1 month ago
አዲስ ዓመት፣ አዲስ አድማስ፦ የኢትዮጵያ የባሕር በር ተስፋ እና የብልጽግና ጉዞ
******************
ከቀን መቁጠሪያው ላይ የጳጉሜ የመጨረሻ ቀናት ተቆጥረው አዲሱ ዘመን ሲጠባ፣ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ሁልጊዜም የአዲስ ተስፋ ብርሃን ይለኮሳል።
አሮጌውን ዓመት በጽናት ሸኝተን አዲሱን ዓመት ለመቀበል በምናደርገው የሽግግር ወቅት፣ አዳዲስ ዕቅዶች እና ታላላቅ ሀገራዊ ራዕዮች ይሰነቃሉ።
የዘንድሮው ዘመን መለወጫ ግን ከወትሮው የተለየ ነው፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ለዘመናት የታሰረችበትን የጂኦፖለቲካዊ ገደብ ሰብራ ወደ ክፍት ውቅያኖስ ለመሸጋገር ስትራቴጂያዊ ተስፋ የሰነቀችበት ወቅት በመሆኑ ነው።
በየማኅበረሰቡ የተመረተው እህል፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተገነባው የማምረት አቅም እና የወጣቱ የፈጠራ ውጤት ድንበር ተሻግሮ ለዓለም ገበያ በሚቀርብበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ ወደብ አልባነት የሚፈጥረውን ማነቆ መፍታት የአዲሱ ዓመት የተስፋ ስንቅ ነው።
የዓመታት የገበያ ዕድገት እና የምርታማነት መጨመር ብቻቸውን ሙሉ የኢኮኖሚ ነፃነትን ሊያረጋግጡ አይችሉም።
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ እና ለተያያዥ የሎጅስቲክስ አገልግሎቶች የምታወጣው ከፍተኛ ወጪ፣ በሸቀጦች ዋጋ እና በዜጎች ኪስ ላይ ከባድ ጫና መፍጠሩን ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ ዕድገት እውነተኛ ትርጉም የሚያገኘው ከታሰረበት ማነቆ ወጥቶ ከዓለም ጋር በሚኖረው ነፃ የንግድ ትስስር ሲረጋገጥ ነው።
ይህ ታላቅ ሀገራዊ መሻት በቀጣናዊ የጋራ ዕድገት መርሕ፣ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ እውን ሲሆን፤ የኢኮኖሚውን መዋቅር ከሥሩ ይለውጠዋል።
የወደብ አገልግሎት ወጪዎች በከፍተኛ ደረጃ መቀነሳቸው የሸቀጦች የዋጋ ግሽበትን በማቃለል ለሕዝብ ታላቅ እፎይታን ያመጣል።
እውነተኛ አዲስ ዓመት እና አዲስ አድማስ የሚሰፍነው የቆዩ እና የማይጠቅሙ የጂኦ-ፖለቲካ ትርክቶችን ለማረም በሚደረግ ጽኑ ሀገራዊ ቁርጠኝነት ነው።
ስለዚህም የመስከረም መግቢያ ከባህል እና ከቀን መቁጠሪያ ለውጥ የዘለለ ጥልቅ መልዕክት አለው።
የባሕር በር ጥያቄ የጂኦፖለቲካ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የትናንቱን የአባቶቻችንን ትውልድ ዕንባ አብሶ የዛሬውን እና የነገውን ወጣት ሕልም ከተቸነከረበት የዘመናት የእስር ሰንሰለት ወደ ሰፊው ዓለም አቀፍ አድማስ እና የብልጽግና ጎዳና የሚያሻገር የማይናወጥ የታሪክ እና የልማት ምዕራፍ ነው።
በሐና ምንዳሁን
#ethiopia #newyear #seaaccess #geopolitics #economicsovereignty #ebc #ebcdotstream

የታሪክ ስብራትን ማቃናት እና የአዲሱ አርበኛ ትውልድ ጥሪ፦ የቀይ ባሕር ደሴቶቻችን ምስክርነት
*************************
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና ውስጥ የነበራት ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስትራቴጂካዊ ሚና የረጅም ዘመናት ታሪክ ያለው ነው። በተለይም በባሕር ላይ ኢንዱስትሪ፣ በባሕር ኃይል እና በንግድ እንቅስቃሴዎች ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት የቀጣናው የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስኬታማ ሥራዎችን አከናውናለች።
ከእነዚህ ታሪካዊ አሻራዎች መካከል በአፍሪካ ቀዳሚ የነበረው እና ከአሰብ ወደብ በስተደቡብ በምትገኘው ሃሌብ ደሴት ላይ ተገንብቶ የነበረው ግዙፍ የባሕር ላይ ኢንዱስትሪ፣ የመርከብ ጥገና ማዕከል እና የባሕር አካዳሚ ዋነኛ ማረጋገጫዎች ናቸው።
ሆኖም በ1983 ዓ.ም. በነበረው የፖለቲካ ለውጥ እና ጂኦፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት ሀገራችን ይህንን ታሪካዊ ሀብቷን እና የባሕር በሯን በማጣት በዓለማችን ትልቋ በየብስ የተከበበች ሀገር ለመሆን ተገደደች።
ይህ ታሪካዊ እና ጂኦግራፊያዊ ስብራት ሀገራችንን በየዓመቱ ለወደብ ኪራይ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ እንድታወጣ አስገድዷታል።
ዛሬ ላይ የባሕር በር ጉዳይ የዘመናት የታሪክ እና የጂኦግራፊ ስብራታችን የሚጠገንበት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራዊ ህልውናችንን የሚያረጋግጥ አዲስ “አርበኛ ትውልድ” የምናሰባስብበት ትልቁ ሀገራዊ አጀንዳችን ነው።
የመደመር መንግሥት ይህንን ስብራት ለመቀልበስ የያዘው እሳቤ በጋራ ተጠቃሚነት (Win-Win) መርህ ላይ የተመሠረተ እንጂ የኃይል አማራጭ አይደለም።
ቀይ ባሕር በዓለማችን ከሚካሄደው የባሕር ንግድ 12 በመቶ የሚሆነው የሚያልፍበት ስትራቴጂካዊ መስመር በመሆኑ፣ በዚሁ ቀጣና ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ጸጥታዊ መረጋጋት ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
በመሆኑም አዲሱ ትውልድ የሃሌብ ደሴትን የመሰሉ ታሪካዊ እምቅ አቅሞችን በመገንዘብ፣ የሀገራችንን ፍትሐዊ ጥያቄ በሰላማዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በመግፋት ለቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና ታሪካዊ አሻራውን ማሳረፍ አለበት።
በሀይማኖት ከበደ
#ethiopia #ebc #redseaaccess #ethiopianhistory #hornofafrica #economicsovereignty #geopolitics

2 months ago
ጥገኝነት የነፃነት ጠላት ነው! ኢትዮጵያ እንዴት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነቷን እያረጋገጠች ነው? ETV | EBC | EBCDOTSTREAM #ethiopia #economicsovereignty #ethiopianeconomy
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

5 months ago
ድንጋይ አቅልጣ ዶላር የምታድነው ኢትዮጵያ፤ የሴራሚክ ምርት ከውጭ ጥገኝነት ወደ ሉዓላዊ አቅም እየተቀየረ ነው። እንዴት ካሉ መልሱን በተከታዩ ሊንክ ያገኙታል ➡️ https://youtu.be/K_Lb1Mknq...
#ceramicindustry #madeinethiopia #importsubstitution #economicsovereignty #taborceramics #ebcworld
5 months ago
ኢትዮጵያ ታመርታለች፤ ምሉዕ ሉዓላዊነቷን የማረጋገጥ ጉዞዋን በሁሉም መስክ አጠናክራ ትቀጥላለች። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ደግሞ የዚህ መርኃችን ዋነኛ ዓምድ ነው።
#ኢትዮጵያታምርት #madeinethiopia #ethiopiatamrit #economicsovereignty #ethiopiandevelopment #manufacturing #industrialrevolution #homegrowneconomy
5 months ago
ኢትዮጵያን ወደ ኢንዱስትሪ ማዕከልነት የሚቀይረው አዲሱ የማዕድንና ኢንዱስትሪ ትስስር
********************
ኢትዮጵያ ከተፈጥሮ ያገኘችውን የማዕድን ሀብት በጥሬው ወደ ውጭ ከመላክ ባለፈ፣ እሴት ጨምሮ ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት በማዋል ረገድ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች።
ከሪፎርሙ በፊት ዘርፉ ለሀገራዊ ምርት ያለው አስተዋጽኦ ከአንድ በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ማዕድንን የኢኮኖሚው ዋነኛ ምሰሶ በማድረግ የኢንዱስትሪ ሽግግር መሠረት እንዲሆን ተደርጓል።
ይህም በየዓመቱ ለነዳጅ፣ ለማዳበሪያና ለብረት ግብዓቶች ግዢ የሚወጣውን ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው።
በተለይም በብረት ማዕድን ዘርፍ ከ1.1 ቢሊዮን ቶን በላይ ክምችት ላይ በመመስረት በዓመት ሦስት ሚሊዮን ቶን ብረት በሀገር ውስጥ ለማምረት ሰፊ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።
በወርቅ ምርት ዘርፍም ቢሆን ከ2010 እስከ 2017 ባሉት ዓመታት ውስጥ የ1241.4 በመቶ ከፍተኛ የኤክስፖርት ዕድገት መመዝገቡ የሪፎርሙን ውጤታማነት በተጨባጭ ያሳያል። በተጨማሪም በ"ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ አማካኝነት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 4.85 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል።
ይህ የማዕድንና ኢንዱስትሪ ትስስር ኢትዮጵያ ከውጭ ጥገኝነት እንድትላቀቅና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነቷን በጽኑ መሠረት ላይ እንድታቆም እያደረገው ያለውን ዘርፈ ብዙ ለውጥ በዝርዝር ለማንበብ ድረ ገጻችንን ይጎብኙ።
#ethiopia #mining #industry #economicsovereignty #ethiopiatamirt #mineralreform #investment

Sponsored by
Surafel
Comments