Logo
Getu Temesgen
⚫ "በእኔ ቤት የገባ መከራ በቤታችሁ አይግባ!"
#ethiopia | ​የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ የሆነው ወንድማችን አቶ ንጋቱ ማሞ፤ የትዳር አጋሩን በሞት ተነጥቋል።

​ባለቤቱ ወ/ሮ መዓዛ አለማየሁ በጡት ካንሰር ህመም ምክንያት ህይወቷ አልፎ የቀብር ስነ-ስርአቷ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በቀጨኔ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

​አቶ ንጋቱ በከባድ ሀዘን ውስጥ ሆኖ "በእኔ ቤት የገባ መከራ በቤታችሁ አይግባ!" ሲል የሀዘኑን ጥልቀት ገልጿል።

​ለአቶ ንጋቱ፣ ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጅ ዘመዶቹ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናትን ይስጥልን።

የወ/ሮ መዓዛን ነፍስ ይማርልን!

​አይዞህ ወንድማችን! እግዚአብሔር ያጥናህ! 🙏🕯

​#condolence #nigatumamo #restinpeace #addisababa

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.