Logo
EBC
ኢትዮጵያ የቀጣናው የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን የጀመረችውን ጉዞ ያፋጠነው ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ
*****************

ኢትዮጵያ ከውጭ ጥገኝነት በመላቀቅ ራሷን የመቻል ራዕይዋን እውን ለማድረግ በተያያዘችው ትግል፣ የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የቀጣይ ብልጽግናችን የማይናወጥ መሠረት ሆኖ ብቅ ብሏል።

ይህን ሀገራዊ ራዕይ መሬት ለማውረድና የማምረት አቅምን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከተገነቡ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መካከል ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተጠቃሽ ነው።

ይህ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀው ግዙፍ የሴራሚክ ፋብሪካ፣ ቀደም ሲል በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ ይገቡ የነበሩ የኮንስትራክሽን ግብዓቶችን ጥራትና ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ በሀገር ውስጥ ለመተካት ያስቻለ ትልቅ ስኬት ነው።

ፋብሪካው በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ማዕቀፍ በተዘረጉ የድጋፍና ማበረታቻ ሥርዓቶች በመታገዝ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶች እና ጥሬ ዕቃዎችን በመጠቀም ውጤታማ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

ከፍተኛ የማምረት አቅም ያለው ግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ የሙያ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፋጠን በማድረግም የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

በተጨማሪም ፋብሪካው ተኪ ምርት በማምረት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪን ከማዳን በተጓዳኝ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የኮንስትራክሽን ዘርፍ የሴራሚክ ፍላጎት በራስ አቅም በመሸፈን በቀጣይ በሴራሚክ ምርት ኤክስፖርት የወጪ ንግድ ገቢን የማሳደግ ራዕይን የሚደግፍ ነው።

የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ እውን መሆን ኢትዮጵያ የቀጣናው የኢንዱስትሪ ማዕከል ለመሆን እና በየዘርፉ ከጥገኝነት ተላቅቃ ራሷን ለመቻል የጀመረችውን የማይቀለበስ ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥን እርሾ ነው።

በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #industry #manufacturing #ethiopiatamirt #madeinethiopia #grandeurceramic #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.