4 months ago
የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia |በኦቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ውስጥ ላለፉት 48 ዓመታት የነበራቸውን የላቀ ልምድና የፈጠራ ሥራዎች የሚተርከው የዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ "The Road to Detroit" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ዛሬ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም በድምቀት ተመርቋል።
በሀራ ኢቨንትስ አስተባባሪነት በተዘጋጀው በዚህ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከኦቶሞቲቭ፣ ከኢነርጂ፣ ከአካዳሚክ እና ከመንግሥት የሥራ ዘርፎች የተወጣጡ ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህ መጽሐፍ ደራሲው በዘርፉ ያሳለፉትን ረጅም ዓመታት ጉዞ የሚዳስስ ሲሆን፣ በተለይም ስለ ወደፊቱ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ፣ ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ስለ ዘመናዊ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂዎች ጥልቅ ዕውቀትና ግንዛቤን የሚያካፍል መሆኑ ተገልጿል።
በምረቃው ወቅት በመስኩ ያሉ የኢንዱስትሪ መሪዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የታደሙ ሲሆን፣ ደራሲው ዶክተር አሸናፊ ጸጋዬ ከመጽሐፉ ይዘት ባሻገር ካላቸው ሰፊ ልምድ በመነሳት ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#theroadtodetroit #drashenafietsegaye #automotiveindustry #booklaunch #innovation #futuremobility #ethiopia #addisababa #technology #successstory

ቻይና የዓለማችን ቀዳሚዋ መኪና ላኪ በመሆን ታሪካዊ የበላይነትን ተቀዳጀች
#ethiopia | ቻይና ለረጅም ዓመታት በዘርፉ በጠነከሩት ጃፓን እና ጀርመን ተይዞ የነበረውን የገበያ የበላይነት በመስበር፣ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ላኪ ሀገር መሆኗ ተረጋግጧል። ይህ ስኬት በዓለም አቀፉ የመኪና ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ የኃይል ሚዛን ለውጥ ማምጣቱ ተነግሯል።
ሀገሪቱ ለኤሌክትሪክ መኪና ምርት በሰጠችው ከፍተኛ ትኩረት የኤክስፖርት መጠኗን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ችላለች።
የቻይና መኪና አምራቾች በባትሪ ቴክኖሎጂ፣ በአቅርቦት ሰንሰለት እና በዘመናዊ የፋብሪካ አውቶሜሽን ላይ ያደረጉት ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ውጤት አምጥቷል።
ጥራቱን የጠበቀና በዋጋው ተወዳዳሪ የሆነ ምርት ማቅረብ መቻሏ በዓለም ገበያ ተመራጭ አድርጓታል።
በአሁኑ ወቅት የቻይና መኪናዎች ወደ አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ገበያ በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
የዘርፉ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ቻይና ትኩረቷን በኤሌክትሪክ መኪናዎች ላይ ማድረጓ የዓለምን የመኪና ኢንዱስትሪ መልክ ሙሉ በሙሉ እየቀየረው ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #china #automotiveindustry #electricvehicles #globaltrade #ev #carexport #techinnovation #economy

7 months ago
''ቴስላ ውሃ በላው''
📌 የቻይናው BYD የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጭ ቴስላን በመብለጥ የዓለም ቀዳሚ ሊሆን ነው
#ethiopia | የቻይናው ግዙፍ ተሽከርካሪ አምራች BYD፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) ሽያጭ የኤለን መስኩን ቴስላ (Tesla) ኩባንያን በመብለጥ በዓለም ቀዳሚው አምራች ለመሆን መቃረቡ ተገለጠ።
ኩባንያው ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት፣ ዓመታዊ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽያጩ በ28 በመቶ እድገት በማሳየት 2 ነጥብ 25 ሚሊየን ደርሷል። ይህ ውጤት BYDን በዘርፉ ቁንጮ ላይ እንዲቀመጥ ያደርገዋል ተብሏል።
የቴስላ ፈተና እና የባለሙያዎች ትንበያ🔎
ቴስላ ዓመታዊ የሽያጭ ሪፖርቱን እስካሁን ይፋ ባያደርግም፣ የዘርፉ ባለሙያዎች ኩባንያው 1 ነጥብ 65 ሚሊየን አካባቢ ተሽከርካሪዎችን ሊሸጥ እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
ይህ ከሆነ ደግሞ ቴስላ ለረጅም ጊዜ ይዞት የቆየውን የመሪነት ስፍራ ለቻይናው ተፎካካሪው ያስረክባል ማለት ነው።
ቴስላ ለገጠመው የሽያጭ መቀነስና ለገበያ ድርሻ መጥበብ እንደ ምክንያቶች የተጠቀሱት፦
* የባለቤቱ የኤለን መስክ አወዛጋቢ ፖለቲካዊ ተሳትፎዎች።
* ከቻይና ተሽከርካሪ አምራቾች እየገጠመው ያለው ብርቱ የዋጋና የቴክኖሎጂ ፉክክር።
* በተለያዩ ሀገራት የታየው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ናቸው።
🚘 BYD በተለይም ዋጋቸው ተመጣጣኝ የሆኑ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አማራጮችን ለገበያ ማቅረቡ ለስኬቱ ትልቁን ድርሻ እንደያዘ ተመልክቷል። ይህ የገበያ ለውጥ የቻይና ኩባንያዎች በዓለም አቀፉ አረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር ውስጥ እያገኙት ያለውን የበላይነት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#byd #tesla #electricvehicles #evmarket #elonmusk #chinatech #automotiveindustry #greenenergy2026

Comments