4 months ago
"ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ያገባናል!"
- የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በኢትዮጵያ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲ የኤፕሪል የኦቲዝም መቀበልና ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን በሃገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚያከብር አስታወቀ።
ሶሳይቲው በመጋቢት 28 ቀን 2026 ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የዘንድሮው ወር "ስለኦቲዝም እንወቅ፣ ሁላችንም ስለኦቲዝም ያገባናል" በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር ገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
የተዛባ አመለካከትን መቀየር፦
ኦቲዝም እርግማንም ሆነ የኃጢአት ውጤት አለመሆኑን ማህበረሰቡ ሊገነዘብ እንደሚገባና ሚዲያዎችም ትክክለኛውን መረጃ ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተገልጿል።
የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጫና፦
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ወላጆች የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫና ለማቃለል የማህበረሰቡ ድጋፍና መቀበል ወሳኝ መሆኑ ተመላክቷል።
የአገልግሎቶች እጥረት፦
እንደ ስፒች ቴራፒ፣ ኦኩፔሽናል ቴራፒ እና የባህሪ ማስተካከያ ያሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች ለልጆቹ ዕድገት ወሳኝ ቢሆኑም፣ በሀገሪቱ ያለው የማዕከላት እጥረት ትልቅ ማህበራዊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።
የሚዲያ ሚና፦
መገናኛ ብዙሃን ስለኦቲዝም ልዩ ልዩ ዘገባዎችን በመስራት፣ አዎንታዊ ምስል በመፍጠርና የመብት ጥሰቶችን በማንሳት ግንዛቤ የማስጨበጫ ወሩን እንዲያከብሩ ተጠይቋል።
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሶሳይቲና የተለያዩ የኦቲዝም ማዕከላት (ጆይ ኦቲዝም፣ ነህምያ ኦቲዝም፣ የኛ ልጆች ኦቲዝም ማህበር እና ብሩህ ፋውንዴሽን) ወሩን ሙሉ ግንዛቤ በመፍጠርና ድጋፍ በመሰብሰብ ተግባራት ላይ እንደሚሰማሩ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣
እባክዎን በዚህ ስልክ ያነጋግሩ፡
መላኩ ብርሃኑ
የኢትዮጵያ ኦቲዝም ሲሳይቲ ቦርድ አባል
የኮሚዩኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ተጠሪ
ስልክ +251-911-403884
#getu #autismawareness #autismacceptancemonth #ethiopia #autismsocietyethiopia #inclusion #supportautism #addisababa #joyautismcenter #neahmiahautismcenter #ኦቲዝም #ግንዛቤ #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
ዳውን ሲንድረም እና ኦቲዝም ይለያያሉ?
#ethiopia | ምንም እንኳን ዳውን ሲንድረም እና ኦቲዝም ሁለቱም የዕድገት ውስንነቶች ቢሆኑም፣ በመንስዔያቸውም ሆነ በባሕሪ መገለጫዎቻቸው እጅግ የተራራቁ መሆናቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች አስታወቁ። እነዚህን ልዩነቶች ጠንቅቆ ማወቅ ለልጆቹ የሚደረገውን ድጋፍ ውጤታማ ለማድረግ ቀዳሚው ተግባር መሆኑ ተመላክቷል።
አካላዊ መገለጫ እና መንስዔ
ዳውን ሲንድረም በቀጥታ ከዘረ-መል (ክሮሞዞም) መብዛት ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በተለይም በ21ኛው ክሮሞዞም ላይ በሚፈጠር ተጨማሪ ቅጂ ምክንያት ይከሰታል። ይህም እንደ፦
* ጠፍጣፋ የፊት ገጽታ፣
* የአንገት ማጠርና የጡንቻ መላላት፣
* እንዲሁም ወጥ የሆነ የመዳፍ መስመርን የመሰሉ ግልጽ አካላዊ ምልክቶችን ያስከትላል።
በአንጻሩ የኦቲዝም መንስዔ በውል ባይታወቅም፣ ከአንጎል አወቃቀር እና ከነርቭ ሥርዓት ዕድገት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይታመናል። ኦቲዝም እንደ ዳውን ሲንድረም ግልጽ የሆነ አካላዊ መልክ የሌለው በመሆኑ፣ ልጆቹ ከሌሎች እኩዮቻቸው ጋር ተመሳሳይ የሰውነት ገጽታ አላቸው።
ማኅበራዊ መስተጋብርና ተግባቦት
ሁለቱ ሁኔታዎች በማኅበራዊ ግንኙነት ረገድ ተቃራኒ ባሕሪን ያንጸባርቃሉ። ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች በአብዛኛው፦
* ተግባቢና ከሰዎች ጋር መገናኘት የሚወዱ፣
* የሌሎችን ስሜት የመረዳት ፍላጎት ያላቸውና ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ በቀላሉ የሚቀላቀሉ ናቸው።
በተቃራኒው ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ከፍተኛ ፈተና ይገጥማቸዋል። ዓይን ለአይን መገጣጠም የሚከብዳቸው ሲሆን፣ ስሜታቸውን የመግለጽ ውስንነት ስላለባቸው ብዙ ጊዜ ብቸኝነትን ይመርጣሉ። በመግባቢያ ክህሎትም ረገድ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች ንግግር ቢዘገይባቸውም ለመግባባት ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ፤ ኦቲዝም ያለባቸው ግን የቋንቋ ዕውቀት ቢኖራቸውም እንኳ ያንን ለግንኙነት የመጠቀም ችግር ሊታይባቸው ይችላል።
የትምህርት አቀባበልና ተሰጥዖ
በትምህርት ረገድ ዳውን ሲንድረም ያለባቸው ልጆች በዕይታ የታገዙ ትምህርቶችን የመረዳት የተሻለ ብቃት አላቸው። በሌላ በኩል ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች በሒሳብ፣ በሥዕል ወይም በሙዚቃ ዘርፍ ልዩ ተሰጥዖ ሊኖራቸው ስለሚችል፣ የሚሰጣቸው ድጋፍ በባህሪ ለውጥ ሥልጠና ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለበት ባለሙያዎች ይመክራሉ።
አልፎ አልፎ ሁለቱም ሁኔታዎች በአንድ ልጅ ላይ ሊከሰቱ ስለሚችሉ፣ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በትኩረት በመከታተል የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባቸው ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #downsyndrome #autismawareness #specialneeds #ethiopia #healtheducation #inclusiveeducation

"ዮም"፦
በኦቲዝም ጥላ ሥር ያለ የሕይወት ተጋድሎና የተስፋ ስንቅ! ✨
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ሥር የሚኖርን ልጅ የማሳደግ ፈተና፣ የወላጆች የሥነ-ልቦና ጫና እና ማህበራዊ መገለልን የሚዳስሰው "ዮም" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በደመቀ ሁኔታ ተመርቋል።
የአባትነት ፍቅር፦
ደራሲው የ11 ዓመት የኦቲዝም ተማሪ የሆነው የዮም አባት ሲሆኑ፣ ልጃቸውን ለማሳደግ የከፈሉትን መስዋዕትነትና ያጋጠማቸውን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጫና በ254 ገጾች ተርከዋል።
የግንዛቤ ጥሪ፦
መጽሐፉ ማህበረሰቡ ለኦቲዝም ያለውን የተሳሳተ አመለካከት እንዲቀይርና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች በዕኩልነት እንዲቀበል ያሳስባል።
የመንግሥት ድርሻ፦
ለኦቲዝም ልዩ ትኩረት የሚሰጡ የትምህርትና የሕክምና ተቋማት እንዲስፋፉ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ መጽሐፍ ለወላጆች መመሪያ፣ ለባለሙያዎች ግብዓት፣ ለተስፋ ለቆረጡ ደግሞ የሞራል ስንቅ ነው!
ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ካልታወቀላቸውና ድጋፍ ካላገኙ በቤታቸው ተዘግተው እንዲቀሩ ይገደዳሉ። "ዮም" ይህንን ግድግዳ ሰብሮ በመውጣት ለውጥ ለማምጣት የመጣ የብርሃን መጽሐፍ ነው።
#ኦቲዝም #ዮም #አዲስመጽሐፍ #ግንዛቤ #ኢትዮጵያ #autismawareness #yombook #ethiopia #inclusion #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
📚 "ዮም"፦
በኦቲዝም ጥላ ሥር ያሉ ልጆችና የወላጆቻቸው የጽናት መስታወት! ✨
#ethiopia | በኦቲዝም ጥላ ሥር የሚኖሩ ልጆችን የማሳደግ ውጣ ውረድ፣ የወላጆች እሮሮ እና የጽናት ጉዞ እንደ መስታወት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል!
📖 ስለ መጽሐፉ፦
"ዮም" የተሰኘው ይህ መጽሐፍ በአቶ ንሴብሆ ፍቅሬ እና በወ/ሮ ሳምራዊት ድንቁ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የራሳቸውን ልጅ በማሳደግ ሂደት ውስጥ ያለፉበትን ፈታኝ መንገድና መሰል ኢትዮጵያውያን ወላጆች የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት ይዳስሳል።
🗓 የምረቃ ሥነ-ሥርዓት መርሃ-ግብር፦
ቀን፦ እሁድ የካቲት 22 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ
ቦታ፦ ሀይሌ ግራንድ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Haile Grand International Hotel)
🌟 የጥሪ መልዕክት፦
በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና እንግዶች የሚገኙ ሲሆን፣ እርስዎም በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ በመገኘት በኦቲዝም ጥላ ሥር ላሉ ልጆችና ለሚደክሙ ወላጆቻቸው ድምፅ እንዲሆኑ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
💰 ማሳሰቢያ፦
መጽሐፉ በዕለቱ በአዳራሹ መግቢያ በር ላይ ለሽያጭ የሚቀርብ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
"የኦቲዝም ልጆችን እና የወላጆቻቸውን የጽናት ጉዞ አብረን እንደግፍ!"
መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ።
#ዮም #ኦቲዝም #autismawareness #ethiopia #booklaunch #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
1 year ago
🇺🇸 በአሜሪካ ሲያትል የኢትዬጵያውያን ኮሚውኒቲ መልዕክት።
የማይረሳ ምሽት!
ባለፈው ረቡዕ ጁላይ 02 ምሽት ከኮሚውኒትያችን አባላት ጋር በአንድ አዳራሽ ተሰባስበን ነበር። ከጠበቅነው በላይ ሆኖ ካገኘነው ከዶ/ር ወዳጄነህ ጋር በአእምሮ ጤና (Mental Health & Mind Care) ላይ በጣም አስደናቂ የትምህርት ጊዜ አሳልፈናል። በኦቲዝም ላይ የቀረበውም ዝግጅት አይን ከፋች ነበር።
የቀረበውን ትምህርት ተከትሎ እጅግ ጠቃሚ ውይይት አካሂደናል። ምሽታችን ተስፋን የሚሰጥ፣ እውቀትን የሚለግስ፣ፈውስን የሚያመጣ ደስ የሚያሰኝ ምሽት ነበር። አዳራሻችን በሰውና በሀይል የተሞላ ነበር። አብረን የምናድገው እንዲህ ስናደርግ ነው!
በስብሰባው ላይ የተገኛችሁትን፣ የደገፋችሁንን፣ ያካፈላችሁንን ሁሉ እናመሰግናለን!
Message from Ethiopian Community in Seattle. (ECS)
https://www.facebook.com/s...
✨ What an unforgettable evening! ✨
On Wednesday, July 2nd, our community came together for an inspiring night of awareness, healing, and hope with the incredible Dr. Wodajeneh Meharene 💙
🎤 The conversations were powerful.
🧠 The lessons on mental health and autism awareness were eye-opening.
We had a packed house, lots of energy, and so much learning. Thank you to everyone who showed up, shared, and supported. This is how we grow—together. 💪🏾💙
#communityhealing #mentalhealthawareness #autismawareness #drwodajeneh #strongertogether #adropofhope #seattlelove #communitystrong #simretbeauty
(የአዘጋጆቹ መልዕክት። ተመሳሳይ ፕሮግራሞ ነገ እሁድ ጁላይ 5 በፖርትላን ኦሪገን ቀጥሎም በሎአንጀለስ፣ በላስቬጋስ፣ በዴንቨር፣ በዳላስ፣ በሚኖሶታ፣ በትላንታ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ይቀርባል። 101 የጥበብ ጠብታዎች በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የዶ/ር ወዳጄነህ መጽሃፍም ለአንባብያን ይቀርባል)

Comments