5 months ago
ጋዜጠኛ ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | በቀድሞ ፋና ሬዲዮ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጠኛ የነበረው ታሪኩ ኦላና ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በ1957 በቀድሞ አጠራሩ ወለጋ ክፍለ ሀገር ጊንቢ አውራጃ ላሎ አሳቢ ወረዳ የተወለደው ጋዜጠኛ ታሪኩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ትምህርቱን እንደጨረሰ ወደ ቀድሞ ፋና የአሁኑ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን በመቀላቀል በአፋን ኦሮሞ ክፍል በሚዲያው ዘርፍ የኦሮሞን ሕዝብ ባሕልና ቋንቋ በማሳደግ ረገድ የበኩሉን ሚና ተጫውቷል።
ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት የነበረው ጋዜጠኛ ታሪኩ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትናንት ሌሊት በተወለደ በ61 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
የጋዜጠኛ ታሪኩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ በሚገኘው ቀጨኔ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ጌጡ ተመስገን ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ ለጋዜጠኛ
ታሪኩ ኦላና ቤተሰቦቹና ዘመድ ወዳጆቹ መጽናናትን ይመኛል።
#fbc
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#tarikuolana #journalism #ethiopia #afaanoromo #fanabroadcasting #mediaicon #restinpeace #journalistlife #ethiopianmedia

Comments