1 month ago
የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻን 46 በመቶ ከፍ ማድረግ የቻለው "ኢትዮጵያ ታምርት" ስኬቶች
*****************
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ይፋ የሆነው ዲጂታል መጽሔት እንደጠቆመው፤ "ኢትዮጵያ ታምርት" ብሔራዊ ንቅናቄ መዋቅራዊ ማነቆዎችን በመፍታት የአምራች ዘርፉን የኢኮኖሚ ምህዳር በአዲስ መልክ እየቀረጸው ይገኛል።
ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት 29 ሚሊዮን ቶን የነበረው የኢንዱስትሪ ግብዓት አቅርቦት በአሁኑ ወቅት ወደ 76 ሚሊዮን ቶን ከፍ ብሏል።
በመሠረተ ልማት ረገድም ባለፉት አራት ዓመታት 3.4 ጊጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የቀረበ ሲሆን፤ በ2018 ዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለባለሀብቶች ተላልፏል።
የፋይናንስ አቅርቦትን በተመለከተ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርበው ብድር ከ8.1 ቢሊዮን ወደ 50 ቢሊዮን ብር ሲያድግ፤ ለከፍተኛ አምራቾች የሚቀርበው ደግሞ ከ52 ቢሊዮን ወደ 262 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል።
የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ለከፍተኛ አምራቾች የቀረበው 2.28 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ አሳድጓል። የዘርፉ ዓመታዊ ዕድገትም በ2017 ዓ.ም 10.7 በመቶ በመድረስ የምርት መጠኑን 195.4 ቢሊዮን ብር አድርሶታል።
ኢትዮጵያ በ2018 ዘጠኝ ወራት ውስጥ ስልታዊ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 4.85 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን የቻለች ሲሆን፤ የሀገር ውስጥ ምርቶች የገበያ ድርሻም ከ30 ወደ 46 በመቶ አድጓል።
በዲፕሎማሲው ረገድ የብሪክስ አባል መሆኗና የተደረጉ ማሻሻያዎች ከ2 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ አስችለዋል።
በተጨማሪም ተዘግተው የነበሩ 993 ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ የተመለሱ ሲሆን፤ ዘንድሮ የሚካሄደው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018" በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በስብጥሩ የላቀ ታሪካዊ ሁነት እንደሚሆን ተመላክቷል።
በላሉ ኢታላ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopiatamirt #pmoethiopia #manufacturingethiopia #madeinethiopia