6 months ago
🕯️ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ 🕯️
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት የባለራዕዩ አቶ አማን ፍስሃጽዮን ሥርዓተ ቀብር ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በጴጥሮስ ወጳውሎስ መካነ መቃብር ተፈጽሟል።
በሥርዓተ ቀብሩ ላይ፦
የሟች ቤተሰቦችና የቅርብ ወዳጅ ዘመዶች፣
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሥራ ባልደረቦችና የጥበብ ሰዎች፣
ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የተለያዩ ተቋማት መሪዎች ተገኝተው የመጨረሻ ስንብት አድርገዋል።
አቶ አማን ፍስሃጽዮን የኢትዮጵያን የሚዲያ ኢንዱስትሪ በማዘመንና ጥበብን ወደ ቤታችን በማድረስ ረገድ የማይረሳ አሻራ ጥለው አልፈዋል። ላበረከቱት ታላቅ አስተዋጽኦ ሁሌም ሲታወሱ ይኖራሉ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የኢቢኤስ ሠራተኞች መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ! 🙏
#ebs #amanfissehazion #ethiopia #medialegend #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

💔 የአቶ አማን ፍስሐጽዮን የሕይወት ታሪክ🕯️
1964 - 2018
#ethiopia | አቶ አማን ፍስሐጽዮን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የካቲት 3 ቀን፤ 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ53 ዓመታቸው በአሜሪካን አገር በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከዚህ ዓለም ድካም በሰላም አርፈዋል። አቶ አማን በህይወት ዘመናቸው ባለራዕይና ስራ ፈጣሪ ታማኝ ባለትዳርና መልካም አባት እንዲሁም ኩሩ ኢትዮጵያዊ ነበሩ።
አቶ አማን ህይወቱና ማንነቱ በእምነት፣ በቁርጠኝነት፣ በተስፋና በጽናት ላይ የቆመ ትጉህ ሰው ነበር። በፈጣሪ ላይ በነበረው ጽኑ እምነትና ለወገኖቹና ለሀገሩ በነበረው የማይነጥፍ ፍቅር የተነሳ የተቸገሩትን ለመርዳት የሌሎችን እንባ ለማበስ የማይታክት ሰው ነበር። ሌሎችን ለማገልገል ያለውን ወደርየለሽ ፍላጎትና ፈገግታው በሚያውቁት ሁሉ የሚናፈቁ የሰብእናው መሰረቶች ናቸው።
አቶ አማን ሐምሌ 3 ቀን 1964 ዓ.ም ከአባቱ ከአቶ ፍስሐ ጽዮን ገብረ ሕይወትና ከእናቱ ከወይዘሮ ሕይወት ተኬ በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። ለቤተሰቡ ስድስተኛና የመጨረሻ ልጅ የሆኑት አቶ አማን እምነትን ማዕከል ባደረገ የቤተሰብ እሴቶች በነበረበት ቤት ውስጥ በወላጆቹ በአያቱ በወይዘሮ ይመስገን ገብረሥላሴ በማይነጥፍ ፍቅርና ምክር ታንጸው አድገዋል።
የአቶ አማን የሰብእና መሰረትና መገለጫ ባህሪይ የሆኑት በጎነት፣ ብሩህ ተስፋ ቆራጥነትና የመሪነት ስብዕና ገና በለጋ እድሜው ከቤተሰቡ ያገኘው እሴቶች ናቸው። አቶ አማን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ሳንፎርድ የእንግሊዝ ትምህርት ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ አሜሪካ በመጓዝ በዮርክ ፔንሰልቬንያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቅቀዋል።
በመቀጠልም ከፔንሰልቬንያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ በኦፕሬሽን ማኔጅመንት እና ማርኬቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። በውጭ ሀገር የነበራቸው ቆይታ የአስተሳሰብ አድማሳቸውን በማስፋት የህይወት ገጠመኛቸውን ቢያዳብራቸውም ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ቁርኝት ግን ምንጊዜም የማይነጥፋቸው መሰረት ስለነበር ትምህርታቸውን እንደጨረሱ ሀገራቸውን ለማገልገል በታላቅ ተነሳሽነትና ዓላማ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
አቶ አማንና የሕይወት አጋሩ ወይዘሮ ማክዳ አሰፋ የተገናኙበት 1989 ዓ.ም ሲሆን ከሁለት ዓመታት በኋላ ሚያዝያ 1 ቀን 1991 ዓ.ም በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ ጋብቻቸውን ፈጽመዋል። ትዳራቸውም በጥልቅ ፍቅር ማደናቀፍ መደጋገፍ ሁኔታዎችና ፈተና በማይበግረው ጽኑ ታማኝነት ላይ የተገነባ የሕይወት ጥምረት ነበር። ሁለት ሆነው እንደ አንድ የኖሩበትን የትዳር ሕይወት በመከባበር በፈሪሃ እግዚአብሔር እና በጋራ ህብረት በተገነባ ጥንካሬ መርተውታል። በዚህም ጊዜ አማኑኤል መቅደላዊትና ሰላም ፍስሐ ጽዮን የተባሉ ሦስት ልጆችን ያፈሩ ሲሆን ኖቫ የተባለች የልጅ ልጅ ለማየትም በቅተዋል። አቶ አማን በሕይወታቸው እጅግ መጠነ ሰፊ የሆኑ ስኬቶች ባለቤት ቢሆኑም ከሁሉም በላይ ትልቁ ኩራታቸውና ደስታቸው ቤተሰባቸው ነበር።
አቶ አማን በ2000 ዓ.ም ከአጋሮቻቸው ከአቶ ሙሴ ፍስሐጽዮን፣ አቶ ዮሃን ፍስሐ ጽዮንና አቶ ነቢዩ ያሬድ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስን (EBS TV) በሲልቨር ስፕሪንግ ሜሪላንድ መሰረቱ።
በታላቅ ራዕይ የተጀመረው ይህ ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተመልካቾች የሚደርስና በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ የመገናኛ ድልድይ ለመሆን በቅቷል።
ኢቢኤስ የአቶ አማንን የፈጠራ ስራ አመራርና አርቆ አሳቢነት የሚያንጸባርቅ በማህበረሰቡ ዘንድ ታማኝነትና ተደማጭነት ያለው ድምፅ ለመሆን በቅቷል።
አቶ አማን በ2003 ዓ.ም ለብዙ ዘመናት ሲመኙት የነበረውን ወደ ሀገር የመመለስ ውሳኔ ተግባራዊ በማድረግ በህይወታቸውና በሙያቸው ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍተዋል። በእሳቸው መሪነት ኢቢኤስ በኢትዮጵያ የሚዲያ እድገት ላይ ጎልቶ ሚና ተጫውቷል።
የነደፉት ራዕይና ከአጋሮቻቸው ጋር ተደምሮ በሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ኢንዱስትሪ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥና ሽግግር እንዲመጣ ረድቷል። ነፃ የመገናኛ ብዙሃን እንዲስፋፋ እና በቴሌቪዥን በመገናኛው ዘርፍ ለአዳዲስ ፈጣሪዎችና ለበርካታ ባለሙያዎች እድልና መድረኮች እንዲፈጠሩ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
አቶ አማን በጣም በርካታ ውጤቶችን ባስመዘገቡበትና መሰረታዊ የሚባል አሻራ ባሳረፉበት ጎልህ የሥራ ዘመናቸው፤ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ውስጥ በበርካታ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የአመራርነትና በቦርድ አባልነትም አገልግለዋል። የቲ.ኤ ብሮድካስቲንግ (TA BROADCASTING INC.) ዋና ሥራ አስፈጻሚ፤ የክሊር ኮሙኒኬሽን (CLEAR COMMUNICATIONS INC.) የማርኬቲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት እና በአዲስ አበባ የአቪዬሽን ኢንተርናሽናል ማኔጅንግ ዳይሬክተር በመሆን ሰርተዋል።
በተጨማሪም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ በአዲስ አበባ የዲያስፖራ ማህበር፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር ውስጥም በስራ አመራር ቦርድ አባልነትና በባለሙያነት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።
ለእነዚህ አበርክቶታቸውና ስኬቶችም በርካታ እውቅናዎችንና አክብሮቶችን አግኝተዋል። ከነዚህም መካከል የኢትዮ - አሜሪካ የንግድ ምክር ቤት የላቀ የንግድ ስራ ሽልማትና የዓመቱ ፈር ቀዳጅ የዲያስፖራ ባለሀብት በመሆን የተሸለሙት ይገኙበታል።
አቶ አማንን በቅርብ የሚያውቋቸው ሁሉ በሙያዊ ስኬታቸው ብቻ ሳይሆን፣ በሰብዕናቸው ጥንካሬ፣ በደግነታቸው፣ በለጋስነታቸው፣ ሌሎችን ሳይቀር በነበረበት አልፎ ለተግባራዊነቱ እንዲተጉ በማነሳሳት ልዩ ችሎታቸው ያከብሯቸዋል፣ ይወዷቸዋል። አቶ አማን ዘንድ ተስፋ መቁረጥ፣ መሸነፍ፣ መረታት ቦታ አልነበራቸውም።
የትኛውንም መሰናክል በማስተዋል፣ በጥበብ እና በብልሃት የሚያልፉ፣ በጊዜያዊ ጫጫታና ሁከት የማይረበሹ፣ ከፍርሃትና ከጥርጣሬ ጨለማ ይልቅ የተስፋን ብርሃን የመረጡ መልካም ሰው ነበሩ። የአመራር መርሆቸውና ከሰው ጋር የነበራቸው መስተጋብር የረጋ መንፈስን እና ቅን ልቦናቸውን መሰረት ያደረገ ነበር።
በጣም ፈታኝ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ እያስፋ እንኳን፣ ነን የተሻስ እንደሚሆን የማይናወጥ እምነት ነበራቸው። ያንን የተሻለ ነገ እውን ስማድረግም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሰርተዋል። አቶ አማን በሕይወት የተለዩት፣ የሚወዷት ባአቤታቸው ወይዘሮ ማክዳ ፍስሐ ጽዮን፣ ልጆቻቸውን እማኑኤል፣ መቅደኣዊትና ሰላም ፍስሐጽዮን፣ የልጅ ልጁን ኖቫ ፍስሐጽዮን፣ አናቱን ወይዘሮ ሕይወት ተኬን፣ ወንድምና እህቶቹን ሜሮንን፣ ሙሴን፣ ኖኀን፣ ነጻንና ሜሪ ፍስሐ ጽዮንን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የቤተሰብ አባላትንና ወደጆቹን ብቻ ሳይሆን የስሯቸውን ፍሬ የሚያውቁትን ሁሉ ነው፡፡
አቶ አማን አሁን በፈጣሪ ፊት በዘላለማዊ ሰላም እና አረፍት እንዳስ እናምናለን። ይሁን አንጂ ታሪካቸው ወደፊት በነጻነት አንዲራመድ ባንዟቸው ባቋቋሟቸው እና በገነቧቸው ተቋማትና ከምንም በላይ በሚወዱት ቤተሰብ ውስጥ ህያው ሆኖ ይኖራል። አቶ አማን በጸና እምነት ተመርተው በታማኝነት ፣ በማገልገል እና እራስን አሳልፎ በመስጠት ሙሉ ሕይወትን ኖረዋል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ታሪክ ውስጥ፣ ባስራእይና የለወጥ ሀይል፣ ለዘርፉ አርአያ የሆነ፣ ፈር ቀዳጅ፣ ሀገር ወዳድና የእምነት ሰው ሆነው ምንጊዜም ሲታወሱ ይኖራሉ።
ሁሌም በልባችህን ትኖራለህ
ፈጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️
#ሼር #share
#amanfissehazion #ebs #ebsworldwide #ethiopia #medialegend #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

💔 ኑ - በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እንሰናበተው🕯️
[ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መሰናበት ይችላል ]
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዋቂው ባለሙያ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን የስንብት መርሃ ግብር
📅 ዛሬ፣ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.
🕒 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የስንብት መርሃ ግብር ይደረጋል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ዘመናዊና ጥራት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖር ካደረጉ ቀዳሚ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️ #ሼር #share

💔 የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን አዲስ አበባ ገባ፤
ነገ የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል 🕯️
#ethiopia | የኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የነበሩት ታዋቂው ባለሙያ የአቶ አማን ፍስሃጽዮን አስከሬን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሷል።
በአየር ማረፊያውም የክብር አቀባበል ተደርጎለታል።
አስከሬኑ በቤተሰቦች፣ በወዳጅ ዘመዶችና በስራ ባልደረቦች ታጅቦ ሳር ቤት አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ደርሷል።
የነገው የክብር ስንብት መርሃ ግብር፦
📅 ነገ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም.
🕒 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ጉዞ ይደረጋል።
📍 ስነ-ስርዓት፦
በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ ልዩ የሽኝትና የስንብት መርሃ ግብር ይከናወናል።
አቶ አማን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ውስጥ ዘመናዊና ጥራት ያለው የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲኖር ካደረጉ ቀዳሚ ባለሙያዎች አንዱ ነበሩ።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሰራተኞች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። 🙏🕯️

Sponsored by
Surafel
Comments