Logo
Getu Temesgen
💔 የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን አዲስ አበባ ገባ፤
ነገ የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል 🕯️
#ethiopia | ​የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዋቂው ባለሙያ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሷል።

በአየር ማረፊያውም የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።

​አስከሬኑ በቤተሰቦች፣ በወዳጅ ዘመዶችና በስራ ባልደረቦች ታጅቦ ሳር ቤት አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ደርሷል።

​የነገው የክብር ስንብት መርሃ ግብር፦

​📅 ነገ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

​🕒 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉዞ ይደረጋል።

​📍 ስነ-ስርዓት፦
በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ ልዩ የሽኝትና የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል።

​አቶ አማን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ዘመናዊና ጥራት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖር ካደረጉ ቀዳሚ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

​ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️

​#amanfissehazion #ebs #ebsworldwide #ethiopia #medialegend #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.