Logo
Getu Temesgen
"ወይኔ ብዙ ሰው ታድሟል፤ እግዚአብሔር ይስጣችሁ!"
- ብርቱካን ሚደቅሳ
#ethiopia | ​የቀድሞዋ የፖለቲካ ሰው እና የህግ ባለሙያ ወይዘሮ ብርቱካን ሚደቅሳ "መመለስ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፋቸውን ትናንት ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም አስመረቁ።

​በምርቃቱ ዕለት ፊታቸው በደስታ ሲያበራ የነበሩት ወይዘሮ ብርቱካን፤ አዳራሹን የሞላውን 821 ታዳሚ ሲመለከቱ በፈገግታ እና በመደነቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

292 ገጾች ያሉት ይህ መጽሐፍ ለንባብ በመብቃቱ "እፎይ አልኩ" ሲሉ እፎይታቸውን ገልጸዋል።

​የመጽሐፉ ይዘት እና አስተያየቶች፡-
በ34 አጫጭር እና ጣፋጭ ርዕሶች የተዋቀረው ይህ መጽሐፍ፤ በይኩኖአምላክ መዝገቡ እና በመሠረት አበጀ አርታኢነት የተዘጋጀ ነው።

​በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኪነ-ጥበብ እና የስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች ስለ መጽሐፉ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡-

📚 ህይወት ተፈራ፣ መዓዛ ወርቁ፣ ቴዎድሮስ አጥላው እና ዳዊት ብርሃኑ መጽሐፉ የግድ መነበብ ያለበት መሆኑን በሙሉ አንደበታቸው መስክረዋል።

​#birtukanmideksa #memeles #newbook #booklaunch #ethiopia

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.