3 months ago
በቦንጋ ከተማ ለወጣት ስፖርተኛ ንቃተ ህሊና የመሬትና የገንዘብ ስጦታ ተበረከተ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ድብልቅ ማርሻል አርት ወይም MMA ውድድር በማስተዋወቅ ስሙን ላስጠራው ወጣት ስፖርተኛ ንቃተ ህሊና ዮሐንስ ምስክር በቦንጋ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል::
ስፖርተኛው ወደ ከተማዋ ሲገባ የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል::
በእለቱ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ ስፖርተኛው ዞኑንና ሀገሩን በስፖርቱ ዘርፍ በማስጠራቱ ምስጋና አቅርበው የዞኑ አስተዳደር ለንቃተ ህሊና 300 ሺህ ብር እንዲሁም ለአዘጋጁና ለአሰልጣኙ እያንዳንዳቸው 100 ሺህ ብር በድምሩ የ500 ሺህ ብር ስጦታ ማበርከታቸውን ገልጸዋል::
በተመሳሳይ የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ተክለዓብ ቡሎ ስፖርተኛው በሀገራችን አዲስ የውድድር ምዕራፍ በመክፈቱ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ 500 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ለስፖርተኛው ንቃተ ህሊና በስጦታ መስጠቱን አብስረዋል::
ከንቲባው አክለውም የከተማው ህዝብ ሁልጊዜም ከስፖርተኛው ጎን እንደሚቆም አረጋግጠዋል::
አሰልጣኝ ማስተር ጌታቸው መለሰ በበኩላቸው ለስፖርተኛው ያላቸውን አድናቆት ገልጸው በቀጣይ ንቃተ ህሊናን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና ሌሎች የአካባቢውን ወጣቶች በዘርፉ ለማሰልጠን ቃል ገብተዋል::
ስፖርተኛ ንቃተ ህሊናም ለተደረገለት የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቦ ይህ ስኬት ገና ጅምር መሆኑንና በቀጣይ በበለጠ ስራ ሀገሩንና ህዝቡን እንደሚያኮራ ተናግሯል::
በመጨረሻም በወጣት ሰዓሊ አብርሃም ተስፋዬ የተዘጋጀ ውብ የስነ ጥበብ ስራ ለስፖርተኛውና ለአሰልጣኙ በስጦታ ተበርክቶላቸዋል::
ፎቶ÷ በሠለሞን ተስፋዬ
የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
#bonga #kaffa #mma #ethiopiansport #nikat_hilina #martialarts #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 months ago
የሆሊውድ የአክሽን ፊልሞች ፈርጥ ቻክ ኖሪስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | ታዋቂው አሜሪካዊ የሆሊውድ ተዋናይ እና የማርሻል አርት ጥበብ መምህር ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰምቷል።
በአክሽን ፊልሞቹና በማይበገረው ማንነቱ የሚታወቀው ኖሪስ፣ በሃዋይ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
የጥበብና የጥንካሬ ጉዞ፦
ጅማሮ፦ በ1940 በኦክላሃማ የተወለደው ኖሪስ፣ ወደ ጥበብ ዓለም ከመግባቱ በፊት በአሜሪካ አየር ኃይል ውስጥ አገልግሏል።
ዝነኛ ሥራዎቹ፦
በተለይም "Walker, Texas Ranger" በተሰኘው ተከታታይ ፊልሙ እንዲሁም ከብሩስ ሊ ጋር በሰራው "Way of the Dragon" እና በሌሎችም በርካታ የአክሽን ፊልሞች ዓለም አቀፍ ዝናን አትርፏል።
ቻክ ኖሪስ ከፊልም ሥራዎቹ ባሻገር፣ በልዩ የማርሻል አርት ችሎታውና በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የሚታወቅ የዘመናችን የጥበብ ምልክት ነበር።
የማይበገረው ቻክ ኖሪስ በ86 ዓመቱ ቢያርፍም፣ በጥበብ ሥራዎቹ ግን በብዙዎች ዘንድ ለዘላለም ሲታወስ ይኖራል።
#getu #chucknorris #hollywood #actionmovies #martialarts #legend #restinpeace #rip #ሆሊውድ #ቻክኖሪስ #አክሽንፊልም #ጌጡተመስገን #getutemesgen

6 months ago
🥋 ከ400 በላይ የቴኳንዶ አሰልጣኞች እና ዳኞች ተመረቁ! 🇪🇹
"ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ የሚወክሉ ባለሙያዎች የተፈጠሩበት ለ15 ቀናት የቆየ ልዩ ስልጠና"
በአዲስ አበባ ቻንግ ሆን ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን ላለፉት 15 ቀናት ሲሰጥ የቆየው 1ኛ ደረጃ የዳኝነት እና የአሰልጣኝነት ስልጠና በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።
የስልጠናው ድምቀቶች:
✅ ተመራቂዎች:
ከ400 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን በብቃት አጠናቀዋል፡፡
✅ አሰልጣኝ:
ስልጠናው በኢትዮጵያ ቻንግ ሆን ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ኤልያስ ኩመል ተመርቷል።
✅ ይዘት:
ሰልጣኞቹ ከአካል ብቃት እና ቴክኒክ በተጨማሪ የስነ-ልቦና ጥንካሬን ያዳበሩበት ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስልጠና ነበር።
በወወከማ አዳራሽ በተደረገው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ሰልጣኞቹ አስደናቂ የቴኳንዶ ትርኢቶችን አቅርበዋል።
ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ኤልያስ ኩመል እንዳሉት፤ "ይህ ስልጠና ሰልጣኞችን በሁሉም ረገድ ብቁ የሚያደርግ እና ሀገር የሚኮራባቸውን ስፖርተኞች ለማፍራት ያለመ ነው" ብለዋል።
እንኳን ደስ አላችሁ! 🥋💪
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#taekwondo #changhong #ethiopia #martialarts #sportstraining #addisababa #eliaskumel #graduation

Comments