5 days ago
ከገጠር እርሻ ወደ ዓለም አቀፍ ዝና! ✨🇪🇹
የኤልሳቤጥ ደስታ ጉዞ የጽናት፣ የክብር፣ እና የማይደበዝዝ የኢትዮጵያ ውበት አስደናቂ ታሪክ ነው።
በተፈጥሯዊ ውብ ቆዳዋ፣ በልዩ ግርማዋ እና በራስ መተማመኗ፣ ኤልሳቤጥ የአዲሱን ትውልድ የኢትዮጵያ ሞዴሎች በኩራት ትወክላለች። በሁሉም የምትሳተፍባቸው የብራንድ ዘመቻዎች የኢትዮጵያን ባህል፣ ልዩነት እና ልቀት ለዓለም ታስተዋውቃለች፣ በስራዋም ብዙዎችን ታነሳሳለች።
ኤልሳቤጥ በBN Advertising & Talent Management Company ብቸኛ አስተዳደር ስር ያለች ተሰጥኦ ሲሆን፣ በታዋቂው በጎ አድራጊ ማስተር አብነት ከበደ ጋር በመተባበር ይህ ፕሮጀክት ተከናውኗል።
የግብይት አማካሪ: ናትናኤል ዘሪሁን | NZ Communications
ፎቶግራፍ: Miki Photo (Fitle Picture) 📸
ሜካፕ: Marzel 💄
ስታይሊስት እና አርት ዳይሬክተር: Hemen ✨
ውበትን ከዓላማ ጋር፣ ተሰጥኦን ከራዕይ ጋር፣ ኢትዮጵያንም በኩራት እናክብር። 🇪🇹❤️
#elsabet #ethiopianbeauty #brandmodel #madeinethiopia #africanbeauty #fashionphotography #bnadvertisingandevents #brooknews #masterabinetkebede #nzcommunications #mikiphoto #marzelmakeup #hemenstylist #portraitphotography #ethiopianmodels #beautywithpurpose #addisababa #proudlyethiopian

1 month ago
የኢትዮጵያ የማዕድን አብዮት - ከ0.2 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ ወደ ዋነኛ የኢኮኖሚ ሞተርነት
*************************
የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በፖሊሲ ክፍተት፣ በሕገ-ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድ እና በተደራጀ ብክነት ምክንያት እምቅ አቅሙ ሙሉ በሙሉ ተዘንግቶ ቆይቷል።
ዛሬ ላይ ግን በአዲሱ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ከሀገራችን 5 ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በመሆን ታሪካዊ ትንሣኤውን አብስሯል።
ሀገራችን ስትገነባው የቆየችው በመንግሥት ከፍተኛ ወጪ ላይ የተመሠረተ እና ለዕዳ ተጋላጭ ያደረጋት የኢኮኖሚ ሞዴል ፈታኝ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።
ይህን በማክሮ ኢኮኖሚ አለመረጋጋት፣ በዋጋ ግሽበት እና በውጭ ምንዛሬ እጥረት የተተበተበ ማነቆ በዘላቂነት ለመቅረፍ የተተገበረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ማዕድንን ከመረሳት ወደ ብሔራዊ ኢኮኖሚ አንቀሳቃሽነት በውጤታማነት አሸጋግሮታል።
ይህ መዋቅራዊ ለውጥ በመረጃ እና በቁጥር ሲመዘን እጅግ አስደናቂ ሆኖ እናገኘዋለን። በ2010 ዓ.ም የማዕድን ዘርፍ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) የነበረው ድርሻ 0.2 በመቶ ብቻ ነበረ። በ2017 ዓ.ም ይህ ቁጥር የ7 እጥፍ ብልጫ በማሳየት ወደ 1.4 በመቶ ማደግ ችሏል።
በተለይም በወርቅ ምርት እና ኤክስፖርት ላይ የታየው ለውጥ በታሪካችን ወደር የማይገኝለት እመርታ ነው።
ባህላዊ የማዕድን ቁፋሮን ወደ መደበኛ የንግድ ሥርዓት በማስገባት በተደረገው ስኬታማ የፖሊሲ ማሻሻያ፣ የሀገራችን የወርቅ ኤክስፖርት ገቢ ከ100 ሚሊዮን ዶላር ወደ 3.48 ቢሊዮን ዶላር በማደግ የ35 እጥፍ ጭማሪ አስመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡ የተገበረው በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ሥርዓት ደግሞ አምራቾች ምርታቸውን በመደበኛው የፋይናንስ ሥርዓት እንዲያቀርቡ በማድረግ ለዚህ ስኬት ትልቅ ሞተር ሆኗል።
በሌላ በኩል "ኢትዮጵያ ታምርት" በተሰኘው ሀገራዊ ንቅናቄ የማዕድን ዘርፉ ከማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ጋር በጥብቅ በመተሳሰሩ፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት ከፍተኛ ድል ተመዝግቧል።
ለአብነት ያህል የአርጆ የድንጋይ ከሰል ማበልጸጊያ ፋብሪካን መመልከት በቂ ነው። ይህ ዘመናዊ ፋብሪካ በየዓመቱ የከሰል ድንጋይ ለማስገባት ይወጣ የነበረውን ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት እንዲተካ አስችሏል።
በተመሳሳይ የኖራ ድንጋይ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ከ17 በመቶ ወደ 75 በመቶ ከፍ ማለቱ፣ እንደ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ እና ሙገር የመሳሰሉ ግዙፍ ፋብሪካዎች የማምረቻ ወጪያቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ አድርጓል።
ይህ በማዕድን ዘርፉ የታየው ዕድገት በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ሰፊ ማኅበራዊ ፋይዳንም አምጥቷል።
በአሁኑ ወቅት ኢንዱስትሪው ከ1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎቻችን ቀጥተኛ የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ከ4 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ኑሯቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በዚህ ዘርፍ ላይ መስርተዋል።
በአጠቃላይ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው የማዕድን ዘርፉን ከድቅድቅ ጨለማ አውጥቶ የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያፋጥን ሞተር አድርጎታል።
ይህ የማዕድን ዘርፍ ስኬት ዘርፉ የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ዕውን የሚያደርግ አስተማማኝ ምሰሶ መሆኑን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #mining #madeinethiopia #economicreform #goldexport #ebc

2 months ago
"ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እና ነፃነት የሚኖራት በሁሉም መስክ ራስን መቻል ሲቻል ነው" - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ
*******************
የአማራ ክልል "ኢትዮጵያ ታምርት" የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብር "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ ክልሉን ተወዳዳሪ እና ቀዳሚ ለማድረግ ሁሉም አካል በቅንጅት እና በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ በራስ አቅም የማደግ፣ የራስን ምርት የማሳደግ እና የመጠቀም እንዲሁም ሀገርን በአንድነት የማበልጸግ እሳቤ የወለደው መሆኑን አቶ አረጋ ገልጸዋል።
"ሀገር የተሟላ ሉዓላዊነት እና ነፃነት የሚኖራት በሁሉም መስክ ራስን መቻል ሲቻል ነው" ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በምርት ራሱን ያልቻለ ሀገር የሌሎች ሀገራት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ጥገኛ መሆኑ እንደማይቀር አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር ብትሆንም፣ የተሟላ ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ሕዝቡን ከድህነት እና ኋላቀርነት ማላቀቅ እንዲሁም በምርት ራስን መቻል የውዴታ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አብራርተዋል።
የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው መምጣቱን ገልጸው፣ ከዚህ ቀደም የነበሩ የኃይል፣ የፋይናንስ አቅርቦት እና ሌሎች ማነቆዎች በሂደት እየተፈቱ መምጣታቸውን ተናግረዋል።
በሀገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የማምረት አቅም ከበፊቱ በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ጠቁመው፣ አሁንም ግን ለአነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ዕድገት ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ በፀጥታ ችግር ውስጥ ማለፉን በማስታወስም፣ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ራሱ የፀጥታ ችግሩን እንደሚፈታው ተናግረዋል።
"ኢኮኖሚው ያደገ ሀገር እና ሕዝብ ወደ ግጭት አይገባም" በማለትም የኢንዱስትሪው ዕድገት ለሰላም ያለውን አስተዋፅኦ አጉልተዋል።
ይህንንም መሠረት በማድረግ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የክልሉ የ25 ዓመታት የአሻጋሪ ዕድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫ መደረጉን ገልጸዋል።
የፀጥታ ችግር ሳይበግራቸው በክልሉ በመሥራት ለውጤት የበቁ ባለሀብቶችን አመስግነዋል።
"የኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የክልሉን ጸጋ ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሀብቶች ለማስተዋወቅ፣ የገበያ ትሥሥር ለመፍጠር እና የመንግሥት እና የባለሀብቱን ቅርርብ ለማሻሻል ዓይነተኛ ሚና መጫወቱን አብራርተዋል።
የክልሉ መንግሥት አዳዲስም ሆነ ነባር ባለሀብቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን በማረጋገጥ፣ ሌሎች ባለሀብቶችም ወደ ሥራ እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።
#ethiopia #ebc #madeinethiopia #industry

በኢንዱስትሪ ሽግግር ጉዟችን ተጨባጭ ለውጥ እያመጣንባቸው ያሉት ተኪ ምርቶቻችን
***********************
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ባለፉት ዓመታት የሀገራችንን የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማነቃቃት፣ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ከውጭ ጥገኝነት ለማላቀቅ እና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ የተጀመረ ግዙፍ ሀገራዊ ንቅናቄ ነው።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ቀጥተኛ አነሳሽነት እና መሪነት ወደ ተግባር የገባ ሲሆን፣ ዋነኛ ስትራቴጂያዊ ምሰሶውም የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ነው።
ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ራስን ለመቻል እየተደረገ ያለው ይህ ጥረት፣ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ መዋቅር ላይ ጉልህ እና ተስፋ ሰጪ ለውጦችን እያሳየ ይገኛል።
ንቅናቄው ወደ ሥራ ሲገባ በዋናነት ትኩረት ያደረገው እና ያበረታታው የሀገር ውስጥ አምራቾችን፣ ወጣት የፈጠራ ባለቤቶችን፣ የሥራ ፈጣሪዎችን እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የተመረቁ ባለሙያዎችን ነው።
ከዚህም ባሻገር ቀደም ሲል በማሽነሪ፣ በኤሌክትሪክ ኃይል ወይም በግብዓት እጥረት ምክንያት ከአቅማቸው በታች ያመርቱ የነበሩ በርካታ ነባር ፋብሪካዎች፣ ችግሮቻቸው ተለይተው እና ተገቢው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲሸጋገሩ አስችሏል።
አምራቾች የፋይናንስ ብድር አቅርቦት ቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉ፣ የታክስና የጉምሩክ ማበረታቻዎች መሰጠታቸው እንዲሁም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ምቹ የመሥሪያ ቦታዎች መመቻቸታቸው ዘርፉን በማሳደግና አዳዲስ ባለሀብቶችን በመሳብ ትልቅ አቅም ፈጥሯል።
በንቅናቄው ማዕቀፍ በተለይ በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በኬሚካል፣ በኮንስትራክሽን ግብዓቶች እና በሌሎችም ቁልፍ ዘርፎች በርካታ ስኬታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።
ከዚህ በተጨማሪም አምራች ኢንዱስትሪዎች ለምርታቸው የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎችን ከሀገር ውስጥ የግብርና እና የማዕድን ዘርፎች ማግኘት እንዲችሉ በማድረግ፣ የኢኮኖሚ ትስስር ሰንሰለትን ማጠናከር ተችሏል።
ይህም የሀገር ውስጥ አርሶ አደሮችና ማዕድን አውጪዎች ምርታቸውን በቀጥታ ለፋብሪካዎች የሚያቀርቡበትን ሰፊ ዕድል በመፍጠር የገበያ ትስስሩን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
በተኪ ምርቶች ላይ የተመዘገበው ይህ ስኬት ለኢትዮጵያ ማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት እጅግ የላቀ መዋቅራዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ዋነኛው ጥቅሙም የሀገራችን ትልቅ ፈተና የሆነውን የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ማቃለል መቻሉ ነው።
ቀደም ሲል ለምግብ ዘይት፣ ለዕለታዊ የፍጆታ ዕቃዎች፣ ለብረት እና ለሲሚንቶ ግዥ ወደ ውጭ ይወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር በሀገር ውስጥ በማስቀረት የንግድ ሚዛን ጉድለቱን ማጥበብ ተችሏል።
በተያያዘም አዳዲስ የተኪ ምርት ኢንዱስትሪዎች ሲስፋፉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች እና ለቴክኒክና ሙያ ምሩቃን ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል።
በሌላ በኩል ተኪ ምርቶችን ከማስፋፋት አኳያ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ያበረከተው የጎላ አስተዋጽኦ፣ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎችን በጅምላ ወደ ውጭ ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ ለገበያ ማቅረብ ማስቻሉ ነው። ይህ ሒደት የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የዕውቀት ክምችትን እያፋጠነ ይገኛል።
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚነሱ የጂኦፖለቲካ ቀውሶችን፣ የዓለም አቀፍ ገበያ መዋዠቅንና የዋጋ ንረትን ተቋቁማ በራሷ እግር እንድትቆም በማድረግ የኢኮኖሚ አቅሟን በእጅጉ ያሳድገዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተጀመሩ የተኪ ምርት ሥራዎች የሀገራችንን የኢንዱስትሪ መሠረት በማጠናከር ረገድ የተለየ እና የላቀ ምዕራፍ የከፈቱ በመሆናቸው፣ የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ዕድል እጅግ ብሩህ ያደርጉታል።
ይህን ስኬት ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠልም፣ ከተኪ ምርት ባለፈ የሀገር ውስጥ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በማድረግ ወደ ውጭ ገበያ በሰፊው ለመላክ የሚያስችል የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊጠናከር ይገባል።
በሄዋን ጌታቸው
#ethiopia #manufacturing #madeinethiopia #importsubstitution #valueaddition #ethiopiatamrit #ebc

ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም
#የኢንዱስትሪ_ሽግግር #ኢትዮጵያ_ታምርት #ceramicindustry #madeinethiopia #importsubstitution
Sponsored by
Surafel
2 months ago
ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም እየተቀየረ ነው። እንዴት ካሉ መልሱን በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል ➡️ https://youtu.be/K_Lb1Mknq...
#ceramicindustry #madeinethiopia #importsubstitution #economicsovereignty #taborceramics #ebcworld
3 months ago
ከዘመናት ቁጭት ወደ ዝላይ ጉዞ
*****************
ዓለም በእንፋሎት ኃይል፣ በኤሌክትሪክ እና በኮምፒውተር አውቶሜሽን ሦስት ግዙፍ የኢንዱስትሪ አብዮቶችን ስታስተናግድ፣ እኛ ኢትዮጵያውያን በውስጥ ሽኩቻ፣ በተዘበራረቁ ፖሊሲዎችና በድህነት አረንቋ ውስጥ ታጥረን የሥልጣኔውን ባቡር በሩቁ ስንሸኝ ኖረናል።
የዓለም ሀገራት በፋብሪካ ጭስ እና በቴክኖሎጂ ግኝት ሰማይ ሲቧጥጡ፣ እኛ ያለንን የተፈጥሮ ጸጋ በባዕዳን እጅ እያስበላን፣ ላባችንን ገብረን ያመረትነውን ጥሬ ዕቃ በሳንቲም እየሸጥን መልሰን በውድ ዋጋ ስንገዛ የኖርንበት የታሪክ ስብራታችን መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም።
ይህ የዘመናት የታሪክ እንቅልፍ፣ ዛሬ ላለነው ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ቁጭትና አንገብጋቢ የለውጥ ጥማት የፈጠረ መሪር እውነት ነው።
ወደ ኋላ መለስ ብለን የኢንዱስትሪ ታሪካችንን ስንፈትሽ የባከኑ ዕድሎችን እናያለን።
በቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በውጭ ባለሀብቶች የተጠነሰሰው የኢንዱስትሪ ጅምር፣ እርሾ ሆኖ ዛሬ ላይ ከፍተኛ ደረጃ የሚያደርሰን የነበረ ቢሆንም፣ በሥርዓቱ ባህርያዊ ችግር ምክንያት ከጅምር ማሳያዎች የዘለለ ዕድገት ሳያሳይ ቀርቷል።
በደርግ ሥርዓት "ካፒታል ከ500 ሺህ ብር ማለፍ የለበትም" በሚል አፋኝ ፖሊሲ የነበረውም ጅምር የግል ዘርፍ የሞት ጽዋ እንዲጠጣ ተደረገ።
በኢሕአዴግ ዘመን ደግሞ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተው የነበረ ቢሆንም፣ ዘርፉ በግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫ እና በስትራቴጂ ባለመመራቱ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሲታነቅ እና በውጪ አቅራቢዎች ጥገኝነት ሥር ሲማቅቅ ቆይቷል።
ይህ የተቆራረጠ ጉዞ የኢንዱስትሪ ባለቤት ሳይሆን የባዕዳን ሸማች አድርጎን ኖሯል።
ዛሬ ግን ያ የቁጭት ዘመን እያበቃ ይገኛል፤ የዕድገቱን ባቡር ደረጃ በደረጃ ለመከተል ጊዜ የለንም።
የአሁኑ ትውልድ እና አመራር ካለፈው የታሪክ ስብራት በመውጣት "የዝላይ ስልትን" በመከተል ዕጣ ፈንታውን በእጁ ቀርጿል።
ሙሉ ትንታኔውን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል።
#ebc #ethiopia #madeinethiopia #industry #leapfrogging

ኢትዮጵያ በ2045 የዓለማችን ግዙፍ 10 ኢኮኖሚዎች ተርታ ትሰለፋለች ፤ አለምን ያስደመመው ስር ነቀል ለውጥ
#ethiopia #ethiocoders #madeinethiopia #ethiopianeconomy2045 #artificialintelligence #ethiopiandevelopment #addisababa #ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያታምርት #ኢትዮኮደርስ #አርቴፊሻልኢንተለጀንስ
3 months ago
ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ ኢንዱስትሪ አንቀሳቃሽነት - የኢትዮጵያ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ!
******************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ ለዘመናት የዓለም ገበያ የጥሬ ዕቃ ማከማቻ ሆና መቆየቷ ያበቃለት ታሪክ እየሆነ ነው።
ዛሬ የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ከቀላል የሼድ ግንባታ ባለፈ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣናነት መለወጣቸው፣ ሀገራችን በዘርፉ የደረሰችበትን የብስለት ከፍታ እና መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
እነዚህ ቀጣናዎች የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከማፋጠን ባለፈ፣ እንደ ማግኔት የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ የሀገራችንን የኢኮኖሚ ደም ሥር እያደሱ ይገኛሉ።
“ሳይደግስ አይጣላም” እንዲሉ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በማምረቻ ዘርፉ ላይ ያጋጠሙንን ስብራቶች ለመጠገን የተወሰዱት የማክሮ ኢኮኖሚ እርምጃዎች ዛሬ ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። ለዚህም እንደ ማሳያ የሚሆነው፣ ሥራ አቁመው የነበሩ ከ830 በላይ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ዳግም የሕይወት እስትንፋስ ዘርተው ወደ ሥራ መመለሳቸው ነው።
ከእነዚህም ጎን ለጎን በመቶዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ግዙፍ ፋብሪካዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ተደምረው የሀገራችንን ምርታማነት ወደ አዲስ የዕድገት ከፍታ አውጥተውታል።
ይህ መዋቅራዊ ሽግግር ግብርና ቀስ በቀስ ስፍራውን ለኢንዱስትሪ መሪነት እየለቀቀ መሆኑን የሚያበስር ሲሆን፣ የዘርፉ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ከ30 በመቶ በላይ መሻገሩም የፖሊሲያችንን ስኬታማነት በዓለም አደባባይ ምስክር ያደርገዋል።
በተለይ ደግሞ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች መካከል 60 በመቶ ያህሉ የሀገር ውስጥ መሆናቸው፣ “የራስ ካልሆነ አይሞቅም፣ ቢሞቅም አይዘልቅም” እንደሚባለው፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን በገዛ ልጆቻችን ክንድ እያረጋገጥን መሆናችንን የሚያሳይ የኩራት ምንጭ ነው።
በተጨባጭም ኢትዮጵያ ራሷን ለመቻል የሰነቀችው ሕልም ወደ መሬት እየወረደ ይገኛል። በማዕድን ዘርፉ የወርቅ እና የድንጋይ ከሰል ምርትን በማሳደግ፣ ለዘመናት የቆየንበትን የጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ታሪክ በመቀየር እሴት ወደሚጨምር ምርታማነት ተሸጋግረናል።
ለተኪ ምርቶች የሚሰጠው ልዩ ትኩረትም የውጭ ምንዛሬን ከማዳን ባለፈ፣ ለሚሊዮን ወጣቶች ዘላቂ የሥራ ዕድል በመፍጠር ማኅበራዊ መረጋጋትን እያረጋገጠ ነው።
ዛሬ ሀገራችን ከትራንስፎርመር እስከ አውቶሞቲቭ ፋብሪኬሽን ያሉ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን በገዛ ልጆቿ እጅ ማምረት መጀመሯ፣ የጀመርነው ጉዞ ወደማይቀለበስበት የከፍታ ምዕራፍ መሸጋገሩን ያሳያል።
እያንዳንዱ የምናመርተው ጫማ፣ አልባሳት እና የተቀናጀ ማሽን የኢኮኖሚ ነፃነታችን ማረጋገጫዎች ናቸው።
በመሆኑም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በመላው አህጉሪቱ የምርት መዳረሻ እና የኢንዱስትሪ ማዕከል የመሆን ጉዞዋን በራስ መተማመን እና በብረት በጠነከረ ክንድ አጠናክራ ትቀጥላለች። ዛሬ የምናየው እያንዳንዱ የፋብሪካ ጭስ የነገዋ የበለጸገች ኢትዮጵያ የድል አርማ ነው!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ebc #ethiopia #industry #madeinethiopia

ኢትዮጵያ ታመርታለች፤ ምሉዕ ሉዓላዊነቷን የማረጋገጥ ጉዞዋን በሁሉም መስክ አጠናክራ ትቀጥላለች። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ደግሞ የዚህ መርኃችን ዋነኛ ዓምድ ነው።
#ኢትዮጵያታምርት #madeinethiopia #ethiopiatamrit #economicsovereignty #ethiopiandevelopment #manufacturing #industrialrevolution #homegrowneconomy
3 months ago
ከመሸመት ወደ ማምረት፡ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ስኬቶች
*************************
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኢኮኖሚ መዋቅሯን ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር ግዙፍና ታሪካዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች።
ይህ የሽግግር ጉዞ የሀገራችንን የብልጽግና ራዕይ ከማሳካት ባለፈ፣ ዘላቂ የሥራ ዕድልን ለመፍጠርና ራስን ለመቻል እንደ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ ተወስዷል።
መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረትና ተግባራዊ የተደረጉት አዳዲስ ፖሊሲዎች፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ከነበረበት የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ወጥቶ ወደ ተሻለ የማምረት አቅም እንዲሸጋገር ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገት ቀደም ሲል ከነበረበት 4.8 በመቶ በአሁኑ ወቅት ወደ 10.7 በመቶ በመመንጠቅ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል።
ሙሉ ዘገባውን በአስተያየት መስጫው ካጋራነው ሊንክ ያገኙታል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #industry #manufacturing #madeinethiopia #ebc

u12e8u1320u1245u120bu12ed u121au1292u1235u1275u122d u12d0u1262u12ed u12a0u1215u1218u12f5 (u12f6/u122d) u12aeu1235u1273u122b u1295u130du130du122d...u12a5u12e8u1208u1218u1291 u1209u12d3u120bu12cau1290u1275 u12e8u1208u121d...u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1273u121du122du1275 |MadeinEthiopia |u12e8u1200u1308u122du1309u12f3u12ed
#pmabiyahemedali #ethiopia #manufacturing #industry #development ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኮስታራ ንግግር...እየለመኑ ሉዓላዊነት የለም...ኢትዮጵያ ታምርት |MadeinEthiopia |የሀገርጉዳይ
#pmabiyahemedali #ethiopia #manufacturing #industry #development
3 months ago
ኢትዮ ቴሌኮም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አቅም ለማሳደግና የገበያ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራረመ
ኩባንያችን በአራተኛው የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ኤክስፖ ላይ ከመሠረታዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ፣ ከጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማኅበራት ጋር የ(B2G) የመግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርሟል።
ስምምነቶቹ ኩባንያችን ለቴሌኮም እና ለኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ሥራዎች የሚውሉ የፋይበር ኦፕቲክስ፣ የኃይል እና የዳታ ኬብሎችን፣ ልዩ ልዩ መለዋወጫዎችን እና የሠራተኞች የደንብ ልብሶችን ከአገር ውስጥ አምራቾች ለመረከብ የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ይህም ኩባንያችን አስተማማኝና ጥራት ያላቸውን ግብዓቶች በአገር ውስጥ እንዲያገኝ ከማስቻሉም በላይ፣ አምራቾች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን እንዲያቀርቡና የአቅርቦት ሰንሰለት ማነቆዎችን እንዲቀርፉ ምቹ ዕድል የሚፈጥር ነው።
በተጨማሪም የሀገር ውስጥ አምራቾችን የማምረት አቅም ለማሳደግ፣ ፈጠራን ለማበረታታትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርቶች በመተካት የውጭ ምንዛሬን ለመቆጠብ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳለጥ እና ዘላቂ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ይኖራቸዋል።
ኩባንያችን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ለሀገራዊ ዲጂታል ኢኮኖሚው ግንባታ ጉል ፋይዳ ያለው በአምራቾች መካከል ያለውን የገበያ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ "ኢ-ታምርት" የተሰኘ የB2B የኢ-ኮሜርስ ፕላትፎርም ሥራ ላይ ማዋሉ ይታወሳል።
#ethiotelecom #ministryofindustry #telebirr #ethiopiatamirt #b2bplatform #digitaleconomy #localmanufacturing #gsma #itu #worldbank #madeinethiopia Ethiopian Ministry of Industry

የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻን 46 በመቶ ከፍ ማድረግ የቻለው "ኢትዮጵያ ታምርት" ስኬቶች
*****************
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ የሆነው ዲጂታል መጽሔት እንደጠቆመው፤ "ኢትዮጵያ ታምርት" ብሔራዊ ንቅናቄ መዋቅራዊ ማነቆዎችን በመፍታት የአምራች ዘርፉን የኢኮኖሚ ምህዳር በአዲስ መልክ እየቀረጸው ይገኛል።
ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት 29 ሚሊዮን ቶን የነበረው የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት በአሁኑ ወቅት ወደ 76 ሚሊዮን ቶን ከፍ ብሏል።
በመሠረተ ልማት ረገድም ባለፉት አራት ዓመታት 3.4 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የቀረበ ሲሆን፤ በ2018 ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለባለሀብቶች ተላልፏል።
የፋይናንስ አቅርቦትን በተመለከተ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበው ብድር ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ሲያድግ፤ ለከፍተኛ አምራቾች የሚቀርበው ደግሞ ከ52 ቢሊዮን ወደ 262 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ለከፍተኛ አምራቾች የቀረበው 2.28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አሳድጓል። የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገትም በ2017 ዓ.ም 10.7 በመቶ በመድረስ የምርት መጠኑን 195.4 ቢሊዮን ብር አድርሶታል።
ኢትዮጵያ በ2018 ዘጠኝ ወራት ውስጥ ስልታዊ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 4.85 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን የቻለች ሲሆን፤ የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻም ከ30 ወደ 46 በመቶ አድጓል።
በዲፕሎማሲው ረገድ የብሪክስ አባል መሆኗና የተደረጉ ማሻሻያዎች ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ አስችለዋል።
በተጨማሪም ተዘግተው የነበሩ 993 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ የተመለሱ ሲሆን፤ ዘንድሮ የሚካሄደው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018" በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በስብጥሩ የላቀ ታሪካዊ ሁነት እንደሚሆን ተመላክቷል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiatamirt #pmoethiopia #manufacturingethiopia #madeinethiopia

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ማዕከል ነው - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
*****************
4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 ላይ የቀረቡት ምርቶች ብዝሃነት እና ጥራት፣ ኢትዮጵያ በጥረቷ እና በልጆቿ የፈጠራ አቅም ብልጽግናዋን ማረጋገጥ እንደምትችል የሚመሰክር ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
ኤክስፖው ሀገር በቀል ፈጠራዎች የደረሱበትን ትልቅ ደረጃም የሚያመላክት ነው ብለዋል ሚኒስትሩ በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር።
በመደመር እሳቤ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ማዕከል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማካሄድ እና የቢዝነስ ምህዳሩን ምቹ በማድረግ፣ ሰፋፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት የማምረት አቅምን በማሳደግ፣ ገቢ ምርትን በመተካት እና ኤክስፖርትን በማሻሻል እንዲሁም የሥራ ዕድልን በመፍጠር ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድም ባለፉት 9 ወራት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 222 ኤግዚቢሽኖች ተዘጋጅተው 17 ሺህ 461 አምራቾች ምርቶቻቸውን ማስተዋወቃቸውን አንስተዋል።
በኤግዚቢሽኖቹ ለህብረተሰቡ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ 3.6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የግብይት ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው፣ ይህም የዜጎችን የሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህል በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ገልጸዋል።
በነስሩ ጀማል
#ethiopia #industry #manufacturing #madeinethiopia #ethiopiadelivers #ebc

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 በይፋ መርቀው ከፈቱ
****************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የአምራች ዘርፍ ለማስፋፋት የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክረውን አራተኛውን 'ኢትዮጵያ ታምርት' ኤክስፖ 2018 ዛሬ በይፋ መርቀው ከፍተዋል።
ኤክስፖው እስካሁን ያሳያቸው እና የተመዘገቡ ዋና ዋና ስኬቶች፦
- የአምራች ዘርፉ ግብዓት አቅርቦት በዓመት ከ9 ሚሊዮን ወደ 15 ሚሊዮን ቶን አድጓል፤
- ለአዳዲስ የኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንቶች ከ3.4 ጊጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ቀርቧል፤
- ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርበው የፋይናንስ አቅርቦት ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ ለከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከ262 ቢሊዮን ብር በላይ ከፍ ብሏል፤
- ለዘርፉ ከ2.28 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ተመድቧል፤
- የፋብሪካዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አድጓል፤
- የማምረት አቅም እና ዕድገት ከ4.8 በመቶ ወደ 10.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በቀጣይም ተጨማሪ ዕድገት ይጠበቃል፤
- ምርትን በሀገር ውስጥ በመተካት እስከ 4.85 ቢሊዮን ዶላር ማዳን የተቻለ ሲሆን የወጪ ንግድም ከፍተኛ እድገት እያሳየ ይገኛል፤
- ከ2 ሺህ 800 በላይ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ የተቻለ ሲሆን፣ ለ1.4 ሚሊዮን ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
ኤክስፖው ኢንዱስትሪዎችን የሚያስተሳስር፣ ኢንቨስትመንትን የሚስብ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ አምራቾችን እና በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን የሚያገናኝ ቁልፍ ሀገራዊ መድረክ ሆኗል።
በአጠቃላይ የኤክስፖው መከፈት የአምራች ዘርፉ ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያለውን ፋይዳ በማጉላት የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ሽግግር እያፋጠነ መሆኑን ያሳያል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ኢትዮጵያ ታምርት ፡ በራስ ላብ፣ የራስ ምርት
********************
(የዕለቱ መልዕክት)
ለዘመናት በገቢ ምርቶች ላይ ብቻ ተንጠልጥሎ የኖረ ኢኮኖሚ የራስን ሉዓላዊነት ሙሉ አያደርገውም። የሀገር ብልጽግና መሠረቱ ደግሞ በባዕድ እጅ የሚሰፈር ሳይሆን በራስ ላብና ጥረት የሚመረት መሆኑ አያጠያይቅም።
ባለፉት ዓመታት በሀገራችን የተጋረጡብንን የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ፈተናዎችን በመሻገር የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከአንቀላፋበት ቀስቅሶ ሕይወት ዘርቶበታል። ይህ ንቅናቄ ዝም ብሎ የቃላት ጋጋታ ሳይሆን “ላብ ካልፈሰሰ፣ አዝመራ የለም” የሚለውን እውነታ በተግባር ያሳየ፣ የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነታችንን ያበሰረ ብርቱ የለውጥ ማዕበል ነው።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ የለውጡ ጉዞ ውጤታማነት በቁጥር ብቻ ሳይሆን በገበያ ድርሻም ተረጋግጧል። ከሦስት ዓመት በፊት 30 በመቶ ብቻ የነበረው የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻ ዛሬ 41 በመቶ ደርሷል። ይህ መሻሻል ዝም ብሎ የመጣ ሳይሆን፣ ሥራ አቁመው የነበሩ 830 ኢንዱስትሪዎችን ዳግም ወደ ማምረት በመመለስና 325 ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን በአዲስ መንፈስ ወደ ሥራ በማስገባት የተገኘ ድል ነው።
በተለይም ከለውጡ በፊት 8 ሺህ ገደማ የነበሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ዛሬ 26 ሺህ መድረሳቸው፣ ኢኮኖሚው ከመንግሥት መርነት ወደ ግሉ ዘርፍ መዘዋወሩንና የዜጎች የሥራ ፈጠራ ተነሳሽነት መጎልበቱን ያሳያል። “ታጥቦ ጭቃ” መሆንን አቁመን፣ በገዛ ደጃችን ተኪ ምርቶችን እያመረትን መገኘታችን የኢኮኖሚ ነፃነታችን ማሳያ ነው።
የግብርናና የኢንዱስትሪ ትስስርም ሌላኛው የንቅናቄው ስኬት ነው። ቡና፣ ሻይና ሩዝ በገበሬው እጅ ብቻ ተመርተው ሳይሆን በፋብሪካዎች እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍ አድርጎታል።
“ሳይቀደሙ መቅደም” እንዲሉ መከላከያና ፖሊስ ከውጭ በውድ ምንዛሬ የሚገዛ የደንብ ልብስን ትተው ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት መተካታቸው፣ እንዲሁም የብቅል ገብስ ዘርን እዚሁ ማምረት መቻላችን 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬን ለማዳን አስችሏል። በተጨማሪም የጨርቃጨርቅ፣ የቆዳና የምግብ ኢንዱስትሪዎች እምቅ አቅማቸውን እያወጡ ይገኛሉ።
የጥራት መንደር አበርክቶ ደግሞ ለዚህ ሁሉ ስኬት ሞተር ነው። በዓመት 5.2 ሚሊዮን ቶን ምርትን የመመርመር አቅም ያለው ይህ ተቋም፣ የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የጥራት ደረጃቸው እንዲጠበቅ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት ይህ ተቋም በዓለም የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ያለንን ተሳትፎ የሚያጎለብት የብልጽግናችን መተማመኛ ነው።
በአጠቃላይ "ኢትዮጵያ ታምርት" ከሸቀጥ ግብይት ባለፈ "የኢትዮጵያ ይሸጥ" የሚል ኩሩ እሳቤን ይዟል። 235 ሺህ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የወጣቶችን ሕይወት የቀየረው ይህ ንቅናቄ፣ ቁልፍ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የኢኮኖሚ ነፃነታችንን የሚያጸና ነው። በጋራ ካመረትንና የራሳችንን ምርት ከተጠቀምን፣ የብልጽግና ጉዟችን የማይቀለበስ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ታምርት፣ ኢትዮጵያ ትበልጽግ!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
#ethiopia #industry #manufacturing #importsubstitution #madeinethiopia #ethiopiadelivers #ebc #ebcdotstream

ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት የውጭ ምንዛሬን ከመታደግ ባለፈ የዜጎችን የምርት አቅም በማሳደግ ላይ ትገኛለች።
የቢራ ገብስ ብቅልን፣ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችንና ስንዴን ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ በማምረት በየዓመቱ ይወጣ የነበረውን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማስቀረት መቻሉን የሚያሳየውን ዝርዝር መረጃ በኢንፎግራፊክሱ ይመልከቱ።
#ethiopia #industry #madeinethiopia #importsubstitution #productivity #ebc

4 months ago
ባሕር ዳር፦ ወጣት ብሩክ የሠራው አዲሱ መኪና
#የጥበበኛ እጆች ባለቤት የሆነውና በባሕር ዳር ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በአውቶ ኤሌክትሪክ ዘርፍ የተመረቀው ወጣት ብሩክ ወንዲፍራው፣ የማይቻል የሚመስለውን በተግባር አሳይቷል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኢንዱስትሪ ማሽኖችን የሠራው ብሩክ፣ አሁን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎች የተሠራች ባለ አራት እግር መኪና ይፋ አድርጓል።
የተሽከርካሪዋ ልዩ መገለጫዎች
ሞተር
ባለ 300 ሲሲ (CC) ሞተር የተገጠመላት።
አቅም
በአንድ ጊዜ 4 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላትና ከባጃጅ የተሻለ ፍጥነት የምትጓዝ።
ክብደት
ከ400 ኪሎ ግራም በላይ ክብደት አላት።
ወጪ
ለመሥራት ከ350 ሺህ ብር በላይ ወጪ ተደርጎባታል።
የብሩክ ትልቅ ራዕይ
የብሩክ ህልም መኪና ሠርቶ ማሳየት ብቻ አይደለም። በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የሚገቡ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በጥራት ማምረት እና ለብዙ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ነው። ድጋፍ ካገኘ ደግሞ በቀጣይ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን የማምረት ትልቅ ዕቅድ አለው።
የነገዋ ኢትዮጵያ ከመግዛት ወጥታ ወደ ማምረት የምትገባው በእንዲህ ያሉ ጀግኖች እጅ ነው።
#ቴዎድሮስ ደሴ ( አሚኮ)
#getu #innovationethiopia #bahirdar #techhero #madeinethiopia #engineeringexcellence #youthempowerment #ethiopiadecides #automotiveinnovation #ባሕርዳር #ፈጠራ #ኢትዮጵያ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

የኢትዮጵያ ምርቶች በዋይልድቤሪስ በኩል ለዓለም ገበያ ቀረቡ
#ethiopia | ለኢትዮጵያ አምራቾችና ላኪዎች አዲስ የገቢ ምንጭ ተከፍቷል! የዓለም አቀፉ የገበያ መድረክ ዋይልድቤሪስ (Wildberries) የኢትዮጵያ ሻጮች ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለዓለም አቀፍ ገዢዎች እንዲያቀርቡ መድረኩን ክፍት ማድረጉን አስታውቋል።
ይህ ዕድል ምን ይዟል?
ቀጥታ የገበያ ትስስር
የሀገር ውስጥ ምርቶች (Manufactured in Ethiopia) ያለምንም መካከለኛ ደላላ ለዓለም አቀፍ ደንበኞች ይደርሳሉ።
ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን
አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች አሰራራቸውን ወደ ዘመናዊው የኢ-ኮሜርስ ስርዓት እንዲቀይሩ ትልቅ አጋዥ ይሆናል።
የግንዛቤ መድረኮች
አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዴት መመዝገብ እንደሚችሉና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን የሚያስረዱ ተከታታይ ስልጠናዎችና የግንዛቤ መድረኮች ይከናወናሉ።
የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸው ይበልጥ እንዲታወቅ የሚያደርግ ታሪካዊ ጅማሮ!
#getu #wildberriesethiopia #ecommerce #ethiopiamanufacturing #globalmarket #digitaleconomy #madeinethiopia #businessnews #addisababa #ኢኮኖሚ #ንግድ #ኢትዮጵያ #ዋይልድቤሪስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

7 months ago
🎁 የበዓል ስጦታ ለ608 ህጻናት! 👗👕
"ግዮን ፋሽን፡ በ95% ሴቶች የሚመራው ሀገር በቀል ተቋም በጎ ተግባር!"
#ethiopia | ለጥምቀት በዓል ስጦታ ይሆን ዘንድ፤ በልጆች አልባሳት ምርት ላይ የተሰማራው ሀገር በቀል ድርጅት ግዮን ፋሽን (Ghion Fashion)፤ ለሙዳይ በጎ አድራጎት ማህበር የ608 ህጻናት አዳዲስ አልባሳትን በድጋፍ አበርክቷል።
ስለ ድጋፉ እና ተቋሙ:
ዛሬ ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም በተደረገው የድጋፍ መርሐግብር ላይ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ናትናኤል ሲሳይ እንደገለጹት፤ እነዚህ አልባሳት በተለይ ለሙዳይ ልጆች ታስበው በፋብሪካው የተመረቱ ናቸው።
ግዮን ፋሽን ከ50 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 95 ከመቶው ሴቶች መሆናቸው ተቋሙን ልዩ ያደርገዋል!
ወ/ሮ ሙዳይ ምን አሉ?
የማህበሩ መስራች ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፤ "ግዮን ፋሽኖች እዚሁ ተገኝተው፣ ልጆቻችንን ጎብኝተውና በልዩ ሁኔታ ልብስ አምርተው ስላመጡልን እናመሰግናለን" ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
እንዲህ ያሉ ሀገር በቀል እና ለወገን የሚደርሱ ተቋማት ይብዙልን!
መልካም በዓል! 🇪🇹🌼
#ghionfashion #mudaycharity #donation #timket #madeinethiopia #womenempowerment #charity #muday #charity #ethiopia

Comments