1 month ago
«የእናቴ ሮሚዮ» መጽሐፍ ተመረቀ
#ethiopia | ከእውነተኛው ሕይወት ገጽታዎች የተቀዱ ውብ አጫጭር ታሪኮችን ያቀፈው የጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው «የእናቴ ሮሚዮ» መጽሐፍ ታዋቂ የሥነ ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ አርቲስቶችና በርካታ አንባብያን በተገኙበት በድምቀት ተመረቀ።
መጽሐፉ ከምርቃቱ ቀደም ብሎ ለአንባብያን የደረሰ በመሆኑ፣ በዕለቱ በሥራው ላይ ጥልቅ ግምገማና ዳሰሳ የቀረበ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ የተወሰዱ ታሪኮችም በታዋቂ ተዋንያን አማካኝነት በመድረክ ላይ ቀርበዋል።
ደራሲዋ መጽሐፉን አስቀድሞ ለንባብ ማብቃቷ አንባብያን ያዩትንና የተሰማቸውን በነፃነት እንዲገልጹ እንዲሁም ገንቢ ሂስና አስተያየት እንዲሰጡበት ሰፊ መድረክ የከፈተ መሆኑን ገልጻለች።
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረገችው ደራሲ ስመኝ ግዛው፣ መጽሐፉን ለመጻፍ ባሳለፈችበት ወቅት ከባድ የጤና እክል ይፈታተናት እንደነበርና ያንን ሁሉ የጽናት ጉዞ አልፋ ለዚህ በመብቃቷ እግዚአብሔርን አመስግናለች።
ለአንድ ደራሲ ከመነበብና በሥራው ላይ ውይይት ከመደረጉ በላይ ትልቅ ሽልማት የለውም ያለችው ደራሲዋ፣ በመጽሐፉ ውስጥ የትዳርና የቤተሰብ ሕይወት ተቋማዊ እሴቶችን ለመጠበቅና ማንኛውም አንባቢ ራሱን የሚያገኝበትን እውነተኛ ታሪክ ለማቅረብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጓን ተናግራለች።
አዳራሹን በነጻ ከመስጠት ጀምሮ እስከ ዝግጅቱ ማብቂያ ድረስ ከጎኗ ለቆሙ ድርጅቶችና ባልደረቦቿ፣ ለሀገር መከላከያ ማርች ባንድ ሙዚቀኞች፣ ለቤተሰቦቿ እንዲሁም ሁልጊዜም ከጎኗ ሆነው ለሚያበረታቷት ወዳጆቿ ልባዊ ምስጋናዋን አቅርባለች።
📷 ከበደ መክብብ
#yenateromeo #semegngizaw #amharicbooks #ethiopianliterature #booklaunch #ethiopianwriters #ethiopianauthors #amharicliterature #ethiopianarts #newbookrelease

Comments