4 months ago
ሦስት የቤተክርስቲያን የዕውቀት መዛግብት በአንድ ላይ ተመረቁ
#ethiopia |የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዕውቀት ምሶሶ የሆኑት፣ የ98 ዓመቱ ዕድሜ ባለጸጋ ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ እና መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ ያዘጋጇቸው ሦስት አዳዲስ መጽሐፍት ዛሬ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ በድምቀት ተመርቀዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ ለንባብ የበቁት መጽሐፍት በሁለቱ ሊቃውንት የተዘጋጁ ሲሆኑ፣ ይዘታቸውም የሚከተለው ነው፦
✅ ሦስቱ ሐዲሳት (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የቤተክርስቲያንን ጥልቅ ትርጓሜ ለትውልድ የሚያስተላልፍ።
✅ ሃይማኖተ አበው (በርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ): የሊቃውንቱን የዘመናት ዕውቀት የሰነቀ መሠረታዊ መጽሐፍ።
✅ የጸሎት መጽሐፍ Prayer Book - The Oriental Orthodox Church (በመጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ): በዓለም አቀፍ ቋንቋ የተዘጋጀ የጸሎት መጽሐፍ።
🔹ርእሰ ሊቃውንት ክንፈርግብ ማርቆስ ከ50 በላይ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቁ አንጋፋ ሊቅ ናቸው። በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ልማት በሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅነታቸው የሚታወቁት ሊቁ፤ በቅዳሴ፣ በቅኔና በሐዲሳት መጽሐፍት ትርጓሜ ያላቸውን ጥልቅ ዕውቀት ለትውልድ ለማሻገር በ98 ዓመት ዕድሜያቸውም በትጋት ላይ ይገኛሉ።
🔹መጋቢ ምስጢር አማኑኤል መንግሥተአብ የቅኔና የሐዲሳት መምህር ሲሆኑ፣ እስካሁን 13 መጽሐፍትን ለቤተክርስቲያንና ለሀገር አበርክተዋል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ላይ መጽሐፍቱን የተመለከተ ሒሳዊ ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን፤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የተክሌ ዝማሜ፣ የበገና መዝሙራት እና በልዩ የቅኔ ድግስ ታጅቦ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
#ethiopia #eotc (Ethiopian Orthodox Tewahedo Church) #booklaunch #ethiopianliterature #churchfathers #gheezliterature #religiousbooks