Logo
Getu Temesgen
🕊️ የሩጫ ንግሥት፤ የመሠረት ደፋር እናት​ እናመሰግናለን🕯️
#ethiopia | ይህ ዜና ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ፣ የሩጫ ንግሥቷ መሠረት ደፋር እና ለመላው ቤተሰቦቿ እንዲሁም ለአድናቂዎቿ እጅግ አሳዛኝ ነው።

ወይዘሮ አስቴር መንገሻ ለሀገር ኩራት የሆነችውን መሰረት ደፋርን ብቻ ሳይሆን፣ ስድስት ልጆችንና 18 የልጅ ልጆችን አፍርተውና ለቁም ነገር አብቅተው ያለፉ ማኅፀነ ለምለም እናት ነበሩ።

​ሀገርን የሚያስጠሩ ጀግኖችን ያፈሩትና ለ54 ዓመታት በፍቅርና በሰላም ትዳራቸውን የመሩት ማኅፀነ ለምለሟ እናት ወይዘሮ አስቴር መንገሻ በተወለዱ በ71 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

​📜 አጭር የሕይወት ታሪክ፦

​ልደት፦
በ1947 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ኢጄሬ ወረዳ (አዲስ ዓለም) ተወለዱ።

​ትዳርና ቤተሰብ፦
በ1964 ዓ.ም ከአቶ ደፋር ቶላ ጋር ትዳር መስርተው ለ54 ዓመታት በጽኑ ፍቅር ዘልቀዋል። የ6 ልጆች እናትና የ18 የልጅ ልጆች አያት ለመሆን በቅተዋል።

​የጀግኖች እናት፦
የዓለምን የሩጫ መድረክ የገዛችውንና በኦሎምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ወርቅ ለሀገሯ ያስገኘችውን የሩጫ ንግሥት አትሌት መሰረት ደፋርን ለኢትዮጵያ ያበረከቱ ታላቅ እናት ነበሩ። ሌሎች ልጆቻቸውም በሙሉ በሕክምናው ዘርፍ ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ አሳድገዋል።

መሰረት ደፋር እ.ኤ.አ በ2007 የአለም ምርጥ አትሌት ተብላ እንድትመረጥና ስሟ በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ እንዲሰፍር ያደረጉትን ዋና ዋና ስኬቶች እንዲህ ማጠቃለል ይቻላል፦

​ የአትሌት መሰረት ደፋር ታሪካዊ ስኬቶች በአጭሩ
​የአለም ክብረ ወሰኖች (World Records):
​5,000 ሜትር፦ በኦስሎ (ኖርዌይ) 14:16.63 በመግባት ቀዳሚ ሆናለች።

​2 ማይል፦ በካሊፎርኒያ እና በቤልጅየም (8:58.58) በመግባት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ9 ደቂቃ በታች የሮጠች የኢትዮጵያ ጀግና ሴት ናት።

​3,000 ሜትር (የቤት ውስጥ/Indoor): በጀርመን ስቱትጋርት 8:23.72 በመግባት ክብረ ወሰን አስመዝግባለች።

​የኦሎምፒክ ድሎች:
​እ.ኤ.አ በ2004 በአቴንስ ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።
​እ.ኤ.አ በ2012 በለንደን ኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ።

​ታሪካዊ እውቅና:
​እ.ኤ.አ በ2007 የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (IAAF) የአመቱ ምርጥ ሴት አትሌት ሽልማት ባለቤት።

​አንዲት እናት ለሀገር የምታበረክተው ከሁሉ የላቀ ስጦታ፣ ሀገሩን የሚወድና ስሟን ከፍ የሚያደርግ ጀግና ትውልድ መፍጠር ነው፤ ወይዘሮ አስቴር ይህንን በተግባር አሳይተዋል።

​ሀገራዊ አገልግሎት፦
ወይዘሮ አስቴር ራሳቸውም ሰላም አስከባሪ በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ ጀግና ነበሩ።

​መንፈሳዊ ሕይወት፦
ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው፣ በቤተክርስቲያን ሥርዓት የተጉና የሰማይ መንገዳቸውን በቅዱስ ቁርባን የጠረጉ እናት ነበሩ።

​🥀 የስንብት ሥነ-ሥርዓት፦

ወይዘሮ አስቴር ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሀገር ውስጥና በውጭ ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው፣ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም አርፈዋል።

የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም (የካቲት 15/2018 ዓ.ም) በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

​ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen) ለጀግናዋ አትሌት መሰረት ደፋርና ለመላው ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል።

​ፈጣሪ የነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን! 🙏🇪🇹

​#መሰረትደፋር #ወይዘሮአስቴርመንገሻ #የሐዘንመግለጫ #meseretdefar #ethiopia #legacy #restinpeace #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.