💔 ቴሪዬ - ደህና ሁኚ!
የኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ "ተፈጥሮአዊ ኃይል"
(Force of Nature) ወ/ሮ ትርሃስ (ቴሪ) ገብረኪዳን
በወፍ በረር
አጭር የሕይወት ታሪክ
#ethiopia | ወ/ሮ ትርሃስ ገብረኪዳን ~ ወዳጆቿ በሚጠሯት የፍቅር ስም ቴሪ፣ በ1965 ዓ.ም ከአቶ ገ/ኪዳን በርሄ እና ከወ/ሮ ክንደ ሃፍቲ በአሥመራ ከተማ ተወለደች። እድሜዋ ለትምህርት ሲደርስም እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ መደበኛ የትምህርት ስርዓት ውስጥ ያለፈች ሲሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በልዑል በዕደማርያም ት/ቤት አጠናቃለች።
"ጥራትን ከለጋስነት ያጣመረች፣ የ30 ዓመታት የውበት ንግሥት!" በኢትዮጵያ የውበት እና የቆዳ እንክብካቤ ዘርፍ ላለፉት 3 አሥርት ዓመታት ስሟ በጉልህ የሚነሳው፤ የTerry Style H₂O መስራች ትርሐስ (ቴሪ) ነበረች።
🌟 ቴሪ፤ በኢትዮጵያ የውበት ኢንዱስትሪ ውስጥ ዘመናዊ አሰራርን በማስተዋወቅ "የውበት እመቤት" ለመባል የበቃች ፈር-ቀዳጅ፤ ሥመ ጥር ባለሙያ ነበረች።
ቴሪ - በአውሮፓ፣ እስያ እና አሜሪካ በመዘዋወር የወሰደችውን ስልጠና ተጠቅማ፤ እንደ ሎሪያል - Loreal ያሉ ዓለም አቀፍ ብራንዶችን ወኪል በመሆን የሜካፕ ዘርፉን ወደ ከፍታ አሸጋግራለች።
ባለ ራዕይ (The Visionary) ቴሪ
ቴሪ ተራ የውበት ሳሎን ሳይሆን የከፈተችው፤ የክብር እና የእንክብካቤ ስፍራን (Sanctuary) ነበር። ስራዋን እንደ ህይወት ዓላማዋ (Purpose) በመቁጠር ያልነበረውን ነገር በምናቧ አይታ ወደ እውነት፤ ወደ ምድር ያመጣች - በተግባር የቀየረች ብርቱ ሰው ነበረች።
✅ ወ/ሮ ትርሐስ (ቴሪ) ገብረኪዳን - አስተማሪ እና አቅም ፈጣሪ (The Mentor) ነበረች
"እውቀት ሲካፈሉት ይበዛል" የምትለው ቴሪ፤ በርካታ ወጣቶች የራሳቸውን የውበት ሳሎን እንዲከፍቱ በሙያ እና በቁሳቁስ በዝምታ ደግፋለች። ስኬቷን ለራሷ ብቻ ሳታደርግ ለሌሎችም የምታካፍል ለጋስ እናት ነበረች።
ግልጽነት ለዘላለም ይኑር!
ቴሪ - ደግነት እና ሰብአዊነቷ አልተነገረላትም። በዚህም ያልተዘመረላት ጀግና፤ ዝምተኛዋ ጀግና የሚል ምወድስ በክብር የሚነገርላት የቸርነት እናት ነበረች።
ችግር ለገጠማቸው ወገኖች ያለምንም ማስታወቂያ እና ዝና ፍለጋ የምትደርስ፤ ፈገግታዋ የማይጠፋ "የሕይወት አፍቃሪ" የምታውቋት ቴሪ ሰውነት ነበር።
በመጨረሻም
👩👧👦 አፍቃሪዋ እናት (ቴሪ )
ከሰሊሆም እና ከኢዮአስ ጋር የነበራት ግንኙነት ልዩ ነበር። "ሰሊሆም ትሙት" እያለች የምትምልላቸው፣ ከህይወቷ በላይ የምትወዳቸው ልጆቿ የህይወቷ ማዕከል ነበሩ።
ቴሪ
ፍቅሯ፣ ራዕይዋ እና ለጋስነቷ ( ሌጋሲዋ ) ለዘላለም ከእኛ ጋር በክብር ይኖራል!
ትርሃስ፣ ባደረባት ህመም ምክንያት በአሜሪካ ህክምና ስትከታተል ቆይታ ጥር 9 ቀን፣ 2018 ዓ.ም በ53 ዓመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች።
ቴሪ - እህተ ማርያ ንስሀ ገብታ ማረፏ ተገልጿል።
ዛሬ ጥር 18 ቀን 2018ዓም በሳዕሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ከቀኑ 6:00 ሰዓት (በእኩለ ቀን) ሥርዓተ ቀብሯ ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጆቿ እና ለሙያ አጋሮቿ መጽናናትን እንመኛለን።
ቴርዬ - እንወድሻለን። እንናፍቅሻለን።
ቴሪዬ - ደህና ሁኚ!
💔🙏
#terrystyle #restinpeace #ethiopianbeautyindustry #legend #tirhasgebrekidan #terryh2o #ethiopia

8 months ago