Logo
Getu Temesgen
⚫ የተሰማን ሀዘን ከባድ ነው! ነፍስ ይማር!
#ethiopia | ​የአልቲማ ሪል እስቴት (Altima Real Estate) የብራንድ አምባሳደር፣ ተወዳጁ የጥበብ ሰው እና የኢቢኤስ "የቤተሰብ ጨዋታ" ፕሮግራም አዘጋጅ አርቲስት ነጻነት ወርቅነህ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

​ነጻነት በስራው ትጋቱ፣ በሰው አክባሪነቱ እና በቅንነቱ የምናውቀው፤ ለኩባንያችንም እንደ ቤተሰብ የነበረ ውድ ወንድማችን ነበር።

​አልቲማ ሪል እስቴት በብራንድ አምባሳደሩ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ፤ ለባለቤቱ፣ ለሦስት ልጆቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

​ፈጣሪ ነፍስህን በአጻድ ጻድቅ ያኑርልን! 🕯️💔

​#restinpeace #netsanetworkneh #altimarealestate #condolence

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.