19 days ago
How to Get Your First Job in Media
Free 3-Hour Career Starter Session for Fresh Journalism Graduates
This practical session will help you move from graduation to your first media opportunity.
See more https://t.me/concepthubeth...
Via Concepthubeth

25 days ago
"ጥፋት ሳናጠፋ ይቅርታ አንጠይቅም!"
የአምስቱ ጋዜጠኞች ውሳኔ እና የሲፒጄ ጥሪ
#ethiopia | በእስር ላይ የሚገኙ አምስት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ምንም አይነት ወንጀል ስላልፈጸሙ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር እንዲፈቱ የቀረበላቸውን ሀሳብ አለመቀበላቸውን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ወይም ሲፒጄ አስታወቀ።
ጋዜጠኞቹ ጎበዜ ሲሳይ፣ መስከረም አበራ፣ ገነት አስማማው፣ ዳዊት በጋሻው እና አባይ ዘውዱ ሲሆኑ በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2023 የተያዙ ናቸው። ከዚያም በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰሰው የፍርድ ቤት ሂደታቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
የተከሳሾቹ ጠበቃ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ እንደገለጹት የማረሚያ ቤት ኃላፊዎች ጋዜጠኞቹን ከሌሎች ታሳሪዎች በመለየትና በማስፈራራት መንግስት ያዘጋጀውን የይቅርታ ወረቀት ፈርመው ከእስር እንዲወጡ እንዲሁም የጋዜጠኝነት ስራቸውን እንዲተዉ ጫና ሲያደርጉባቸው ነበር። ነገር ግን ጋዜጠኞቹ ምንም ያጠፉት ጥፋት በሌለበት ሁኔታ ራሳቸውን እንደ ወንጀለኛ አድርገው መቁጠርና ማመንን ባለመቀበል የቀረበላቸውን ጥያቄ ፈፅመው ውድቅ አድርገውታል ብለዋል።
የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋዜጠኞቹን ለረጅም ጊዜ ካሰሩ በኋላ በፍርድ ቤት ማረጋገጥ ያልቻሉትን ወንጀል በግዴታ አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ የሚያደርጉትን አካሄድ ኮንነዋል።
አስተባባሪዋ አክለውም በጋዜጠኞቹ ላይ የሚፈጸመው ያልተገባ ጫና በአስቸኳይ እንዲቆም፣ የተመሰረተባቸው ክስ ተነስቶ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንዲሁም ሙያቸውን በነጻነት ማከናወን እንዲችሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በሽብርተኝነት የተከሰሱ ከ300 በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የተለያዩ ግለሰቦች የይቅርታ ቅጽ እንዲፈርሙ መጠየቃቸው ተመልክቷል። ነገር ግን ከነዚህ መካከል 30 የሚሆኑ ተከሳሾች ጉዳያቸው ገና በህግ ሂደት ላይ እያለ ራሳቸውን ጥፋተኛ አድርገው እንደማይፈርሙ በመግለጽ ጥያቄውን አለመቀበላቸው ታውቋል።
መንግስት ለጋዜጠኞቹ ያቀረበው ጥያቄ የተለመደ የይቅርታ አሰራር እንደሆነ ቢገልጽም ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ግን በሃገሪቱ ሕግ መሰረት ይቅርታ ሊደረግ የሚችለው አንድ ግለሰብ በስርዓቱ ፍርድ አግኝቶ ጥፋተኛ ከተባለ በኋላ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል።
የጋዜጠኞቹ የችሎት ጊዜ በተደጋጋሚ በመሰረዙ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ለኖቬምበር 19 ተቀጥሯል።
#journalism #pressfreedom #ethiopianews #cpj #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago
የሮይተርስ መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ታግዶ የነበረው የሥራ ፈቃድ ታደሰ
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላለፉት ስድስት ወራት ታግደው የነበሩ የሦስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ ማደሱን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ከዓለም አቀፉ የዜና ተቋም ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ኒክ ታተር እና የአፍሪካ ኤዲተር ሲልቪያ አሎይሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት ተቋሙ ባለፉት ሰባት ወራት ያሰራጫቸው አንዳንዶቹ ዘገባዎች የሀገሪቱን ሕግ፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንዲሁም ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ያልጠበቁ እንደነበሩ የክትትል ውጤቶችን በማስደገፍ አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክቷ አክለውም የሮይተርስ ዘገባዎች ሚዛናዊነት፣ ትክክለኝነትና ተአማኒነት ጎድሏቸው ወደ አንድ ወገን ያደሉ እንደነበሩ በመጠቆም ለተፈጠሩት የሕግና የሙያ ጥሰቶች የዜና ተቋሙ አስፈላጊውን እርማትና ማስተካከያ ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
የሮይተርስ ኃላፊዎች በበኩላቸው ተቋማቸው ገለልተኛ መሆኑን በመግለጽ ዘገባዎችን ከአድልዎ በጸዳ መልኩ ለመሥራት ጥብቅ መመሪያዎችን እንደሚከተል አስረድተዋል።
አልፎ አልፎ ለተከሰቱ ስህተቶች ይቅርታ በመጠየቅ ማስተካከያ እንደሚያደርጉና የኢትዮጵያን ሕግ፣ ባህላዊ እሴቶችና ብሔራዊ ጥቅም አክብረው ለመሥራት እንደሚጉ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይም ታግዶ የቆየው የሮይተርስ ዘጋቢዎች ፈቃድ እንዲታደስ የተደረገ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለጋዜጠኞቹ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።
#reuters #ethiopiamedia #journalism #pressfreedom #ema #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago
54 የሚዲያ ተቋማት፤ 461 ጋዜጠኞች የምክክሩን ሂደት እየዘገቡ ነው
#ethiopia | ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ያለውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለመዘገብ ፍላጎት ኖሯቸው ከኮሚሽኑ ጋር ግንኙነት የፈጠሩ 54 የሚዲያ ተቋማት 461 ዘጋቢዎችን በጉባኤው ቦታ አሰማርተው የጉባኤውን ሂደት ለህዝብ እያደረሱ ይገኛሉ፡፡
የሚዲያ ተቋማትን የዘገባ ተሳትፎ እና የመረጃ ተደራሽነትን በተመለከተ ኮሚሽኑ ያዘጋጀው ሪፖርት እንዳመለከተው ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክሩ ከመካሄዱ በፊት በርከት ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአጋርነት ማጠናከሪያ መድረኮችን ከመገናኛ ብዙሃን ሀላፊዎችና ባለሙዎች ጋር አካሂዷል፡፡
በእነዚህ መድረኮች በተፈጠረው ግንዛቤና በተደረሰው መግባባት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት በርካታ የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች እንዲሳተፉ መደላድል ከመፍጠሩ ባሻገር መረጃዎች በሙያዊና ሀገራዊ ሃላፊነት እንዲሰራጩ ማስቻሉን በዚሁ ሪፖርት ተጠቅሷል፡፡
ተሳትፎው ሁሉንም የመገናኛ ብዙሃን አይነቶች እንዳካተተ እንዲሁም የተቋማቱን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ባከበረ መልኩ መረጃዎችን ተደራሽ የሚያደርጉበት ነፃነት በኮሚሽኑ በኩል የተረጋገጠ መሆኑንም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡
ኮሚሽኑ በምክክሩ ቦታ ተገኝተው እንዲሁም ከኮሚሽኑ ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች እና በስፍራው ከሚገኘ መገናኛ ብዙሃን መረጃዎችን እየተጋሩ ለህዝብ እያደረሱ ላሉ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማትና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርቧል፡፡ ይህንን ተሳፎ እስከ ድህረ ምክክር አጠናክረው እንዲቀጥሉም ተጠይቋል፡፡
ህብረተሰቡ ወደ ምክክሩ ቦታ እየገቡ መረጃዎችን ተደራሽ ከሚያደርጉ መገናኛ ብዙሃንና ባለሙያዎች መረጃዎችን በማግኘት ከተዛቡ መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅም ኮሚሽኑ አስገንዝቧል፡፡
ኮሚሽኑ ይህንን ሪፖርት ያስደመጠው ከተለያዩ የዘርፉ ተቋማት ለተውጣጡና ኮሚሽኑን እየደገፉ ላሉ የሚዲያ ስራዎች አጋዥ አካላት ነው፡፡
#ethiopiannationaldialogue #mediacoverage #pressfreedom #ethiopia #journalism #nationalconsultation #mediainethiopia #informedcitizens #journalists #ethiopiannews

Sponsored by
Surafel
3 months ago
ያልተመዘገቡ ዲጂታል ሚዲያዎችን ወደ ሕጋዊ መስመር የሚያመጣ የአዋጅ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አሁን ላይ በበይነ መረብ (ዲጂታል) ሚዲያው ዘርፍ የሚታየውን የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ስርጭት ለመግታት፣ ያልተመዘገቡ ሚዲያዎችን ወደ ሕጋዊ የምዝገባ ሥርዓት የሚያስገባ የአዋጅ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ ይህንን የገለጹት፣ “ብቃት ያለው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የሚዲያ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ዳይሬክተሯ በዚሁ ጊዜ እንዳብራሩት፣ ከአመታት በኋላ በሚዲያው ዘርፍ የተደረገውን ሰፊ ሪፎርም ተከትሎ ድረ-ገጾችን የማፈንና የመዝጋት አሰራር በመቅረቱ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ጠንካራና ሚዛናዊ የዲጂታል ሚዲያዎች ሊፈጠሩ ችለዋል።
ይሁን እንጂ ይህንን ምቹ ሁኔታ ተጠቅመው የሕዝብን አመኔታ ካገኙት ባሻገር፣ የተወሰኑት የዲጅታል ሚዲያዎች የሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር የሚያሰራጩ እንዲሁም የሀገርን ሉዓላዊነትና የጋራ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላት መበራከታቸውን ዳይሬክተሯ በንግግራቸው አብራርተዋል።
ይህንን አሳሳቢ ተግዳሮት ለመቅረፍም ባለሥልጣኑ በርካታ ተከታዮች እያሏቸው ነገር ግን ሳይመዘገቡ በዘፈቀደ የሚንቀሳቀሱ ሚዲያዎችን ሕጋዊ ለማድረግ የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቀዋል።
አዲሱ አሰራር በፓርላማ ጸድቆ ሲተገበርም፣ ማንኛውም ዲጂታል ሚዲያ በሕጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ ገብቶ ለሀገር ሰላምና ለብሔራዊ ጥቅም በኃላፊነት ስሜት መሥራት እንደሚኖርበት አሳስበዋል።
የባለሥልጣኑ ዋና ዓላማ ተቋማትን መቅጣት፣ መዝጋት ወይም መቆጣጠር ብቻ አለመሆኑን ያነሱት ወ/ሮ ኃይማኖት፣ ተቋሙ ከቁጥጥር ይልቅ በአቅም ግንባታ፣ በምክክር እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።
በመሆኑም ሕጋዊ ሆነው ለሚመዘገቡ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎች የጋዜጠኝነት መታወቂያ ከመስጠት ጀምሮ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፎችን የሚያካትቱ የማበረታቻ ሥርዓቶች እንደሚዘረጉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የዘርፉ ባለሙያዎች እርስ በርስ የሚተራረሙበት፣ ለሙያዊ ሥነ-ምግባር መከበር የሚቆምና በሌሎች ሀገራት እንደሚታየው ራሳቸውን በራሳቸው እንዲቆጣጠሩ የሚያስችል ጠንካራ የጋዜጠኞች ማኅበር በማቋቋም በጋራ እንዲሰሩ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በጌትነት ተመስገን
📷 ኢመብባ
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #ethiopianmedia #digitalmedia #journalism #mediaregulation #ethiopianews

5 months ago
የታሪክ ምስክርነቱ እና የካሜራዬ የሕይወት ጉዞ
* ከምፅዋ እስከ ራያ ግንባር
#ethiopia | ለእኔ ካሜራዬ ተራ የሥራ መሣሪያ ሳይሆን የኢትዮጵያን ፈታኝ ወቅቶች፣ የጀግንነት ታሪኮችንና ወሳኝ ኩነቶችን በከፍተኛ መስዋዕትነት የዘገብኩበት ታማኝ የትግል አጋሬ ነው።
እያንዳንዱ በምስል የቀረጸው ትዕይንት ከጀርባው የእኔን የሕይወት ተጋድሎ ይዟል።
በአሁኑ ወቅት የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አጭርና ፍሬ ነገር ላይ ያተኮሩ ታሪኮችን የሚመርጥ በመሆኑ፣ እኔም በታሪካዊ የታሪክ መጋጠሚያዎች ላይ ተገኝቼ በሌንሴ ያስቀረሁትንና ያለፍኩበትን የሕይወት መስዋዕትነት እንደሚከተለው በአጭሩ አጋራችኋለሁ።
የታሪክ ምስክርነት ከምፅዋ እስከ ባድመ
በደርግ ሥርዓት ወቅት ገና በለጋ ዕድሜዬ በምፅዋ በረሃዎች ውስጥ የነበረውን የጦርነት እሳት በካሜራዬ እየቀረጽኩ የሀገርን ዋጋ በተግባር ተረድቻለሁ።
በዚያ አስቸጋሪ ወቅት ሌንሴን ወደ ጠላት ጥይትና ወደ ወገኖቼ ተጋድሎ ባዞርኩበት ቅጽበት የሀገር ፍቅር ትርጉም በውስጤ ይሰርጽ ነበር። እያንዳንዱን ገድል ለትውልድ እንዲተላለፍ በምስል ስዘግብ እኔም የታሪኩ አካል ነበርኩ።
ይህ በምፅዋ የጀመረው ጉዞ በኢህአዴግ ዘመን በባድመና በፆረና ግንባሮችም ቀጥሏል። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር የተደረገውን ተጋድሎ ከጥይት ይልቅ የካሜራዬን ድምጽ እያስቀደምኩ በታማኝነት መዝግቤያለሁ።
ድንበር ተሻጋሪው ሌንስ በባይደዋና ሞቃዲሾ
የካሜራዬ ጉዞ ከሀገር ድንበር ተሻግሮ በጎረቤት ሶማሊያ ባይደዋና ሞቃዲሾ ምድረ በዳዎች ድረስ ዘልቋል። ስጋትና አቧራ በነገሰበት በዚያ ቀጠና የኢትዮጵያ ሠራዊት ለሰላም የከፈለውን ዋጋና የህልውና ትግሉን በምስል በመክተብ የታሪክ ድርሻዬን ተወጥቻለሁ። በእያንዳንዱ ምስል ውስጥ ቆራጥነትንና የጀግንነት ታሪክን ለዓለም አሳይቻለሁ።
የቅርቡ ተጋድሎ ከቅራቅር እስከ ራያ
ሀገራችን ወደ አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ስትሸጋገር የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ለመዘገብ በግንባር ቀደምትነት ተሰማርቼ ነበር። ከቅራቅር እስከ ቆላ ተንቤን፣ ከጋሸና እስከ ራያ ግንባር ድረስ የድል ብስራቶችንና ልዩ ልዩ ሁነቶችን በካሜራዬ ስዘግብ ቆይቻለሁ።
በራያ ግንባር በፈንጂ በደረሰብኝ ጉዳት ካሜራዬ ለጊዜው እንዲያርፍና በአካሌ ላይ ድካም ቢፈጠርም መንፈሴ ግን አልተሰበረም። በዚያ አስከፊ ፍንዳታ ወቅት እንኳ ካሜራዬን አጥብቄ መያዜ የጽናቴ መገለጫ ነበር። ያ አጋጣሚ በደሜና በቁስሌ የጻፍኩት የሀገር ፍቅር አሻራ ሆኖ በታሪክ ውስጥ ይኖራል።
በበረሃ አቧራና በጦርነት እሳት ውስጥ የታጠቡት እነዚህ ምስሎች ለእኔ ምስክርነት ብቻ ሳይሆኑ ለሀገሬ የከፈልኩት መስዋዕትነትና የሕይወቴ ትልቁ ኩራት ናቸው።
ይህ ታሪክ በጽናትና በጀግንነት የተገነባ ሕያው ምስክርነቴ ነው።
ዳኜ አበራ
ፎቶግራፈር
#history #journalism #heroism #documentary #warcorrespondent #ethiopianarmy #resilience #photography #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
7 months ago
ጋዜጠኛ ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | በቀድሞ ፋና ሬዲዮ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ የነበረው ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በ1957 በቀድሞ አጠራሩ ወለጋ ክፍለ ሀገር ጊንቢ አውራጃ ላሎ አሳቢ ወረዳ የተወለደው ጋዜጠኛ ታሪኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ ቀድሞ ፋና የአሁኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን በመቀላቀል በአፋን ኦሮሞ ክፍል በሚዲያው ዘርፍ የኦሮሞን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ በማሳደግ ረገድ የበኩሉን ሚና ተጫውቷል።
ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት የነበረው ጋዜጠኛ ታሪኩ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊት በተወለደ በ61 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የጋዜጠኛ ታሪኩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በሚገኘው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ ለጋዜጠኛ
ታሪኩ ኦላና ቤተሰቦቹና ዘመድ ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል።
#fbc
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#tarikuolana #journalism #ethiopia #afaanoromo #fanabroadcasting #mediaicon #restinpeace #journalistlife #ethiopianmedia

8 months ago
🏆 ኩራት፦ ለሰባት ኢትዮጵያውያን የ"ጳጉሜን አዋርድ" ሽልማት ተሰጠ!
✨
#ethiopia | በካሊፎርንያ ግዛት ሎሳንጀለስ ከተማ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነ ደማቅ ስነ-ሥርዓት፣ የጷጉሜን የኢትዮጵያውያን መዝናኛና ባሕል ማዕከል (PEEC) ለሀገርና ለወገን ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰባት ኢትዮጵያውያን እውቅናና ሽልማት አበርክቷል።
🌟 የዘንድሮው የ"ጳጉሜን አዋርድ" ተሸላሚዎች፦
አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ)፦
በቱሪዝም ዘርፍ ከ86 በላይ ሀገራትን በመዞር ታሪካዊ ስፍራዎችን ያስተዋወቀ ልዩ ተሸላሚ።
ጋዜጠኛ ጌታቸው ወልዩ፦
ለ40 ዓመታት በጋዜጠኝነት፣ በታሪክና በዓባይ ተፋሰስ ጥናት ሀገሩን በታማኝነት ያገለገለ።
አርቲስት ተፈሪ አስፋ (Posthumous)፦
በኢትዮጵያ ሙዚቃ እድገት ላይ ላበረከተው የማይተካ ሚና (በድኅረ-ሕይወት) የክብር ሽልማት የተሰጠው።
ዶክተር ሐዋኒ ንጉሤ፦
በበጎ አድራጎትና በትምህርት ዘርፍ ለሕጻናትና ለትውልድ ግንባታ ለሰሩት የላቀ ስራ።
ደራሲ ወልደገብርኤል አስጌ፦
በሥነ-ጽሑፍና ታሪክ ዘርፍ "የነቢዩ መሐመድ ታሪክ" የተሰኘ ታሪካዊ ሰነድ በማኖራቸው።
ጋዜጠኛ ተወልደ በየነ (ተቦርነ)፦
የኢትዮጵያን የሙዚቃ ታሪክ በሰነድና በማኅደር በማቆየት ለተጫወቱት ሚና።
አቶ ፍስሐ ወልደ-አማኑኤል፦
በእግር ኳስ ስፖርት ታሪክ ውስጥ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ።
🙏 እንኳን ደስ አላችሁ!
እነዚህ ታላላቅ ግለሰቦች ለሀገራችን ብርሃን የሆኑ፣ በተሰማሩበት መስክ ሁሉ ጥበብንና እውነትን የተከሉ ባለሙያዎች ናቸው።
በባዕድ ሀገር ሆነው የሀገራቸውን ልጆች አበርክቶ የሚያከብሩት የጷጉሜን የባህል ማዕከል አባላትም ምስጋና ይገባቸዋል።
ለተሸላሚዎቹ ያላችሁን ደስታና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በኮሜንት አጋሩን። 👏
#pagumenawards #ethiopia #excellence #losangeles #ethiopianheros #art #journalism #sport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📖 "እንዲህም ተኑሯል"
— የአንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሕይወት ታሪክ ዛሬ ይመረቃል 🖋️✨
#ethiopia | ከ21 በላይ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃውና ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበብ ሐያሲነት ለበርካታ ዓመታት በጽናት ያገለገለው አንጋፋው ባለሙያ አበራ ለማ፣ የሕይወት ታሪኩን በ550 ገጾች ከሽኖ አቅርቧል።
ስለ መጽሐፉና ስለ ደራሲው፦
📚 ርዕስ፦ "...እንዲህም ተኑሯል"
📜 ይዘት፦
የደራሲውን የሕይወት ውጣ ውረድ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች የነበረውን ቆይታ እንዲሁም የሥነ-ጽሑፍ ጉዞውን በሰፊው ይዳስሳል።
🌟 የታወቁ ሥራዎቹ፦
"ኩል ወይስ ጥላሸት"፣ "ሽበት"፣ "ሕይወትና ሞት" እና "ሞገደኛው ነውጤ" የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በሥራዎቹም የአንባቢያንን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
የምረቃ መርሐ-ግብር፦
📅 ቀን፦ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 ቦታ፦ በወመዘክር (ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት) ኅሩይ አዳራሽ
🕒 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ክብር እንግዶች፦
ታላቁ ምሁር ዶክተር ኃይሉ አርአያ የክብር እንግዳ ሲሆኑ፤ እመቤት ሆይ ፍሬዓለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር በመድረኩ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።
በዕለቱ በመገኘት ለጥበብ ሰው የሚገባውን ክብር እንድንሰጥና የታሪክ ተካፋይ እንድንሆን ተጋብዘናል።
#aberalema #ethiopianliterature #biography #newbook #addisababa #journalism #getutemesgen #getu #ጡ #ጌጡተመስገን

📸 "አንድ ምስል ከሺህ ቃላት በላይ ይናገራል!"
— የጥበብና የቅጽበት ውጤት
#ethiopia | በመሪዎች ጉብኝት ወቅት የሚፈጠረውን ግርግር፣ ሩጫና ውክቢያ ውስጥ ሆኖ አንድን ድንቅ ታሪክ በካሜራ ሌንስ አነጣጥሮ መያዝ ቀላል ስራ አይደለም።
ጋዜጠኛ #አሸናፊ እንዳለ ይህንን እውነታ በምስል የታገዘ ትዝብቱን እንዲህ አጋርቶናል፦
📌 የታሪኩ ፍሬ ነገር፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ለመመልከትና ያለውን ፍቅር ለመግለጽ አንድ ወጣት ከጸጉር ቤት በድንገት ይወጣል። በፊቱ ላይ የተቀባው "ስክራፕ" ሳይታጠብ፣ ሽርጡን እንደለበሰ በዚያ ውክቢያ ውስጥ ሲሮጥ የካሜራ ባለሙያው ይህንን አጋጣሚ አላመለጠውም።
💡 ለምን ይደንቃል?
🎯 ትኩረት (Precision):
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ባሉበት ግርግር ውስጥ፣ ይህን ለየት ያለ ትዕይንት ለይቶ መቅረጽ ከፍተኛ ንቃት ይጠይቃል።
🎭 ስሜት፦
ምስሉ የወጣቱን ንጹህ ፍቅርና ጉጉት ያለምንም ማጋነን ይናገራል።
🎨 ሙያዊ ብቃት፦
ካሜራው ከቴክኒክ ባለፈ የሰውን ልጅ ስሜትና ታሪክ የመተረክ አቅም እንዳለው ያሳየበት አጋጣሚ ነው።
ጋዜጠኛ #አሸናፊ እንዳለው፤ እንዲህ አይነት ጥበብን "አለማድነቅ ንፉግነት ነው።" ለካሜራ ባለሙያው ክብር ይግባው! 👏
እናንተስ በምስሉ ላይ ስላለው ወጣት ስሜትና ስለ ባለሙያው ብቃት ምን ትላላችሁ? አስተያየትዎን በኮሜንት ያጋሩን።
👇
#photography #journalism #ethiopia #abiyahmed #artoftiming #storytelling #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

📖 "እንዲህም ተኑሯል" — የአንጋፋው ደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሕይወት ታሪክ ሊመረቅ ነው! 🖋️✨
#ethiopia | ከ21 በላይ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃውና ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበብ ሐያሲነት ለበርካታ ዓመታት በጽናት ያገለገለው አንጋፋው ባለሙያ አበራ ለማ፣ የሕይወት ታሪኩን በ550 ገጾች ከሽኖ አቅርቧል።
ስለ መጽሐፉና ስለ ደራሲው፦
📚 ርዕስ፦ "...እንዲህም ተኑሯል"
📜 ይዘት፦
የደራሲውን የሕይወት ውጣ ውረድ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች የነበረውን ቆይታ እንዲሁም የሥነ-ጽሑፍ ጉዞውን በሰፊው ይዳስሳል።
🌟 የታወቁ ሥራዎቹ፦
"ኩል ወይስ ጥላሸት"፣ "ሽበት"፣ "ሕይወትና ሞት" እና "ሞገደኛው ነውጤ" የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በሥራዎቹም የአንባቢያንን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
የምረቃ መርሐ-ግብር፦
📅 ቀን፦ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 ቦታ፦ በወመዘክር (ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት) ኅሩይ አዳራሽ
🕒 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ክብር እንግዶች፦
ታላቁ ምሁር ዶክተር ኃይሉ አርአያ የክብር እንግዳ ሲሆኑ፤ እመቤት ሆይ ፍሬዓለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር በመድረኩ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።
በዕለቱ በመገኘት ለጥበብ ሰው የሚገባውን ክብር እንድንሰጥና የታሪክ ተካፋይ እንድንሆን ተጋብዘናል።
#aberalema #ethiopianliterature #biography #newbook #addisababa #journalism #getutemesgen #getu #ጡ #ጌጡተመስገን
#ethiopia | ከ21 በላይ መጻሕፍትን ለንባብ ያበቃውና ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበብ ሐያሲነት ለበርካታ ዓመታት በጽናት ያገለገለው አንጋፋው ባለሙያ አበራ ለማ፣ የሕይወት ታሪኩን በ550 ገጾች ከሽኖ አቅርቧል።
ስለ መጽሐፉና ስለ ደራሲው፦
📚 ርዕስ፦ "...እንዲህም ተኑሯል"
📜 ይዘት፦
የደራሲውን የሕይወት ውጣ ውረድ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች የነበረውን ቆይታ እንዲሁም የሥነ-ጽሑፍ ጉዞውን በሰፊው ይዳስሳል።
🌟 የታወቁ ሥራዎቹ፦
"ኩል ወይስ ጥላሸት"፣ "ሽበት"፣ "ሕይወትና ሞት" እና "ሞገደኛው ነውጤ" የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በሥራዎቹም የአንባቢያንን ልብ ማሸነፍ ችሏል።
የምረቃ መርሐ-ግብር፦
📅 ቀን፦ ቅዳሜ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም.
📍 ቦታ፦ በወመዘክር (ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት) ኅሩይ አዳራሽ
🕒 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ክብር እንግዶች፦
ታላቁ ምሁር ዶክተር ኃይሉ አርአያ የክብር እንግዳ ሲሆኑ፤ እመቤት ሆይ ፍሬዓለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር በመድረኩ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።
በዕለቱ በመገኘት ለጥበብ ሰው የሚገባውን ክብር እንድንሰጥና የታሪክ ተካፋይ እንድንሆን ተጋብዘናል።
#aberalema #ethiopianliterature #biography #newbook #addisababa #journalism #getutemesgen #getu #ጡ #ጌጡተመስገን
8 months ago
🎙️ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አዲስ አበባን ሊዘግቡ ገብተዋል
ለ1000 ጋዜጠኞች የ24 ሰዓት አገልግሎት ተዘጋጅቷል
🌍
#ethiopia | ኢትዮጵያ ለጉባኤው ለሚመጡ 500 የውጭ ጋዜጠኞች በሮችዋን ክፍት አድርጋለች።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን፤ 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤን ለመዘገብ ወደ አዲስ አበባ ለሚገቡ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች የ24 ሰዓት የተሳለጠ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።
የዝግጅቱ ስፋት:
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናታን ተስፋዬ እንዳሉት፤ ጉባኤውን ለመዘገብ እስከ 500 የሚጠጉ የውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች እና ሌሎች 500 የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች (በድምሩ 1000 የሚጠጉ) ተመዝግበዋል።
የሚሰጠው አገልግሎት:
እንግዶቹን ያለ እንግልት ለማስተናገድ፦
✅ ቦሌ አየር መንገድ፣
✅ በአፍሪካ ህብረት የባጅ ማዕከል እና
✅ በባለስልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት ለ24 ሰዓት የሚሰራ ቡድን ተደራጅቷል።
ፋይዳው:
ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሚዲያ ባለሙያ መግባት፤ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ እና የቱሪዝም መስህቦችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ነው።
እንኳን ደህና መጣችሁ!
#ausummit #ethiopia #mediaauthority #journalism #addisababa #africa #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

"ውሳኔው ይነሳ! የዋዜማ ሬዲዮ ፈቃድ ይመለስ!"
- የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#ethiopia | "ባለስልጣኑ የወሰደው እርምጃ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፤ የሚዲያ ምህዳሩን በፍርሃት ይሞላል!"
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በዋዜማ ሬዲዮ ላይ ያሳለፈውን የሥራ ፈቃድ እግድ በተመለከተ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል።
የማኅበሩ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች:
🛑 እግዱን መቃወም:
ማኅበሩ ባለስልጣኑ በዋዜማ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በጽኑ የተቃወመ ሲሆን፤ የሚዲያ ተቋሙ ላይ የቀረበው "ሚዛናዊነት ይጎድለዋል" የሚለው ውንጀላ ከእውነታው የራቀ ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።
🛑 የመፍትሔ አግባብ:
ስህተቶች ቢኖሩ እንኳን በ "ሚዲያ ካውንስል" ደንብ መሰረት መታረም ሲገባቸው፤ ፈቃድ መንጠቅ ግን ለዲሞክራሲ ግንባታው ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሚፈጥር ጠቁሟል።
🛑 የሚዲያ አፈና:
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚዲያዎች ላይ የሚደረገው ጫና መጨመሩን ያወሳው መግለጫው፤ አሻም ቲቪ ከስራ ውጪ መደረጉን እንዲሁም ጋዜጠኞች (ዮናስ አማረ፣ አብዱልሰመድ መሐመድ እና ተስፋለም ወልደየስ) ለእስር መዳረጋቸውን በማሳያነት ጠቅሷል።
ጥሪ:
ባለስልጣኑ ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤን እና የዋዜማ ሬዲዮ የስራ ፈቃድ ተመልሶ ወደ ስራ እንዲገባ ማኅበሩ ጠይቋል።
ምንጭ፡
የኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ማኅበር በካናዳ
#wazemaradio #pressfreedom #ethiopia #aejc #mediarights #journalism

9 months ago
🎙️ "ይህ ፖሊስ ፕሮግራም ነው..."
የምትለዋ ድምፁ ዛሬም በጆሮአችን አለች!
#ethiopia | በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) የፖሊስ ፕሮግራም ላይ በልዩ የድምፅ ቀለም እና በብቃት አቀራረቡ የብዙዎቻችንን ልብ የገዛው አንጋፋው ጋዜጠኛ ሰለሞን አንባቸው፤ በ Alive Podcast ድንቅ እንግዳችን ሆኖ ቀርቧል።
በዚህ ልዩ ቆይታ ከተወዳጁ ጋዜጠኛ ሰለሞን ጋር፡-
👮 ስለ ፌደራል ፖሊስ ጋዜጠኝነት የካበተ ልምዱ፣
🎤 ስለ ሙያዊ ፈተናዎች እና ድሎች፣
📜 እንዲሁም ስለ ህይወት እና ጥልቅ የሆኑ ትዝታዎቹ በሰፊው አውግተናል።
ይህንን ትምህርት እና ትዝታ ያዘለ ድንቅ ቆይታ እንዳያመልጥዎ!
ሙሉውን ቪዲዮ ለመከታተል ሊንኩን ይጫኑ: 👇
🎥 https://youtu.be/0-yown_Gy...
#alivepodcast #solomonambachew #journalism #ethiopia #etv #interview #lifeexperience

የፖለቲካው ገሞራ
በለውጡ መባቻ - ቅጽ - ፩
በቀለ አመነ
በቅርብ ቀን
***
የጋዜጠኛ በቀለ አመነ የሙያ እና የትምህርት ጉዞ
በኢትዮጵያ የብሮድካስት ሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ በአመራርነት፣ በአዘጋጅነት እና በፕሮግራም አቅራቢነት ረጅም ዓመታትን ያገለገለው ጋዜጠኛ በቀለ አመነ፤ በሙያዊ ብቃቱ እና በትምህርት ዝግጅቱ የሚጠቀስ ባለሙያ ነው።
የትምህርት ዝግጅት
ጋዜጠኛ በቀለ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት እና ሥነ-ተግባቦት (Journalism and Communication) የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ግሪንዊች (University of Greenwich) በዓለም አቀፍ ቢዝነስ አስተዳደር (MBA-IB) የማስተርስ ዲግሪውን በመቀበል የትምህርት አድማሱን አሰፍቷል።
የሥራ ልምድ
በተለያዩ የሚዲያ እና የልማት ተቋማት በከፍተኛ ኃላፊነት ያገለገለው ጋዜጠኛ በቀለ፦
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV)፦ በዜና እና ወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል በአዘጋጅነት (Editor) እና በዜና አንባቢነት፤
በናሁ ቴሌቪዥን፦ የዜና እና ወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል ዳይሬክተር፣ እንዲሁም "ምን ይላሉ?" የተሰኘው ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ በመሆን፤
በአዋሽ 90.7 ኤፍ ኤም ሬዲዮ፦ በዋና ዳይሬክተርነት ጣቢያውን የመራ ሲሆን፤ "የሀገር ልጅ ወግ" እና "የወንዝ ዳር ጨዋታ" የተሰኙ ተወዳጅ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት እና በማቅረብ፤
በኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት፦ የማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በመሆን አገልግሏል።
በአሁኑ ወቅትም ተወዳጅ የሆነውን "ምን ይላሉ?" የተሰኘ የቴሌቪዥን ፕሮግራም በማዘጋጀት እና በማቅረብ በሙያው ላይ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።

12 months ago
ጋዜጠኛ ዓለምሰገድ አበበ በኢትዮጵያ
የግብርና ባዮቴክኖሎጂ የቴሌቭዥን ዘገባ የማስፋፋት ስራ ላይ አምባሳደር ሆኖ ተመረጠ
ጋዜጠኛ ዓለምሰገድ አበበ ላለፉት 11 አመታት በቴሌቭዥን ዘርፍ ለሰራው የሳይንስ ጋዜጠኝነት ስራ "Ambassador in Science Journalism and Communication on Agricultural Biotechnology Research & Development in Ethiopia" በሚል የግብርና ባዮቴክኖሎጂ በቴሌቭዥን ዘርፍ አምባሳደር ሆኖ እንዲሰራ ተመርጧል ።

Comments