehiryakos #addisababa #ethiopianorthodox #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ተመረቀ!
#ethiopia | "ለቤተክርስቲያናችን ቀዳሚ የሆነው ይህ ፕሮጀክት በብፁዓን አበው ቡራኬ ተከፍቷል"
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ አየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን፤ በቡልቡላ መንገድ ያሠራው ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ (EV Charging Station) በዛሬው ዕለት በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
የምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ድምቀት:
በምርቃቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ (የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ)፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ (የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ) እና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ) እንዲሁም ሌሎች ብፁዓን አበው እና የቤተክህነት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የፕሮጀክቱ ልዩነት:
ይህ የልማት ተቋም ከመደበኛ የነዳጅ አቅርቦት በተጨማሪ፤ ዓለም ወደ ደረሰበት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ቴክኖሎጂ የገባ መሆኑ ለቤተክርስቲያኒቱ የልማት ስራዎች ፈር ቀዳጅ ያደርገዋል።
ለቤተክርስቲያኒቱ እና ለምእመኑ እንኳን ደስ አላችሁ!
EOTC TV
#eotc #development #stgeorgechurch #bolebulbula #evcharging #fuelstation #addisababa #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ አየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቡልቡላ መንገድ ያሠራው ለቤተክርስታያናችን ቀዳሚ የሆነው የነዳጅ ማደያ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ሰብሳቢ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የደቡብ ምሥራቅ ትግራይና የራያ አህጉረ ስብከት፣ ሊቀ ጳጳስ፣ በመንበረ ፓትርያርክ የቅርሳ ቅርስ ጥበቃና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሙዚየም መምሪያ የበላይ ኃላፊ እና የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀገረ ሀዲያ እና ሥልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናውኗል ።
በዝግጅቱ ላይ ንቡረእድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ምሕረት ቆሞሰ አባ ገብረመድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነብርሃን የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ መልአከ ሰላም ይትባረክ አሰፌ የቦሌ አየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ
፣የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎችና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ኃላፊዎች የአድባራት እና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
የነዳጅ ማደያው ከነዳጅ ምርቶች በተጨማሪ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ ቻርተር የተካተተበት ዘመናዊ የተሽከርካሪ አገልግሎት መስጫ ነው።
©Eotc tv

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመጀመሪያው ዘመናዊ የነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማደያ ተመረቀ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ አየር ማረፊያ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በቡልቡላ መንገድ ያስገነባውና በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ቀዳሚ የሆነው ዘመናዊ የነዳጅ ማደያ እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ በይፋ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
🌍 ዓለም አቀፍ ተሞክሮና የቤተክርስቲያን ልማት
ይህ ዓይነቱ የቤተክርስቲያን የልማት ተሳትፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደና ውጤታማነቱ የተመሰከረለት ነው። ለምሳሌ፦
በእንግሊዝ (Church of England): በርካታ አብያተ ክርስቲያናት በአሁኑ ወቅት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ (EV Chargers) በግቢያቸው ውስጥ በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለገቢ ማስገኛነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
በቫቲካን (Vatican City): ቫቲካን ሙሉ በሙሉ በታዳሽ ኃይል ለመጠቀም በምታደርገው ጥረት፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችንና የኃይል መሙያ ማዕከላትን በስፋት በማስገንባት ግንባር ቀደም ሆናለች።
በግሪክና ሩሲያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት: አብያተ ክርስቲያናቱ ሰፋፊ መሬቶቻቸውን ለነዳጅ ማደያ፣ ለገበያ ማዕከላትና ለኢንዱስትሪዎች በማዋል ራሳቸውን ለመቻል የሚጠቀሙበት ዋነኛ መንገድ ነው።
የፕሮጀክቱ ይዘት
ዘመናዊ የነዳጅ አገልግሎት: ቤንዚንና ናፍጣ።
የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ: ለዘመናዊ መኪኖች ተመራጭ አገልግሎት።
ገቢ ማመንጫ: ለደብሩ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች ቋሚ የገቢ ምንጭ።
👥 የምርቃቱ ታዳሚዎች
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና ሌሎች ከፍተኛ የቤተክርስቲያኒቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
"ቤተክርስቲያናችን በመንፈሳዊው አገልግሎት ጎን ለጎን በልማት ሥራዎች ራሷን መቻልና ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩሏን ድርሻ መወጣት እንዳለባት ማሳያ ነው" — ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
ምንጭ፦ EOTC TV / የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ ባለውለታና መንፈሳዊ አባት አጣች። የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው ተሰምቷል።
ብፁዕነታቸው በሀገር ውስጥ በነበራቸው ሐዋርያዊ አገልግሎት ብቻ ሳይወሰኑ፣ በኢየሩሣሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ለብዙ ዓመታት ቤተክርስቲያንን በታማኝነት አገልግለዋል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለEOTCTV እንደገለጸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የገዳማት መምሪያ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ የብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ሥርዓተ ቀብር ነገ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተማሩበት በመነኮሱበት እና ለረጅም ዓመታት ባገለገሉበት በታላቁ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ይፈጸማል።
ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን።
seledadotio

9 months ago
✨ የሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል አዲሱ ቤተ መቅደስ ተመረቀ! ✨
#ethiopia | "በ240 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ ዕንቁ!"
በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ውበት በሆነው ሲኤምሲ (CMC) አካባቢ፤ ለዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው አዲሱ እና ግርማ ሞገስ የተላበሰው የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ህንጻ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ምን አለው?
🏛 ልዩ የኪነ-ህንጻ ጥበብ:
ጥንታዊውን የኢትዮጵያ የኪነ-ህንጻ ጥበብ ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር አዋህዶ የያዘ እና በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንን በአንዴ መያዝ የሚችል።
💰 የምእመናን ትብብር ውጤት:
ከ240 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይህ ህንጻ፤ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ምእመናን እንዲሁም በበጎ አድራጊዎች የተሰራ የህዝብ እምቅ አቅም ማሳያ ነው።
📚 ሁለገብ አገልግሎቶች:
ዘመናዊ የአስተዳደር ቢሮዎች እና መሰብሰቢያ አዳራሾች።
ለወጣቶች እና ህጻናት የሰንበት ትምህርት ቤት ክፍሎች እና ቤተ-መጻሕፍት።
ለጸሎት ምቹ የሆኑ አረንጓዴ ስፍራዎች እና ሰፊ የመኪና ማቆሚያ።
ለዚህ ቅዱስ ተግባር አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋችሁን ይክፈላችሁ! እንኳን ለቤቱ ምረቃ አብሮ አደረሰን
#eotc #stmichael #cmc #churchinauguration #addisababa #ethiopia #orthodoxtewahedo

🌿 የቃና ዘገሊላ በዓል በታሪካዊቷ ጎንደር በድምቀት እየተከበረ ነው!
#ethiopia | "ውሃውን ወደ ወይን የለወጠበት ተአምር በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት እየተዘከረ ነው"
የጥምቀት በዓል ማሳረጊያ የሆነው የቃና ዘገሊላ በዓል በጎንደር ከተማ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።
የበዓሉ ድባብ:
በዓሉ በተለይ በጎንደር አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ በልዩ ክብር የሚከበር ሲሆን፤ የዕለቱን ታላቅነት የሚዘክሩ ያሬዳዊ ወረቦችና ጣፋጭ የቤተክርስቲያን መዝሙራት በሊቃውንቱ እየቀረቡ ነው።
የአባቶች ቡራኬ:
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ፤ ከበርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እና የሃይማኖት አባቶች ጋር በመሆን ለህዝቡ ትምህርት እና ቡራኬ ሰጥተዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በቦታው ተገኝተው በረከቱን እየተካፈሉ ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!
#kanazegelila #gondar #eotc #timket #ethiopianorthodox #abuneyohannes #celebration

⚫ አሳዛኝ ዜና! 4 የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወታቸው አለፈ 🕯️
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የሀዘን መግለጫ አስተላለፉ።
#ethiopia | በሸገር ሀገረ ስብከት በኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ በፋንታ መድሃኔዓለም ደብር አገልጋይ የሆኑ 4 ወጣቶች በኤሌክትሪክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
ለሐዋርያዊ አገልግሎት ጎንደር የሚገኙት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፤ በተፈጠረው አደጋ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸው፡-
"ወጣት ልጆቻችን ሕይወታቸውን እንዳጡ ስንሰማ ታላቅ ሐዘን ተሰምቶናል። ልዑል እግዚአብሔር ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንዲሰጥልንና ነፍሳቸውንም ከአብርሃ፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጎን እንዲያኖርልን የዘወትር ጸሎታችን ነው።"
ለቤተሰብ እና ለወዳጆች መጽናናትን እንመኛለን!
ነፍስ ይማር! 🙏
#eotc #condolence #abunesawiros #sheger #sadnews #ethiopia

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው
* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል
* የአእላፋት ዝማሬ ቀን የአእላፋት ቅዳሴ ቀን ይሆናል::
* የቅዳሴ ተሰጥዎ ትምህርት ዐቢይ ጾም ላይ ይጀምራል
#ethiopia | 3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተካሔደ:: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ የአዲስ አበባ የሐዲያና ሥልጤ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት በዚህ ዝማሬ ላይ የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የጉባኤ መምህራን ፣ ሰባኪያንና ዘማርያን እንዲሁም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ታድመዋል::
የአእላፋት ዝማሬው በጃን እስጢፋኖስ በመሐረነ አብ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን ጸሎተ ወንጌል ደርሶ የዕለቱ ወንጌል በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ ተነብቦ የሰርክ ኪዳን ደርሶአል:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዶ/ር አካለ ወልድ ተሰማ የተመራው ጉባኤው በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ቃለ ምዕዳን ተከፍቶአል::
ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው "ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንት ጀምሮ በቅዱስ ያሬድ ዜማ በሊቃውንት ድርሰት በዓለ ልደትን ከዋዜማው በመነሣት ሌሊቱን በቅኔ ማኅሌትና በሥርዓተ ቅዳሴ ሐዋርያዊ ትውፊትን ጠብቃ በዝማሬ ስታከብር ኖራለች ዛሬም እያከበረች ትገኛለች፡፡ ይኽንኑ ፍጹም መንፈሳዊ የሆነ የተቀደሰ ትውፊት መሠረት በማድረግ፣ በጌታችን ልደት በዓልምእመናን በተለይም ወጣቶች ከመንፈሳዊ ሥርዓት ውጭ በአልባሌ ቦታዎች ቀኑንና ሌሊቱን እንዳያሳልፉ፣ መዝሙራትን አጥንተው፣ ከዋክብት ብሩሃንን ሆነው የጌታችንን ልደት በምስጋና ለመቀበል መሰባሰባቸው የሚያስመሰግንና በረከትን የሚያሰጥ የተቀደሰ ተግባር ነው" ብለዋል::
የአእላፋት ዝማሬ መድረክ በጥንታዊው የክብ ቤተ ክርስቲያን ቅርፅ የተሠራ ሲሆን በደመራ ቦታው ላይ ደግሞ የቤተልሔም ግርግምን የልደት የብራና ሥዕል በማድረግ ምእመናን ወደ ተወለደበት ሥፍራ ሕሊናቸውን እንዲመልሱ የሚያደርግ ሆኖአል::
ሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ በብፁዕ ሥራ አስኪያጁ አብሣሪነት በይፋ የተከፈተ ሲሆን በጃን እስጢፋኖስ ዲያቆናት ወረብ ተከፍቶ ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረዋል:: በሁለተኛ ዙር ከዲያቆናት "መድኃኒነ ተወልደ ነዋ" የሚል ወረብ በማስከተል ዐሥራ አምስት መዝሙራት ተዘምረው በበኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ "እንደ ቸርነትህ" ጸሎት ተደርጎ በሰላም ተጠናቅቆአል:: የአእላፋት ዝማሬው ላይ የታደሙት ምእመናን ቁጥራቸው ከተጠበቀው በላይ ቢሆንም የጸጥታ አካላትን ባስደነቀ ፍጹም ሰላማዊ መንፈስና በእርጋታ ወደየ በአታቸው ሔደዋል:: በዕለቱ የታደሙ ምእመናን የጧፍ መባቸውን ለታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ሠጥተዋል::
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ዘንድሮ በመስቀል አደባባይ ያካሔደውን የአእላፋት ዝማሬ በድኅረ ሁነት ውይይቱ በጥንቃቄ የገመገመ ሲሆን እግዚአብሔር ቢፈቅድ የአእላፋት ዝማሬን ወደ አእላፋት ማሕሌትና የአእላፋት ቅዳሴ ለማሳደግ ሲያወርግ የነበረውን ጥረት በ2019 ዓ.ም. የአእላፋት ዝማሬ ላይ ዕውን ለማድረግ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና ብፁዓን አባቶችን በማማከር ድምዳሜ ላይ ደርሶአል::
የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ መካሔዱ የታየው አዲስ ነገር የአደባባዩ ጠባይ ፣ የተሳታፊው ብዛት ፣ ሰልፍና ፍተሻው የሚወስደው ታሳቢ ሆኖ ጸሎትና ዝማሬው ብቻ አምስት ሰዓታትን የሚወስድ መሆኑ ፣ ሕዝቡ ከአደባባዩ ለመውጣት የሚፈጅበት ጊዜ ከአክፍሎትና ወደየአጥቢያው ለመድረስ ከሚደረግ ጉዞ ጋር አዳጋች እንደሚሆን ተስተውሎአል::
በዚህ ምክንያት ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬ አንድ ቀን ቀድሞ በዋዜማው ዋዜማ እንዲደረግና በዋዜማው ዕለት ደግሞ የአእላፋት ቅዳሴ ዘመቻ እንዲጀመር ተወስኖአል:: ይህ መደረጉም ማሕሌት የሚቆሙ ምእመናን ከአእላፋት ማግሥት ዕረፍት አድርገው እንዲቆሙ ፣ ወደ ቅዱስ ላሊበላና ወደ ሌሎች ቅዱሳት መካናት ጉዞ የሚያደርጉም ተሳትፈው በማግሥቱ በረራዎች እንዲሔዱ እንዲሁም ልደትን በቅዳሴ አሳልፈው የማያውቁም በዋዜማው ዝማሬ መንፈሳቸው ለቅዳሴ እንዲዘጋጅና በየአጥቢያው ሔዶ እንዲያስቀድስ ያበረታታል::
የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ቅዳሴ በተሰኘው ፕሮጀክቱ አማካኝነት ቅዳሴ ለማስተማር ትምህርታዊ ቪድዮ ከመማሪያ ሞጁል ጋር ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ሲሆን የአእላፋት ሳምንት ዐውደ ርእይ ላይ በ3D Model የቅዳሴ ትዕይንት ለብዙኃን ማስጎብኘቱም ይታወቃል:: ከመጪው ዐቢይ ጾም ጀምሮ ይህንን የቅዳሴ ተሰጥኦ ትምህርት ለምእመናን በይፋ የሚጀምር ሲሆን በ2019 ዓ.ም. በአእላፋት ዝማሬ ላይ የታደመውን ሕዝብ ያህል በየአጥቢያው በቅዳሴ ላይ ተገኝቶ የዝማሬውን ድምፅ በተሰጥዎ ድምፅ እንዲደግም ለማድረግ ዕቅድ ተይዞአል:: ጃን ቅዳሴ ከ፳፬ቱ የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ሦስት ዙር የቅዳሴ ተሰጥዎ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቆአል:: በተቋማት ደረጃ የቅዳሴ ተሰጥዎ ለመማር ጥያቄ ላቀረቡ የሙያ ማኅበራትም እንዲሁ ከሥራ ሰዓታቸው ጋር የተስማማ የመማሪያ መርሐ ግብር ነድፎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የጃን ቅዳሴ ሰብሳቢ ዲያቆን ኃይለ ኢየሱስ ተሻለ ገልጸዋል::
በመስቀል አደባባይ የተካሔደውን ሦስተኛውን የአእላፋት ዝማሬ ከቀደሙት ሁለት የአእላፋት ዝማሬዎች እጅግ የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ምእመናን የታደሙበት ሲሆን በኦንላይን ደግሞ ሚልዮኖች ተመልክተውታል:: የEOTC TV ፣ ሀገሬ ቲቪ ፣ አርትስ ቲቪ ፣ ቃና ቲቪ ፣ ፋና ቲቪ ፣ ኢቢሲ ፣ አሶሽየትድ ፕሬስ ፣ BBC ፣ ሮይተርስ ፣ ዶቼቬሌ ፣ ቪዮሪ ቲቪ ፣ ስፖትኔክ ሬድዮ ለሦስተኛው የአእላፋት ዝማሬ ሽፋን የሠጡ ሚድያዎች ናቸው::
የኢትዮጵያ ጃንደረባው ትውልድ
#እንዳላስቀድስ_የሚከለክለኝ_ምንድነው #የአእላፋት_ዝማሬ #ሠረገላው_እንዲቆም_አዘዘ

የአእላፋት ዝማሬ ወደ የአእላፋት ቅዳሴ ሊያድግ ነው::
ጃንደረባው ሚድያ | ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
* የአእላፋት ዝማሬ በዋዜማው ዋዜማ እንዲካሔድ ተወስኖአል
* የአእላፋት ዝማሬ ቀን የአእላፋት ቅዳሴ ቀን ይሆናል::
* የቅዳሴ ተሰጥዎ ትምህርት ዐቢይ ጾም ላይ ይጀምራል
3ኛው የአእላፋት ዝማሬ በመስቀል አደባባይ በተሳካ ሁኔታ ተካሔደ:: የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና የሸገር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የማኅበራት ምዝገባና ክትትል መምሪያና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ፣ የአዲስ አበባ የሐዲያና ሥልጤ አህጉረ ስብከቶች ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት በዚህ ዝማሬ ላይ የየመምሪያው ኃላፊዎች ፣ የጉባኤ መምህራን ፣ ሰባኪያንና ዘማርያን እንዲሁም በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ታድመዋል::

በዚህ ምክንያት ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ የአእላፋት ዝማሬ አንድ ቀን ቀድሞ በዋዜማው ዋዜማ እንዲደረግና በዋዜማው ዕለት ደግሞ የአእላፋት ቅዳሴ ዘመቻ እንዲጀመር ተወስኖአል:: ይህ መደረጉም ማሕሌት የሚቆሙ ምእመናን ከአእላፋት ማግሥት ዕረፍት አድርገው እንዲቆሙ ፣ ወደ ቅዱስ ላሊበላና ወደ ሌሎች ቅዱሳት መካናት ጉዞ የሚያደርጉም ተሳትፈው በማግሥቱ በረራዎች እንዲሔዱ እንዲሁም ልደትን በቅዳሴ አሳልፈው የማያውቁም በዋዜማው ዝማሬ መንፈሳቸው ለቅዳሴ እንዲዘጋጅ ያበረታታል::

10 months ago
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባልታወቀ ምክንያት በተነሳ እሳት ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደሙ ተገለጸ።
በደቡብ አፍሪካ የቬንዳ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በቃጠሎ አደጋ መውደሙ ተሰምቷል።
በደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት የምትገኘው የቬንዳ ቅዱስ ሩፋኤል መቃኞ ቤተክርስቲያን በትላንትናው ዕለት በደረሰ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ መውደሟ ተረጋግጧል።
ቃጠሎው የተነሳው በሌሊት በመሆኑና በወቅቱ እርዳታ ማግኘት ባለመቻሉ፣ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ የነበረው ንብረት ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋው መነሻ እስካሁን አልታወቀም።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን ብርሃኑ ተክለያሬድ በአደጋው ሥፍራ ተገኝተው ምእመናንን አጽናንተዋል ።
ይህ በመንፈሳዊ አገልግሎቱና በምዕመናን አንድነት የምትታወቀው ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰው አደጋ በደቡብ አፍሪካ ለሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ታላቅ ሃዘን ሆኗል።
© Eotc Medhanalem

Comments