Logo
EBC
የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ማዕከል ነው - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
*****************

4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2018 ላይ የቀረቡት ምርቶች ብዝሃነት እና ጥራት፣ ኢትዮጵያ በጥረቷ እና በልጆቿ የፈጠራ አቅም ብልጽግናዋን ማረጋገጥ እንደምትችል የሚመሰክር ነው ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ኤክስፖው ሀገር በቀል ፈጠራዎች የደረሱበትን ትልቅ ደረጃም የሚያመላክት ነው ብለዋል ሚኒስትሩ በኤግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር።

በመደመር እሳቤ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የብሔራዊ ሉዓላዊነታችን ማዕከል ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት፣ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማካሄድ እና የቢዝነስ ምህዳሩን ምቹ በማድረግ፣ ሰፋፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ምክንያት የማምረት አቅምን በማሳደግ፣ ገቢ ምርትን በመተካት እና ኤክስፖርትን በማሻሻል እንዲሁም የሥራ ዕድልን በመፍጠር ተጨባጭ ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ረገድም ባለፉት 9 ወራት ብቻ በመላ ሀገሪቱ 222 ኤግዚቢሽኖች ተዘጋጅተው 17 ሺህ 461 አምራቾች ምርቶቻቸውን ማስተዋወቃቸውን አንስተዋል።

በኤግዚቢሽኖቹ ለህብረተሰቡ ምርትን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ 3.6 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ የግብይት ሥራ መከናወኑን ጠቅሰው፣ ይህም የዜጎችን የሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ባህል በከፍተኛ ሁኔታ መቀየሩን ገልጸዋል።

በነስሩ ጀማል
#ethiopia #industry #manufacturing #madeinethiopia #ethiopiadelivers #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.