3 months ago
የሲኤንኤን (CNN) መስራች ቴድ ተርነር አረፉ
#ethiopia | የዓለማችንን የዜና አቀራረብ እና የሚዲያ አጠቃቀም የቀየሩት ዝነኛው ባለሀብት ቴድ ተርነር በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ተቋማቸው ሲኤንኤን (CNN) አረጋግጧል።
በፈረንጆቹ 1980 የመጀመሪያውን የ24 ሰዓት የዜና ጣቢያ በመመስረት የሚታወቁት ተርነር፣ በወቅቱ የማይታሰብ የነበረውን የ"ቀጥታ ስርጭት" የዜና ጥበብ ለዓለም በማስተዋወቅ የሚዲያ ታሪክን የለወጡ ታላቅ ሰው ነበሩ።
ዜና በየሰዓቱ እና በየደቂቃው ለዓለም መድረስ እንዳለበት በማመን የመጀመሪያውን የ24 ሰዓት የዜና ኔትወርክ መስርተዋል።
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) 1 ቢሊዮን ዶላር በመለገስ በሰብአዊ መብት እና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ከፍተኛ አሻራ አሳርፈዋል።
ከተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በተጨማሪ በስፖርቱ ዓለምም እንደ አትላንታ ብሬቭስ ያሉ ተቋማት ባለቤት በመሆን ስማቸው ገዝፎ የሚነሳ ሰው ነበሩ።
ቴድ ተርነር በቢዝነስና በሚዲያ ዓለም ካሳዩት ብቃት ባሻገር፣ በግልጽ የመናገር ስልታቸውና በፈጠራ የታጀበ አመራራቸው በብዙዎች ዘንድ ዘላቂ ክብርን አትርፎላቸዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#tedturner #cnn #mediaicon #legacy #breakingnews #restinpeace #ethiopia #የሚዲያ_ታሪክ

የቡናው አንጋፋ ተጫዋች ተስፋዬ መኮንን (ጅማ) ከዚህ ዓለም ተለየ
#።Ethiopia | የኢትዮጵያ ቡና ቀድሞ ተጫዋች ተስፋዬ መኮንን "ጅማ" ባደረበት ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።
በጅማ ቡና ተክል ክለብ በነበረው ድንቅ ብቃት ወደ ቡና ገበያ (ኢትዮጵያ ቡና) ያቀናው ተስፋዬ፣ በግራ መስመር ተጫዋችነቱና በነበረው ልዩ ተሰጥኦ በ1980ዎቹ የእግር ኳስ ወዳጅን ቀልብ የገዛ ተወዳጅ ተጫዋች ነበር።
ባለ ትዳርና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር።
ነገ ዓርብ ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በሜክሲኮ ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን የቀብር ስነ-ስርዓቱ ይፈጸማል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰብ ትልቅ ኮከቡን አጥቷል። በዛ ድንቅ ዘመን በግራ መስመር የሚያሳየው ፈጣንና ቴክኒካዊ ጨዋታ በብዙዎቻችን ትዝታ ውስጥ ሁሌም ይኖራል። ለባለቤቱ፣ ለልጁና ለመላው የቡና ደጋፊዎች መጽናናትን እመኛለሁ። ተስፋዬ መኮንን (ጅማ) በሰራው ስራ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።
ተስፋዬ ሆይ! በሰላም እረፍ! 🙏🕊️
***
በወርቃማው ዘመን፤ የእግር ኳስ ጥበበኛ ተስፋዬ (ጂማ) ኳሷ እግሩ ሥር ናት።
#getu #ethiopiabunna #tesfayemekonnen #jimma #ethiopianfootball #legend #restinpeace #ኢትዮጵያቡና #ተስፋዬመኮንን #ጅማ #እግርኳስ #ዜናእረፍት #ጌጡተመስገን #getutemesgen

4 months ago
ቀብር
#ethiopia | የአዲስ አውቶሞቲቭ የሬዲዮ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (EBC) አንጋፋ የዜና አንባቢ የጋዜጠኛ ሰለሞን ጥዑመልሳን እናት ወይዘሮ ቀኑብሽ አባማነው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓት መረጃ፦
ረቡዕ መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም.
በፈረንሳይ ለጋሲዮን ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከቀኑ 8:30 ይፈጸማል።
ለጋዜጠኛ ሰለሞን ጥዑመልሳን፣ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ለሟች እናታችንም
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን።
#getu #ethiopia #solomontiumelsan #ebc #addisautomotive #condolences #restinpeace #addisababa #ሐዘን #ቀብር #ሰለሞንጥዑመልሳን #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

5 months ago
የሆሊውድ የአክሽን ፊልሞች ፈርጥ ቻክ ኖሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | ታዋቂው አሜሪካዊ የሆሊውድ ተዋናይ እና የማርሻል አርት ጥበብ መምህር ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
በአክሽን ፊልሞቹና በማይበገረው ማንነቱ የሚታወቀው ኖሪስ፣ በሃዋይ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የጥበብና የጥንካሬ ጉዞ፦
ጅማሮ፦ በ1940 በኦክላሃማ የተወለደው ኖሪስ፣ ወደ ጥበብ ዓለም ከመግባቱ በፊት በአሜሪካ አየር ኃይል ውስጥ አገልግሏል።
ዝነኛ ሥራዎቹ፦
በተለይም "Walker, Texas Ranger" በተሰኘው ተከታታይ ፊልሙ እንዲሁም ከብሩስ ሊ ጋር በሰራው "Way of the Dragon" እና በሌሎችም በርካታ የአክሽን ፊልሞች ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል።
ቻክ ኖሪስ ከፊልም ሥራዎቹ ባሻገር፣ በልዩ የማርሻል አርት ችሎታውና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የሚታወቅ የዘመናችን የጥበብ ምልክት ነበር።
የማይበገረው ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ቢያርፍም፣ በጥበብ ሥራዎቹ ግን በብዙዎች ዘንድ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።
#getu #chucknorris #hollywood #actionmovies #martialarts #legend #restinpeace #rip #ሆሊውድ #ቻክኖሪስ #አክሽንፊልም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
5 months ago
ጋዜጠኛ ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | በቀድሞ ፋና ሬዲዮ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ የነበረው ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በ1957 በቀድሞ አጠራሩ ወለጋ ክፍለ ሀገር ጊንቢ አውራጃ ላሎ አሳቢ ወረዳ የተወለደው ጋዜጠኛ ታሪኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ ቀድሞ ፋና የአሁኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን በመቀላቀል በአፋን ኦሮሞ ክፍል በሚዲያው ዘርፍ የኦሮሞን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ በማሳደግ ረገድ የበኩሉን ሚና ተጫውቷል።
ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት የነበረው ጋዜጠኛ ታሪኩ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊት በተወለደ በ61 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የጋዜጠኛ ታሪኩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በሚገኘው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ ለጋዜጠኛ
ታሪኩ ኦላና ቤተሰቦቹና ዘመድ ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል።
#fbc
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#tarikuolana #journalism #ethiopia #afaanoromo #fanabroadcasting #mediaicon #restinpeace #journalistlife #ethiopianmedia

🕊️ የሩጫ ንግሥት፤ የመሠረት ደፋር እናት እናመሰግናለን🕯️
#ethiopia | ይህ ዜና ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የሩጫ ንግሥቷ መሠረት ደፋር እና ለመላው ቤተሰቦቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ እጅግ አሳዛኝ ነው።
ወይዘሮ አስቴር መንገሻ ለሀገር ኩራት የሆነችውን መሰረት ደፋርን ብቻ ሳይሆን፣ ስድስት ልጆችንና 18 የልጅ ልጆችን አፍርተውና ለቁም ነገር አብቅተው ያለፉ ማኅፀነ ለምለም እናት ነበሩ።
ሀገርን የሚያስጠሩ ጀግኖችን ያፈሩትና ለ54 ዓመታት በፍቅርና በሰላም ትዳራቸውን የመሩት ማኅፀነ ለምለሟ እናት ወይዘሮ አስቴር መንገሻ በተወለዱ በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
📜 አጭር የሕይወት ታሪክ፦
ልደት፦
በ1947 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ኢጄሬ ወረዳ (አዲስ ዓለም) ተወለዱ።
ትዳርና ቤተሰብ፦
በ1964 ዓ.ም ከአቶ ደፋር ቶላ ጋር ትዳር መስርተው ለ54 ዓመታት በጽኑ ፍቅር ዘልቀዋል። የ6 ልጆች እናትና የ18 የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል።
የጀግኖች እናት፦
የዓለምን የሩጫ መድረክ የገዛችውንና በኦሎምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ለሀገሯ ያስገኘችውን የሩጫ ንግሥት አትሌት መሰረት ደፋርን ለኢትዮጵያ ያበረከቱ ታላቅ እናት ነበሩ። ሌሎች ልጆቻቸውም በሙሉ በሕክምናው ዘርፍ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳድገዋል።
መሰረት ደፋር እ.ኤ.አ በ2007 የአለም ምርጥ አትሌት ተብላ እንድትመረጥና ስሟ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ እንዲሰፍር ያደረጉትን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲህ ማጠቃለል ይቻላል፦
የአትሌት መሰረት ደፋር ታሪካዊ ስኬቶች በአጭሩ
የአለም ክብረ ወሰኖች (World Records):
5,000 ሜትር፦ በኦስሎ (ኖርዌይ) 14:16.63 በመግባት ቀዳሚ ሆናለች።
2 ማይል፦ በካሊፎርኒያ እና በቤልጅየም (8:58.58) በመግባት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ9 ደቂቃ በታች የሮጠች የኢትዮጵያ ጀግና ሴት ናት።
3,000 ሜትር (የቤት ውስጥ/Indoor): በጀርመን ስቱትጋርት 8:23.72 በመግባት ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።
የኦሎምፒክ ድሎች:
እ.ኤ.አ በ2004 በአቴንስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።
እ.ኤ.አ በ2012 በለንደን ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።
ታሪካዊ እውቅና:
እ.ኤ.አ በ2007 የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (IAAF) የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማት ባለቤት።
አንዲት እናት ለሀገር የምታበረክተው ከሁሉ የላቀ ስጦታ፣ ሀገሩን የሚወድና ስሟን ከፍ የሚያደርግ ጀግና ትውልድ መፍጠር ነው፤ ወይዘሮ አስቴር ይህንን በተግባር አሳይተዋል።
ሀገራዊ አገልግሎት፦
ወይዘሮ አስቴር ራሳቸውም ሰላም አስከባሪ በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ ጀግና ነበሩ።
መንፈሳዊ ሕይወት፦
ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው፣ በቤተክርስቲያን ሥርዓት የተጉና የሰማይ መንገዳቸውን በቅዱስ ቁርባን የጠረጉ እናት ነበሩ።
🥀 የስንብት ሥነ-ሥርዓት፦
ወይዘሮ አስቴር ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፣ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አርፈዋል።
የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም (የካቲት 15/2018 ዓ.ም) በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen) ለጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋርና ለመላው ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።
ፈጣሪ የነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን! 🙏🇪🇹
#መሰረትደፋር #ወይዘሮአስቴርመንገሻ #የሐዘንመግለጫ #meseretdefar #ethiopia #legacy #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

6 months ago
🕯️ ዜና እረፍት
የጀግናዋ አትሌት መሠረት ደፋር እናት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ 🕯️
#ethiopia | በሁለት የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያዎች እና በአራት የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ድሎች የሀገራችንን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋ ያስቀመጠችው የጀግናዋ አትሌታችን መሠረት ደፋር ወላጅ እናት ወ/ሮ አስቴር መንገሻ ጫላ በዛሬው ዕለት ማለዳ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
📌 ስለ እናታችን ወ/ሮ አስቴር መንገሻ፦
እናታችን ወ/ሮ አስቴር ጀግናዋን አትሌት መሠረት ደፋርን ጨምሮ የስድስት ልጆች (የ2 ወንዶችና የ4 ሴቶች) እናት ነበሩ።
በአደረባቸው ሕመም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሕክምና ሲከታተሉ የቆዩ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት ማለዳ ሕይወታቸው አልፏል።
💔 የመሠረት ደፋር መሪር ሐዘን፦
ሁልጊዜም ስለ እናታቸው ፍቅርና ታላቅነት በኩራት የምትናገረው አትሌት መሠረት ደፋር፣ እናቷን ለማዳን ያልፈነቀለችው ድንጋይና ያልደከመችበት ጥረት ባይኖርም፤ ዛሬ የምትወዳትን እናቷን በሞት መነጠቋ እጅግ መሪር ሐዘን ሆኖባታል።
🙏 የሐዘን መግለጫ፦
ለጀግናዋ አትሌታችን መሠረት ደፋር፣ ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ እንዲሁም ለመላው የስፖርት ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን። ለእናታችን ወ/ሮ አስቴር መንገሻ አምላክ ዘላለማዊ እረፍትን ይስጥልን።
#meseretdefar #ethiopia #mourning #athleticsethiopia #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

🕯️ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ 🕯️
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የባለራዕዩ አቶ አማን ፍስሃጽዮን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈጽሟል።
በሥርዓተ ቀብሩ ላይ፦
የሟች ቤተሰቦችና የቅርብ ወዳጅ ዘመዶች፣
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሥራ ባልደረቦችና የጥበብ ሰዎች፣
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ተቋማት መሪዎች ተገኝተው የመጨረሻ ስንብት አድርገዋል።
አቶ አማን ፍስሃጽዮን የኢትዮጵያን የሚዲያ ኢንዱስትሪ በማዘመንና ጥበብን ወደ ቤታችን በማድረስ ረገድ የማይረሳ አሻራ ጥለው አልፈዋል። ላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የኢቢኤስ ሠራተኞች መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ! 🙏
#ebs #amanfissehazion #ethiopia #medialegend #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

💔 የአቶ አማን ፍስሐጽዮን የሕይወት ታሪክ🕯️
1964 - 2018
#ethiopia | አቶ አማን ፍስሐጽዮን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የካቲት 3 ቀን፤ 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ53 ዓመታቸው በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከዚህ ዓለም ድካም በሰላም አርፈዋል። አቶ አማን በህይወት ዘመናቸው ባለራዕይና ስራ ፈጣሪ ታማኝ ባለትዳርና መልካም አባት እንዲሁም ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።
አቶ አማን ህይወቱና ማንነቱ በእምነት፣ በቁርጠኝነት፣ በተስፋና በጽናት ላይ የቆመ ትጉህ ሰው ነበር። በፈጣሪ ላይ በነበረው ጽኑ እምነትና ለወገኖቹና ለሀገሩ በነበረው የማይነጥፍ ፍቅር የተነሳ የተቸገሩትን ለመርዳት የሌሎችን እንባ ለማበስ የማይታክት ሰው ነበር። ሌሎችን ለማገልገል ያለውን ወደርየለሽ ፍላጎትና ፈገግታው በሚያውቁት ሁሉ የሚናፈቁ የሰብእናው መሰረቶች ናቸው።
አቶ አማን ሐምሌ 3 ቀን 1964 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ፍስሐ ጽዮን ገብረ ሕይወትና ከእናቱ ከወይዘሮ ሕይወት ተኬ በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። ለቤተሰቡ ስድስተኛና የመጨረሻ ልጅ የሆኑት አቶ አማን እምነትን ማዕከል ባደረገ የቤተሰብ እሴቶች በነበረበት ቤት ውስጥ በወላጆቹ በአያቱ በወይዘሮ ይመስገን ገብረሥላሴ በማይነጥፍ ፍቅርና ምክር ታንጸው አድገዋል።
የአቶ አማን የሰብእና መሰረትና መገለጫ ባህሪይ የሆኑት በጎነት፣ ብሩህ ተስፋ ቆራጥነትና የመሪነት ስብዕና ገና በለጋ እድሜው ከቤተሰቡ ያገኘው እሴቶች ናቸው። አቶ አማን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ሳንፎርድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ አሜሪካ በመጓዝ በዮርክ ፔንሰልቬንያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
በመቀጠልም ከፔንሰልቬንያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በኦፕሬሽን ማኔጅመንት እና ማርኬቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። በውጭ ሀገር የነበራቸው ቆይታ የአስተሳሰብ አድማሳቸውን በማስፋት የህይወት ገጠመኛቸውን ቢያዳብራቸውም ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ቁርኝት ግን ምንጊዜም የማይነጥፋቸው መሰረት ስለነበር ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ሀገራቸውን ለማገልገል በታላቅ ተነሳሽነትና ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
አቶ አማንና የሕይወት አጋሩ ወይዘሮ ማክዳ አሰፋ የተገናኙበት 1989 ዓ.ም ሲሆን ከሁለት ዓመታት በኋላ ሚያዝያ 1 ቀን 1991 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል። ትዳራቸውም በጥልቅ ፍቅር ማደናቀፍ መደጋገፍ ሁኔታዎችና ፈተና በማይበግረው ጽኑ ታማኝነት ላይ የተገነባ የሕይወት ጥምረት ነበር። ሁለት ሆነው እንደ አንድ የኖሩበትን የትዳር ሕይወት በመከባበር በፈሪሃ እግዚአብሔር እና በጋራ ህብረት በተገነባ ጥንካሬ መርተውታል። በዚህም ጊዜ አማኑኤል መቅደላዊትና ሰላም ፍስሐ ጽዮን የተባሉ ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ኖቫ የተባለች የልጅ ልጅ ለማየትም በቅተዋል። አቶ አማን በሕይወታቸው እጅግ መጠነ ሰፊ የሆኑ ስኬቶች ባለቤት ቢሆኑም ከሁሉም በላይ ትልቁ ኩራታቸውና ደስታቸው ቤተሰባቸው ነበር።
አቶ አማን በ2000 ዓ.ም ከአጋሮቻቸው ከአቶ ሙሴ ፍስሐጽዮን፣ አቶ ዮሃን ፍስሐ ጽዮንና አቶ ነቢዩ ያሬድ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስን (EBS TV) በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ መሰረቱ።
በታላቅ ራዕይ የተጀመረው ይህ ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች የሚደርስና በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ የመገናኛ ድልድይ ለመሆን በቅቷል።
ኢቢኤስ የአቶ አማንን የፈጠራ ስራ አመራርና አርቆ አሳቢነት የሚያንጸባርቅ በማህበረሰቡ ዘንድ ታማኝነትና ተደማጭነት ያለው ድምፅ ለመሆን በቅቷል።
አቶ አማን በ2003 ዓ.ም ለብዙ ዘመናት ሲመኙት የነበረውን ወደ ሀገር የመመለስ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ በህይወታቸውና በሙያቸው ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። በእሳቸው መሪነት ኢቢኤስ በኢትዮጵያ የሚዲያ እድገት ላይ ጎልቶ ሚና ተጫውቷል።
የነደፉት ራዕይና ከአጋሮቻቸው ጋር ተደምሮ በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥና ሽግግር እንዲመጣ ረድቷል። ነፃ የመገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፋ እና በቴሌቪዥን በመገናኛው ዘርፍ ለአዳዲስ ፈጣሪዎችና ለበርካታ ባለሙያዎች እድልና መድረኮች እንዲፈጠሩ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
አቶ አማን በጣም በርካታ ውጤቶችን ባስመዘገቡበትና መሰረታዊ የሚባል አሻራ ባሳረፉበት ጎልህ የሥራ ዘመናቸው፤ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ውስጥ በበርካታ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የአመራርነትና በቦርድ አባልነትም አገልግለዋል። የቲ.ኤ ብሮድካስቲንግ (TA BROADCASTING INC.) ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ የክሊር ኮሙኒኬሽን (CLEAR COMMUNICATIONS INC.) የማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በአዲስ አበባ የአቪዬሽን ኢንተርናሽናል ማኔጅንግ ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በአዲስ አበባ የዲያስፖራ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር ውስጥም በስራ አመራር ቦርድ አባልነትና በባለሙያነት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ለእነዚህ አበርክቶታቸውና ስኬቶችም በርካታ እውቅናዎችንና አክብሮቶችን አግኝተዋል። ከነዚህም መካከል የኢትዮ - አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት የላቀ የንግድ ስራ ሽልማትና የዓመቱ ፈር ቀዳጅ የዲያስፖራ ባለሀብት በመሆን የተሸለሙት ይገኙበታል።
አቶ አማንን በቅርብ የሚያውቋቸው ሁሉ በሙያዊ ስኬታቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሰብዕናቸው ጥንካሬ፣ በደግነታቸው፣ በለጋስነታቸው፣ ሌሎችን ሳይቀር በነበረበት አልፎ ለተግባራዊነቱ እንዲተጉ በማነሳሳት ልዩ ችሎታቸው ያከብሯቸዋል፣ ይወዷቸዋል። አቶ አማን ዘንድ ተስፋ መቁረጥ፣ መሸነፍ፣ መረታት ቦታ አልነበራቸውም።
የትኛውንም መሰናክል በማስተዋል፣ በጥበብ እና በብልሃት የሚያልፉ፣ በጊዜያዊ ጫጫታና ሁከት የማይረበሹ፣ ከፍርሃትና ከጥርጣሬ ጨለማ ይልቅ የተስፋን ብርሃን የመረጡ መልካም ሰው ነበሩ። የአመራር መርሆቸውና ከሰው ጋር የነበራቸው መስተጋብር የረጋ መንፈስን እና ቅን ልቦናቸውን መሰረት ያደረገ ነበር።
በጣም ፈታኝ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ እያስፋ እንኳን፣ ነን የተሻስ እንደሚሆን የማይናወጥ እምነት ነበራቸው። ያንን የተሻለ ነገ እውን ስማድረግም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል። አቶ አማን በሕይወት የተለዩት፣ የሚወዷት ባአቤታቸው ወይዘሮ ማክዳ ፍስሐ ጽዮን፣ ልጆቻቸውን እማኑኤል፣ መቅደኣዊትና ሰላም ፍስሐጽዮን፣ የልጅ ልጁን ኖቫ ፍስሐጽዮን፣ አናቱን ወይዘሮ ሕይወት ተኬን፣ ወንድምና እህቶቹን ሜሮንን፣ ሙሴን፣ ኖኀን፣ ነጻንና ሜሪ ፍስሐ ጽዮንን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቤተሰብ አባላትንና ወደጆቹን ብቻ ሳይሆን የስሯቸውን ፍሬ የሚያውቁትን ሁሉ ነው፡፡
አቶ አማን አሁን በፈጣሪ ፊት በዘላለማዊ ሰላም እና አረፍት እንዳስ እናምናለን። ይሁን አንጂ ታሪካቸው ወደፊት በነጻነት አንዲራመድ ባንዟቸው ባቋቋሟቸው እና በገነቧቸው ተቋማትና ከምንም በላይ በሚወዱት ቤተሰብ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል። አቶ አማን በጸና እምነት ተመርተው በታማኝነት ፣ በማገልገል እና እራስን አሳልፎ በመስጠት ሙሉ ሕይወትን ኖረዋል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ታሪክ ውስጥ፣ ባስራእይና የለወጥ ሀይል፣ ለዘርፉ አርአያ የሆነ፣ ፈር ቀዳጅ፣ ሀገር ወዳድና የእምነት ሰው ሆነው ምንጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ።
ሁሌም በልባችህን ትኖራለህ
ፈጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️
#ሼር #share
#amanfissehazion #ebs #ebsworldwide #ethiopia #medialegend #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

💔 ኑ - በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እንሰናበተው🕯️
[ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መሰናበት ይችላል ]
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዋቂው ባለሙያ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን የስንብት መርሃ ግብር
📅 ዛሬ፣ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.
🕒 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የስንብት መርሃ ግብር ይደረጋል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ዘመናዊና ጥራት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖር ካደረጉ ቀዳሚ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️ #ሼር #share

💔 የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን አዲስ አበባ ገባ፤
ነገ የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል 🕯️
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዋቂው ባለሙያ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሷል።
በአየር ማረፊያውም የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።
አስከሬኑ በቤተሰቦች፣ በወዳጅ ዘመዶችና በስራ ባልደረቦች ታጅቦ ሳር ቤት አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ደርሷል።
የነገው የክብር ስንብት መርሃ ግብር፦
📅 ነገ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.
🕒 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉዞ ይደረጋል።
📍 ስነ-ስርዓት፦
በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ ልዩ የሽኝትና የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ዘመናዊና ጥራት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖር ካደረጉ ቀዳሚ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️

⚫️ የጽናት እና የአብሮነት ተምሳሌቱ መቶ አለቃ ለማ አስፋው አረፉ 🕯️🇪🇹
#ethiopia | ከአየር ኃይል መኮንንነት እስከ አለማ ፋርምስ ስኬት... የብርቱው ባለሙያ እና የቅን ሰው ሽኝት
በሀገራችን የግብርና ቢዝነስ (Agribusiness) ውስጥ ስመ ጥር የሆነው የ"አለማ ፋርምስ" መስራች አባል የነበሩት መቶ አለቃ ለማ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
መቶ አለቃ ለማ እና ጓደኛቸው ሻለቃ አለማየሁ አምደማርያም ከአየር ኃይል ተሰናብተው በችግር ውስጥ በነበሩበት ወቅት፤ እጃቸውን ለልመና ሳይዘረጉ በዶሮ እርባታ የጀመሩት ጉዞ ዛሬ ግዙፍ ተቋም ሆኖ ቆሟል።
ለምን ይዘከራሉ?
የጽናት ምሳሌ፦
ወታደራዊ ማዕረጋቸው ሳይገግዳቸው በጓሮ አትክልት እና በዶሮ እርባታ ስራን የጀመሩ፣ "ሰው በላቡ ይኑር" የሚለውን መርህ በተግባር ያሳዩ ብርቱ ሰው ነበሩ።
የአብሮነት ተምሳሌት፦
ከሻለቃ አለማየሁ ጋር ለረጅም ዓመታት በአንድነት፣ በመከባበር እና በመግባባት የገነቡት ተቋም ለሀገራችን የቢዝነስ ዘርፍ ብርቅ የሆነ "የጋራ ስኬት" አርአያ ነው።
ሰብአዊነት እና ቅንነት፦
የቅርብ ወዳጆቻቸው እንደሚመሰክሩት፤ መቶ አለቃ ለማ ሁሉን አክባሪ፣ ሳቂታ፣ ለሙያ አጋሮቹ እውቀቱን እና ቁሳቁሱን የማይሰስት ደግ ሰው ነበሩ።
በደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ኪዳነ ምህረት ቤተ-ክርስቲያን የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸው ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለልብ ጓደኛቸው ለሻለቃ አለማየሁ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍ!
#lemaasfaw #alemafarms #ethiopianentrepreneur #successstory #bishoftu #inspiration #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የስኑፕ ዶግ ሴት ልጅ ኮሪ ብሮደስ የልጇን ህልፈት ተናገረች
የስኑፕ ዶግ ሴት ልጅ የሆነችው ኮሪ ብሮደስ ገና በጨቅላነቷ ላይ የነበረችው ልጇ (የስኑፕ ዶግ የልጅ ልጅ) ማለፏን በከፍተኛ ሀዘን ገልጻለች።
ኮሪ ይህንን መርዶ በማህበራዊ ሚዲያ ገጿ ላይ ያጋራች ሲሆን፣ "ልቤ ተሰብሯል" ስትል ስሜቷን ገልጻለች። ህጻኗ ቻያ ትባላለች። ኮሪ ልጇን "ውድ መልአካችን" ስትል የጠራቻት ሲሆን፣ ህልፈቷ ለቤተሰቡ ትልቅ ድንጋጤ ሆኗል።
ብዙ ታዋቂ ሰዎችና ደጋፊዎቿ ለኮሪ እና ለቤተሰቧ ያላቸውን አጋርነትና መጽናናትን እየገለጹ ይገኛሉ። ኮሪ ቀደም ሲል "Lupus" (ሉፐስ) በተባለ የጤና እክል ስትሰቃይ እንደነበርና በቅርቡም የጭንቅላት ደም መፍሰስ አጋጥሟት እንደነበር ይታወሳል። ይህ አዲስ ሀዘን ደግሞ በቤተሰቧ ላይ ተጨማሪ ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል።
#fastmereja #snoopdogg #coribroadus #celebritynews #restinpeace #hollywoodgossip #dailymail #heartbreaking #ስኑፕዶግ #የታዋቂዎችወሬ #ሀዘን #ትኩስመረጃ

በኮሎምቢያ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ የባለሥልጣናትን ሕይወት ጨምሮ የ15 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በሰሜን ምሥራቅ ኮሎምቢያ ከቬንዙዌላ ድንበር አቅራቢያ በደረሰ አሰቃቂ የአውሮፕላን የመከስከስ አደጋ፣ የሕግ ባለሙያዎችንና ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችን ጨምሮ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተረጋገጠ።
እንደ ዘገባዎች ከሆነ፣ አውሮፕላኑ በረራ ላይ እያለ አደጋው ያጋጠመው ፓለቲከኞችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ ሳለ ነው። በአደጋው ሕይወታቸው ከጠፋው መካከልም የሚከተሉት ታዋቂ ግለሰቦች ይገኙበታል፦
* ዲዮጀነስ ኩንቴሮ፡ የኮሎምቢያ የተወካዮች ምክር ቤት የካታቱምቦ ክልል ተወካይ።
* ካርሎስ ሳልሴዶ፡ የኮንግረንስ ምርጫ እጩ።
የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር በሰጡት መግለጫ፣ በአደጋው ክፉኛ ማዘናቸውን ገልጸው በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩት ባለሥልጣናት መካከል በሕይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩን ይፋ አድርገዋል።
ምንም እንኳ የኮሎምቢያ ባለሥልጣናት የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ ለማወቅ ምርመራ እያደረጉ ቢሆንም፣ አውሮፕላኑ ከመከስከሱ ቀደም ብሎ ግን የድንገተኛ አደጋ ምልክት መብራቱ (Emergency light) አገልግሎት እየሰጠ እንዳልነበር ፍንጮች መኖራቸው ተጠቁሟል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #colombia #planecrash #breakingnews #aviationsafety #restinpeace #ኮሎምቢያ #የአውሮፕላንአደጋ #ዜና

💔 ቴሪዬ - ደህና ሁኚ!
የኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ "ተፈጥሮአዊ ኃይል"
(Force of Nature) ወ/ሮ ትርሃስ (ቴሪ) ገብረኪዳን
በወፍ በረር
አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | ወ/ሮ ትርሃስ ገብረኪዳን ~ ወዳጆቿ በሚጠሯት የፍቅር ስም ቴሪ፣ በ1965 ዓ.ም ከአቶ ገ/ኪዳን በርሄ እና ከወ/ሮ ክንደ ሃፍቲ በአሥመራ ከተማ ተወለደች። እድሜዋ ለትምህርት ሲደርስም እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ያለፈች ሲሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በልዑል በዕደማርያም ት/ቤት አጠናቃለች።
"ጥራትን ከለጋስነት ያጣመረች፣ የ30 ዓመታት የውበት ንግሥት!" በኢትዮጵያ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ዘርፍ ላለፉት 3 አሥርት ዓመታት ስሟ በጉልህ የሚነሳው፤ የTerry Style H₂O መስራች ትርሐስ (ቴሪ) ነበረች።
🌟 ቴሪ፤ በኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ዘመናዊ አሰራርን በማስተዋወቅ "የውበት እመቤት" ለመባል የበቃች ፈር-ቀዳጅ፤ ሥመ ጥር ባለሙያ ነበረች።
ቴሪ - በአውሮፓ፣ እስያ እና አሜሪካ በመዘዋወር የወሰደችውን ስልጠና ተጠቅማ፤ እንደ ሎሪያል - Loreal ያሉ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወኪል በመሆን የሜካፕ ዘርፉን ወደ ከፍታ አሸጋግራለች።
ባለ ራዕይ (The Visionary) ቴሪ
ቴሪ ተራ የውበት ሳሎን ሳይሆን የከፈተችው፤ የክብር እና የእንክብካቤ ስፍራን (Sanctuary) ነበር። ስራዋን እንደ ህይወት ዓላማዋ (Purpose) በመቁጠር ያልነበረውን ነገር በምናቧ አይታ ወደ እውነት፤ ወደ ምድር ያመጣች - በተግባር የቀየረች ብርቱ ሰው ነበረች።
✅ ወ/ሮ ትርሐስ (ቴሪ) ገብረኪዳን - አስተማሪ እና አቅም ፈጣሪ (The Mentor) ነበረች
"እውቀት ሲካፈሉት ይበዛል" የምትለው ቴሪ፤ በርካታ ወጣቶች የራሳቸውን የውበት ሳሎን እንዲከፍቱ በሙያ እና በቁሳቁስ በዝምታ ደግፋለች። ስኬቷን ለራሷ ብቻ ሳታደርግ ለሌሎችም የምታካፍል ለጋስ እናት ነበረች።
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
ቴሪ - ደግነት እና ሰብአዊነቷ አልተነገረላትም። በዚህም ያልተዘመረላት ጀግና፤ ዝምተኛዋ ጀግና የሚል ምወድስ በክብር የሚነገርላት የቸርነት እናት ነበረች።
ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ያለምንም ማስታወቂያ እና ዝና ፍለጋ የምትደርስ፤ ፈገግታዋ የማይጠፋ "የሕይወት አፍቃሪ" የምታውቋት ቴሪ ሰውነት ነበር።
በመጨረሻም
👩👧👦 አፍቃሪዋ እናት (ቴሪ )
ከሰሊሆም እና ከኢዮአስ ጋር የነበራት ግንኙነት ልዩ ነበር። "ሰሊሆም ትሙት" እያለች የምትምልላቸው፣ ከህይወቷ በላይ የምትወዳቸው ልጆቿ የህይወቷ ማዕከል ነበሩ።
ቴሪ
ፍቅሯ፣ ራዕይዋ እና ለጋስነቷ ( ሌጋሲዋ ) ለዘላለም ከእኛ ጋር በክብር ይኖራል!
ትርሃስ፣ ባደረባት ህመም ምክንያት በአሜሪካ ህክምና ስትከታተል ቆይታ ጥር 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በ53 ዓመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች።
ቴሪ - እህተ ማርያ ንስሀ ገብታ ማረፏ ተገልጿል።
ዛሬ ጥር 18 ቀን 2018ዓም በሳዕሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ሰዓት (በእኩለ ቀን) ሥርዓተ ቀብሯ ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጆቿ እና ለሙያ አጋሮቿ መጽናናትን እንመኛለን።
ቴርዬ - እንወድሻለን። እንናፍቅሻለን።
ቴሪዬ - ደህና ሁኚ!
💔🙏
#terrystyle #restinpeace #ethiopianbeautyindustry #legend #tirhasgebrekidan #terryh2o #ethiopia

7 months ago
💔 የ30 ዓመታት የውበት ንግሥት - ቴሪ
* የኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ "ተፈጥሮአዊ ኃይል" (Force of Nature) አረፈች! 🕯️
* "ጥራትን ከለጋስነት ያጣመረች የ30 ዓመታት የውበት ንግስት - ቴሪ (Terry Style H₂O)"
#ethiopia | በኢትዮጵያ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ዘርፍ ላለፉት 3 አስርት ዓመታት ስሟ በጉልህ የሚነሳው፤ የTerry Style H₂O መስራች ወ/ሮ ትርሐስ (ቴሪ) ገብረኪዳን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
የቴሪ የማይረሳ አሻራ:
✅ ፕሮፌሽናሊዝም:
ደንበኞቿ ምርጥ አገልግሎት እንዲያገኙ በአውሮፓ፣ እስያ እና አሜሪካ እየተዘዋወረች በመሰልጠን ዓለም አቀፍ ደረጃን ወደ ሀገር ቤት ያመጣች፤ በጥራት ላይ የማትደራደር ባለሙያ ነበረች።
✅ አቅም ፈጣሪ:
ስኬቷን ለራሷ ብቻ ሳታደርግ፤ በርካታ ወጣቶች የራሳቸውን የውበት ሳሎን እንዲከፍቱ በሙያ እና በቁሳቁስ የደገፈች ታላቅ እናት ናት።
✅ ደግነት:
ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ያለምንም ማስታወቂያ እና ዝና ፍለጋ የምትደርስ፤ ፈገግታዋ የማይጠፋ "የሕይወት አፍቃሪ" ነበረች።
ቴሪ፤ በኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ አሻራ ጥላ አልፋለች።
ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጆቿ እና ለሙያ አጋሮቿ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍስሽን በገነት ያኑርልን!
ቴሪዬ እንወድሻለን! 💔🙏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#terrystyle #restinpeace #ethiopianbeautyindustry #legend #tirhasgebrekidan #terryh2o

⚫ "ብቻዬን ነው የተውከኝ!"
ፈጣሪ ያፅናህ አስኔ 💔
#ethiopia | "ፈጣሪ ያፅናህ አስኔ፤ የልብ ወዳጅን ማጣት ቀላል አይደለም!"
አስናቀ (አስኔ) እና ነጻነት ወርቅነህ (ነፂ) ከ29 ዓመት በላይ የዘለቀ፣ ከወዳጅነትም በላይ የሆነ ወንድማማችነት ነበራቸው።
ነፂ ስለ አስኔ እንዲህ ብሎ ነበር፡-
"አስኔ የልጅነት ጓደኛዬ፣ ሸኚዬ፣ ተቀባዬ... ኑርልኝ!"
ዛሬ ግን ሸኚውም፤ ተቀባዩም አስኔ ብቻውን ቀርቷል። የቀብር ስነስርዓቱ ላይ አስኔ እንደተናገረው፤ "እሱ መኪና ውስጥ ጋቢና እኔ ነኝ የምቀመጠው። ልብስ እየተቀያየርን ነው የምንለብሰው..." ሲል የነበራቸውን ጥብቅ ቁርኝት አስታውሷል።
ወዳጅን እንደወንድም ሆኖ ማግኘት መታደል ነው።
ማጣት ደግሞ መሪር ነው።
" ... ኒፂ የ29 ዓመታት የልብ ጓደኛዬ ነው 😭 በ28 ዓመት ጓደኝነታችን ውስጥ ተለያይተን የምናውቀው ለአንድ ወር እንኳን አይሞላም።"
አስኔ... ፈጣሪ ያጽናናህ!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#netsanetworkneh #bestfriend #asnake #brotherhood #condolences #love #tribute #restinpeace #ethiopia

⚫አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር
#ethiopia | "አባዬ... ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" 💔
የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ልጅ የሀዘን መግለጫ...
ዛሬ ስለ አባቴ ስለ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ሳስብ ልቤ በሀዘን ቢከብድም፣ በእሱ ልጅነቴ ግን እጅግ ኮራለሁ። አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር።
የኔ ጀግና...
በሄደበት ሁሉ ፈገግታን የሚዘራ፣ ለሰው አሳቢና እጅግ ሩህሩህ ሰው ነበር። አባዬ፣ ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ። ሊገቡኝ የሚገቡ የህይወት ትምህርቶችን በትግስት አስተምረኸኛል፤ ከአባት የሚጠበቀውን እውነተኛ ፍቅርም ያለ ስስት መግበኸኛል።
መጽናናታችን...
ያንተን ድምፅ አለመስማትና መለየትህ ለእኔና ለቤተሰቤ እጅግ የሚከብድ ቢሆንም፣ አሁን አንተ ከፈጣሪህ ጋር በተሻለ ስፍራ ላይ እንዳለህ በማወቃችን እንጽናናለን።
ፍቅርህ እና ትዝታህ ለዘላለም በልባችን ይኖራል! ❤️🙏
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#myfather #netsanetworkneh #love #tribute #restinpeace #ethiopia

⚫ የተሰማን ሀዘን ከባድ ነው! ነፍስ ይማር!
#ethiopia | የአልቲማ ሪል እስቴት (Altima Real Estate) የብራንድ አምባሳደር፣ ተወዳጁ የጥበብ ሰው እና የኢቢኤስ "የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም አዘጋጅ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ነጻነት በስራው ትጋቱ፣ በሰው አክባሪነቱ እና በቅንነቱ የምናውቀው፤ ለኩባንያችንም እንደ ቤተሰብ የነበረ ውድ ወንድማችን ነበር።
አልቲማ ሪል እስቴት በብራንድ አምባሳደሩ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለባለቤቱ፣ ለሦስት ልጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።
ፈጣሪ ነፍስህን በአጻድ ጻድቅ ያኑርልን! 🕯️💔
#restinpeace #netsanetworkneh #altimarealestate #condolence

⚫ የተወዳጁ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ህልፈት ተሰማ! 😭
"የቤተሰብ ጨዋታው ናፋቂ... በድንገት ተለየን!"
#ethiopia | በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በሚተላለፈው "የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም እና በተለያዩ የፊልም ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ የተወደደው አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ፤ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ምክንያት ዛሬ ረፋድ ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ነጻነት በስነ-ምግባሩ፣ በፈገግታው እና በሙያ ፍቅሩ የሚታወቅ ታላቅ ባለሙያ ነበር። ነፍስሄር ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር።
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንት እና ሰራተኞች በደረሰው ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው፤ ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ባልደረቦቹ እና ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ተመኝተዋል።
ድጋሚ የማናገኘው ድንቅ ሰው!
ፈጣሪ ነፍስህን በአጻድ ጻድቅ ያኑርልን! 🕯️💔
#restinpeace #netsanetworkneh #ebs #ethiopianartist #familygame #legend

⚫ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አሜሪካ ውስጥ በድንገት አረፉ
"ባደሩበት ሆቴል ሞተው ተገኝተዋል!"
#ethiopia | ለስራ ጉዳይ ወደ አሜሪካ ተጉዘው የነበሩት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የፊዚክስ ምሁሩ ዶ/ር ለታ ተስፋዬ፤ በትናንትናው ዕለት ባደሩበት ሆቴል ውስጥ ህይወታቸው አልፎ መገኘቱ ተሰማ።
ዩኒቨርሲቲው በሰጠው መግለጫ፤ ዶ/ር ለታ ለ6 ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ባገለገሉበት ወቅት "ትውልድን ማብቃት" በሚል መርህ በትጋት የሰሩ እና በህዝቡ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ መሪ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ አሟሟታቸውን "ያልተጠበቀ ህይወተ እልፈት" ሲል ገልጾታል።
ዶ/ር ለታ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራር እና በፊዚክስ ዘርፍ ትልቅ አሻራ ያሳረፉ ውድ የሀገር ልጅ ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሙያ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን።
ነፍስ ይማር! 🕯️
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#drletatesfaye #dembidolouniversity #restinpeace #ethiopia #education

⚫ "በእኔ ቤት የገባ መከራ በቤታችሁ አይግባ!"
#ethiopia | የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆነው ወንድማችን አቶ ንጋቱ ማሞ፤ የትዳር አጋሩን በሞት ተነጥቋል።
ባለቤቱ ወ/ሮ መዓዛ አለማየሁ በጡት ካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቷ አልፎ የቀብር ስነ-ስርአቷ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
አቶ ንጋቱ በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆኖ "በእኔ ቤት የገባ መከራ በቤታችሁ አይግባ!" ሲል የሀዘኑን ጥልቀት ገልጿል።
ለአቶ ንጋቱ፣ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናትን ይስጥልን።
የወ/ሮ መዓዛን ነፍስ ይማርልን!
አይዞህ ወንድማችን! እግዚአብሔር ያጥናህ! 🙏🕯
#condolence #nigatumamo #restinpeace #addisababa

10 months ago
'ከዚህ በኋላ በእኔ ምክንያት ዋጋ አትከፍልም፤ደህና ሁን''
እራሱን ያጣፋው የ29 አመቱ ጋዜጠኛ💔
አሳዛኝ ዜና ከወደ ኬንያ ኬንያ ተሰምቷል። ጋዜጠኛ ኪማኒ ምቡጉዋ በአንድ ወቅት በCitizen TV እና NTV ስክሪኖች ብዙዎችን ያስደመመ ጎበዝ ባለታሪክ ነበር። ነገር ግን ከካሜራ ብርሃን ጀርባ ባይፖላር ዲስኦርደር እና ድብርት ብዙ ቀናትን ብቻውን ጨለማ ቤት ውስጥ እንዲያሳልፍ አድርጎታል። በዚየአእምሮ ጤና ፈተናዎችን እየታገለ እንደሚገኝ በድፍረት በአደባባይ ተናግሯል።
ትላንት ግን አልቻለም የአእምሮ ጤና ክትትል ከሚያደርግበት Mombasa Women Empowerment Network Mental Rescue / Rehabilitation Centre ለአባቱ ብጣሽ ወረቀት ፅፏል። 'ከዚህ በኋላ በእኔ ምክንያት ዋጋ አትከፍልም፤ደህና ሁን'' ይላል። በገዛ እጁ ህይወቱን ነ*ጠቀ
የጋዜጠኛው ሞት በቅርቡ እየተባበሰ ለመጣው የጋዜጠኞች የአእምሮ ጤና ዘርፍ ትኩረት እንዲሰጠው የማንቂያ ደወል ነው። በኢትዮጵያ ብዙ ጋዜጠኞች በዝምታ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ከባድ የስራ ጫና፣ ዝቅተኛ ክፍያ፣ የonline ጥቃት እና ዛቻ፣ አንዳንድ ጊዜ ደሞ ሽፋን የምንሰጣቸው ዘገባዎች በራሳቸው የሚያመጡብን የስነ ልቦና ጉዳቶች ቀላል አይደሉም። ሆኖም የአእምሮ ጤና News room ውስጥ ብዙም አይወራም ወይም ሽፋን አይሰጠውም!!
ዝምታውን ለመስበር ጊዜው ነው!!
እርዳታ መፈለግ ጥንካሬ እንጂ ድክመት አይደለም!!!
🕯️ Rest well, Kimani. Your story will continue to inspire a conversation we all need to have. 💔
#kimanimbugua #mentalhealthawareness #journalistsmatter #ethiopia #mediawellbeing #restinpeace Tiblets Tesfaye Ritha

11 months ago
አትሌት ሸዋረግ አለን አማረ አረፈች
#ethiopia | አትሌቷ ትላት በአዲስ አበባ ዙሪያ በልምምድ እያለች ነው የድካም ስሜት ተሰምቷት ወደ ሆክፒታል ተወሰዳ እንዳረፈች ነው የደረሰኝ መረጃ የሚጠቁመው ።
ኑሮዋን በላቲን አሜሪካ ሜክስኮ ያደረገችው ፤ አለሽኝ የ2025 የሲውድን ስቶኮልም ማራቶን አሸናፊ ስትሆን ለልምምድ አዲስ አበባ መጥታ ነው ህይወቷ ያለፈው።
አትሌቷ የቀድሞ አትሌት አለነ አማረ ልጅ ስትሆን የቀድሞ አትሌት አለነ አማረ ደግሞ ኑሮውን በአሜሪካ ኒዮርክ ካደረገ ከ25 አመት በላይ ሆኖቷል።
Shewarge Alene, our 2025 Stockholm Marathon champion.
Mexico City Marathon - 2012 & 2014
Santiago de Chile Marathon - 2013 & 2014
Maratón Internacional Lala - 2014
Via #ethiorunners
#restinpeace #foreverourchampion #gonebutneverforgotten

Comments