በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ መጽሐፍ የዓረብኛ ትርጉም ተመረቀ
*************************
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት“ የአረብኛው ትርጉም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አቡዳቢ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በአቡ ዳቢ የተመረቀው ይህ መጽሐፍ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ሁሉም አረብኛ ተናጋሪ ሀገራትና ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በመደመር መንግሥትና ፍልስፍና እያራመደች የምትገኘውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የለውጥ እንቅስቃሴ ትልሞች በጥልቀት እንዲገነዘቡት ዓላማ ያደረገ ነው።
በመጽሐፍ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው “የመደመር መንግሥት” አረብኛ ትርጉም እውን መሆን በኢትዮጵያና በተቀረው የአረቡ ዓለም በኩል ያሉ የጋራ ጥቅሞችን አስተሳስሮ ለማስቀጠልና የጋራ ጥቅሞቻችንን ለማስጠቅ እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሸክ ሻክቡት ቢን ናህያን አልናህያን፣ መጽሐፉ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ መቅረቡ በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መካከል የቆየውን ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገሪቱ ሚኒስትሮች፣ አምባሳደሮች፣ ዲፕሎማቶችና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ታድመዋል።
በሰለሞን ኃይለኢየሱስ ከአቡዳቢ
#ethiopia #medemer #abiyahmed #uae #abudhabi #booklaunch #diplomacy

5 months ago