Logo
Getu Temesgen
የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" መጽሐፍ ተመረቀ

​#ethiopia |​በኦቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላለፉት 48 ዓመታት የነበራቸውን የላቀ ልምድና የፈጠራ ሥራዎች የሚተርከው የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ተመርቋል።

በሀራ ኢቨንትስ አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኦቶሞቲቭ፣ ከኢነርጂ፣ ከአካዳሚክ እና ከመንግሥት የሥራ ዘርፎች የተወጣጡ ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

​ይህ መጽሐፍ ደራሲው በዘርፉ ያሳለፉትን ረጅም ዓመታት ጉዞ የሚዳስስ ሲሆን፣ በተለይም ስለ ወደፊቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ፣ ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ስለ ዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂዎች ጥልቅ ዕውቀትና ግንዛቤን የሚያካፍል መሆኑ ተገልጿል።

በምረቃው ወቅት በመስኩ ያሉ የኢንዱስትሪ መሪዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የታደሙ ሲሆን፣ ደራሲው ዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ ከመጽሐፉ ይዘት ባሻገር ካላቸው ሰፊ ልምድ በመነሳት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ

​#theroadtodetroit #drashenafietsegaye #automotiveindustry #booklaunch #innovation #futuremobility #ethiopia #addisababa #technology #successstory

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.