4 months ago
የቲክቶክ ንጉስ ካቢ ላሜ የግል አካውንቱ ውስጥ ድንቡሎ የለውም ተባለ
#ethiopia | በቲከቶክ ማኅበራዊ ገጽ ላይ ንግግር ሳይጠቀም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማዝናናት የሚታወቀው ካቢ ላሜ፣ አሁን ላይ የግል ህይወቱና የፋይናንስ አያያዙ አነጋጋሪ ሆኗል።
በተለይም ከባለቤቱ ጋር እያደረገ ያለው የፍቺ ሂደት፣ የኮከቡን ያልተጠበቀ የሀብት አያያዝ ምስጢር ይፋ አድርጓል።
ምንም እንኳን የካቢ ላሜ አጠቃላይ የተጣራ ሀብት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት ቢገለጽም፣ በፍቺ ሂደቱ ወቅት የቀረቡ የፍርድ ቤት ሰነዶች ግን ሌላ እውነትን አመልክተዋል።
እንደ ሰነዶቹ ገለጻ፣ ካቢ ላሜ በራሱ ስም የተመዘገበ ምንም ዓይነት ዋና ንብረት ወይም የባንክ ሂሳብ የለውም።
የምርመራ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ የካቢ ላሜ የቅንጦት ቤቶችና አብዛኛው የፋይናንስ ይዞታዎች የተመዘገቡት በአባቱ ስም ነው።
ይህ ዓይነቱ አካሄድ በታዋቂ ሰዎች ዘንድ የተለመደ የሀብት መከላከያ ስልት እንደሆነ ይነገራል። ዓላማውም በፍቺ ወቅት የሚመጣን የሀብት ክፍፍል ወይም ከፍተኛ የቀለብ ክፍያን (Alimony) ለመቀነስ ታስቦ የሚደረግ መሆኑ ይገመታል።
ይህ ግኝት በፍርድ ቤቱ ቀጣይ ውሳኔ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል። የፍርድ ቤቱ ባለሙያዎች ይህንን የሀብት ሽግግር እንደ "ንብረትን የመደበቅ ሙከራ" ካዩት፣ ኮከቡ ከባድ የገንዘብ ቅጣት ወይም የሀብት ክፍፍል ሊገጥመው ይችላል።
በማኅበራዊ ገጾቹ ላይ ሁሌም ዝምታን የሚመርጠው ካቢ፣ በዚህ አነጋጋሪ የገንዘብ ጉዳይ ላይ እስካሁን የሰጠው ምላሽ የለም።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#መናኸሪያfm #getutemesgen #getu #khabylame #tiktok #celebritynews #finance #divorce #wealthmanagement #internationalnews #ካቢላሜ #ቲከቶክ #ዜና #ኢትዮጵያ

6 months ago
የስኑፕ ዶግ ሴት ልጅ ኮሪ ብሮደስ የልጇን ህልፈት ተናገረች
የስኑፕ ዶግ ሴት ልጅ የሆነችው ኮሪ ብሮደስ ገና በጨቅላነቷ ላይ የነበረችው ልጇ (የስኑፕ ዶግ የልጅ ልጅ) ማለፏን በከፍተኛ ሀዘን ገልጻለች።
ኮሪ ይህንን መርዶ በማህበራዊ ሚዲያ ገጿ ላይ ያጋራች ሲሆን፣ "ልቤ ተሰብሯል" ስትል ስሜቷን ገልጻለች። ህጻኗ ቻያ ትባላለች። ኮሪ ልጇን "ውድ መልአካችን" ስትል የጠራቻት ሲሆን፣ ህልፈቷ ለቤተሰቡ ትልቅ ድንጋጤ ሆኗል።
ብዙ ታዋቂ ሰዎችና ደጋፊዎቿ ለኮሪ እና ለቤተሰቧ ያላቸውን አጋርነትና መጽናናትን እየገለጹ ይገኛሉ። ኮሪ ቀደም ሲል "Lupus" (ሉፐስ) በተባለ የጤና እክል ስትሰቃይ እንደነበርና በቅርቡም የጭንቅላት ደም መፍሰስ አጋጥሟት እንደነበር ይታወሳል። ይህ አዲስ ሀዘን ደግሞ በቤተሰቧ ላይ ተጨማሪ ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል።
#fastmereja #snoopdogg #coribroadus #celebritynews #restinpeace #hollywoodgossip #dailymail #heartbreaking #ስኑፕዶግ #የታዋቂዎችወሬ #ሀዘን #ትኩስመረጃ

ከትልቅ የገንዘብ ስምምነት እስከ ቤተሰባዊ አለመግባባት
ዴቪድ ቤካም በአንድ በኩል ትልቅ የንግድ ስኬት እያስመዘገበ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከልጁ ከብሩክሊን ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተነግሯል።
ዴቪድ ቤካም ከታዋቂው የቢራ ምርት Stella Artois ጋር የብዙ ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት መፈረሙን በይፋ አስታውቋል። ይህ ስምምነት የቤካምን የንግድ ግዛት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።
ዴቪድ ይህንን ትልቅ ስኬት ቢያበስርም፣ ከትልቁ ልጁ ብሩክሊን ቤካም ጋር ያለው ግንኙነት ግን ጥያቄ ምልክት ውስጥ ወድቋል። ዘገባው እንደሚያመለክተው፣ ብሩክሊን በአባቱ ጥላ ስር መሆን ሰልችቶታል፤ የራሱን ማንነት ለመፍጠር በሚያደርገው ጥረት እና በሚከተለው የአኗኗር ዘይቤ ምክንያት ከአባቱ ጋር አለመግባባቶች ተፈጥረዋል።
እናቱ ቪክቶሪያ ቤካም በባሏና በልጇ መካከል ያለውን ሁኔታ ለማለስለስና ቤተሰቡን አንድ ለማድረግ እየጣረች እንደሆነ ተጠቁሟል።
#fastmereja #davidbeckham #brooklynbeckham #victoriabeckham #familydrama #celebritynews #thesun #showbiz #beckhamfamily #ዴቪድቤካም #የታዋቂዎችወሬ #ሾውቢዝ #ቤተሰብ

Comments