10 days ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን AHEFT ሽልማትን ተቀበለ
#ethiopia | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የተዘጋጀውን Africa Higher Education for Transformation (AHEFT) Prize በመጀመሪያው ዙር ከተሸለሙ አምስት የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንዱ ሆኖ ተቀብሏል።
ሽልማቱ በተቋማዊ ደረጃ ዘላቂ ለውጥ በማምጣት ላይ ያሉ የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ ሲሆን፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሽልማቱን ያገኘው በምርምርና ፈጠራ ዘርፍ ባሳየው ተቋማዊ ለውጥና እድገት ነው።
ዩኒቨርሲቲው ሽልማቱን መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም. በጋና አክራ በተካሄደው የመጀመሪያው Higher Education Transformation Convening ላይ ተቀብሏል። መድረኩ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችን፣ የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮችን፣ የመንግሥት ተቋማትን፣ የፋይናንስና የግል ዘርፍ አጋሮችን፣ የልማት አጋሮችን እና ወጣቶችን አሰባስቧል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የቡርኪና ፋሶው International Institute of Water and Environmental Engineering፣ የጋናው Kwame Nkrumah University of Science and Technology፣ የዩጋንዳው Muni University እና University of Rwanda የ2026 የAHEFT Prize ተሸላሚዎች ሆነዋል።
እያንዳንዱ ተሸላሚ ተቋም ለወጣቶች የትምህርት ዕድሎችን ለማስፋትና ተቋማዊ ለውጥን ለማጠናከር ሥራዎቹን እንዲያስፋፋ 3 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያገኛል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመድረኩ በተቀዳ የቪዲዮ መልዕክት የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ወጣቶችን ለወደፊቱ ዓለም ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊቱን ዓለም እንዲቀርጹ የማስቻል ኃላፊነት እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተዋል።
የAHEFT ሽልማት በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ ተማሪዎችን ወደ ሥራ ዓለም በማሸጋገር እና በጤና ውጤቶች ላይ ዘላቂ ተቋማዊ ለውጥ እያመጡ ያሉ የአፍሪካ ተቋማትን ለመደገፍ የተጀመረ ዓመታዊ ሽልማት ነው።
በ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የተደገፈው መርሐ ግብሩ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ቢያንስ 150 የአፍሪካ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እውቅና ለመስጠት ያለመ ነው።
በአክራው መድረክ የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት፣ የምርምር፣ የፈጠራ እና የችግር ፈቺ ሐሳቦች ማዕከላት ሆነው ሊያበረክቱ ስለሚችሉት ሚና ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱም በተለይ በከፍተኛ ትምህርት፣ በኢንዱስትሪና በማኅበረሰብ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር፣ ወጣቶችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ፈጣሪና መሪ እንዲሆኑ ማስቻል እና ምርምርን ወደ ኢንዱስትሪና ማኅበረሰብ ማድረስ ላይ አተኩሯል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያዎቹ የAHEFT Prize ተሸላሚዎች አንዱ መሆኑ፣ በመማርና ማስተማር፣ በምርምርና ፈጠራ፣ በአጋርነት እና ለወጣቶች ዕድል በመፍጠር የሚያከናውናቸውን ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች ለማጠናከር የሚያግዝ እውቅና ሆኗል።
#aau #education #africa #aheft #mastercardfoundation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

21 days ago
1 month ago
የምዝገባው ቀን ነገ ማለትም ነሐሴ 29/2018 ዓ/ም ይጠናቀቃል። ይሄ መልካም ዕድል እንዳያልፋችሁ።
በሚከተለው ሊንክ ኦንላይን መመዝገብ ትችላላችሁ:-
https://admission.aau.edu....
በሚከተለው ሊንክ ኦንላይን መመዝገብ ትችላላችሁ:-
https://admission.aau.edu....
2 months ago
የዶክተር ደረጀ ዘለቀ የሁለት ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት በሀገር ፍቅር ቴአትር ተከናወነ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህርና ተመራማሪ የነበሩት የዶክተር ደረጀ ዘለቀ ህልፈተ ሕይወት ሁለተኛ ዓመት መታሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አዳራሽ ተካሂዷል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ የስራ ባልደረቦች፣ ተማሪዎች፣ ጋዜጠኞችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ የዶክተር ደረጀን በጎ ስራዎች የሚያስታውሱ ንግግሮች፣ የክራር ድምፀ ውበት፣ መነባንብ እና የተለያዩ የኪነ ጥበብ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በዕለቱ ንግግር ያደረጉ እንግዶች አባታቸው፣ ወዳጃቸውና መምህራቸው የነበረው ዶክተር ደረጀ በህግ ትምህርት ዘርፍ የነበረውን የጠለቀ እውቀትና ያበረከታቸውን የጥናትና ምርምር ስራዎች አውስተዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በስሙ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን "የዶክተር ደረጀ መታሰቢያ አፀደ ህፃናትና ቤተ መጻሕፍት" ለመደገፍ የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህራን፣ ከድርጅቶችና ከግለሰቦች ጋር በመተባበር በህግ ምርምር ላይ ለተሰማሩ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግና በየዓመቱ የህግ ትምህርት ውድድር ለማዘጋጀት እቅድ መያዙን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
በዛሬው መርሃ ግብር ለህፃናት አፀደ ህፃናትና ቤተ መጻሕፍቱ ግብዓት የሚሆኑ በርካታ መጻሕፍትና የመማሪያ ቁሳቁሶች ከተሳታፊዎች መሰብሰብ ተችሏል።
ይትባረክ ዋለልኝ
#drderejezeleke #memorialprogram #aau #lawschool #hagerfikirtheatre #charity #education #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
2 months ago
ተለቀቀ
#ethiopia | ቴዎድሮስ አምዴ ለ16 ዓመታት የደከመበት «ምስክር» የተሰኘው የኢትዮ-ጃዝ አልበም ለሕዝብ ተበሰረ
በሀገራችን የድራም ሙዚቃ አጨዋወት ከፍተኛ ስም ያተረፉት የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ አምዴ 11 የኢትዮ-ጃዝ ሥራዎችን ያካተተውን «ምስክር» የተሰኘ አዲስ አልበም በናሆም ሬከርድስ የዩቲዩብ ቻናል አማካኝነት በይፋ አስተዋውቀዋል።
ይህ አልበም ለጥናት፣ ለልምምድና ለፈጠራ ሂደቱ በአጠቃላይ 16 ዓመታትን የወሰደ ሲሆን፣ ለሀገራችን የሙዚቃ ዘsector ልዩና አዲስ ኦሪጅናል የጃዝ አልበም እንደሆነ ተገልጻል።
በዚህ ሥራ ላይ 8 ታዋቂ የቤዝ ጊታር ተጫዋቾችን (አብይ ሰለሞን፣ ሄኖክ ተመስገን፣ ዳግማዊ አሊ እና ሌሎችንም ጨምሮ) በሊድ ጊታር፣ ኪቦርድ፣ ትሮምቦን እና ፍሉት የታወቁ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
በተጨማሪም የሙዚቃ ባለሙያው ቴዎድሮስ አምዴ የደብል ቤዝ ድራም አጨዋወትን ያለ አስተማሪ ለመማር የሚያስችል ባለ 218 ገጽ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ለአንባቢዎች ያቀረበ ሲሆን፣ መጽሐፉ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍትና በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ይገኛል።
ልዩ መታሰቢያ ይህ አልበም በሥራው ዝግጅት ወቅት አብረው ለሠሩትና አሁን በሕይወት ለሌሉት ታዋቂው የትራምፔት ተጫዋች ሻምበል መኮንን መርሻ እና የቤዝ ጊታር ተጫዋች ፋሬው መንግስቱ መታሰቢያነት የተበረከተ ነው።
https://youtube.com/playli...
#ethiojazz #tewodrosamde #misikir #nahomrecords #ethiopianmusic #doublebassdrum #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

AAU ከ500 በላይ ሰራተኞቹን አሰናበተ‼️
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት መብቱን ለመተግበር ባደረገው የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት ከ500 በላይ አስተዳደራዊ ሰራተኞች እና 50 መምህራን ያለ ምደባ ቀርተዋል።
ይሁን እንጂ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ማንም ሰራተኛ እንዳልተባረረ ገልጸው፣ የተጎዱት በጡረታ፣ በካሳ ወይም በቅርቡ በሚጀመሩ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደሚካተቱ አረጋግጠዋል።
ምደባው ለአስተዳደር ሰራተኞች በፈተና፣ ለመምህራን ደግሞ በትምህርት ዝግጅት አግባብነት ላይ ተመስርቶ የተከናወነ ነው።
በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚዘጋጁት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል።
Seledadotio

3 months ago
3 months ago
u12e8u12a0u12f2u1235 u12a0u1260u1263 u12e9u1292u1268u122du1232u1272 u12e8u1270u121bu122au12ceu127d u121du1228u1243 u1225u1290 u1225u122du12d3u1275
#aau #addisbabauniversity #graduation ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዓት
#aau #addisbabauniversity #graduation
4 months ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች አመልካቾችን መቀበል ጀምሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለ Masters ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች እንዲሁም ለ PhD ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች አመልካቾችን ይቀበላል፡፡
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞቹን ዝርዝር በ https://admission.aau.edu.... መመልከት ይችላሉ፡፡
አመልካቾች በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መውሰድና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የ GAT ማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ የሕይወት ተሞክሮ ላይ የሚያተኩር አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቃ
#ethiopia | በአይናለም አዱኛ (ዶክተር) የተሰናዳውና በውጭ አገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕይወትና ተግዳሮቶች ላይ የሚያጠነጥነው "Walking Between Worlds: Letter to the Next Generation of the Ethiopian Diaspora" የተሰኘው መጽሐፍ በይፋ ተመርቋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትናንት በተከናወነው የገበያ ማቅረቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፣ ታዋቂ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና በርካታ የክብር እንግዶች ታድመዋል።
በዕለቱም በምሁራንና በተሳታፊዎች አማካኝነት ስለ ዲያስፖራው ማኅበረሰብ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
ለአምስት አሥርት ዓመታት ገደማ (ከ38 ዓመታት በላይ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የኖሩት ደራሲዋ ዶክተር ዓይናለም አዱኛ፣ መጽሐፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ስለ አገራቸው በቂ ዕውቀት እንዲኖራቸውና የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በስደት ዓለም ያሳለፉትን የረጅም ጊዜ የሕይወት ተሞክሮና ገጠመኝ መሠረት በማድረግ ያዘጋጁት ይህ መጽሐፍ ለሌሎች ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ዶክተር ዓይናለም ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር ማከናወናቸውንና እንዲህ ዓይነቱ አበረታች ሥራ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተጻፈው ይህ መጽሐፍ ባለ 480 ገጽ ሆኖ ለንባብ መብቃቱ ታውቋል።
#diaspora #ethiopiandiaspora #booklaunch #aau #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 months ago
"ታዲያስ ሰይፋ" ምሽት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ!
ሰይፉ ፋንታሁን የክብር እንግዳ ነው!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ለ53ኛ ጊዜ የሚያዘጋጀው ታላቅ የኪነ-ጥበብ ምሽት ረቡዕ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።
የዘንድሮው ምሽት ልዩ የሚያደርገው፣ ተወዳጁ የሚዲያ ሰውና የ"ታዲያስ አዲስ" ፕሮግራም አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን የክብር እንግዳችን ሆኖ በመካከላችን መገኘቱ ነው።
ሰይፉ ፋንታሁን ሙያዊ ልምዱንና የስኬት ጉዞውን ለታዳሚው ያካፍላል።
ግጥሞች፣ ወግ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ በባህል ማዕከል አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ ይቀርባሉ።
ዝግጅቱ ከቀኑ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ይጀምራል።
ሰይፉ ፋንታሁን በኢትዮጵያ ሚዲያ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያረፈ ሰው ነው። ከእሱ ልምድ መማርና በኪነ-ጥበብ ምሽት መታደም ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን፣ ለአዲስ አበባ ስነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን ትልቅ ዕድል ነው።
ሼር በማድረግ እንተባበር፤ ኪነ-ጥበብን በጋራ እናክብር!
#getu #seyfufantahun #tadiyasseyfa #aau #culturecenter #artnight #literatureethiopia #poetrymusicmonologue #አዲስአበባዩኒቨርሲቲ #ባህልማዕከል #ሰይፉፋንታሁን #ኪነጥበብ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
የነገው የጤና ተስፋዎች
📌የዶ/ር መቅደስ ዳባ መልዕክት ለተመራቂዎች
#ethiopia | የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚንስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት የምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ለተመራቂ ተማሪዎች ደማቅ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር መቅደስ በንግግራቸው ወቅት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጤናው ዘርፍ ጥራትና ለባለሙያዎች ደህንነት የሰጠውን ትኩረት አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል። ሚኒስትሯ በዋናነት የሚከተሉትን ነጥቦች አንስተዋል፡-
* የትምህርት ጥራትና ማሻሻያ፡ ከአካዳሚክ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የህክምና ትምህርትን የማዘመንና የሬዚደንሲ ፕሮግራሞችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑን።
* የሆስፒታል ሪፎርም፡ በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማሻሻልና የስፔሻሊቲ እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ስልጠናዎችን ተደራሽ ለማድረግ በትጋት እየተሰራ እንደሚገኝ።
* የባለሙያዎች ደህንነት፡ በተለይም የሬዚደንቶችን የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻልና አበረታች የስራ ሁኔታን ለመፍጠር ልዩ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።
ይህ ምርቃት በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ ላይ አዳዲስ አቅሞችን እንደሚጨምር የታመነ ሲሆን፣ ተመራቂዎችም በታማኝነትና በሙያ ስነ-ምግባር ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ethiopia #healthministry #aau #medicalgraduation #doctormekdesdaba #healthcareethiopia #futuredoctors

9 months ago
🏆 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በምስራቅ አፍሪካ 1ኛ ደረጃን ያዘ!
🎓
#ethiopia | "የ75 ዓመት የዕውቀት ጎታው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጠናውን መራ!"
ሰሞኑን 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ የሚገኘው አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ በዘንድሮው የ"QS World University Rankings" መሰረት ከምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 1ኛ ደረጃን በመያዝ አኩሪ ድል አስመዝግቧል።
የምስራቅ አፍሪካ "Top 4" ደረጃ:
1️⃣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ኢትዮጵያ)
2️⃣ ማካሬሬ ዩኒቨርሲቲ (ዩጋንዳ)
3️⃣ ናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ (ኬንያ)
4️⃣ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካርቱም (ሱዳን)
ለምን ተመረጠ?
እንደ አፍሪካን ኢንሳይደር ዘገባ፤ ደረጃው የተሰጠው በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቀጠናው ልማት ላይ ባበረከቱት አስተዋፅኦ ነው።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተለይም በሂውማኒቲስ፣ በሶሻል ሳይንስ፣ በኢንጂነሪንግ እና በጤና ሳይንስ ዘርፎች በሰራቸው ጠንካራ ስራዎች ቀዳሚ ሊሆን ችሏል።
ለ75 ዓመታት የኢትዮጵያ የዕውቀት የጀርባ አጥንት ሆኖ ፖሊሲ አውጪዎችን እና ምሁራንን ያፈራው ተቋማችን እንኳን ደስ አለህ!
የዚህ ታላቅ ተቋም ምሩቃን እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! 👏
#aau #addisababauniversity #numberone #eastafrica #education #ethiopia #qsworldranking #75thanniversary

10 months ago
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቀረበ
#ethiopia | “ያለፈውን በማክበር የተሻለ ነገን ማለም” (Honoring Our Past Reimagining Our Future) በሚል መሪ ቃል 75ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹን (Alumni) ወደ “ቤታችሁ ኑ’ በሚል መርህ ከታህሳስ 18-24፤ 2018 ዓ.ም. ለተዘጋጀው ፕሮግራም በመላው አለም ለሚኖሩ የቀድሞ ተማሪዎቹ ጥሪ አቀረበ።
75ኛ የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በያዝነው ህዳር እና ታህሳስ ወር በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚያከብር ዛሬ ህዳር 18፣ 2018 በዩኒቨርሲቲው ግቢ በተሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫውን የሰጡት ዶ/ር መሳይ ገ/ማርያም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሉምናይ ቢሮ ዳይሬክተር፣ ወ/ሮ ሀና ደምሴ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚዲያ አማካሪ እንዲሁም ዘሪሁን ብርሃኑ (ረ/ፕ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ት/ት መምህር እና የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት የሚዲያ አማካሪ ናቸው። 75ኛ የአልማዝ ኢዩቤልዩ በዓሉን በተመለከተ ዛሬ እና ነገ (ህዳር 18 እና 19) ከሚደረገው የባለ ድርሻ አካላት ውይይት እንዲሁም ቅዳሜ ህዳር 20 ከሚጀምረው የዩኒቨርሲቲዎች የእግር ኳስ ውድድር ጀምሮ በርካታ ፕሮግራሞች ተሰናድተዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን የ75 ዓመታት ጉዞ እና ታሪክ የሚሰንድ መፅሀፍ በዩኒቨርሲቲው እውቅ ምሁንራ የሚዘጋጅ ሲሆን በዋናነት ዩኒቨርሲቲው ያለፈበትን የሰባ አምስት ዓመታት ታሪክ ይዘክራል።
ከዚህ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው በዘመን ጉዞ ውስጥ፣ በክፍል ውስጥ ከሚደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶች ባሻገር በሀገሪቱ ተለዋዋጭ የፖለቲካ እና የታሪክ ለውጦች ውስጥ የነበረውን ከፍተኛ ሚና አጉልቶ የሚያሳይ፣ አሁን የደረሰበትን የራስ ገዝነት አቋም እና ሁኔታ እንዲሁም ወደፊት ለመጓዝ የተለመውን መንገድ በሰፊው የሚያስቃኝ ዶኩመንታሪ እየተዘጋጅ ይገኛል።
ከነዚህ የታሪክ ስነዳዎች ባሻገር መነሻውን አራት ኪሎ አድርጎ እስከ ዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የሚደረግ የእግር ጉዞ የሚኖር ሲሆን ጉዞው ከቦታ ዳሰሳ ባሻገር የዩኒቨርሲቲውን ሰፊ ታሪክ የሚያይሳዩ የተለያዩ የቴአትር፣ ሙዚቃ፣ ስዕል ፣ ትረካ እና ልዩ ልዩ የጋራ የክዋኔ እንቅስቃሴዎች ይኖሩታል።
በተጨማሪም በተማሪዎች መሃል የሰባ አምስት ዓመት ልቀት በሰባ አምስት ሰኮንዶች (75 years of excellence in 75 seconds) የተሰኘ ሽልማት የሚያስገኝ የአጭር ፊልም ውድድር የሚኖር ሲሆን ተማሪዎች ውድድሩ ተርማሪዎች ስለዩኒቨርሲቲው ያላቸውን ግንዛቤ ያሰፋል፣ ሃሳባቸው ኪነጥበባዊ መንገድን በመጠቀም እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው ያግዛቸዋል ተብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በርካታ ተማሪዎችን እና የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንዲሁም ሰፊውን ባለ ድርሻ አካላት የሚያሳትፉ ፕሮግራሞች ይኖራሉ።
የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በምርምር የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ተከታታይ ፓናል እና ኮንፈረሶችም የዝግጅቱ አካላት ናቸው።
በተከታታይ በሚደረጉ የአካዳሚክ ሴሚናሮች እና ፓናል ውይይቶች የሚቀርቡ ጥናቶች የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጪም ለሚገኙ ሁሉ ክፍት የሚሆን ሲሆን፣ የሚቀርቡት ርዕሰ ጉዳዮችም ከአካድሚያዊ የምርምር ርዕሰ ጉዳዮች ባሻገር በሀገራዊ አንገብጋቢ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎቹን ዳግም ማግኘት እና መወያየት እንደሚፈልግ የገለፁት አሰናጆቹ በመላው ዓለም የሚገኙ ማንኛውም የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ምሩቃን በ https://alumni.aau.edu.et/... ድረ ገፅ በመግባት መመዝገብ እንደሚችሉ በመገለጫው ጥሪ ተደርጓል።
በተለይ ደግሞ ከታህሳስ 18 እስከ 24 ለአንድ ሳምንት በሚደረገው የአልሙናይ ሳምንት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ደግሞ ልዩ የሆነ መመዝገብያ QR code የተዘጋጀ ሲሆን በጋዜጣዊ መግለጫውም ይፋ ተደርጓል።

12 months ago
የጤና ሚኒስቴር የህይወት ዘመን ተሸላሚ ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም
#ethiopia | የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ሽልማት ተሰጣቸው።
በጉራጌ ዞን በሙህርና አክሊል ወረዳ ተወለዱ።
የመጀመሪያ ደረጃና መልስተኛ 2ኛ ደርጃ ትምህርታቸውን በዲላ ከተማ አጼ ዳዊት ት/ቤት፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በይርጋዓለም ከተማ ራስ ደስታ ዳምጠዉ ክፍተኛ 2ኛ ድርጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የመጀመሪያና የማስተርስ ድግሪያቸውን በፋርማሲ ዘርፍ ከአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ፣ የፒ.ኤች ዲ. ድግሪያቸውን ከUniversity of Wales በፋርማሲ ዘርፍ በማዕርግ አግኝተዋል።
በጀርመን ሀገርም post-doctoral ምርምር አካሂደዋል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አግኝተዋል፡፡
ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ ከ30 ዓመታት በላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ የፋርማሲቲካል ዲፓርትመንት በኃላፊነት፣ የፋርማሲቲካል ትምህርት ቤት በዲንነት፣ የድህረ ምረቃ ጥናትና ምርምር በም/ፕሬዝዳንትነትነት ያገለገሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ በፋርማሲቲካል ቴክኖሎጂ ዘርፍ በምርምር፣ በማስተማር እና በማማከር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የቂሊንጦ ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ፓርክ ፍኖተ ካርታ ዝግጅት ላይ፣ የባዮቴክኖሎጂ R&D እቅድ እና ግብይት ስትራቴጂ ዝግጅት፣ የ10 ዓመት የኢትዮጵያ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ የሳይንስ አካዳሚ ብሔራዊ የምርምር ካውንስል ማቋቋሚያ ላይ የጋራ ስምምነት ጥናት፣ የብሔራዊ መድሃኒቶች ፖሊሲ ክለሳ ላይ ተሳትፈዋል፣ ባላቸው የላቀ የስራና የትምህርት ዝግጅት እንዲሁም ብሔራዊ እና ክልላዊ ስትራቴጂዎችን ለመቅረጽ አስተዋፅዖ ያደረጉ ቴክኒካል ሰነዶችን አዘጋጅተዋል።
በአ/አ/ዩ 50ኛ ኢዩቤልዩ በዓል በምርምር የወርቅ ሚዳልያ እና ሰርተፊኬት፣ የታዋቂዉና ታላቅ ክብር ያልዉን የጆርጅ ፎርስተር የምርምር ሽልማት፣ ከአሌክሳንደር ቮን ሁምቦልት ፋውንዴሽን ሽልማት አግኝተዋል፣ AAU የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህይወት ዘመን ምርጥ ተመራማሪ ሽልማት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የላቀ የፋኩልቲ ሽልማት፣ ሁምቦልት አምባሳደር ሳይንቲስት የወርቅ ሜዳሊያ ሽልማት፣ ከኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል ማኅበር ሽልማትንም አግኝተዋል፡፡
ከ50 በላይ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር የረጅም ጊዜ አቅም ግንባታን በድህር/ምረቃ ፕሮግራሞችን ምርምር ላይ አመቻችተዋል፡፡
ከ175 በላይ የምርምር ውጤቶችን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መሥራችና አባል፣ የአርማወር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሳይንስ አማካሪ ቦርዱ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም፤ የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡
ከጤና ሚኒስቴር

1 year ago
ስትገባም፤ ስትወጣም አይተንሃል!
* ብዙ መረጃና የጥናትና ምርምር ሥራዎቼን የያዘው ላፕቶፔን ተሰረቅሁ ውድ ኢትዮጽያዊያንተባበሩኝ!
(ይትባረክ ዋለልኝ)
#ethiopia | በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ግቢ ዉስጥ ከስድስት ወር በፊት የካቲት 27/2017 ዓ ም ከተማሪዎች ማንበቢያ ከፍል ላፕቶፑ የተሰረቀበትን የለማ ሚደቅሳን ታሪክ ምክንያት አድርጌ በዩንቨርስቲዉ የቴሌግራም ቻናል AAUMEREJA ላይ የወጣዉንም መረጃ አያይዤ ድርጊቱን ዘግቤዉ ነበር። ዛሬም የላፕቶፕ ኮምፒዉተር ስርቆት ቀጥሏል።
መሰረት ተጫኔ ትባላለች :: በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፓለቲካ ሳይንስ PhD ተማሪ ናት። ለህትመት የተዘጋጁ የጥናት ስራዎች : ለአመታት የደከመችበትን የጥናትና ምርምር ፅሑፎች: የመስክ የጥናት መረጃዎችን እንዲሁም በርካታ ዶክመንት የያዘውን lap top (DELL) ኮምፒዩተሯን ሐሙስ መስከረም 8/2018 ዓ ም የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ማንበቢያ ክፍል (PhD Students' Reading Room) ዉስጥ ተሰርቃለች። ስርቆቱ የተፈፀመዉ ከተቀመጠችበት ቦታ ተነስታ የማንበቢያዉ ክፍል በር ላይ ለሚጠብቃት ሰዉ መልእክት ለማድረስ በሄደችበት 4:16-4:22 ባለው በ6 ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ነዉ።
ተበዳዩዋም ድርጊቱ እንደተፈፀመ ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሚመለከተው ክፍል አመልክታለች። የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲም የሰረቀውን ግለሰብ የሚያሳይ #thief_caught_at_aau by Security Camera በድሕንነት ካሜራ የተቀረፀዉን ምስል እና ቪዲዮ ሰጥቷታል። በቪድዬ ላይ እንደሚታየው ከ4:16-4:22 በስድስት ደቂቃ ዉስጥ ወደ ማንበቢያ ክፍል ሲገባ ከዚያም ላፕቶፑን በሌላ ቦርሳ ይዞ ከሬጅስትራር የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ማንበቢያ ክፍል ይዞ ሲወጣ ይታያል ። ይሄ ሀሉ የሆነው እንግዲህ በ6 ደቂቃ ዉስጥ ነው።
በዚህ ምስል ላይ ያለሐው ግለሰብ ከ PHD ቤተ መጻሕፍት (ከዋናው ሬጅስትራር) የወሰድከውን PC ለደሕንነትሕ በማያሰጋ መልኩ ከዚሕ በታች በምናስቀምጥልሕ ስልክ ወይም በቴሌግራም በማዋራት እንድትመልስ እንጠይቃለን ፣ ይሕ ካልሆነ ግን በድሕንነት ካሜራ የተቀረፀ ምስል እና ቪዲዮ ስላለ በቀጣይ በማሕበራዊ ትስስር ገፆች ላይ የምንለጥፍ እና በሕግም የምንጠይቅህ ይሆናል።
በ PC' ውስጥ ብዙ የተለፋበት የምርምር ስራ ስላለው እንዲመለስልኝ ሁላችሁም ይሕን መልዕክት ለዚሕ ግለሰብ እንዲደርስ እባካችሁ ይህንን መረጃ ለሌሎች #share በማጋራት ተባበሩኝ!! አመሰግናለሁ!!
ባለ ንብረት፣ መሰረት ተጫኔ
ስልክ:- +251 91 172 4665

ኢትዮ ቴሌኮም እና ሁዋዌ በሰሜን አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የላቀ የ4G ቴክኖሎጂ ዘረጉ
#ethiopia | ኢትዮ ቴሌኮም እና ሁዋዌ በሰሜን አፍሪካ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የላቀውን "GigaAAU FDD Tri-Band Massive MIMO" የተሰኘው ቴክኖሎጂ በስራ ላይ ማዋላቸው ተገልጿል።
ይህ በዘርፉ ታሪካዊ ነዉ ተብሎ የተገለጸው መፍትሄ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ አፈጻጸም እና የተጠቃሚ ልምድ ላይ ከፍተኛ መሻሻል አስመጥቷል ተብሏል።
የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው፣ የ4G ትራፊክ ፍሰት በ70% ያደገ ሲሆን፣ አማካይ የኔትወርክ ፍጥነት ደግሞ በ68% ጨምሯል።
ይህም ተጠቃሚዎች ቪዲዮዎችን ያለመቆራረጥ እንዲመለከቱ፣ የኦንላይን ጨዋታዎችን ያለምንም ችግር እንዲጫወቱ እና ፋይሎችን በፍጥነት እንዲያወርዱ ማስቻሉንም ተመላክቷል።
የሁዋዌ GigaAAU ቴክኖሎጂ ሦስት የተለያዩ የኔትወርክ ባንዶችን (1.8 GHz፣ 2.1 GHz እና 2.6 GHz) በአንድ ላይ በማዋሃድ የኔትወርክ አቅምን ከማስፋት ባሻገር፣ የኃይል ቁጠባ ስርዓት በመጠቀም የኃይል ፍጆታን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተገልጿል።
ይህ ዘመናዊ መፍትሄ በዓለም ዙሪያ ከ20 በላይ ኔትወርኮች ላይ ተፈትኖና እውቅና አግኝቷል ሲል ካፒታል አስነብቧል።

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ታሪክ በኢንሳይክሎፔዲያ መልክ ሊዘጋጅ ነው
#ethiopia | የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር የጀግኖች አርበኞችን ታሪክ በሳይንሳዊ መንገድ ለማጥናትና በኢንሳይክሎፔዲያ መልክ ለማዘጋጀት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ነሐሴ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ የተዋደቁ አርበኞች ታሪክ በትክክለኛና በተሟላ መንገድ ተደራጅቶ እንዲሰነድና ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ያለመ ነው።
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ስምምነቱ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖችን ታሪክ በጥናትና ምርምር በሳይንሳዊ ዘዴ በመምራት ፣ በማዘጋጀት እና በማሳተም ለትውልድ ማስተላለፍ ጠንካራ አገራዊ አንድነት ለመፍጠርና ቀጣዩ ትውልድ ለአገሩ በአርበኝነት እንዲቆም በእጅጉ ያግዛል ሲሉ የጥናቱን ጠቀሜታ አብራርተዋል፡፡
በፊርማው ሥነሥርዓት ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው ጥናቱ ጥራቱን ጠብቆ አንዲካሄድ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው ተገቢውን ባለሙያ፣ ሃብትና አመራር እንደሚመድብ አስረድተዋል፡፡(AAU)

Comments